ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Tue Aug 30, 2016 3:57 pm

ሰላም ሰላም የዋርካ ሰፊ ህብረትሰብ ዋርካ በጣም ለረጂም ጊዜ ተዘግቶ ሲከፈት ... ቤቱ ቡዋራ በ ቡዋራ ይሆናል ብዬ ገምቼ ያላመጣሁት የትስዳት እቃ እልነበረም ግን እግዜር ይስጣቸው ራሳቸው በደንብ አትስድተውት ነው የከፈቱት ... በ አጋጣሚ ጥሩ የ ፖልቲካ ትኩሳት ባለበት ወቅት ነው የከፈቱት ..ምናልባትም አዲሲቱ ዋርካ በ አዲስ መንግስት ....፡D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ዋናው » Tue Aug 30, 2016 8:30 pm

ሠላም ደጉዋችን ስላየሁ ደስ ብሎኛል፡፡
እኔ እራሴ በደሕና ግዜ የከፍትክዋቸሁን ቤቶች ድጋሚ ሳገኛቸው ገርሞኛል ፈራርሰው ይጠብቁኛል ብዬ ነበር፡፡
በእውነቱ ከሆነ ከዋርካዊያን ጋር ድጋሚ እንገናኛለን የሚል እምነት አልንበረኝም፣ ቀስ በቀስ ብዙዋኑ እንደሚሰባሰብ ተስፋ አለኝ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2802
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Wed Aug 31, 2016 10:08 am

ዋናው ወንድማችን ሰላም ሰላም እኔም ስላየሁህ በጣም ነው ደስ ያለኝ .... ያ ልክ ነህ የነበረውን እንዳልነበረ ያደርጉታል ብዬ ነበር እኔም :D ደግነቱ ግን ምንም ልሆነም ግን የጎደለ ነገር ያለ ይመስለኛል የ ፕርይቬት መልክት መላኪያ ላይ እልቻልኩም ፡) ዋናው ልክ ነህ ቀስ በቀስ ሁሉም ባይሆኑ ብዛኞቹ ይመጣሉ ብዬ አስባለሁ ...፡) መልካም ጊዜ!!
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ገልብጤ » Wed Aug 31, 2016 10:42 am

ደጉ እኛም ወደ ዋርካ በዛሬው ለት ብቅ ብንል ያው የድሮው ስማችን ከነፖስቶቻችን እንዳለች አለች
የሚገርመው ከ2 አመት በህዋላ መክፈታቸው ነው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Thu Sep 01, 2016 4:36 pm

ገልብጤ wrote:ደጉ እኛም ወደ ዋርካ በዛሬው ለት ብቅ ብንል ያው የድሮው ስማችን ከነፖስቶቻችን እንዳለች አለች
የሚገርመው ከ2 አመት በህዋላ መክፈታቸው ነው

ገልብጤ ሰላም ወንድማችን ከነ ፖስቶቻችን መመልሳቸው ጥሩ ነው ለነገሩ ከድሮም ዋርካን ሲያድሱ ፖስት የተደርጉትን አያበላስሁም በጥንቃቄ አውጥተው ካፀዱ በሁዋላ መለሰው በ ስነ ስርአት መደርደሪያዎቹ ላይ እንደነበሩ ያስቀምጡዋቸዋል ... :P ልክ ነህ ሁለት አመት ሆናቸው ቀላል ስራ እንዳልነበረ መገመት ይቻላል ፡፡ ቀስ በቀስ የዋርካ ህብረተሰብ ሚመለስ ይመስለኛል እስከዛ እያሙዋሙዋቅን መጠበቅ ነው ... :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ጌታ » Thu Sep 01, 2016 7:49 pm

መጣና መጣና ባዲስ ዓመት!!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3030
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ገልብጤ » Thu Sep 01, 2016 9:34 pm

ጌች እጅ ከምን
ሠው እንዴት አርጅቷል ግን
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

ሲያምረኝ አትሰጠኝም

Postby ቻላቸው » Mon Sep 12, 2016 11:16 am

[quote="ሊስትሮው"]አቶ ደጉ እስኪ ባክህ ቤቢ ገርልን ንገርልኝ በምን ቋንቋ እንደሚገባት አላቅም ና እባክህ እርዳኛ .....
ሊስትሮው ነኝ
ከንትን ሰፈር

አመሰግናለሁ ለትብብርህ አባ

እስኪ ይቅናኝ ደሞ በዚህ ካልሆነም ......

ባይ[ሚስትየ ሲያምርኝ አትሰጠኝም ምን ትላላችሁ]
ቻላቸው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 306
Joined: Mon Nov 23, 2009 4:24 am
Location: politics

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Sat Sep 17, 2016 8:46 pm

ሰውየው ቡና ቤት እንደ ገባ አህያ ቡና ቤት ውስጥ አየ አሉ ...አሉ ነው ከዛ የ ቡና ቤቱን ባልቤት ....ወንድማችን አህያው እዚህ ምን ያደርጋል ሲለው ...ባለቤቱም ይልቅ አህያውን ካሳቅከው 10 ሺ ብር እሰጥሀለው ይለዋል ...ሰውየውም ለ አህያው በጆሮው ሹክ አለው ...አህያውም መሳቅ ጀመረ...ባልቤቱም እሺ አሁን ደግሞ አህያውን ካስለቀስከው 10 ብር እጨምርልሀለሁ አለው ....ሰውየውም አህያውን ብቻ ሊያይበት ወደ ሚችል ጥግ ቦታ ወስዶ አሳየው.....አህያውም ማልቀስ ጀመረ ....ባልቤቱም ያየውን ማመን አልቻለም ...ግን አለው እንዴት ነው አህያውን ልታስቀውና ልታስለቅሰው የቻልከው ብሎ ጠየቀው ...ሰውየውም መጀመሪያ የኔ አብሮ አደግ ካንተ ይበልጣል አልኩት ...ከዛ እሾፍኩት ;-)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Mon Sep 19, 2016 7:42 am

ከ ፐብሊክ ሚዲያ ላይ ያገኘሁት :-)

ምክትል ጠ/ ሚ ተብዬው ደመቀ መኮንን ላደረበት( ይቅርታ ለከረመበት) ህመም እስራኤል ሀገር ሄዶ አጠቃላይ ምርመራ ካደረገ በኋላ ውጤቱን ለመስማት ዶክተሩ ጋር ይቀርባል ።
ዶክተሩም ውጤቱን ከወረቀቱ እያነበበ
" ውጤቶቹ ሁለት ናቸው!! ያው አንደኛው የምርመራው ውጤት አለብህ ነው የሚለው!!"
" ምንድን ነው ያለብኝ ዶክተር!??!!" በድንጋጤ እየተርበተበተ !!
" መሀይምነት ነው ያለብህ !! ግን እንዳትከፋ!! ሁለተኛው ውጤትህ ደሞ ነፃ ነህ ይላል'ኮ" ዶክተሩ ቀጠለ።
" ከምን ??!!" በድንጋጤ ጠቁሮ የነበረ ገፁ ፈካ ማለት እየጀመረ!!
" ከእውቀት ነፃ ነህ!!" :-)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Fri Oct 07, 2016 5:13 pm

አንድ ጊዜ ድሮ ልጆች እያለን መንግስት አባይን ለመገደብ ጊዜ እና ገንዘብ አጥቶ በነበረበት ወቅት ...እኛ የሰፈር ልጆች በራሳችን አነሳሽነት ክረምት ሲሆን በሰፈራችን ቦዮች እሚያልፈውን ጎርፍ ለመገደብ ጥረት እናደርግ ነበር .... ያን ግድብ ስንገድበው በ ጭቃና በ ድንጋይ አድርገን ነበር ..ግንቡ የቻለውን ያክል ውሀ ከያዘ በሁዋላ ቀስ በቀስ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ውህ መስረቅ ይጀምራል ...እኛም ያንቺ ችግር የታየባትን ቦታ ለመድፈንና የ ግድቡ እድሜ እንዲረዝም እንሞክር ነበር .... ችግሩ ግን አንድ ጊዜ ውሀ እዚህም እዛም ቀስ በቀስ መውጫ መንገድ ሲያገኝ የጠቅላላ ግድቡን ህልውና እያሳጣው ና ግድቡም መቁዋቁዋም እማይችለው ደረጃ ይደርስና ከሚመጣው ጎርፍ ጭምር የገደብነው የ ጭቃ ግድብ መናድና መፍረስ ይጀምርና በተጠራቀመው ውሀና ተጨማሪ በሚመጣው ጎርፍ ጠቅላላ ግድቡ ተጠርጎ ይሄዳል፡፡
አሁን ሚታየኝ ችግርና መፍትሄ እየሰጠ ያለው የመሰለው ክፍል ይሄን ግዜ ያስታውሰኛል.... ቅቅቅቅቅ
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Sun Oct 09, 2016 2:53 pm

ፑ !!!! ሰሞኑን መንግስት ሁሉ ነገር ሱሪ ባንገት የሆነበት መሆኑን በግልፅ ለህዝብ በ አስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ አሳውቁዋል ...ያ ማለት በፊትም ያልነበረ የዲሞክራሲ መብትን እስከ መግፈፍ ይደርሳል ማለት ነው... ቅቅቅቅቅቅ የተናቀ ምን ያስረግዛል እንደሚባለው እያጋጨን እድሜ ልክ እንኖራለን እሚለው ሀሳብ እና አመታት መንግስት ነኝ ሚለው ክፍል ሲደክምበት የነበረው እርስ በርስ የማጋጨት ስራ በ አንድ ጊዜ አፈር በልቶ ...ጥቂቶች የ ክንፍ ተጭዋቾች እነጀታቸው ማረሩን እዚህ ዋርክ ላይ እያየን መሆኑ ...ከምር እኔን በጣም እያሳቀኝ ነው ...ዝምብሎ ማየትን የምሰለ ነገር የለም 1000 ር እስ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ መፈብረክ እና ለማሳመን መሞከር ዛሬ ሁሉን ነገር በ ተለያዩ ሚዲያዎች ለምናየው ቀላል ትግል ይጠይቃል...?? ቅቅቅቅቅ ደግሞ ከሁሉ እሚያስቀው ... የ ግብፅ እጅ እግር አለበት ብለው እሚያቅራሩት ነው ...ህዝብ አሸነፈን ላለማለት ይመስላል ...ለሁሉም እነሱም ስልጣን ሲይዙ ሻቢያም ሆነ ሱዳን ግብፅ ኩዌት እና ሌሎችም የ አረብ አገሮች ያልተባብሩዋቸው ይመስል አሁን ሻቢያ እረዳ ግብፅ እረዳ እሚያስለቅሳቸው ነገር አይገባኝም፡፡ በ ጦርነትም ሆነ በሰላማዊ መንገድ መታገል የፈለጉት ድርጅቶች መብታቸው እንደሆነ አምናለሁ፡፡ በሰልማዊ መንገድ እሚታገሉት የተቃዋሚ ድርጅቶች በነፃነት መንቀሳቀስ አይችሉም ቢሮአቸው በየጊዜው እየተበረ እና መሪዎቻቸው በየጊዜው እየታሰሩ ነው፡፡ ያለ ምንም ተቃዋሚ 100% በ ምርጫ ያሸነፈው መንግስት (እዚህ ጋ አንዴ አብረን እንድንስቅ እጠይቃለሁ..ቅቅቅቅቅቅ) በየትኛውም የ አለም ክፍል 100 % አሸንፎ ስልጣን የያዘ የ ፖለቲካ ድርጅት ባልመኖሩ ...:-) አፍሪካ ውስጥ ግን "ይቻላል!!" ቅቅቅቅ ያም ሆነ ይህ ህዝብን በመበደልና በማፈን የትም መድረስ እንደማይቻል ... በአገሪቱ ውስጥ በልማታዊ ዲሞክራሲ ስም ለተወሰኑ ዜጎች ጥቅም ብቻ እሚውሉ መዋቅሮች መዘርጋታቸው ከዛም አልፎ የ አባይን ድልድይ በቤንሻንጉል ክልል ከዛም ቤን ሻንጉልን በካርታ እንዳየነው ከመተህራ እና ከሌሎች የ አማራ ክልል ተብለው ከሚጠሩት ጋር አንድ በማድረግ የታልቅዋ ትግርይን ምስረታን ለማሳካት የነብራቸውን ህልም ከድሮም ጀምሮ ሲነገረን የነበረ እና በካርታ ተደግፎ ስናየው የነበርን ሲሆን ...እነደ ራስ ዳሽን ያለ ተራራ መሰረቁን እና መመለሱን ከይቅርታ ጋር ስንሰማ ከምር ነገሩ ከማሳቅም አልፎ ያሳዝናል ...ያም ሆነ ይህ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም ይባላል ... እኛ መንግስት እሚሰራውን የደከመ ቲያትርም እናያለን .... ተቃዋሚዎቹም የጀመሩት መንገድ አምራሩ ላይ ያሉትን ጥቂት ሰዎች እንዴት እንዳስጨነቀም እያየን ነው እናያለንም... :-)
በ አቶ ህይለ ማሪያም ቀልድ ልለያችሁ ...
አሉ ነው ....ቅቅቅቅቅ አቶ ህይለማሪያም እንደውም ሰሞኑን የሰማሁትን ታሪክ ልንገራችሁ ብለው ...ኢሬቻ ላይ አንዱ ወጣት መሳሪያ የታጠቀውን ፖሊስ ወደ ገደሉ ሲገፋው ..ፖሊሱም "ዛሬ ግፋኝ ግድ የለም ተሸንፌአለሁ" ብሎ ወደ ገደል ገብቶ ሞተ ... :-( እዚህኛው ጆክ ላይ ህዝቡ እንደ መጀምሪያው ጆክ ልጁን ይዞ አለመግረፋቸው በጣም ነው እሳዘነኝ ...ያ እሚይሳየው ህዝቡ የመጀምሪያውንም ወጣት ያለ ጥፋቱ ይዘው መግረፋቸው የ ቆጫቸው ይመስልል ...ቅቅቅቅቅ
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Tue Oct 11, 2016 3:23 pm

ከ የኔ ቲዩብ ....
ምስጋና ለ ፀህፊው ...መልካም ጊዜ ... :-)
ይሁንተኞች
""""""""""""""
በ ዳኒኤል ክብረት
በአንድ ሀገር ውስጥ አንደ የዝንጀሮ አለቃ ነበር አሉ ኦሮሞዎች ሲተርቱ፡፡ በመልክ እና በቁመት፣ በትከሻ እና በክብደት የሚመስሉት በዛ ያሉ ዝንጀሮዎች በመንጋው ውስጥ ነበሩ፡፡ ታድያ ለንጉሡ አጎንብሱ በሚለው መመርያ መሠረት የሚመሩ ጥቂት ዝንጀሮዎች አለቃቸውን ለማስደሰት አሰቡ፡፡ አስበውም አልቀሩ እንዲህ አሉት፡፡ «እርስዎን ከሌሎች ዝንጀሮዎች መለየት አልቻልንምና፣ ለየት የሚያደርግ ምልክት ያድርጉ» አሉት፡፡ እርሱም በራሱ ላይ የብረት አክሊል ለማድረግ ወሰነ፡፡
እነዚያ እበላ ባይ ዝንጀሮዎች እየተከተሉ አባራ ሳይነካው ልብሱን ያራግፉለታል፡፡ ሳያስነጥሰው ይማርህ ይሉታል፡፡ ሳያመው ተሻለዎት? ብለው ይጠይቁታል፡፡ ሳይቀልድ ይስቁለታል፡፡ ሳያዝን ያለቅሱለታል፡፡ ያልተናገረውን ይጠቅሱለታል፡፡ ባልሆነው ነገር ያወድሱታል፡፡
ይህንን ሲመለከት ጊዜ ጠባዩ እየተቀየረ መጣ፡፡ ተሳስተሃል የሚለውን ማንኛውንም ዝንጀሮ እንደ ጠላት ማየት ጀመረ፡፡ ሲጠሩት አቤት፣ ሲልኩት ወዴት የማይለውን ሁሉ ለመቅጣት ተዘጋጀ፡፡ እርሱ ከሚያስበው በተለየ የሚያስበውን ዝንጀሮ ዝንጀሮነቱን ይጠራጠር ጀመር፡፡
ቀስ በቀስ አለቃው ቤተ መንግሥት እርሱ ያለውን ብቻ በሚቀበሉ ዝንጀሮዎች እየተሞላ መጣ፡፡ በጥንት ጊዜ በቤተ መንግሥት ውስጥ ሦስት ዓይነት ባለሟሎች ይቀመጡ ነበር አሉ፡፡ ከንጉሡ የሚበልጡ፣ ከንጉሡ የሚስተካከሉ፣ ከንጉሡ የሚያንሱ፡፡
ከንጉሡ የሚበልጡት ይገሠጹታል፤ ከንጉሡ የሚስተካከሉት ይሟገቱታል፣ ከንጉሡ የሚያንሡት ይከተሉታል፡፡ ከንጉሡ የሚበልጡ ብቻ ከሆኑ ንጉሡ ሥራ መሥራት አይችልም፡፡ በእነርሱ ተጽዕኖ ውስጥ ብቻ ይወድቃልና፡፡ ከንጉሡ የሚተካከሉ ብቻ ከሆኑ ሲሟገት ብቻ መኖሩ ነው፡፡ ከንጉሡ የሚያንሱ ብቻ ከተሰበሰቡ ምክር ቤቱ በይሁንተኞች ይሞላና እርሱ ያለውን ብቻ እየተቀበሉ ገደል ሊከቱት ነው፡፡
ይኼኛው የዝንጀሮ አለቃ ግን ሁለቱን ዓይነት አማካሪዎች አጠፋቸው፡፡ ከእርሱ የሚበልጡትን እና ከእርሱ የሚስተካከሉትን፡፡ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ይሁንተኞች ብቻ ሞሉ፡፡ ምክሩን የሚቀበል እንጂ እርሱን የሚመክረው ጠፋ፡፡ ከእርሱ ዕውቀት የሚፈልገ እንጂ ሊያሳውቀው የሚሄድ ጠፋ፡፡ የሚያመሰግነው እንጂ የሚወቅሰው ጠፋ፡፡ የሚያደንቀው እንጂ የሚተቸው ጠፋ፡፡
ምን ጥቁር ቢበሉ ነጭ ነው ኩስዎ
ምን ከሩቅ ቢጮኹ ይሰማል ድምጥዎ
አሁን የርስዎን ልጅ ምን አገኘብዎ
ብለው አህዮች ለጅብ እንደ ተቀኙት ዓይነት ቅኔ ብቻ በየጊዜው ይዘንብለት ጀመር፡፡
የዝንጀሮው አለቃ በይሁንተኞች ብቻ መከበቡን ሲረዳ እንዲህ የሚል ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ «ከዛሬ ጀምሮ እኔ የምለውን ብቻ መቀበል እንጂ ለምን? እንዴት? ብሎ እኔን መጠየቅ ያስቀጣል፡፡ ማንኛውም የእኔ ባለሟል የማሳየውን ብቻ ያደርጋል፤ የምናገረውን ብቻ ይናገራል»
እናም ለብዙ ጊዜ እርሱ የተናገረውን እየተናገሩ እርሱ የሚያደርገውንም እያደረጉ ከሚኖሩ ባለሟሎቹ ጋር ኖረ፡፡ እርሱ ሲጮኽ ይጮኻሉ፡፡ ለምን እንደሚጮኽ እነርሱም ለምን አብረውት እንደጮኹ ግን አያውቁም፡፡ እርሱ ሲዘል ይዘላሉ፤ እርሱ ዛፍ ላይ ሲወጣ ይወጣሉ፡፡ እርሱ ሲንጠላጠል ይንጠላጠላሉ፡፡ የቆረጠውን ይቆርጣሉ፡፡ የጣለውን ይጥላሉ፡፡ የወደደውን ይወድዳሉ፤ የጠላውን ይጠላሉ፡፡
ኑሮ እንዲህ ሆነ፡፡
የዝንጀሮዎች አለቃ እየበላ እና እየጠጣ በሄደ ቁጥር እየወፈረ መጣ፡፡ ሲወፍርም በራሱ ላይ ያጠለቀው የብረት ዘውድ እያጣበቀው መጣ፡፡ ሊያወልቀው ቢሞክርም እምቢ አለው፡፡ አንድ ቀን በእልፍኙ እያለ ዘውዱ አጣብቆ ያዘው፡፡
ወዲያው እየተጣደፈ ከእልፍኙ ወጣና ባለሟሎቹ ወደ ተሰበሰቡበት አዳራሽ ገባ፡፡ ሁሉም ቆሙ፡፡ እየጮኸ «ይኼንን ዘውድ አውልቁልኝ» አላቸው፡፡ የምለውን ብቻ በሉ፡፡ የማደርገውንም ብቻ አድርጉ የተባሉት ባለሟሎቹ፡፡
«ይኼንን ዘውድ አውልቁልኝ» አሉና እርሱ እንዳለው አሉ፡፡
ተናደደ፤ ተናደዱ
«እውነቴን ነው» አላቸው
«እውነቴን ነው» አሉ እነርሱም፡፡
«አትቀልዱ» አለ
«አትቀልዱ» አሉ ተከትለውት፡፡
«ልትገድሉኝ እኮ ነው» አለ እየጮኸ፡፡
«ልትገድሉኝ እኮ ነው» አሉ እነርሱም እየጮኹ፡፡
ተበሳጭቶ እየሮጠ ወደ እልፍኙ ገባ፡፡ እነርሱም እየሮጡ ወደየ እልፍኛቸው ገቡ፡፡
ተመልሶ ከእልፍኙ ወጣ፡፡ እነርሱም ወጡ፡፡
ይበልጥ እያጣበቀው ሲመጣ ኡኡ ብሎ ጮኸ፡፡ እነርሱም ኡኡ ብለው ጮኹ፡፡ የዝንጀሮው መንጋም ኡኡ እያለ ተሰበሰበ፡፡
«ሞትኩ» ይላል አለቃቸው
«ሞትኩ» ይላሉ እነርሱም፡፡
እየሮጠ ወደ መድኃኒት ዐዋቂው ጋ ሄደ፡፡ ሁሉም ተከትለውት ወደ መድኃኒት ዐዋቂው ጋ ሄዱ፡፡
መንገድ ላይ አንድ ሰው አገኘ፡፡ «የመድኃኒት ዐዋቂው ቤት የት ነው?» ብሎ ጠየቀው፡፡ ያም ሰው መልሶ «የመድኃኒት ዐዋቂው ቤት የት ነው?» አለና መለሰለት፡፡
«የማትነግረኝ ከሆነ እቀጣሃለሁ» አለው፡፡ ሰውዬውም መልሶ «የማትነግረኝ ከሆነ እቀጣሃለሁ» አለው፡፡ ሲጨንቀው መንገዱን ቀጠለ፡፡ በየቤቱ እየዞረ ፈለገው፡፡ መንጋውም አብሮት ፈለገ፡፡ አንድ በር ሲከፍት መድኃኒት ቤቱን አገኘው፡፡ ነገር ግን በውስጥ ያለው ሌላ መድኃኒተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ያኛው መድኃኒተኛ እንደ አለቃው ሁሉ ሌላ መድኃኒት ቤት ሄዷልና፡፡
ዘልሎ አልጋ ላይ ተኛ፡፡ መንጋውም በየአልጋው ተረፈረፈ፡፡
«አጣብቆኛል» አለው ዐዋቂውን፡፡
ዐዋቂውም መልሶ «አጣብቆኛል» አለው፡፡
«አውጣልኝ ከራሴ» አለው የዝንጀሮው አለቃ፡፡
«አውጣልኝ ከራሴ» አለ መድኃኒት ዐዋቂውም፡፡
ከድካሙ ብዛት ተራበ፡፡ እናም «ራበኝ» አላቸው፡፡ እነርሱም «ራበኝ» እያሉ መጮኽ ጀመሩ፡፡ «እባካችሁ ውኃ» አለ፡፡ እነርሱም ተከትለውት «እባካችሁ ውኃ» አሉ፡፡
ሲጨንቀው ንጉሱ ተነሣና ከተደረደሩት መድኃኒቶች አንዱን ቅጠል አንሥቶ በላ፡፡ ተከታዮቹም እንደርሱው እያነሡ በሉ፡፡ ባለ መድኃኒቱም ያ ቅጠል እንደሚያሳብድ ቢያወቅም መከተል ስላለበት አብሮ በላ፡፡ እናም መላው የዝንጀሮ መንጋ አበደ፡፡
አለቃው በእብደት መንፈስ ተነሣና እየዘፈነ ይሮጥ ጀመር፡፡ መንጋው ሁሉ እየዘፈኑ ተከተሉት፡፡
እየጨፈረ፣ እየጨፈሩ ሄደው ገደል ዳር ደረሱ፡፡ ያንን ያጣበቀውን የብረት ዘውድ ከገደሉ ዐለት ጋር እያጋጨ ሊያላቅቀው ሞከረ፡፡ መንጋውም እንደርሱ ራሳቸውን ከዐለቱ ጋር ያጋጩ ጀመር፡፡
ራሱን ከዐለቱ ጋር ለብዙ ሰዓት ሲያጋጭ ዕብደቱ ጨመረ፡፡ የመንጋውም ዕብደት ጨመረ፡፡ አንዱን የዐለት ፍላጭ አንሥቶ የቅርብ ባለሟሉን መታው፡፡ መንጋውም እርሱን ተከትሎ የዐለት ፍላጭ እያነሣ የቅርብ ወዳጁን ይመታ ጀመር፡፡
እርስ በርስም ፍጅት ሆነ፡፡
ዕብደቱ ከልክ በላይ ሲያልፍ ዘለለና ገደል ውስጥ ተወረወረ፡፡ መንጋውም እርሱን ተከትለው ገደል ውስጥ ተወረወሩ፡፡
እናም «ሰውን ከላይ ሆነው ከሚቆጡት፣ ከጎንም ሆነው ከሚሞግቱት ይልቅ ከሥሩ ሆነው የሚከተሉት ጀሌዎች ይበልጥ ይጎዱታል፤ ከላይ ሆነው ከሚያሳዩት ታላላቆቹ፣ ከጎን ሆነው ከሚገዳደሩት እኩዮቸ$ ይልቅ፣ ከሥር ሆነው ይሁን ብቻ የሚሉት አንጋሾቹ ይበልጥ ይጎዱታል» ተባለ፡፡
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Wed Oct 12, 2016 3:27 pm

ከዚህ በታች ያለው መረጃ በውስጥ መስመር የመጣ ነው። በጣም ከሚታመን የፌዴራል ፖሊስ የተገኘ ስለሆነ መረጃውን ለማካፈል ወድጃለሁ ያለው አንድ ወዳጃችን። እነሆ፦
"ወዳጄ እንዴት ከርመሃል? እኛ እንደምታውቀው ሸገርን እያመስናት እንገኛለን። ከቻልክ ይህችን መልእክት ለህብረተሰቡ እንዲደርስ አድርግልኝ። በአዱገነት በድሬዳዋ በአዳማ በባህርዳር በጎንደር በሻሸመኔ በአሰላ በአምቦ በጅማና በሌሎች ከተሞች ድንገተኛ ፍተሻዎች እንዲደረጉ መመሪያ ወርዷል። ሸገር ከእሁድ ጀምሮ ፍተሻ እየተደረገ ነው። በእነዚህ ፍተሻዎች ላይ የተሰማሩት የእኛና የደህንነት ሰዎች አስፈላጊ የተባለ ማናቸውንም እርምጃ መውሰድ እንችላለን። እነዚህ ፍተሻዎች የሚደረጉት ጨለማን ተገን ተደርገው ነው። ለፍተሻ በተመረጡባቸው አካባቢዎች አስቀድሞ መብራት እንዲጠፋ ይደረጋል። ከላይ የወረደው መመሪያ ህገወጥ መሳሪያ እንድንፈትሽ ቢሆንም በፍተሻ ወቅት የተገኘ ገንዘብ በተለይ ዶላር ዩሮ ምናምን ሁሉ ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው። ከእሁድ ማታ ጀምሮ በተደረገው ፍተሻ ብቻ ከተለያዩ ሰዎች በጣም ብዙ ገንዘብ የተወሰደ ቢሆንም እስካሁን ማንም ገቢ ያደረገ ሰው ግን የለም። አባሉ እርስ በርሱ ተከፋፍሏል። በተለይ ዶላር ቤት ውስጥ ይዘው የተገኙ ሰዎች ገንዘባቸውን መወረስ ብቻ ሳይሆን ለእስራትም እየተዳረጉ ናቸው። ወጣቶች ደግሞ ስልኮቻቸው ላይ በዋትሳፕና ቫይበር በኢሞ መልእክቶችን ተጻጽፈው ከተገኘ ትኩረት እንድናደርግ ተነግሮናል። መልእክቶቹ ምንም አይነት ቢሆኑ ችግር የለም። የፍቅርና የሰላምታ መልእክቶች ኮድ ሊሆኑ ይችላሉ ተብለናል። የውጭ ሀገር የስልክ ቁጥሮች በስልክ አድራሻ የመዘገቡ ካሉ ከጸረ ሰላም ሀይሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ ጥብቅ እርምጃ እንድንወስድ ተነግሮናል። ስለዚህ ሰዎች የወዳጅ ዘመዶቻቸው እንኳን ቢሆን በውጭ ሀገር የሚኖር ሰው ስልክ ቁጥር በስልክ አድራሻ እንዳይዙ ለሰው ቢነገር ጥሩ ነው። ወደሌላ ቦታ ግዳጅ ሳልሄድ አልቀርም። መሄዴ ቁርጥ ከሆነ ምልክት አደርግልሃለሁ ሰላም ሁን"

ይሄን ማስጠንቀቂያ እንቁ ቲቪ ከሚል ፔጅ ላይ ነው ያገኘሁት ..እናም መረጃው ትክክለኛ ከሆነ (ትክክለኛም ይመስላል) የ ዶላር እና የ ኢይሮ ዝርፊያው ድርጅቱ ያለበትን የውጪ ምንዛሪ ችግር ለማቃለል በዝርፊያ መልክ ከህዝብ ለመዝረፍ የታሰበ ይመስላል የ እስቸኩዋይ ጊዜ አዋጁ... ቅቅቅቅቅ ሌላው እሚያስቀው በ ቫይበር ወይም በ ተለያዩ መገናኛዎች የተላላኩ ቴክስቶችን ወይም ፈን የሆኑ ፎቶዎችም ካሉ ሊታሰሩ ነው ማለት ነው..? ቅቅቅቅቅ ተራራን ያንቀጠቀጠው ትውልድ እራሱ እየተንቀጠቀጠ ነው ..!!! ከምር በጣም ያስቃል ...ዶላርና ኢይሮ ለመዝረፍ ብቻ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ ...!! ቅቅቅቅ እሚገርመው ስንት ለ አገር እሚያስቡ ግለሰቦች ..ምሁራኖች ...እና የተለያዩ የ ህብረተሰቡ ክፍሎ ከድሮ ጀምሮ የተሳሳተ መስመር ላይ ናችሁ ሲሉዋቸው ሳይሰሙ አሁን የ ህዝቡ ብሶት ጨምሮ አፍንጫቸውን ሲይዝ እና ሱሪ በ አንገት ሲሆንባቸው... በጣም ተራ የውንብድና ስራ በ አስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅ ከለላ መስራት አንድ መንግስት ነኝ ብሎ ለሚያስብ ድርጅት በጣም አሳፋሪ ነው፡፡
እስኪ እንደገና ከላይ ያለውን የዝንጀሮ መንግስት አመራር እንደገና ላንበው .... መመሳሰል ይታየኛል ...ቅቅቅቅቅ
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ETHIOPIAN FUN & ( .) ( .)

Postby ደጉ » Mon Oct 17, 2016 4:30 pm

https://www.youtube.com/watch?v=KqnfQZ2h1Ys&feature=youtu.be
ቅቅቅቅቅ...አንዳዴ ወደን አይደለም እምንስቀው ...ከላይ ያስቀመጥኩትን ቪዲዮ ሳየው ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ ... :D በቁም ነገር ኢትዮጵያ በ ልማታዊ ዲሞክራሲ አመራር ቅቅቅቅ ወደ ድንጋይ ዘመን ጊዜ ወደ ሁዋላ እየተመለሰች ነው .... ያን ግዜም አርግጠኛ ነኝ በገዛ ጆሮአችሁ አትስሙ...በገዛ አፋችሁ አትናገሩ ....በገዛ እጃችሁ ምልክት አትስጡ የተባለበት ጊዜ መኖሩንም አልሰማሁም...ዛሬ ተራራን አንቀጥቅጦ ተራራውን የስረቀውን ትውልድ እሚመራው በ ፍርሀትና በጭንቀት ሊሞት ነው፡፡ እምትሰሙት ያስጨንቀኛል ..እምታዩት ሰላም ይነሳኛል ...ኢንተርኔትም ለ ስልጣኔ በጣም ስጋት ላይ ጥሎኛል ...ክብሪትና ላይተር ፈቃድ ሳይኖራችሁ ይዛችሁ እንዳትገኙ ....ቢላና ስለት ያለው ነገር ከማድቤት ውጪ መንገድ ላይ ገዝታችሁም ቢሆን ስትመጡ እንዳናይ ....የቴክስት ሜሴጅ ለመላክ እንዳትሞክሩ ብትልኩ ከ 3 አመት እስከ 5 አመት አስራለሁ ...ቅቅቅቅ የወያኔን መንግስት አይደለም አደባባ ላይ ወጥቶ በሰለፍ ማውገዝ .... በሆዳችሁም ማማት አትችሉም....በ ሆዳችሁ ስታሙ የሰማም ቢሆን በ አስቸኩዋይ ጊዜ ኮማንድ ፖስቱ እርምጃ ይወስደበታል ...:-)
በ ቁም ነገር መፍራት እና መጨነቅ ሲበዛ ወደ እብደት ይወስዳል ማንም ያውቃል ...ግን እንደዚህ ተራ እና የሰማውን ሰው ሁሉ እሚያስቅ ህግ በዚህ ባለንበት ክፍለ ዘመን መስማት ያሳፍራል ..ያሸማቅቃል ..ይሰቀጥጣልም ... እውነት ሀላፊነት ያሉት ሰዎች ትንሽም ብትሆን ጭንቅላት አላቸው ወይ ያስብላል ...አንድ የስራ ባልደረባ የጣሊያን ዜጋ ይሄን ዜና ስነግረው ..የትኛው አለም ላይ ነው እሚኖሩት 'ቦርኮ' በላቸው አለኝ ቅቅቅቅ ከሁሉ ያሳቀኝ እድሜያቸው የገፋ ሽማግሌዎች ናቸው ስለው ....Italy ውስጥ እማውቀው የ ሲኒየሮች ዳይፐር ሱቅ አለ ኮንታክት አድርግላቸው አለኝ ... :-D ስራቸው ያውጣቸው እኔ ምን አገባኝ፡፡
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4493
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests