ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Re: :-)

Postby ደጉ » Fri Dec 28, 2012 4:07 pm

Gosa wrote:ሰላም ደጉ ሰው!
"ንፋሳም " ያልከው በጣም ነበር ያሳቀኝ:: በነገራችን ላይ ሰውየው አሁን በሕይወት የሉም:: ሲበዛ "ተጫዋች "ነበሩ::

....አይይይይ በጣም ያሳዝናል ....ጠንቁዋይ ለራሱ አያውቅም ...ህኪምም እራሱን አያድንም ይባላል መሰለኝ...;) ከምር መሞታቸውን ስሰማ በጣም ነው ያዘንኩት...በዚህ አጋጣሚ ነፍሳቸውን ይማር...በምድር ህይወታቸውም ሴት በጣም ይወዱ እንደነበር አውቃለሁ,,,ፈጣሪ ይሄን አይቶ ሲመኙዋት የነብሩዋትን ከጎናቸው ያድርግላቸው...
...ስለ እሳቸው ትዝ የምለኝ ነገር የከለር ምርጫቸው ነው:: ቢራ ሲጠጡ እንደ ስፕራይት ጠርሙስ ባለ አረንጓዴ ቀለም ካልቀረበላቸው አይጠጡም ይባላል::

.....ቅቅቅቅቅቅ...ለጥንቃቄ ይመስለኛ የአገር ቤት ቢራ ጠርሙስ እኮ አልፎ አልፎ በደንብ አይታጠብም....በአረንጉዋዴው ጠርሙስ ቆሻሻው በደንብ ይታያል ከ ቀዩ ይልቅ...አንድ ጊዜ ጎረቤት ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብሎ ቢራ ያዘዘ ሰው ዝልግልግ ነገር በአረንጉዋዴው ጠርሙስ አይቶ ሲመልስ አይቻለሁ...በቀዩ ቢሆን ጠጥቶት ነበር.. :D

... ማን ትሆን እንዲህ ሰፍ ያልክላት? ለነገሩ ካመንክባት ያለመድሀኒት በግል ምክር ብቻም ልታድንህ ትችል ይሆናል :D

.....ለነገሩ ስሙዋ አሁን ትዝ አይለኝም...ግን ባል ነበራት ..እኔን ለማዳን እንኩዋን ትህትናዋ አያንስም ነበር....ስማ አንድ ጊዜ እኮ አንዱ ገበሬ የከብት መድህኒት ግማሹን ውጦ ትንሽ ከውህ የቀጠነ ከ ጀት የፈጠነ (ከነዳው) በሁዋላ ድኑዋል .... :D
....ይልቅ ካስታወስክ አንድ ወንድና ሴት ከኩባ የመጡ ነበሩ...ሴትዋ ቆንጆ እና ሰውነትዋም በጣም እሚያምር ነበረች....ወደ በሁዋላ ግን ከነርሰሪ ሳይት የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ሮል ሸጡ ተብለው ታስረው ነበር ...የኩባ ተማሪ እኮ ጤና የለውም ....አንድ ጊዜ ኩባ እና ኢትዮጵያ በሶሻሊዝም በጉዋደኝነት በነነሩበት ወቅት ነው አሉ...ህረር አንዱ ኩባ ዶሮ ከነ ጫጩቶችዋ ሰርቆ "ኩኩ ኮምበሌት እይለ" ለመሸጥ ሲያዞር ነበር ይባላል ...:)
..ስለ አባ ጆ መጽሀፍ ፍንጩን ካገኘህ በተለይ " Guji Oromo culture in southern Ethiopia " እንደምትጠቁመኝ እተማመናለሁ:: እኔ ጉግል አድርጌ አርእስቱን ባገኝም መጽሀፉን ማግኘት አልቻልኩም::
ሰላም ሁንልን

....እስኪ እጠይቅልህለሁ እኔም እሱን መጽህፍ እጃቸው ላይ ነው ያየሁት ባልሳሳት ረቂቁን መሰለኝ....ከዛ ለኔ እዛ ስትሰራ ይረደህል ብለው የ ጉጂ መዝገበ ቃላት ሰጡኝ...እሱ አዲስ አበባ ነው ያለኝ ከ 1 አመት በሁዋላ ሳልሄድ አልቀረም የዛን ጊዜ አምጥቼው ኮፒ አድርጌ ልልክልህ እችላለሁ.::

ሰላም ሁ[/quote]
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby Gosa » Fri Dec 28, 2012 5:42 pm

ሰላም ደጉ!
በምድር ህይወታቸውም ሴት በጣም ይወዱ እንደነበር አውቃለሁ ,,,ፈጣሪ ይሄን አይቶ ሲመኙዋት የነብሩዋትን ከጎናቸው ያድርግላቸው
:lol: :lol: እንደዚያ አይነት ገነት ቢኖር ኖሮ ከምር ሀይለኛ ሀይማኖተኛ እሆን ነበር:: መጽሀፉ ግን ወንድና ሴት ብሎ ነገር የለም ነው የምለው መሰለኝ: ባይልም ግን የግል ክፍል እንደሌለ ሰምቻለሁ:: ሁሉም ረዘም ያለ ነጭ ልብስ ለብሶ ነው አሉ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ የሚመላለሰው:: ታዲያ ያ ሁሉ ሰው እያለ ምንም መሆን የሚቻል አይመስለኝም:: ያው ስንሞት እንደውሾቹ ዲ-ሴክስ ሳንደረግ እንቀራለን ብለህ ነው እዚያ ሄደን ጨዋዎቹን እንዳንበጠብጣቸው:: :D
አንድ ጊዜ ጎረቤት ጠረጴዛ ላይ ቁጭ ብሎ ቢራ ያዘዘ ሰው ዝልግልግ ነገር በአረንጉዋዴው ጠርሙስ አይቶ ሲመልስ አይቻለሁ ...በቀዩ ቢሆን ጠጥቶት ነበር ..
ምን ይሆን ያ ዝልግልጉ ነገር :D :: ተንኮለኞች የማያደርጉት ነገር የለም'ኮ:: ባዮሎጂውንም እየተመራመሩ ልሆን ይችላል::
ይልቅ ካስታወስክ አንድ ወንድና ሴት ከኩባ የመጡ ነበሩ ...ሴትዋ ቆንጆ እና ሰውነትዋም በጣም እሚያምር ነበረች ....ወደ በሁዋላ ግን ከነርሰሪ ሳይት የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ሮል ሸጡ ተብለው ታስረው ነበር ...የኩባ ተማሪ እኮ ጤና የለውም

እንደዚያ አይነቱን ሰው ባለማስታወሴ ደስ ብሎኛል :D ኩባዎች ሌቦች ናቸው እንዴ? ልማድ ካልሆነ በስተቀር አሁን የችግኝ ማሸጊያ ፕላስቲክ ምን ይሰራላታል? መቼም ቀልብህ የከጀላት ልጅ የፕላስቲክ ሌባዋ አይደለችም አይደል? :D
ስለ መዝገበ ቃላቱ ብዙም አትጨነቅ:: ያኛውን ነበር በጣም የፈለኩት:: በጣም ብዙ ሰዎችን በመጠየቅ ስለ ባህል የጻፉት መጽሀፍ ስለሆነ ነበር ያንን የፈለኩት:: ለማንኛውም በጣም እግዜር ይስጥልን::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

:-)

Postby ደጉ » Tue Jan 08, 2013 5:00 pm

..እንኩዋን ለአዲስ አመት / ለገናም በአል አደረሳችሁ...!!

...ሰላም ሰላም ጎሳ....

Gosa wrote:.....እንደዚያ አይነቱን ሰው ባለማስታወሴ ደስ ብሎኛል :D ኩባዎች ሌቦች ናቸው እንዴ? ልማድ ካልሆነ በስተቀር አሁን የችግኝ ማሸጊያ ፕላስቲክ ምን ይሰራላታል? መቼም ቀልብህ የከጀላት ልጅ የፕላስቲክ ሌባዋ አይደለችም አይደል? :D
ስለ መዝገበ ቃላቱ ብዙም አትጨነቅ:: ያኛውን ነበር በጣም የፈለኩት:: በጣም ብዙ ሰዎችን በመጠየቅ ስለ ባህል የጻፉት መጽሀፍ ስለሆነ ነበር ያንን የፈለኩት:: ለማንኛውም በጣም እግዜር ይስጥልን::

...ተገላገልክ ...አይ ከምር ግን ልጅትዋ በጣም ቆንጆ ልጅ ነበረች በመልክም በሰውነትም ....ኖ እሱዋ ከከብት ህክምና ጋ እሚያገባኛት ነገር አልነበረም ... :D ልጁ አታልዋት መሆን አለበት እንጂ እሱዋ እንደዛ አይነት አትመስልም....ቅቅቅቅቅ ኖ ሁሉም ሌባ ናቸው ማለቴ አይደለም...አጋጣሚው እንጂ....:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Tue Jan 08, 2013 5:12 pm

PostPosted: Mon Mar 27, 2006 8:53 pm Post subject: :-) Reply with quote Edit/Delete this post

--------------------------------------------------------------------------------

.... ከኔቸር መጋዚን ላይ ያገኘሁት እንዲህ ይላል ....በደቡብ አሜሪካ ነዋሪ የሆኑ "ማያ " እሚባሉ ጎሳዎች መንገድ ሲጉዋዙ አቅጣጫ ከጠፋባቸው ...አንበጣ ይዘው አንበጣው እስኪያዞረው ድረስ አሽከርክረው ሲዞርበት ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ያስቀምጡታል ..አንበጣውም ትንሽ ከዞረ በሁዋላ አናቱ ወደ ሰሜን ሲሆን መዞሩን ያቆማል ...በዚህ ግዜ እነሱም የሳቱትን አቅጣጫ ያገኛሉ ...Smile

...እነዚህ ሰዎች እራሳቸው ዞሮባቸው የአንበጣ ራስ እሚያዞሩ ...የአለም መጨረሻን እናውቃለን ብለው የሰውንም አናት ከ አንድ አመት የበለጠ ያዙሩ ...?? :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby Senayte » Wed Jan 16, 2013 5:54 am

ሰላም ደጉ, እንዴት ነህ? እንኳን ለ 2013 አደርስህ!

ወደ አፍጋኒስታን መቼ ሙቭ አደርግህ?? ሎል
" Every problem has a solution. If it doesn't ,it isn't a problem but a fact ,and you must learn to live with it."
Senayte
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 241
Joined: Thu Nov 18, 2004 5:00 am
Location: Lieville.....

:)

Postby ደጉ » Mon Jan 28, 2013 2:17 pm

Senayte wrote:ሰላም ደጉ, እንዴት ነህ? እንኳን ለ 2013 አደርስህ!

ወደ አፍጋኒስታን መቼ ሙቭ አደርግህ?? ሎል

...ሰንዬ የኔ ቆንጆ እንዴት ነሽልኝ ...እንኩዋን አብሮ አደረሰን ...አፍጋኒስታን ከገባሁ እኮ ቆየሁ ...ከድሮም እዛው ነኝ... :D
...አንቺ የስንዴ አገር ቁጭ ብለሽ ቀልጂ ....:)
...እስኪ ከገባሁ አይቀር yahoo ላይ ከወጡት 10 አደገኛ አየር መንገዶች (ወይ እናንተን ወይ ሻንጣችሁን) ብቻ ከሚያደርሱት ውስጥ አስሩ እነዚህ ናቸው...

1- China Airline

2- TAM Airline

3- INDIAN Airline

4- GOL Transport

5. SOUTH KOREAN AIR

6- SAUDIAN Air

7- TURKISH AIRLINE

8- THAI Airways

9- South African Airways

10- SKY west Airline

....እነዚህ እንግዲህ ከ 300 ሰው በላይ ህይወት የጠፋባቸውና በአለም ላይ በአደገኝነት የተመዘገቡ አየር መንገዶች ናቸው....በነዚህ አየር መንገዶች ለምትበሩ ከወዲሁ መልካም በረራ ይሁንላቸው (ከ እነ እቃቸው ያግባችሁ ) :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Fri Feb 08, 2013 11:42 am

...ሰላም ሰላም በህይወት ያላችሁ .. :D ዋርካ በቁም እየሞተች ይመስላል ጥቂት ሰዎች ዋርካ ለምንቀሳቀስ እግራቸውን ከምትጠቀምባቸው ሌላ ...:)
.....የዋርካ አድሚኖች ዋርካ እንዳይገቡ ባን ተደርገዋል ላልሰማችሁ ለመንገር ያክል ነው .. :D
....ዛሬ ከሌሎች ቀናቶች የተለየ ደስ ብሎኛል .. :D ለምን እንደሆነ አውቀዋለሁ ....;)
....አንድ ጥቅስ ተናጋሪ ስሙን ባላስታውሰውም .... እንደ ሰው እሚያስብ እንስሳ ባያጋጥመኝም ...እንደ እንስሳ እሚያስቡ ሰዎች ግን ብዙ አጋጥመውኛል ብሎ ነበር .. :D ከምር እውነቱን ነው ...
...በጣም ---- የሆኑ ሰዎች መጥላት ማለትና መውደድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልዩነቱን አያውቁትም በህይወት በሚቆዩበት እድሜን (እድሜ ልካቸውን) ያንን አይረዱትም ... :lol:
....እነዚህን ሰዎች ውስጣቸውን ስታዩዋቸው ብዙ ጊዜ ተስፋ የቆረጡና የነሱ ህይወት ገህነብ ስለገባ የሌላውን ህይወት ቢችሉ ገህነብ ለማስገባት ሌት ተቀን እንቅልፍ እሚያጡ ናቸው.. :D ችግሩ ያለው ---- ከመሆናቸው እንጂ ለዛ እሚያጠፉትን ጊዜና ገንዘብ (ጊዜአቸውን በገንዘብ ብንቀይረው) እነሱ ጭራሽ በማያስቡበት መንገድ ባስብ እሚያተርፉት ድካም እና ጭንቀት ነው በራሳቸው ላይ...ከጭንቀትና አእምሮን እረፍት እስኪነሳ ከማሰብ እሚያተርፉት ደግሞ ልብ ድካም እና የደም ግፊትን መጨመር ነው...1 ነገር ግን ለ ሁላችን ጥሩ የሆነ ነገር እና ደስ እሚለን ነገር አለ ከ እነዚህ ሰዎች...ቢያንስ የተወሰኑ ሰዎች ስለ እናንተ ህይወት ያለ እረፍት እሚጨነቁ እንዳሉ ስታውቁ ...ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን እናንተን እሚተብቀው እነዚህም ሰዎች እንደ ፐርሰናል ሴኩሪቲ ከሁዋላችሁ እንደ ጭራ አለኡላችሁ.... NO FEAR!! :lol:
....አንዳንዱ ደግሞ ሱፐር ጅል ከመሆኑ ጋ ተደመሮ ስራውን ድርጊቱን እያወቃችሁ ስትይዙት አይደለሁም ብሎ ይምላል ያለቅሳል.... አንድ ጊዜ ስልክ ቁጥሩን እየዘጋ እየደወለ ሳነሳው እሚዘጋ ሰው ነበር ይህ ሰው እንቅልፍ አጥቶ ያን ያደርጋል ...እሱ በልቡ የስልክ ቴረር ማደረጉ ነው ...ይሄን ማደርግ እራሱ ከቴረሪዝማ ጋ የተያያዘ መሆኑን በሱ የዶሮ ጭንቅላት ሊገባው አልቻለም ...መቼም አይግባውምም ....ዛሬ ቴክኖሎጂ ስልክ እስካልተዘጋ ድረስ የት እንዳለ አይደለም ፖሊስ ማንም እንዲያውቅ እሚያደርገን ሶፍት ዌር አለ ....ለዚህ በቅርብ ለሽርሙጥና ስራ በ ሂውማን ትራፊከርስ ተይዛ የነበረች ልጅ እንዴት ከአፈኑዋት ሰዎች እንደዳነች ማየት ይበቃል....
...ደሞ እሚገርመው አንድ ጊዜ በመህል አገር ቤት መሄዱን አውቄ ሁሉ ነገር ሰላም ሆኖ ምንም ያልታወቀ ጥሪ ጠፍቶ ከርሞ ሲመጣ እንደግና ጀመረ ...ከምር በሳቅ ነው የሞትኩት :lol: ይሄ ሰው ብቻውን እሚሰራው ትያትር (የትያትር ሲሪየስ) መቼ እንደሚጨርሰው ባላውቅም ....የዛሬ ስልክ በ Ear phone selemisera እሚደውለው እንደማይሰማ ....የማይታወቅ ቁጥር አለመነሳትም እንደሚቻል ከ እለታት አንድ ቀን ይገባው ይሆናል ...ይሄ አይነህን ጨፍን ላሞኝህ የጅል ጨዋታውም ለራሱም ሳይገባው ወደ አፈር ይይመለሳል ...ለነገሩ እንዲህ አይነት ሰው ኖረ አልኖረ ማን ኢንተረስት ይኖረዋል ....ከምር አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ሰዎች ከመወለዳቸው በፊት ለማገድ እንዲረዳ ..አንድ ቤተሰቦቻቸው ምን አይነት የሴክስ ፖዝሺን እንደተጠቀሙ ቢታወቅ አሪፍ ነበር ....ወይም እዛው ማህጸን ውስጥ እንዳሉ ውህ አድርጎ ማስቀረት እንዲቻል የሚጠቁም አሪፍ እንደ አልትራ ሳውንድ አይነት መሳሪያ ቢኖር ...እንደዚህ አይነት ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያም ህእግራችን ስለ ሰው ኑሮ ሌት ተቀን ከሚጨነቁ ግን ምንም ለማያመጡ ሰዎች መኖሪያ ሳትሆን ቴክኖሎጂ እየተከታተሉ አገራቸውን ለማሳደግ እሚሞክሩ ዜጎች ይኖሩዋት ነበር.. :D
...አባቶች እሚሉትን ምቀኛ አታሳጣኝ እሚሉትን አባብል ረስቼ ብዙ ጻፍኩ ቅቅቅቅቅ ይቅር ይበለኛ ይሄን ምቀኛ ብቻ ሳይሆን ሌላም ይጨምርልኝ ... :lol:
...ምናልባት አንድ ተከታታይ ታሪክ ይወጣው ይሆናል ዋርካን ከተኛችበት ለማንቃት .. :D

ሰላም

I love to Corner ppls :lol:
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Wed Feb 27, 2013 3:09 pm

... ዋርካ ስትታመም ጊዜ ነው መስለኝ በጣም የደከመች ትመስላለች ...እሚያንቀሳቅሱዋት ሰዎች ጠፉ ....ለነገሩ ብዙዎቻችን አንድ ነገር ጤናማ ሲሆን ብቻ ነው እምንወደው ....;)
.... በህይወቴ ውስጥ አንድ አጋጥሞኝ እማያውቅ ነገር ገጥሞኝ እስቃለሁ....እስቃለሁ....
....ነገሩ እንደዚህ ነው ማን እሚባል ተናጋግሪ ...እንደ ሰው እሚያስብ አህያ ባያጋጥመኝም እንደ አህያ እሚያስቡ ብዙ ሰዎች ግን አጋጥመውኛል ብሎ የተናገረውን ያስታውሰኛል... .
....ብዙ ግዜ ጎበዝ የሆነ ሰው ጥላቻችሁን ከፊታችሁ ወይም ከተግባራችሁ አይቶ ካካባቢያችሁ እራሱን ያርቃል....እነዚህ አይነቶቹ ሰዎች ...በራሳቸው እሚተማመኑና እናተን ቀረቡ አልቀረቡ ልክ እንደ እናንተው ግድ እማይኖራቸው ናቸው....አንዳንዶቹ ደግሞ እምትሰጡዋቸው ማንኛውም የ ኢግኖር ምልክቶችም ሆነ ተግባር ጭራሽ አይገቡዋቸውም.... ለ እንደዚህ አይነቶቹ ጥላቻችሁን በግልጽ ትነግሩዋቸዋላችሁ.... እዚህ ልላይ እንደነዚህ አይነት ሰዎች በሁለት ይከፈላሉ....ምልክቶቹን ሳይገቡዋቸው ቀርተው ሲነገራቸው ገብቷቸው እሚሄዱና ....በጣም ደንቆሮ የሆኑት እና በራሳቸው ፍጹም እማይተማመኑት ደገሞ ...መንገር ብቻ አይደለም ህሊናቸንውንም ሆነ ሰውነታቸው እንደ አህያ ብትረግጡዋቸው አይገባችውም...በቃ ተፈጥሯቸው ነው ብፍጹም አይገባቸውም....እንደ እነዚህ አይነት ሰዎችን እናነት ምን እንድምታደርጉ አላውቅም ....እኔ ግን አንድ አደገኛ መፍትሄ አለኝ ...;)
...ልጁ እድሜው 25 ቦሪስ ይባላል...ልጅትዋ 20 ነች ...ልጅትዋ በጣም ትወደዋለች እሱ ደግሞ እንደ አብዛኞቹ በዛ እድሜ እንዳሉ ወንዶች ቁዋሚ የሆነ ጉዋደኝነት አይፈለግም....ልጅትዋ ደግሞ ያው የሴት ነገር በረጂም አላማና ተስፋ ከሱ መለየት አትፈልግም...እሱዋ እምታስበው ከሱ ጋ ተጋብታ ..ልጅ ወልዳ ወዘተ..:)
.....ይህቺ ልጅ ቦሪስ ከ እሱዋ እንዳይሄድባት በብዙ መልኩ መያዝ ትፈልጋለች ....ቦሪስ ደገሞ የአለም ሰልችታዋለች..ነገራት ነገራት አይገባትም....አንድ ጊዜ የ እናትዋን ካሜራ ሸጣ ..እናትዋ ቤት ውስጥ ገንዘብ ከሚያጠራቅሙበት ማጠራቀሚያ ውስጥ ገንዘብ ወስዳ ቦሪስ በደህና ግዜ አብረው እያሉ ሰአት ቤት ውስጥ በመስታወት ያዩትን ውድ ሰአት (እሱ እሚወደውን) ገዝታለት ይዛ ሄዳ ስጦታ ሰጠችው ....ቦሪስ ወንድማችን ስጦታውን አመስግኖ ተቀብሎ ለ እሱዋ ያለው ህሳብ ግን አልተቀየረም....ጭራሽ ሶፋ ላይ የሌላ ሴት ጡት ማስያዣ ስታይ አበደች ..እሱም አስወጥቶ አባረራት...
...በሁዋላ አንድ ጠንቁዋይ ቤት ቦሪስን እጁዋ እሚያስገባላት እሚያስችል ማስታወቂያ ተለጥፎ ታይና እዛ ትሄዳለች ...ያቺ ጠንቁዋይ ...ለ አንድ ጊዜ ጥንቆላ 280 ኢይሮ ትጠይቃትና ከብድር ባንክ ሄዳ 3ሺ ኢይሮ ትበደርና ከ እጅሽ እንዳይለይ ብላ የሰጠቻትን ትንሽዬ ከረጢት ነገር ..ቦሪስ ጋ ሄዳ ፊቱ ብታወዛውዝ ከ እጁዋ ነጥቆ ወረወረው ... :lol:
....እናትዋን ይዛ ቦሪስ ቤት ሄደው ሲደውሉ ሰአቱ በመስኮት ወረወረላቸው....ልጅትዋ ቦሪስ ላይ እንደ ሙጫ ተጣብቃ አልላቀቅ ብትለው እና ከ አዲስዋ ገርል ፍሬንዱ ጋ ሰላም ብታሳጣው በፍርድ ቤት ቴስት ሜሴጅ እንዳትልክ....እሱ ባለበት አካባቢ በ 2ሜትር ዙሪያ እንዳትገኝ እና ሌሎችንም ፕራይቬቶቹን እንዳትዳፈር በፍርድ ቤት አስወሰነባትና ቦሪስ ተገላገለ... :D
....በቁም ነገር ግን ሰው ለመን አልፈልግም ሲባል በዛ ላይ በተግባር እያየ እንደማይገባው አይገባኝም...ምናልባት እንደ እነሱ አህያ ብንሆን ሊገባን ይችል ይሆን....? :lol:
....ከምር የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ወደ 92 ሚሊየን ገባ ይባላል....ከምትወዱትና ከሚያወዱዋችሁ ዘመድ አዝማድና ጉዋደኞች..ወዳጆች ውጪ እናተን በመጥላት ግን ስለ እናንተ ሁሌ በመጨነቅ ጊዜ እሚያስልፉ ሰዎችን ማድነቅ ይገባችሁዋል በቁም ነገር...ምንም አይደለንም ብላችሁ እምታስቡ ከሆናችሁ እነዚህ ሰዎች ከ እናንተ በታች ስላለሉ አትጨነቁ ...ቢያንስ ከነሱ የተሻለ ኮንፊደንስ አላችሁ ስለ እነሱ እማያስጨንቃችሁ.. :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby Gosa » Wed Feb 27, 2013 5:26 pm

ሰላም ደጉ ሰው!
ያጫወትከን ታሪክ አሳዛኝ ነው:: ነገሮችን እንደየአመጣጣቸው ተቀብለን የማስተናገድ ችሎታችን ልበል ስጦታችን በእጅጉ ይለያያል:: አንዱ ባለ ስስ ልብ ፍቅርም ሆነ ጥላቻ በጣም የሚጎዳው ሲሆን ሌላው ደግሞ እንደ ቦሪስ አይነቱ በሮለር የማይጨፈለቅ "ተማመን" ልብ ያለው ነው::
ታዲያ ልጅቷ በጣም ነው የምታሳዝነው:: ምነው ከጅምሩም ባትነካካ ቅቅቅ:: ቦሪስ ዙሪያውን እየቃኘ የፈለገውን ሲያደርግ እና ሶፋዎች በ'ብራ" ሲሞሉ እያየች እንዴት ትቻለው:: ፍቅር ላይ አንዲት ጠብታ ቅናት ስትጨመርበት አይደለም ጠንቋይ ቤት ሌላውንም ያስሞክራል (ገመድ ምናምን):: እና የምልህ...እኔ ምንም በልጅቷ አልፈርድም:: እንደ "ሱፐር ፋስት ጄት" በጥቂት ሰአታት አለምን የሚዞሩ ሴቶች እንዳሉ ሁሉ ከሚያፈቅሩት ሰው ተለይተው አንድ እርምጃ መራመድ አቅቷቸው በፍቅር የተነሳ ከሰው በታች ሆነው የሚኖሩ ለፍቅር ብቻ የተፈጠሩት ሴቶችም መኖራቸውን አንርሳ:: ያልታደለችው የቦሪስ ጓደኛ እንደዚህ አይነት ሴት ትመስለኛለች:: ቦሪስን ካገኘኽው ቢያንስ 'ብራ"ዎችን ከመንገድ በማንሳት አእምሮዋን እንዲጠብቅላት ምከረው::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ደጉ » Sat Mar 02, 2013 10:10 pm

ጎሳ ሰላም ወንድማችን:)

...ልክ ነህ ነገሮችን እንደ አመጣጣቸው ተቀብሎ ማስተናገድን የምሰለ ነገር የለም....ህይወት መንገድዋ ቀጥ ያለ አይደለም ...እኛ እንጂ እንደ መንገዱ መጠማዘዝ ያለብን መንገዱ አይደለም.....ችግሩ ብዙ ጊዜ ሰዎች የህይወትን መንገድ በነሱ መንገድ ለመጠምዘዝ መሞከራቸው ነው...;)
....ፍቅር ካለ ጥላቻ አይኖርም ....ጥላቻ ካለ ደግሞ ፍቅርም አይኖርም....አንዳንድ የመንፈስ ደካሞች የሆኑ ግን በጥላቻ ፍቅርን ለማግኘት ይሞክራሉ....ልጅትዋ ስታደርግ የነበረው ይሄን ነው ...በጣም ስትጨቃጨቀው ልጁን ወደ ጥላቻ መራችሁ ....እሱዋን ማየት እስኪያስጠላውና ከዛም አልፎ በ ፍርድ ቤት እስኪገላገላት. :D እሱዋ ያልገባት ከልክ በላይ ማፍቅርዋና ከልኩ በላይ ከሱ ጋ ለመጣበቅ ያደርገችው ነገር ከሮ መበጠስ ደረጃ ደረሰ....እኔም በ እሱ ቦታ ቢሆን እንድዛ ልሆን እችል ይሆናል ....ሲበዛበት እማይሰላች አይኖርም .. :D
....ቅናት እኮ ራሱን የቻለ ነገር ነው ...ቅናት ሲበዛ በሽታ ነው ...ለሚቀናበት ሳይሆን ለሚቀናው ሰው ችግሩ....እሚቀናበትማ የበለጠ ይደስትበታል.. :D አስበቅ የኛ ህዝብ ብዛት ወደ 90 ሚለየን ገብቱዋል ...ከዛ ሁሉ ህዝብ በአንድ አንተ እሚቀናብህ ሲገኝ ደስ ሊልህ አይገባም...?:) ምንም አይደለሁም ብለህ እምታስብ ከሆንክ እሚቀናብህ ሰው እንድሆንክ ታውቃለህ....ከዛ ልክ እንደ እኔ ትኮራለህ .. :D
...ልክ ነህ ለፍቅር የተፈጠሩ ሴቶች አሉ ...እድለኛ ከሆንክ ታገኛቸው ይሆናል ....አንዳንዶች ደግሞ ለፍቅር ሳይሆን ለገረድነት እማትመኛቸውም አሉ ....እንደ እነዚህ አይነቶቹ ራሳቸውን ያውቁታል ..Die Hard አይነቶች ናቸው ...እሚፈልጉትንም አያውቁም ቅናታቸውም ወሰን የለውም እድሜ ልካቸውን እራሳቸውን እንዳቃጠሉ ይኖራሉ...በአንተ ህይወት ላይም ምንም እሚጨምርሩትም እሚቀንሱትም አይኖርም....ድካማቸውን ግን ፈጣሪ ጊዜ ካገኘ ይቆጥርላቸው ይሆናል .. :D
....ቦሪስን አላገኘውም በፍርድ ቤት ከተገላገለ በሁዋላ በሰላም ከ አዲስዋ ገርል ፍሬንዱ ጋ በሰላም እየኖረ ነው....ደህና የተገላገለውን ባላነሳበጽ.. :D

ሰላም ሁን :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Tue Mar 05, 2013 9:47 pm

..ዛሬ እዚህ ዋርካ ላይ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የወጣ አንድ የአባይን ግድብ በተመለከተ የተጻፈ ነገር አንብቤ ነበር....በዚህ ነገር አንድ ግራ የገባብኝ ነገር አለ....ግድቡን ለመገደብ መጀምሩን እምቃወምበት ምንም ምክንያት የለም ...ምክንያት ቢኖረኝም ምናልባት ሊፈጥር ይችል ይሆናል ስለሚባለው የኢንቫሮሜንታል ተጽእኖ ጋር ካለሆነ አረቦች ይከፋቸዋል ወይ ያብዳሉ ተብሎ ህዝባችን ወንዞቹን ገድቦ አይጠቀም ማለት ጅልነት ነው::
....ቁም ነገሩ ወያኔ አሰራ ሌላ ሰራ ሳይሆን ዋናው ግድቡ መሰራቱና ለተፈለገበት ጥቅም መዋሉ ነው ...በበኩሌ ወያኔ ጥሩ ሰራ የተባለውን እና ለህዝብ ይጠቅማል ብዬ እማምንበትን እምቃወምበት ምክንያት የለኝም....ወያኔ የሰራውን ጥፋት ነው ብዬ እማምንበትንም አልቀበልም .....ግን በደፈናው ወያኔን ስለጠላሁ ብቻ አገርና ህዝብ እሚጠቀምበትን እንዳይሰራ መቃወም ግን ለኔ ሌት ተቀን ከማይተኙልን አረቦች ጋር አብሮ እንደማበር ነው እምወስደው....በምንም አይነት የፖለቲካ መነሻ ይሁን ግድቡ ከተገደበ አይደለም አባይ ሁሉም ወንዞች ይገደቡ ....አገሪቱን በሬ ተምዶ ከማረስ እሚያድን እስከሆነ ድረስም ይሁን....መሬት ያለ አገባብ ከገብሬው እየተነጠቀ ለ አበባ እርሻ መሰጠቱን አልደግፍም ....ወይም የራሱ ህዝብ በቂ ሳያገኝ ቀጥታ ወደ ውጪ ለሚላክ የ እህል ፍጆታም ወገናችን ሲሰቃይ ማየትም አልፈልግም... በተለይ ከ አረቦች ጋር እሚደረግ ማንኛውማይነት ውል በደንብ መጠናት እንዳለበት ይህን ጉዳይ እሚያስፈፅሙት እሚያውቁት ይመስለኛል...አለዛም ከሌሎች አገሮች መኮረጃቸው አይቀርም...;)
..ከዛ ውጪ ያልገባኝ ግን የአባይን ግድብ በሚመለከት ለምን በውጪ ያሉም ሆነ ተቃዋሚዎች ከረቦች ጎን ለመቆም እንደ ፈለጉ አይገባኝም...? እዚህ እምታነቡ ጸረ ወያኔ የሆናቸሁ የዋርካ አባላቶችና...እንዲሁም ወያኔ የሆናችሁ የዋርካ አባላቶች መልሱልኝ...:) ጊዜ ካላችሁ ነው ከሌላችሁ ተውት ጎግል አደርጋለሁ እራሴው ...:)
....ስለ ገድቡ ስራ መደገፍ ወያኔ መሆን..አለምደገፍ ደግሞ ተቃዋሚ መሆን ተብሎ እንዳይታስብ ከወዲሁ አስታውቃለሁ...:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: (-:

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Tue Mar 05, 2013 11:04 pm

ሠላም ደጉ

አስተያየቴን ከመፃፌ አስቀድሜ ምድቤን ማሳወቅ ያለብኝ ይመስለኛል :wink: አስር ቁጥር ለብሼ በአጥቂ ቦታ ላይ የተሰለፍኩኝ የወያኔ ደጋፊ :D

ወደጥያቄህ ስመጣ.......እስከዛሬም እንዴት እንዳላስተዋልከው ገርሞኛል......ተቃዋሚዎች የሚያዩት እኮ ሐሳብን ወይንም የአንድን የልማት ስራ ጥቅምና ጉዳት አመዛዝነው ሳይሆን ምንም ሆነ ምን ወያኔ የሰራውን ስራ ሁሉ መቃወም ለእነሱ ፖለቲካ ይመስላቸዋል :D ......አባይ ይገደብ ሲባል እሪ ይላሉ; ስኳር ፋብሪካ ይቋቋም.....አሁንም እዬዬ :D.......የሰገራ ፍሳሽ በደጃፋቸው እየፈሰሰ በፈረሰ ቤት ውስጥ ለሚኖሩ የከተማ ነዋሪዎች እጅግ የተሻለና ለኑሮ አመቺ የሆነ የጋራ መኖሪያ ቤት ይሰራላቸው ሲባል.....ለምን ከሰገራ ላይ ይነሳሉ ብለው ኡኡታ :lol: ብቻ ስንቱን ቆጥሬ እዘልቀዋለሁ.......በአጭሩ ግን ወያኔን በሐሳብና በፖሊሲ ላይ ተመስርተው መቃወምና መብለጥ ስላልቻሉ ያላቸው አማራጭ የልማት ስራዎችን ሁሉ በጠቅላላ መቃወም ነው.......ለዚህም ነው ያለፉትን 21 ዓመታት እንኳን ብንመለከት የተቃውሞ ፖለቲካ "አድሮ ቃሪያ; ከርሞ ጥጃ" የሆነው

ሠላም

ደጉ wrote:..ዛሬ እዚህ ዋርካ ላይ ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ የወጣ አንድ የአባይን ግድብ በተመለከተ የተጻፈ ነገር አንብቤ ነበር....በዚህ ነገር አንድ ግራ የገባብኝ ነገር አለ....ግድቡን ለመገደብ መጀምሩን እምቃወምበት ምንም ምክንያት የለም ...ምክንያት ቢኖረኝም ምናልባት ሊፈጥር ይችል ይሆናል ስለሚባለው የኢንቫሮሜንታል ተጽእኖ ጋር ካለሆነ አረቦች ይከፋቸዋል ወይ ያብዳሉ ተብሎ ህዝባችን ወንዞቹን ገድቦ አይጠቀም ማለት ጅልነት ነው::
....ቁም ነገሩ ወያኔ አሰራ ሌላ ሰራ ሳይሆን ዋናው ግድቡ መሰራቱና ለተፈለገበት ጥቅም መዋሉ ነው ...በበኩሌ ወያኔ ጥሩ ሰራ የተባለውን እና ለህዝብ ይጠቅማል ብዬ እማምንበትን እምቃወምበት ምክንያት የለኝም....ወያኔ የሰራውን ጥፋት ነው ብዬ እማምንበትንም አልቀበልም .....ግን በደፈናው ወያኔን ስለጠላሁ ብቻ አገርና ህዝብ እሚጠቀምበትን እንዳይሰራ መቃወም ግን ለኔ ሌት ተቀን ከማይተኙልን አረቦች ጋር አብሮ እንደማበር ነው እምወስደው....በምንም አይነት የፖለቲካ መነሻ ይሁን ግድቡ ከተገደበ አይደለም አባይ ሁሉም ወንዞች ይገደቡ ....አገሪቱን በሬ ተምዶ ከማረስ እሚያድን እስከሆነ ድረስም ይሁን....መሬት ያለ አገባብ ከገብሬው እየተነጠቀ ለ አበባ እርሻ መሰጠቱን አልደግፍም ....ወይም የራሱ ህዝብ በቂ ሳያገኝ ቀጥታ ወደ ውጪ ለሚላክ የ እህል ፍጆታም ወገናችን ሲሰቃይ ማየትም አልፈልግም... በተለይ ከ አረቦች ጋር እሚደረግ ማንኛውማይነት ውል በደንብ መጠናት እንዳለበት ይህን ጉዳይ እሚያስፈፅሙት እሚያውቁት ይመስለኛል...አለዛም ከሌሎች አገሮች መኮረጃቸው አይቀርም...;)
..ከዛ ውጪ ያልገባኝ ግን የአባይን ግድብ በሚመለከት ለምን በውጪ ያሉም ሆነ ተቃዋሚዎች ከረቦች ጎን ለመቆም እንደ ፈለጉ አይገባኝም...? እዚህ እምታነቡ ጸረ ወያኔ የሆናቸሁ የዋርካ አባላቶችና...እንዲሁም ወያኔ የሆናችሁ የዋርካ አባላቶች መልሱልኝ...:) ጊዜ ካላችሁ ነው ከሌላችሁ ተውት ጎግል አደርጋለሁ እራሴው ...:)
....ስለ ገድቡ ስራ መደገፍ ወያኔ መሆን..አለምደገፍ ደግሞ ተቃዋሚ መሆን ተብሎ እንዳይታስብ ከወዲሁ አስታውቃለሁ...:)
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Re: (-:

Postby ደጉ » Wed Mar 06, 2013 10:57 am

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ሠላም ደጉ

አስተያየቴን ከመፃፌ አስቀድሜ ምድቤን ማሳወቅ ያለብኝ ይመስለኛል :wink: አስር ቁጥር ለብሼ በአጥቂ ቦታ ላይ የተሰለፍኩኝ የወያኔ ደጋፊ :D

ወደጥያቄህ ስመጣ.......እስከዛሬም እንዴት እንዳላስተዋልከው ገርሞኛል......ተቃዋሚዎች የሚያዩት እኮ ሐሳብን ወይንም የአንድን የልማት ስራ ጥቅምና ጉዳት አመዛዝነው ሳይሆን ምንም ሆነ ምን ወያኔ የሰራውን ስራ ሁሉ መቃወም ለእነሱ ፖለቲካ ይመስላቸዋል :D ......አባይ ይገደብ ሲባል እሪ ይላሉ; ስኳር ፋብሪካ ይቋቋም.....አሁንም እዬዬ :D.......የሰገራ ፍሳሽ በደጃፋቸው እየፈሰሰ በፈረሰ ቤት ውስጥ ለሚኖሩ የከተማ ነዋሪዎች እጅግ የተሻለና ለኑሮ አመቺ የሆነ የጋራ መኖሪያ ቤት ይሰራላቸው ሲባል.....ለምን ከሰገራ ላይ ይነሳሉ ብለው ኡኡታ :lol: ብቻ ስንቱን ቆጥሬ እዘልቀዋለሁ.......በአጭሩ ግን ወያኔን በሐሳብና በፖሊሲ ላይ ተመስርተው መቃወምና መብለጥ ስላልቻሉ ያላቸው አማራጭ የልማት ስራዎችን ሁሉ በጠቅላላ መቃወም ነው.......ለዚህም ነው ያለፉትን 21 ዓመታት እንኳን ብንመለከት የተቃውሞ ፖለቲካ "አድሮ ቃሪያ; ከርሞ ጥጃ" የሆነው

ሠላም

....10 ቁጥር ዳግማዊ ሰላም ሰላም :D ለሰጠህኝ አስተያየት አመሰግናለሁ....እኔ ደግሞ የ 1 ሰው (የራሴ) ተቃዋሚ ፓርቲ አባል ነኝ.... :D እረ እስከዛሬ እስከዛሬ ሳላስተውለው ቀርቼ አይደለም ....በዚህ ጉዳይ ግን በየቦታው እሚወራውን እሚጻፈውን ስሰማ ግን ግራ የገባኝ እኔ ነኝ ወይስ እነሱ ብዬ ማሰቤ አልቀረም.. ሲበዛብኝ...:D ከላይ የጠቀስካቸው አይነት ህዝብን ይጠቅማሉ ተበለው ለሚሰሩ ስራዎች እንቅፋት መሆንና ህዝቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን ማድረግ ከተጠቃሚው ህዝብ ጥላቻን እንጂ ልቡን እንዲያሸንፉ አያደርግም ....መቃወም ባለባቸው መቃወም...መደገፍ ባለባቸው መደገፍ ደግሞ አዋቂነትም ብልጥነትም ነው...;) በሙያ ደረጃ እሚያመጣ የጤና ችግር ወይ ለጥቂት ሰዎች ገንዘብ ተብሎ የብዙህኑን ባህላዊና አኑዋኑዋር መንገድ እሚቀይር ከሆነ የተለየ ጥናትና እና ዝግጅት ተደርጎበት ስራው እንዲሰራ ወይ እንዳይሰራ ፖዘቲቭ በሆነ መልኩ መቃወም አንድ ነገር ነው....በአጠቅላይ እሚሰሩ ጥሩ ስራዎችን ግን በወያኔ መንግስት ስር ተሰራ ብሎ መቃወም ግን አይታየኝም....10 ቁጥR ስማኝ እናንተ ስልጣን ለመልቀቅ ህሳብ ያላችሁ አይመስልም...ከዚህ በሁዋላ እንበልና 20 አመት ብትቆዩ ...እንደ ተቃዋሚዎቹ የአለማሰራት ተቃውሞ ህዝቡ እንዴት ይኑር ነው...?
...ሌላው ደግሞ አገር ውስጥ ገብተው ለመስራት ያስቡ ዜጎችን ከወያኔ ጎን የመመደብ ጉዳይ ነው....:) እኛ ውጪ ያለን ምናልባትም ምንም ልንሰራበት የምንችልበት ገንዘብ የሌለን ልንሆን እንችላለን ባብዛኛውም ነን አለዛም ደግሞ አፋችን እንጂ እጃችን ብሮ ይዞ አገር ውስጥ ነው...;) ሌላውን እንደዛ እያልን ተቃዋሚ መሆናችንን ለማሳየት ትያትር እምንሰራ አለን....እኔ ቤተሰቦቼ ዘመድ አዝማድ ጉዋደኞቸ ሁሉ እዛ አገር ውስጥ ይኖራሉ... እዛ ስለሚኖሩ የወያኔ ደጋፊ ስለሆኑ ነው ብዬ ማሰብ አለብኝ...? ከ 90 ሚሊየን በላይ የሆነው ህዝብ የወያኔ ደጋፊ አለምሆኑን ለማሳየት ከአገር መውጣት አለበት ማለት ነው..?.;)
...10 ቁጥር ወንድማችን ዳግማዊ ....የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን ፍቱ ወተው ላይፍን ኢንጆይ ያደርጉ ...:) አገር ውስጥ ያለውን ኮራፕሽን አስወግዱ ካልቻላችሁ በስምምነት ቀንሱ ....ህዝቡ በማንኛውም ነገር አጠቃቀም እንዲማር አድርጉ ....በመነድ ስነ ስራት አጠቃቀም....በታክሲ እና ትራንስፖርት አጠቃቀም.....የትራስፖርት መኪኖች ቴክኒካል ችግር የብዙ ሰዎችን ህይወት እይጠፋ እንደሆነ ግልጽ ነው...በትራንስፖርት መኪኖች ላይ ከባድ የተክኒካል ቁጥጥር ይደረግባቸው ..የ እህል ዋጋን ቀንሱ አሻጥረኛ ነጋዴዎችን አብዛኞቹ የናንተ ሰዎች ናቸው ይባላል ተቆጣተሩዋቸው ...ነጻ ገበያ ማለት ነጻ ዝርፊያ አለምሆኑን አስተምሩ ....ከምር አንድ ጊዜ ኤድናሞል አካባቢ ያለ ግሮሰሪ 45 ብር የተጻፈበት ቆሎ 50 ምናምን ብር ካሸር ጋ ተጠይቄበታለሁ ...:( መንገስት እንደ እነዚህ ያሉ ነጋዴዎችን በገንዘብ ቢቀጣ አባይን ብቻ አይደለም. ባሮንም እንገድብ ነበር ...;)
መልካም ቀን
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: (-:

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Wed Mar 06, 2013 5:06 pm

ሠላም ደጉ

እኔም ለምላሽህ በጣም አመሰግናለሁ

ሀሳቦችህን እስማማባቸዋለሁ......እንደውም የብቻህ የሆነውን የተቃዋሚ ፓርቲ "ማኒፌስቶ" አሳውቀኝና እኔም ሁለተኛ ተቀዳሚ አባል ብሆን ደስተኛ ነኝ :D

አይደለም እንደኢትዮጵያ ባለች ለዘመናት በተወሳሰቡ ችግሮች በተተበተበች ደሀ ሀገር ይቅርና በብዙ መስክ ወደፊት ተራምደዋል በሚባሉ ሀገሮችም ጭምር ያሉ መንግስታት ማሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች አሉ......አንተም እንዳልከው ወያኔ እንደመንግስት ትኩረት ሊሰጥባቸውና በየጊዜው ሊያስተካክላቸው የሚገቡ ብዙ የአፈፃፀምና የመመሪያ ጉዳዮች አሉ...ይኖራሉም.......እነዚህ ህፀጾች መጠቆምና መቃወም የአባት ነው....ግን እንዲያው በጥላቻ ብቻ እየተንደረደሩ 21 ዓመታት ሙሉ ከህዝብ ልማትና ጥቅም ጋር መላተም ግን የእኛው ጉዶች "ተቃዋሚዎች" የሙሉ ጊዜ ስራ ሆኗል......እንደውም አንዳንዴ ሳስበው የወያኔ ተቃዋሚ ነን ይላሉ እንጂ ሳያውቁት ከእኔ በላይ ዋነኛ የወያኔ ደጋፊዎች ናቸው :D

በመጨረሻም ከአንተ ጋር የማልስማማበትን ብቸኛ ነጥብ ላስቀምጥ

የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን ፍቱ ወተው ላይፍን ኢንጆይ ያደርጉ ...:)

በእኔ እምነትና መረጃ መሰረት በእስር ላይ የሚገኙ ሁሉ ወንጀለኞች ናቸው....እርግጥ ነው በተለያየ ሙያ የተሰማሩ እስረኞች አሉ......ወንጀለኛ ግንበኛ; ወንጀለኛ አናፂ; ወንጀለኛ ጋዜጠኛ; ወንጀለኛ ፖለቲከኛ; ወንጀለኛ ሹፌር; ወንጀለኛ መሀንዲስ; ወንጀለኛ ሊስትሮ....ወዘተ :D ስለዚህ ወንጀለኛ እስከሆነ ድረስ ፖለቲከኛ ሆነ ሊስትሮ ለውጡ አይገባኝም.....ለሁሉም የእስረኛ መብታቸው ተጠብቆ ፍርዳቸውን ሲያጠናቅቁ ይፈታሉ.....ከዛ ሁሉም "ላይፋቸውን ኢንጆይ" ማድረግ ይችላሉ :D

በድጋሚ አመሰግናለሁ
ደጉ wrote:
ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ሠላም ደጉ

አስተያየቴን ከመፃፌ አስቀድሜ ምድቤን ማሳወቅ ያለብኝ ይመስለኛል :wink: አስር ቁጥር ለብሼ በአጥቂ ቦታ ላይ የተሰለፍኩኝ የወያኔ ደጋፊ :D

ወደጥያቄህ ስመጣ.......እስከዛሬም እንዴት እንዳላስተዋልከው ገርሞኛል......ተቃዋሚዎች የሚያዩት እኮ ሐሳብን ወይንም የአንድን የልማት ስራ ጥቅምና ጉዳት አመዛዝነው ሳይሆን ምንም ሆነ ምን ወያኔ የሰራውን ስራ ሁሉ መቃወም ለእነሱ ፖለቲካ ይመስላቸዋል :D ......አባይ ይገደብ ሲባል እሪ ይላሉ; ስኳር ፋብሪካ ይቋቋም.....አሁንም እዬዬ :D.......የሰገራ ፍሳሽ በደጃፋቸው እየፈሰሰ በፈረሰ ቤት ውስጥ ለሚኖሩ የከተማ ነዋሪዎች እጅግ የተሻለና ለኑሮ አመቺ የሆነ የጋራ መኖሪያ ቤት ይሰራላቸው ሲባል.....ለምን ከሰገራ ላይ ይነሳሉ ብለው ኡኡታ :lol: ብቻ ስንቱን ቆጥሬ እዘልቀዋለሁ.......በአጭሩ ግን ወያኔን በሐሳብና በፖሊሲ ላይ ተመስርተው መቃወምና መብለጥ ስላልቻሉ ያላቸው አማራጭ የልማት ስራዎችን ሁሉ በጠቅላላ መቃወም ነው.......ለዚህም ነው ያለፉትን 21 ዓመታት እንኳን ብንመለከት የተቃውሞ ፖለቲካ "አድሮ ቃሪያ; ከርሞ ጥጃ" የሆነው

ሠላም

....10 ቁጥር ዳግማዊ ሰላም ሰላም :D ለሰጠህኝ አስተያየት አመሰግናለሁ....እኔ ደግሞ የ 1 ሰው (የራሴ) ተቃዋሚ ፓርቲ አባል ነኝ.... :D እረ እስከዛሬ እስከዛሬ ሳላስተውለው ቀርቼ አይደለም ....በዚህ ጉዳይ ግን በየቦታው እሚወራውን እሚጻፈውን ስሰማ ግን ግራ የገባኝ እኔ ነኝ ወይስ እነሱ ብዬ ማሰቤ አልቀረም.. ሲበዛብኝ...:D ከላይ የጠቀስካቸው አይነት ህዝብን ይጠቅማሉ ተበለው ለሚሰሩ ስራዎች እንቅፋት መሆንና ህዝቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን ማድረግ ከተጠቃሚው ህዝብ ጥላቻን እንጂ ልቡን እንዲያሸንፉ አያደርግም ....መቃወም ባለባቸው መቃወም...መደገፍ ባለባቸው መደገፍ ደግሞ አዋቂነትም ብልጥነትም ነው...;) በሙያ ደረጃ እሚያመጣ የጤና ችግር ወይ ለጥቂት ሰዎች ገንዘብ ተብሎ የብዙህኑን ባህላዊና አኑዋኑዋር መንገድ እሚቀይር ከሆነ የተለየ ጥናትና እና ዝግጅት ተደርጎበት ስራው እንዲሰራ ወይ እንዳይሰራ ፖዘቲቭ በሆነ መልኩ መቃወም አንድ ነገር ነው....በአጠቅላይ እሚሰሩ ጥሩ ስራዎችን ግን በወያኔ መንግስት ስር ተሰራ ብሎ መቃወም ግን አይታየኝም....10 ቁጥR ስማኝ እናንተ ስልጣን ለመልቀቅ ህሳብ ያላችሁ አይመስልም...ከዚህ በሁዋላ እንበልና 20 አመት ብትቆዩ ...እንደ ተቃዋሚዎቹ የአለማሰራት ተቃውሞ ህዝቡ እንዴት ይኑር ነው...?
...ሌላው ደግሞ አገር ውስጥ ገብተው ለመስራት ያስቡ ዜጎችን ከወያኔ ጎን የመመደብ ጉዳይ ነው....:) እኛ ውጪ ያለን ምናልባትም ምንም ልንሰራበት የምንችልበት ገንዘብ የሌለን ልንሆን እንችላለን ባብዛኛውም ነን አለዛም ደግሞ አፋችን እንጂ እጃችን ብሮ ይዞ አገር ውስጥ ነው...;) ሌላውን እንደዛ እያልን ተቃዋሚ መሆናችንን ለማሳየት ትያትር እምንሰራ አለን....እኔ ቤተሰቦቼ ዘመድ አዝማድ ጉዋደኞቸ ሁሉ እዛ አገር ውስጥ ይኖራሉ... እዛ ስለሚኖሩ የወያኔ ደጋፊ ስለሆኑ ነው ብዬ ማሰብ አለብኝ...? ከ 90 ሚሊየን በላይ የሆነው ህዝብ የወያኔ ደጋፊ አለምሆኑን ለማሳየት ከአገር መውጣት አለበት ማለት ነው..?.;)
...10 ቁጥር ወንድማችን ዳግማዊ ....የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን ፍቱ ወተው ላይፍን ኢንጆይ ያደርጉ ...:) አገር ውስጥ ያለውን ኮራፕሽን አስወግዱ ካልቻላችሁ በስምምነት ቀንሱ ....ህዝቡ በማንኛውም ነገር አጠቃቀም እንዲማር አድርጉ ....በመነድ ስነ ስራት አጠቃቀም....በታክሲ እና ትራንስፖርት አጠቃቀም.....የትራስፖርት መኪኖች ቴክኒካል ችግር የብዙ ሰዎችን ህይወት እይጠፋ እንደሆነ ግልጽ ነው...በትራንስፖርት መኪኖች ላይ ከባድ የተክኒካል ቁጥጥር ይደረግባቸው ..የ እህል ዋጋን ቀንሱ አሻጥረኛ ነጋዴዎችን አብዛኞቹ የናንተ ሰዎች ናቸው ይባላል ተቆጣተሩዋቸው ...ነጻ ገበያ ማለት ነጻ ዝርፊያ አለምሆኑን አስተምሩ ....ከምር አንድ ጊዜ ኤድናሞል አካባቢ ያለ ግሮሰሪ 45 ብር የተጻፈበት ቆሎ 50 ምናምን ብር ካሸር ጋ ተጠይቄበታለሁ ...:( መንገስት እንደ እነዚህ ያሉ ነጋዴዎችን በገንዘብ ቢቀጣ አባይን ብቻ አይደለም. ባሮንም እንገድብ ነበር ...;)
መልካም ቀን
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

(-:

Postby ደጉ » Wed Mar 27, 2013 4:58 pm

...ተመስገን ዋርካ እንደግና ነፍስ ዘራች .. :D ለነገሩ ሰው ብቻ አይደለም ሳይበርምን ቫይረስ ያጠቃዋል ፕሮቴክትድ ያልሆነ ግንኙነት ሲፈጽም ...;)

...... በ እስራኤልና አረቦች ጦርነት ላይ ነው ...ጦርነቱ በጣም ጦፉዋል ...ከ እስራኤል ወታደሮች አንዱ ....መቼም ከአረቦቹ ወታደሮች መህል አሊ እሚባል አይጠፋም አለና .... ጮክ ብሎ አሊ ብሎ ተጣራ ....ከዛ አንዱ አሊ የሆነው ....ወይ አለው ...ከዛ የ እስራኤሉ ወታደር .... ልንጭህ አለው.....አሊ ተናደደ....ትንሽ ሲዋጉ ቆዩና አሁንም እንደግና አሊ ብሎ ጠራው....አሊ አሁንም ወይ አለው...የ እስራኤሉ ወታደር ልንጭህ አለው....አሊ በጣም ተናደደ...ከዛ ከ እስራኤል ወታደሮች መቼም ሙሴ እሚባል አይጠፋም አለና....ጮክ ብሎ ...ሙሴ ብሎ ተጣራ ...የ እስራኤሉ ወታደር አሊ ነህ አለው...አሊም አዎ ! አለው..የስራኤሉ ወታደር ...አሁንም ልንጭህ አለው ይባላል...:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron