ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

(-:

Postby ደጉ » Sun Mar 31, 2013 2:02 pm

...ትናትና ማታ ዝም ብዬ ቲቪ ላይ ዛፕ ሳደርግ አንድ የሆነ ቶክ ሾው ላይ የተላለፈ ነገር እየመረጡ እሚያቀርቡበት አይነት ፕሮግራም ነበር....ቻናሉ ላይ ቆሜ መነሻውን ለመስማት ትንሽ ጠበኩ....ሴትየዋ ታለቅሳለች .... ቺት አደርገኝ እያለች ነው በጣም እምታለቅሰው ....ብዙ ስለምታለቅስ ከ እሱዋ 1 ቃል ለማግኘት ብዙ የ እንባ ጠብታዎች መፍሰስ ነበረባቸው....ከዛ ባሌ ቺት አደርገኝ ....ከ 2 0 አመታት በላይ አብረን ነው እምንኖረ ቺት እንዳደረገኝ እስካወቁበት ትናትና ግን በጣም አምነው ነበር ነው እምትለው....በመህል ታነበዋለች ...ከምር እኔም የወላድ አንጀት ስላለኝ ነው መሰልኝ አሳዘነችኝ...ከዛ የፕሮግራሙ አዘጋጅ በመህል ዝም ስትል ትጠይቃታለች....ባልሽ ቺት ያደርገሽ በሌላ ሴት ነው..? ሴትየዋ እያለቀሰች አይደለም ብላ አሁንም ታለቅሳለች....ትንሽ ዝም ስትል አዘጋጅዋ ..ባልሽ ቺት ያደርገሽ በሌላ ወንድ ነው...? ሴትየዋ አይደለም ....እንደግና ለቅሶ ...ከዛ የ ፕሮግራም አዘጋጅዋ ግራ ገብቱዋት ..ባልሽ ታዲያ በማን ነው ቺት ያደርገሽ ስትላት ሴትየዋ ....አንድ ምንም በማትረባ ነው ቺት ያደርገኝ ታላለች ....እኮ ነግሪን ስትላት "በላስቲክ ሴት" ነው ቺት ያደርገኝ ...ጭራሽ እቤት አስገብትዋት አብራን ትኖራለች ብላ ስቅስቅ ብላ ማለቀስዋን ቀጠለች... :D
...ግን በቁምነገር እንዲህ አይነት ነገር ቢያጋጥማችሁ ...ላስትክ ሴትየዋ የተነፋችበትን አየር አስወጥቶ ላስቲክዋን ከቤት ድራሽዋን ማጥፋት ሲቻል ..ሴንቴቲክ ሴትዮ ጋ ክስ ቲቪ ጣቢያ ድረስ መሄድ አለባት...? እርግጥ ሰውየው ሴትየዋን እንደ ሰደባት ነው እሚቆጠረው ...በህይወት ያለች ሴት እቤቱ እያለችው በገዛ ትንፋሹ የነፋት የላስቲክ ሴት ጋ ውድ ሚስቱን ቺት ማድረጉ ያሳዝናል....ምናልባት ከሚስቱ እማያገኘውን እከሱዋ አግኝቶ ይሆናል ማን ያውቃል... :D
....ለምን ባልየው ያለን አፌር በውጪ ያደርግም ብዬም አስቤ ነበር...ከዛ አንድ ጊዜ በዚሁ ጉዳይ ያጋጠመኝ ትዝ አለኝ ...እዚህ ዋርካም ክወደ ሁዋላ ጽፌዋለሁ አሁን ከታሪኩ ጋ አብሮ ለማንሳት ያክለ ንው እንጂ.. :D
....አንድ ሰው ጫካ ውስጥ ወክ እሚያደርግ ስልክ ለፖሊስ ይደውላል ....አንድ ያልታወቀ ሰው የሆነች ብሎንድ ጽጉር ያላት ሴት ከደፈረ በሁዋላ ገድሎ እመኪናው ሁዋላ ሲያስገባ አይቻለሁ ብሎ ነው ሰውየው ለፖሊስ የደወለው....ፖሊሶቹም በፍጥነት ቦታው ይደርሱና ሰውየውን እገዛ መርሰዲሱ ላይ አስደግፈው ከፈተሹት በሁዋላ የሁዋላ ኮፈኑን እንዲከፍት ትዛዝ ይሰጡታል...የሁዋላ ኮፈኑ ሲከፈት ያገኙት ነገር ቢኖር ይቺኑ የፈረደባት ምስኪን የላስትክ ሴት ነበር....በነገሩ እንሱም ስቀው ሰውየው ሌላ ቀን ጫካ ውስጥ እንዲህ አይነት ስድ ነገር እንዳይሰራ መክረው ለቀቁት... :D
...እነዚህ የላስቲክ ሴቶች ባይናገሩም ይህው ትዳርና የሰዎችን ሴክስ ህይወት እያበላሹ ነው እና ተጠንቀቁ... :D .
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Wed Apr 03, 2013 8:59 pm

..ሄይ ዋርካዎች አንድ ጊዜ የሆነ ሰው ከሱዳን አንድ ዜና አምጥቶ እዚህ ዋርካ አስነብቦን ነበር....እኔ ደገሞ ሲፈጥረኝ አንድ ታሪክ የተጀመረ መጨረሻውን መስማት እወዳለሁ...ምናልባት ህፒ ኢንድ ካለው በሚል ጉጉት...:)
...ታሪኩ እንዲህ ነበር እምታስታውሱት ካላችሁ....አንድ ሱዳናዊ ከፍየል ጋር ሴክስ ሲያደርግ ይያዝና ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርድ ቤቱ በአንቀጽ *** እዝባር *** ፍየልውን እንዲያገባ ይፈርድበታል::
...እኔ አሁን በጣም ያጉዋጉዋኝ ....ሰውየው ፍርድ ቤት ከወሰነ በሁዋላ ሰርጋቸው እንዴት እንደ ነበር .....ህኒ ሙናቸው እንዴት እንደ ነበር..አሁን ከፍየልዋ ስንት ልጆች እንደወለዱ ....የ እረፍት ግዜያቸውን የት እንዳሳለፉ ...ቤትና መኪናም ገዝተውም ከሆነ.....በገዙት መኪና እሱዋ የጸህይ መነጽር አድርጋ ሲት ቤልትዋን አድርጋ ምናምን ...ልጆችዋ ግምሽ ፍየል ግማሽ ሱዳናዊ ከሁዋላ በልጆች ወንበር ላይ ተቀምጠው ምናምን ... :D ከምር ብዙ ብዙ ነገር ማወቅ ፈለኩ ስለ እዛ ቤተሰብ....የደርሱበትን እምታውቁ ነግሩን ተፋተውም ከሆነ እንወቀው .. :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ገልብጤ » Wed Apr 03, 2013 9:17 pm

ቅቅቅቅ
ፍየሏ ስትሞት አላዘንኩም ወንድማችንን አላጽናናሁም ለማለት ነው :?:
እኛስ በጊዜው ነፍስ ይማር ብለናል
ክሪስታል የሚሉት ኒክ ኔም ነበር
ፌሽታውንም
መርዶውንም ይዞ የመጣው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby እብድሳይንቲስ » Thu Apr 04, 2013 2:40 am

የአቶ ቶምቤ እና ወ/ሮ ሮዝ ትዳር የተቁዋጨው በ ቶምቤ ዘልዛላነት የ ቤት ወጭ እሱዋንና ልጃቸውን በመከልከሉ ጎዳና ለጎዳና ምግብ ፍለጋ በ Juba ጎዳናወች ስትንከራተት ነበር:: የ አይን እማኞች ልጅየው ምኑም ቶምቤን እንደማይመስልና በ እጅጉም በአባቱ ያፍር እንደነበር ያወሳሉ::
መኪና ስለመግዛታቸውና ሮዝ መነጽር አርጋ ጋቢና ስለመቀመጥዋ የተዘገበ ነገር የለም:: ዳሩ ግን ከ ቶምቤ አፍቅሪ ቅምቀማነትና ፍየል አፍቃሪነት እንኩዋን መኪና መግዛት ይቅርና በረባሶ መግዛትም እንዳልቻለና በቸርኬ እንደሚነካው መገመት ቀላል ነው::
My take on this news:
They say "All women are attractive when a man is drunk." But Tombe proved, for some weirdos, that is not only the case.

ዜናውን እንደገና ለመገረብ ከታች ያለውን link ይጫኑዋል::
http://news.bbc.co.uk/2/hi/6619983.stm
እብድሳይንቲስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 16
Joined: Fri Oct 19, 2012 11:14 pm

(-:

Postby ደጉ » Thu Apr 04, 2013 12:25 pm

...ገልብጤና እብድ ሳይንቲስት አሳዛኙን ዜና ስላሰማችሁን እና ለሊንኩም ከልብ አመሰግናለሁ ....እኔ ወ/ሮ ሮዝ (ወ/ሮ ፍየል) መሞትዋን አለሰማሁም ነበር...ብሰማ ኖሮ ባለትዳሮቹ ትዝ ባላሉኝ ነበር....አንዳንዴት እድለኛ ትዳር አለ አንዳንዴ እደለ ቢስ የሆነ ትዳር አለ...እንደዚህ አይነት ትዳር ደግሞ ከ እድለ ቢስ ትዳር ነው እሚመደበው RIP Mrs Rose :(
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Tue Apr 09, 2013 7:12 pm

http://www.youtube.com/watch?v=AkrElfwdYKc&feature=youtu.be
....ይሄን ሊንክ እባካችሁ እንደ እኔ የወላድ አንጀት ያላችሁ አትዩት....ወንድ ልጅ ሲያለቅስ ጨክኖ ማየት እሚያስችላችሁ ጨካኝ ሴቶች እና ወንዶች ካላችሁ ግን እዩት...:)
....ግን ትዳር ይሄን ያክል ያስፈራል....? :(
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Sun Apr 21, 2013 11:27 am

... ለ ለንደን ማራቶን ልሄድ አስቤ ነበር ቦምብ ሳይሆን ውሾች ፈርቼ ቀረሁ....;) በቁም ነገር ግን አሁን የ ቦስተን ነዋሪዎች ንጹህ አየር መተንፈስ ጀምረዋል ....የ ከቤት እንዳትወጡ ትእዛዝ መቼም ሳያስጨንቃቸው አይቀርም... የሚዲያው ቀኑን ሙሉ ማጋነን ወደ ጎን ለትወው ...አዲስ ወሬ ተገኝቶ ስለ ሰሜን ኮርያ ወዲያው ተረሳ ቅቅቅ
.....ወንጀለኞቹ መያዛቸው ወይ መገደላቸው ዋጋቸው ነው ...ሰላማዊ ሰውን በፈንጂ ማጥፋት ሞራል የሌለው ተግባር ነው ...ግን ወንድማማቾች መሆናቸው ከታወቀ በሁዋላ ...FBI ታላቅየውን በራሽያ ሴኩሪቲ በኩል በደረሳቸው ኢንፎርሜሽን መሰረት ተከታትለው ምንም ስላላገኙበት መተዋቸውንም ጨምሮ ስለ ልጆቹ ቤተሰቦችና ህይወት ምንም የቀረ ነገር የለም ሰሞኑን ስንሰማ...:) ያልገባኝ ግን ኢራቅ እና አፍጋኒስታን ላይ የዘመቱ ይመስል ለ ሁለት ሰው የጎማ ታንኮች ያን ሁሉ ወታደር አሰማርተው እራሳቸውንም አገሬውንም ሲያስጭንቁ ማየት ግን ትያትር ነበር :D ...እኔ በቀላል ያስብኩት ከ ሆሊ ውድ አንደ ራምቦ ...ሸዋዚንገር...አይነት አርበኞች አምጥተው ይይዙዋቸዋል ብዬ ነበር...ከሁሉ ደግሞ ያሳቀኝ በ CNN የሆነ ሰው ለፖሊስ ልጁ ትንሽ ጀልባ ውስጥ መደበቁን እና ደም ማየቱን ከተናገረ በሁዋላ ፖሊስ ሄሊኦፕተር ላይ ባለ ልዩ መሳሪያ ልጁ እዛ መደበቁን እንድት እንደ ተደበቀ ማየት መቻላቸውና ከዛ ፖሊስ ወደ ቦታው መሄዱንና ልጁን ተደራድረው መያዛቸው ነው :lol: ሌላ ሰው ከመጠቆሙ በፊት በ ሂሊኮፕተር አግኝተውት ቢሆን ስለ መሳሪያው ባደንቅኩ ነበር ...አለዛ ግን ያን መሳሪያ መጠቀሙ አስፈላጊነቱ አልታየኝም...ተኛ ቆመ እግሩ ታየ አልታየ ምንም ሊጠቅም ...እንደው ወሬ ማራዘሚያ ካልሆነ :D
...መረጃ የደረሰው ክፍል ቸልተኝነት ነው እንጂ በጥንቃቄ የሰዎቹን እንቅስቃሴ ቢከታተሉ ይሄን ሁሉ ጦር ከማውጣት ቦርሳውን እንደ ተሸከሙ አደጋውን ሳያደርሱ በያዙዋቸው ነበር ...በጊዜ ያልታሹት ለምርኩዝ ያበቃል ሆነ ታሪኩ ...;)
...ኢሮፕ ውስጥ እንደዚህ አይነት ነገሮች ካንድም ሁለት ሶሶት ጊዜ ተከስተው ነበር ....በጋዜጣ ላይ ብቻ ነበር የተነበበው ....አሁን ያን ሁሉ የ CNN እና ሌሎች ሚዲያዎች ማጋነን ያየ ሌላ ጥፋት ለማድረስ እማያስብበት ምንም ምክንያት አይኖርም .. :D

ለሁሉም ከቦምብ ይሰውራችሁ :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby የጃማ ጦስኝ » Wed May 01, 2013 11:27 am

እንኵን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ


http://youtu.be/WTMZyphw4YM
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby ደጉ » Thu May 02, 2013 5:50 pm

የጃማ ጦስኝ wrote:እንኵን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ

....ወንድማችን እዚህ ድረስ በ እግርህ መተህ እንኩዋን አደረሳችሁ በምለትህ ከልብ አመሰግናለሁ እንኩዋን አብሮ ከሌሎቹም ጋ አደረሰን :)
...በዚህ አጋጣሚ ሰውነታችሁ ለማጽዳት የጾማችሁ ...ነፍሳችሁን ከ ስትሰሩ ከከረማችሁት ህጢአት ለማንጻት ለጾማችሁ ...እንደ እኔ ደግሞ እምትወዱትን ነገር ብቻ በመተው ለጾማችሁ ሁሉ እንኩዋን አደረሳችሁ...:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Thu May 16, 2013 12:29 pm

....ሰላም ሰላም ላላችሁ ለሌላችሁ ደግሞ ይሄን ፕሮግራም እንደ ጨረስን በቅናሽ እንሸጥላችሁዋለን...;)
....ባለፈው ሳምንት እሁድ ከሰአት በሁዋላ ነው አንድ ሲንግል ምናምን እሚል ሩም ስገባ ክብ ሰርተው አይባልም ለካ ፓልላይ ተሰልፈው ልበል ያወራሉ ...እሚወራው ሚስትህ ወይም ገርል ፍሬንድህን ሌላ ሰው ቢያውጣት ምን ታደርጋለህ ወይ ታደርጋላችሁ ነገር ነው ...አንድ የመንግስቱ ህይለማርያም ወንድም አለ አድሚን የሆነ እልህ እየተናነቀው ነበር እሚናገረው ....ልጅትዋን ጫፍዋን አልነካትም አለ ..ከዛ ወንዱን ግን አደርገዋለሁ ላለው ነገር መቼም ወንዱን ፈጣሪው ይሁነው እንጂ እንድሚያወራው ሰው ምንም እሚተርፍ አይምሰለኝም.. :lol:
....ቁም ነገሩ ግን እውነት ሚስቴ ወይ የሴትግ ጉዋደኛዬ ፈልጋ ላደርገችው ነገር እሱዋም ሆኑ ወንዱ መደብደብ አለባቸው ወይ ነው ...?
...እኔ በበኩሌ እንደ ተናጋሪው ጉልበተኛ አይድለሁም ...ግን ማንም ቱቦ ራስ ተነስቶ ሊመታኝም እሚችለኝ አይነት አይደለሁም ...ግን ሰው ላይ ቦክስ ለመጨበጥ በቂ ምክንያት ሊኖረኝ ይገባል ...
...በመጀምሪያ ደረጃ ወንዱን ጥፋተኛ እምጠላውም ሆነ እማጠፋው እኔ ከ አንዥቴ ከ ልብ ስሬ እምወዳትን ልጅ በግድ ከደፈረ ... እሱዋ በድርጊቱ ለተበደለችው ከ ሚያደርስባት የሳኮሎጂ ችግር እምትወጣበትን መንገድ ቶሎ መፈለግ የመጀምሪያው ሲሆን ከዛ በሁዋላ በሆነው ነገር ስሜትዋ እንዳይጎዳ መጠበቅና ለ እሱዋ ፍቅርን እንደ ቀድሞው መስጥት እና ማሳየት ሲሆን ...ወንዱን ግን ያው ጆሮውን ይዞ የውስጥ እግሩ እንደ ቃጫ እስኪበተን እንደ ጅራፍ ማጮህ ነው....በ እንደዚህ አይነት ሰው እሚጨክን ልዩ ልብ አለኝ ...የምሬን ነው ...እዘለዝለዋለሁ...:)
....በፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ ከተደረገ ደግሞ ያለውን ትያትር ይቀይረዋል...መጀመሪያ አንዲት ሴት ልጅ ከምትወደው ሰው ውጪ ከሄደች አንድ የተቸገረችበት እና ባልዋ እማይፈታአት ችግር አለባት...ያን በግልጽነት ከባልዋ ጋር ባለመወያየትዋ ወይም ባልዋ በቂ ጊዜ ስላልሰታት ባጠቃላይ ባልዋ እሚያደርግላት የነበረው እንክብካቤ ሲቀንስ እና ከመጠን በላይ ሲሆን ሴቶች ቶሎ ይጠቃሉ...እስካሁን ባሳልፍኩት ታሪክ ወዳው ወዱአት በ እሱ ላይ የሄደች ሴት አጋጥሞኝ ወይ ሰምቼ አላውቅም ....እኛ ወንዶች ግን ችግር የለብንም ከፈለግን ሄደት ብለን (ዞር ዞር ብለን) እተነሳንበት ቦታ ላይ ማረፍ እንችላለን...;) እነሱ ግን ተፈጥሯቸው አይደለም ....እንደ ወንድ የሆነ ጸባይ ያላቸው የሉም ማለቴ አይደለም ...እንደዛ አይነት ሴቶችም አሉ...ግን ደም ብዛት ያለባቸው ናቸው :)
....በንደዚህ አይነት ሁኔታ ባለ ሪሌሽን ውስጥ ያለች ሴት ሚስቴ ብትሆን እና ከሌላ ሰው ጋ ስትናጭ ባገኛት ..እሱዋ በገዛ ገላዋ ፈቅዳ ላደርገችው ....ያ ሰው ደካማ በሆነ ጎን ገብቶ እሺ ብላው ፈቅዳ እስካደርገ ድረስ ሁለቱንም እምደበድብበት ምንም ሞራሉ አይኖረኝም ...ተናጋሪው እንዳለው ሚስቱን መከላከል እማይችል ወንድ ወንድ አይደለም እንዳለው ሳይሆን እዚህ ላይ የኔ ወንድነትን ጥያቄ ላይ እሚያስገባው ምንድነው ነው..? እኔ በሰው ገላ ሰው ካልገደልኩ እና ካልቀበርኩ እያልኩ ባለገላዋ ቦታ እና ጊዜ እየመረጠች ድርጊቱን እምትፈፅም ከሆነ የኔ በማያገባው መግባት ወንድነት ጀግንነት ቆራጥነት ድል አድራጊነት አይመስለኝም...ባይሆን ለሁለቱም ቆንጆ ካርድ ገዝቶ መልካም እድል ተመኝቶ እንደ መሸኘት ያለ ምን አለ....?
...ሌሎቻችሁ ምን እንደምታስቡ አላውቅም እኔ ግን ከዚህ ህሳብ ሚሜትር ንቅንቅ አልልም.. :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu May 16, 2013 5:06 pm

ሰላም ደጉ:-

እንዴት ነህ? ባለፈው አንድ በአሲድ ተነክሮ እንኳን ተጠርቦ ሊስተካከል የማይችል የደደቢት ደንጊያ ወያኔ ስትወቅር አይቼህ አንተ ለደከምኸው አዘንኩልህ :)

በዚህ የባል እና የሚስት መሠራረቅ ጉዳይ የአንተ አመለካከት እንደ ጻዲቁ ዮሐንስ (የጎንደሩ ንጉሥ : የአፄ ፋሲል ልጅ) ነው ማለት ይቻላል:: በዚሁ ያዝልቅልህ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

(-:

Postby ደጉ » Sun May 26, 2013 10:50 am

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ደጉ:-

እንዴት ነህ? ባለፈው አንድ በአሲድ ተነክሮ እንኳን ተጠርቦ ሊስተካከል የማይችል የደደቢት ደንጊያ ወያኔ ስትወቅር አይቼህ አንተ ለደከምኸው አዘንኩልህ :)

..ሰላም ተድላ ወንድማችን .....ቅቅቅቅቅቅ@ በአሲድ ተነክሮ ....እኔ እኮ ሰው በየሄደበት እንደ እስጢፋኖስ በድንጋይ ሳይሆን በ ቃላት ሲወገር ሳይ ያስዝነኛል ....አእምሮው ተዛብቶ እሚያስብ ሰውን እኮ ቀስ ብለህ ነው መመለስ እምትችለው ....ሆይ ሆይ ሲባል ነው ካስተሳሰቡ ጋ ያበደው...እዚህ ደግሞ ታውቃለህ ሰው ማሳበድ ይችልበታል...ቅቅቅቅ

በዚህ የባል እና የሚስት መሠራረቅ ጉዳይ የአንተ አመለካከት እንደ ጻዲቁ ዮሐንስ (የጎንደሩ ንጉሥ : የአፄ ፋሲል ልጅ) ነው ማለት ይቻላል:: በዚሁ ያዝልቅልህ::

....ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ የ እሳቸውን እመልካከት ባላውቀውም ግን ሎጂክ እኮ ነው ...አለዛ በሰው ገላ ህላፊነት ወስደን መሰቃየታችን ነው...;)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

(-:

Postby ደጉ » Sun May 26, 2013 2:14 pm

....አንድ ጊዜ አዲስ አበባ አልበላም አልጠጣም ብዬ ካጠራቀምኩት ገንዘብ ላይ 50 የኢትዮጵያ ብር ኢንቬስት አድርጌ አንድ የ ጠበሳ መጽህፍ ገዛሁ...ከወደድካት አርካት...ጠበሳ 2 ይላል ....እኔም ለ እንደዚህ አይነት ነገር እጅግም ባልሆን (በግል ጥረቴ ያካበትኩትን) ነው እምመርጠው...ቢሆንም ግን እኔ ከማውቀው የተለየ ይኖረው ይሆናል በዛ ላይ ይቺ አገር ዲሞክራሲ ጥግ ድረስ ...ነጻ ገበያም ማለት ህዝቡ 150% እንደተረዳው በማሰብ (ስቀልድ ነው) ለነገሩ የፖለቲካ ተቃውሞ እስካልኖረው ድረስ ...ከባህል ጋ አብሮ ይሄዳል አይሄድም መንግስት ነኝ ባዩም ደንታ የለውም:: ለሁሉም ግን ገዝቼ መጣሁ....በስንት አመቱ ሰሞኑን ጊዜ አግኝቼ ባንበው ...ከምር በሳቅ ልሞት ነበር...ብሞት ኖሮ ይቺንም መጻፍ ባልቻልኩ...;) መጽህፉን በቁሙ ለመገምገም ወይም ለመውቀስ አይደለም...ምን አገባኝና ! ግን አንድናድ እማይሆኑ ነገሮችን ግን አይቼ ማለፍ ያልቻልኩትን ለማንሳት ያክል ነው....ሴቶችና ቀልድ በሚለው ስር ምን ይላል....የምታገኛት ሴት በጣም ቀልደኛ ልትሆን ትችላለች ...ነገር ግን ቀልድዋ እምብዛም ያልገባህ ማስመሰል አለብህ...ይላል...;) የኔ ጥያቄ ቀልደኛ ሆና ቀልዱዋ እሚያስቅ ከሆነ ለምን የማስመሰል ጨዋታው አስፈለገ ነው...;) እርግጥ ቀልድዋ ሳያስቀኝ እሱዋን ደስ እንዲላት ብዬ መሳቅ የለብኝም....እኔ እምናገረውም ቀልድ ካላሳቃት ...ያው አላሳቃትም ...እኔም ላስቃት አልቻልኩም ማለት ነው...ከሁሉ መጥፎ ደግሞ ማሳቀንደማልችል እያወኩ ለማሳቅ እማደርገው ሙከራ ነው....የኔ ልምድ ምን ይላል ...ማሳቅ እማትችል ከሆነ ጨርሶ ለማሳቅ አትሞክር ነው...;)
...እዛው ገጽ ልይ ደግሞ ብዙ አታውራ ይልና ሴቶች ብዙ እሚሰማ እንጂ እሚያወራ ወንድ አይወዱም ይላል...ከዛም 2 መስመር ሳይርቅ ...ዝጋታም አትሁን ከ እሱዋ ጋ ማውራት መቻል አለብህ ይላል....ከምር እዚህ ጋ እኔ እራሴ ተቸገርኩ.... እዛ ጋ ያለውን እቃ ይዘህልኝ ና ግን ከዚች ቦታ እንዳትንቀሳቀስ ማለት አይነት...;)
...መጽህፉ የተተርጎመ መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ ለምን በራሱ አገላለጽ ለመጠቀም እንዳልሞከረ ግን አልገባኝም...ለዛች ቀጭን መጽህፍ 50 ብር ሲበዛባት ነው.. :D
...ቆይ ደግሞ ሶሶት የብልት አይነቶች ብሎ ጥንቸል ..ኮርማ...ፈረስ ..ያላቸውን ልዝለላቸው....ከቤት እንስሳት ጋ ሊያጋጨኝ ነው...;)እረፍት አድርጌ ለመለስበት ....:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

:-)

Postby ደጉ » Sun Jun 09, 2013 11:23 am

....በቀደም ሩሲያ ውስጥ በሚገኝ ጎቴ ኢንስቲቲዩት ውስጥ አንድ ዝግጅት ነገር አድርገው ...ሰዎች ስትሞቱ በመጨረሻ ምን ምን ይዛችሁ መሄድ ትፈልጋላችሁ ብለው ባዶ ሻንጣ አስቀምጠው ነበር....:) ህሳቡ አሪፍ ነበር....ሰው ከሞተ በሁዋላ ምንም ስለማያስፈራው ኮንዶም ይዞ መሄድ አያስፈልገውም....ማጨስም አልኮልም መጠጣት እሚፈልግ ካለ ከሞተ እሚያሳስበው ነገር አይኖርም...:) የ አንዳንዱ ግን ከምር ያስቃል አንዱ ላፕ ቶፑ ላይ ፌስቡክ አካውንት አዘጋጅቶ እንድሚይዝ ሲናገር ...አንዱዋ እንደ እኔ ደግ ይሆነችው ደግሞ እዛ ላሉት ሁሉ ሮዝ አበባ ልትሰጥ ሻንጣውን ሞልታው ነበር.... አንድ ጊዜ ሞባል ፎን እንደ ተጀምረ ....ድንገት መሞት የነበረባቸው ሰዎች ሲሞቱ ..የመቃብራቸው ህውልት በ ሞባይል ፎን ቅርጽ እንዲሰራላቸው ተናዘው የሞቱ ነበሩ....ሞባይል መቼ እንደ ተጀመረ የወደፊቶቹ አርኪዎሎጂስቶች ቆፈረው ካልገኙት በቀላሉ ያውቁታል ማለት ነው...;)
...እውነት ግን ሆኖ አይሆንም እንጂ ቢቻል ይዛችሁ እምትህእዱት ምን ሊሆን ይችላል...? :D እኔ እሺ አትልም እንጂ እንጂ ገርልፍሬንዴን ይዣት ብሄድ ደስ ይለኛል..እዛ አዲስ ከመፈለግ ...:)
....መኪና ግን አታስቡ እዛ ከፍተኛ የኢንቫሮሜንት ቁጥጥር ስላለ አይቻልም... :D ከላሽንኮቭና እና ዙ 23 ምናምንም አይቻለም ...ስለዚህ ወያኔ የሆነ ጠበንጃ ራስ መሄድ አይችላም ማለት ነው...ሶሪ..:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

:-)

Postby ደጉ » Wed Jul 24, 2013 10:44 am

.....እስኪ ደግሞ ...

አንድ ዶክተርና አንድ የ መህንዲስ ..አንዲት ልጅ ይወዳሉ (በጋራ) እናም ....ዶክተሩ ቀን በቀን ጽጌረዳ አበባ ሲሰጣት...መህንዲሱ ደግሞ ቀን በቀን አፕል ይስጣታል....ለጅትዋ ወደ መህንዲሱ ስታደላ ያየው ዶክተር ነገሩ በጣም አናዶት...ስማ እኔ ሁል ጊዜ አበባ ስሰጣት አንተ ለምንድነው አፕል ብቻ እምትሰጣት ቢለው ..ዶክተሩም ONE APPEL A DAY KEEP THE DOCTOR AWAY አለው ....ዶክተሩ ተናደደ ...መህንዲሱ ፈነደቀ....;)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4507
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests