የአዲስ አበባ ልጆች ከች በሉ/ፋራዎች እንዳትገቡብን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby alun » Tue Jul 27, 2010 11:52 pm

ጊጃ ሁሉ
alun
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Wed Mar 11, 2009 5:26 pm

Postby ጨምጫሚ » Wed Jul 28, 2010 12:14 am

ተው ባክህ ድንቄም አራዳ :lol: :lol: :lol:
ማታቅ መሆንህን አለማወቅህ አራሱ አለማወቃቸውን ካወቁት በታች ያርግሀል :lol: :lol: :lol: :lol:
HD wrote:ጨምጫሚ አካም ጂርታ, ፈያ, የአራዳ ልጅ ምንድነው አልክ? የአራዳ ልጅማ አንተ ሳታየው ከቅንድብህ ላይ ሽበት የሚነቅል, በእንግሊዘኛ መርቆ በአማርኛ ሙድ የሚይዝብህ ነው :lol:,ካለድ እንዳለው የአራዳ ፈሱ ሁሉ መዳኒት ነው , :lol:,
ጨምጫሚ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Sun Sep 20, 2009 6:44 am

Postby HD » Wed Jul 28, 2010 3:48 am

alun wrote:ጊጃ ሁሉ
አሉን ሰላም , ጌጃ ለማለት ፈልገህ እንደሆነ ገቢቶ ብሎኛል , በዘነገራችን ላይ , ጌጃ ሰፈርን የሚያውቀው አለ ? አቤት የሰካራም ብዛት , መንገድ ላይ ኤቭሪ 100 ፊት ከአንድ ሰካራም ጋር መጋጨት የተለመደ ነው , ጠጅ ቤቶቹ እራሳቸው መዐት ናቸው, በአስራ አንድ ቁጥር ወክ እየበላን እንሄዳለን ካላቹማ በቃ ጫማቹ የተሰጣ ብቅል ረጋግጦ ከብቅል የተሰራ መስሎ ነው ዱቅ የሚለው, እኔ ባይገርማቹ ኪንደርጋርደን እያለሁ ማስትሬቴን የሰራሁት እዛ ሰፈር ወልዶ መጣያ ከሚባለው ትምሮ ቤት ነው , አንድ ሰሞን የቄራ ልጅ የሆነ ጀለሴ ከኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ነው ምናምን ለትሬኒንግ ተብሎ እዛ ቢመድቡት በሶስት ቀን ሽበት አውጥቶ ዱቅ አለላቹ , ወይኔ ያኔ የሳኩት ሳቅ , ልጁ ደሞ ገና አዲስ ቲቸር ሆኖ ነው መሰለኝ ስነምግባር ላስተምራቹ ሲላቸው ለካ የሌለ ሙድ ይዘውበት እንዳውም አንድ ቀን የለበሳት አሮጌ ጋወን ላይ ሳያያቸው በጀርባው ፎር ሴል የሚል ለጥፈውበት ሼም በሼም አድርገውት ላኩት , በዛ ላይ እዛ ሰፈር ያሉ ቤቶች በጠቅላላ ቀበሌ 10 ቀበሌ 8 እየተባሉ ነው የሚጠሩት, ለምን እንደሆነ ነቄ ብላቿል? 10 ልጅ ያለበት ቤት ከሆነ ቀበሌ አስር ተብሎ ሲጠራ 8 ልጅ ቤቱ ውስጥ ካለ ደሞ ቀበሌ 8 ይባላል, በተለይ አንድ ሰውዬ ልጆቹ በጣም ብዙ ናቸው ከ10 ሁላ ይበልጣሉ, ግማሾቹ አረብ አገር ግማሾቹ እስር ቤት ምናምን ያሉት ተቆጥረው ነው ታድያ እና ሰውዬው ደሞ ማታ ማታ ሁል ጊዜ እንቅፋት ቤት ገብቶ ናፍጣ ሞልቶ ሰክሮ ነው የሚወጣውና በመንገድ ላይ ሲያልፍ አርብቶ አደር ነው የምንለው, ቀይ መስቀል ተብለው የሚጠሩም አሉ, አሼ በል እስኪ እዚህ ዘው በልና ስለ አራት ኪሎ አጫውተን, ጨምጫሚ ኬፍ ተብሏል,
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby HD » Wed Jul 28, 2010 3:54 am

አይ ፎን ገዝቼ ባለ ሀብት ሆኘላችኋለው , ዋርካን ሸኖ ቤት ሁላ ሆኜ መመንጠር እችላለው
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby የፎካ ልጅ » Wed Jul 28, 2010 5:34 am

HD wrote:አይ ፎን ገዝቼ ባለ ሀብት ሆኘላችኋለው , ዋርካን ሸኖ ቤት ሁላ ሆኜ መመንጠር እችላለው


በአይ ፎን
አንድ) ዋርካ በመግባትህ
ሁለት) ስለመንደር ጠጅ ቤት ስለብቅልና ስለሰካራም እንደ ሀይስኩል ልጃገረድ አይነት ስታይል በደከመ እንግሊዝኛና አማርኛ ቀላቀለህ በአይፎን ተጠቅመህ አይፎንን ስላጎደፍክ

ስቲቭ ጆብ ይሄን ያህል ደክሜ የሰራሁት አይፎን ለመመላገጫ አደለም ብሎ በጥፊ ካላሰህ በኍላ ያለምንም ሪፈንድ አይፎንህን ቀምቶ በል ጥፋ ነው የሚልህ

:lol: :lol: :lol:
የፎካ ልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 454
Joined: Fri Jul 17, 2009 3:46 pm

Postby እዮባ » Wed Jul 28, 2010 6:26 pm

የፎካው ልጅ ሰላም ነው ብሮ, ዋርካ ፍቅር ላይ ካሉት ጥቂት ኢንተርቴይነሮች አንዱ ሊሆን ይችላልና እባካቹ አናት አናቱን እያላቹ እንዳታባርሩት, ድክም የሚያረግ ፍንዳታ ነው :lol:
A+T ርኛ

MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC.
እዮባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 906
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:30 am
Location: In the state of peace

Postby HD » Wed Jul 28, 2010 7:41 pm

ይህውላችሁ እኔ ወንድማችሁ በዋርካ ላይ ሀይ ዴፍኔሽን ሆኜ ከች ያልኩት ብራዘር ዛሬ ጠዋት አንቀልቅሎ ወደ ካምፓስ ይዞኝ የሄደው መልዐክ የስራውን ይይለትና , ዛሬ እያንዳንዱ የኔ ዲፓርትመንት ተማሪ ደም ዶኔት ካደረገ ኤክስትራ ክሬዲት ይሰጠዋል የሚል ብሰማ ያው እንደምታውቁት የኔ ክሬዲት ካርድና ኮሌጅ ክሬዲት ፋክድ አፕ በመሆኑ :lol: እስኪ ከጠቀመኝ ብዬ ጂም ደም ወደሚለገስበት ሄጄ ያቺን ያለችኝን ለግሼ ስወጣ ሰማዩና ምድሩ ዞሮብኝ እንደምንም ቤት ገብቼ ይህው አንድ ጋሎን ኮካ ኮላ ጠርሙስ ገዝቼ እየተጋትኩ ነው :lol:, ትላንት ከኦልድ ካንትሪ ቡፌት ስመጣ የግርማ ወልደ ጊዮርጊስን አክሎ የነበረ ሆድ ዛሬ የሉሲን ሆድ መስሎላችኋል, ጨምጫሚ ሙት, አንተ ግን ደህና ነህ? እንደኔ ያለ ደግ እሩህሩህ እንዲህ ደሙን አሳልፎ ይሰጣል ይህውልህ, አንተስ ደም ሰጥተህ ታቃለህ? ለነገሩ አንተ የኔ ቢጤ አራዳ ባትሆንም እኔ ባለፍኩበት ካለፍክ እራሱ አንድ ነገር ነው, እኔ ለክሬዲት ባይሆን ኖሮ እንኳን ደሜን ልሰጥ ቀርቶ ሽንትህ የታመመ ያድናል ቢሉኝ እራሱ አልሰጥም, ሽንት የታመመ የሚያድን ቢሆንማ የሸገር ልጆች ለአለም ኤክስፖርት በማድረግ አንደኛ እንሆን ነበር እኮ, አቤት ሰዉ ይሸናል ነው የሚባለው, :lol: , ለነገሩ የአራዳ ልጆች ባይሸኑ ኖሮ ቦሌ አካባቢ ያሉ ፍራፍሬ ቤቶች ምን ይውጣቸው ነበር? የቀበና ወንዝን ወንዝ ያረገው ዝናብ መስሏቹ ነው እንዴ? ቆይ መጣሁ ትን አለኝ
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby ኣሸወይና » Wed Jul 28, 2010 8:44 pm

ኣቦ HD የጌጃ ሰፈርን ጨዋታ ስታመጪዉ! አቦ የሰፈሬ የይገባዋል ጠጅ ቤትን እውነተኛ ቢጫ ፊኛ አፈንጂዎችን አስታወሺኝ!!አንዱ ባደግ አንድ ሰሞን ቢጫ ፊኛ ማፈንዳት ለምዶ ይገባዋልጠጅ ቤት! ደርግና ወያኔ የሚባለዉፕሮግራም በየሰከንዱ ተዘባርቆበት ቤተ መንግስትን ሲመርቅና ሲሳደብ ማየት ያዝናና ነበር!!
ለምን እንደሆነ በሳይንስ ባናረጋግጠዉም እስካሁን የተጠና ማስረጃ ባይኖርም ለጊዜዉ በጄ! የክፍለአተ አገራት ልጆች ለአዱ ገነታችን ጥላቻቸዉ በነፍ ነዉ! :lol:
ለነዕርሱ አራድነት ማለት መደበኛ ት/ቤት ይመስላቸዋል!!በአራዳ ልጆች ቅዱስ መጽሀፍ ግን አራድነትን በብዙ መልኩ ዲፋይን እናደርገዋለን!!
መደበኛ እስኩል ለኛ ማለት የሆነ ትሬኒንግ ሴንተር ነዉ በቃ በአንድ ሙያ ትሬን ተደርጎ መዉጣት ከዛም የስራ ልምድ መያዝ ከዛም በዛዉ ሙያ ማስተር ማድረግ!!አራድነት ዕና የአራዳ ልጅነት የሚገኘዉ ከዚህ ለየት ባለ መልክ ነዉ!!አንድ በዉልደት!አልያም በጥምቀት ብቻ ነዉ!!እዛዉ ተወልደዉ አድገዉ ተጠምቀዉ የአራድነትን ጠበል ካልተጠጣ!!እንዴት አራዳ ነዉ ሊባል ይችላል!! እንዴት ከገጠር ልጆች መግባባት ይፈጠራል!!
አንዱ ታዋቂ የክፈል ሀገር ልጅ በአንድ ወቅት የሰጠዉ ዕማኝነት እንዲህ ይል ነበር!! ~~አንድ አራዳ ሞተ ብለዉ ከሚሉኝ የ500 ፋራ መርዶ ይንገሩኝ~~ብሎ በመግጠሙ የክብር የአራድነት ናቹራላይዜሽንን ሪዋርድ ሰጥተነዋል!!
ይሄም የገጠር ልጅ አበጣጥሮ ሲናገር''ከተማረ የገጠር ልጅ የአበደ የአዲስ አበባ ልጅ 100%ይሻላል!!በማለት ለሁለተኛ ዙር ዕና ለከፈተኛ የአራድነት ኮርስ ወደፒያሳ ሊላክ ሲል በመሀል ዕኔ ዲቪ ደርሶኝ ከች ብዬ ፊልሙን ሳልጨርሰዉ እዚሁ ኒዮርክ ከች ብያለሁ!! :lol:
በነገራችን ላይ ጃንሜዳ ኳስ ለመጫወት ሄጄ ያኔ ሁለት ቢምቢዎች ያዉ በነርሱ ኣጠራር አጋዚዎች በኳስ ይጣሉና ድብድብ ይጀምራሉ;ጀለሳቸዉ ድብድቡን መከለም ቀጠለ በመሀልም ሁለቱም ጺላዎች ቦምብ ከጃቸዉ አዉጥተዉ ቡኣይ ተባብለዉ እርስ በራሳቸዉ ቦምብ ይወራወሩና እዛዉ ሜዳ ላይ ሁለቱም ወደሰማይ ቤት ይፈልላሉ!! ቆሞ ይመለከት የነበረዉ ጺላ :lol: ቡኣይ ይህንንማ ፊልም እዛዉ ሰማይ ቤት ሄጄ መጨረስ አለብኝ ብሎ ዕርሱም የያዘዉን ቦምብ እጁ ላይ አፈንድቶ ደየመ!!
:roll: በተረፈ እስቲ አሁን ሽቀላ ላይ ነኝ ማታ እመለሳለሁኝ!!የጀመርኩትን ጭዉቶ አቅዉጠዋለሁ!! ይሄ አዲስ የመጣ አለቃዬ የሞስኮ የአራዳ ልጅ ነዉ የገባዉ!!ዕናም ሲነቃ ይቀራል ልሸብለል!!
ኣሸወይና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Sat Sep 12, 2009 1:31 am

Postby HD » Wed Jul 28, 2010 9:42 pm

አሼ !! የአራዳ ሰላምታዬ በዌስተርን ዩንየን ይድረስሽ , የክፍለሀገር ልጆች ለምን በአዱገነታችን እንደሚቀኑ አይገባኝም , እነሱን ስል ሁሉንም ማለቴ ሳይሆን የማይወዱንን ነው እንጂ ስንት የገባቸው የክፍሌክስ ልጆች ነፍ ናቸው የምታቃቸውም እዚህ መተው ጠራ ያለ ወግ ሲለቁብን ነው , ሸዋዬዎች ግን የሆነ መዳኒት የሌለው ኮምፕሌክስ ነገር አለባቸው, እኛ እንዳውም ከአገራቸው በካቻማሌ ተሳፍረው ሼባዎቹ ጋቢያቸውን ዱቅ እንዳደረጉ ወጤዎቹም ቁምጣቸውን ገድግደው ዱላቸውን አንግተው ዘመድ ለመጠየቅ ከች ሲሉ ''ቱሪስት '' ብለን ስም ባወጣንላቸው ለምን እንደጠመዱን አይገባኝም, :lol: :lol: የሰካራም ነገርማ ተወርቶ አያልቅም :lol: , በተለይ እዛ አብነት አካባቢ አንድ አላሙዲን ብለን የምንጠራው ጎዳና ተዳዳሪ ነበር አልኩሽ, ከዛ የዛ ሰፈር ሽሜዎች ጠዋት ቤተክርስትያን ሄደው ሲመለሱ መንገድ ላይ ካገኙት ቼላ ምናምን አሽረውት ነው የሚሄዱት, ከዛ ማታ ላይ ናፍጣ ሞልተው እየተንገዳገዱ ሲራመዱ ረጋግጠው ተፍተውበት ምናምን ያልፋሉ, አንዳንዴ ቴሌ የቆፈረው ጉድ ጓድ ውስጥ ይወድቁና ለሊቱን እዛው የሚያድሩበት ጊዜም ነበር:: የአጋዚዎች ነገርማ ተወኝ ተወርቶ አያልቅም ከነሱ በላይ የምንበጣበጠው ግን ከፌደራሎች ጋር ነበር :lol: :lol: እነሱ ኤቭሪ ደይ በዛ ጋር ሲያልፉ የአራዳ ልጅ ጠቅላላ ወደ ማዘር ጓዳ ነው የሚገባው :lol: ደሞ የሚገርምሽ ረብሻ ሲነሳ አንድ የአራዳ ልጅ አይታፈስም, በመኪና ተጭነው ቾቤ የሚወረወሩት ሰርቶ አደሮችና ሸዋዬዎች ናቸው, ከዛ እነሱን ወስደው ምን እያሉ እንደሚያሰቃይዋቸው ታቂያለሽ? ቦምቧ ላይ ይወስዷቸውና የቧንቧ ውሀ ጨርሱ ይባላሉ, ከዛ ምድረ ሸዋዬ የቧንቧ ውሀ ሲጠጣ ውሎ ሆዱ ሮቶ የውሀ ማጠራቀሚያ ሲያክል ወደ ቤታቸው ይመልሷቸዋል, ከዛ እኛ ደሞ ተቀብለን የውሀ ቦቲ መኪና መጣ እያልን ሙድ እንይዝባቸዋለን :lol: , አይ ሸዋዬዎች አዱ ገነት ሲመጡ እኛ ቢዝነስ እንዳላስተማርናቸው አሁን እዚህ መተው ይላጡብን ጀመር, :roll: በፊት ደሞ ምን ሆነ መሰለሽ ወደ አሜሪካ ዲፖርት ሳልደረግ በፊት ወደ ቄራ አካባቢ ሙቭ አድርገን ነበር (ያው የኤኮኖሚ መሻሻል) ከዛ እዛ ጎፋ አካባቢ ያሉ ቆምጬዎች የመጬ አድክም ናቸው, በተለይ ልክ ከአገራቸው ሲመጡ ያቺን አረንጓዴ ቁምጤክሳቸውን አርገው ይመጡና በቃ እዛ አስፋልት ዳር ሆነው መኪና ሲቆጥሩ ይውላሉ, እዛ ታድያ ድንገት ካፍሽ አምልጦሽ እናትህ እንዲህ ትሁን ካልክ በቃ አለቀልህ, ''እንዴ እምዬን እናቴን?'' ብሎ በያዘው ዱላ ድራሽህን ያጠፋዋል, አንድ 2 አመት ከሆናቸው በሁዋላ ግን እሱ ራሱ እናትህን ልብዳት እያለ ሲሳደብ ትሰማዋለህ :lol:, የምታውቅ ከሆነ ደሞ እዛ ያሉ ቆምጬዎች የሚተዳደሩት በመሸከም ነው, እና ሴልፎን የመጣ ሰሞን እንጠራቸውና ''ሞባይል ትሸከማለህ?'' ስንለው ''አዎ ምን ያህል ከባድ ነው? የት ነው ያለው?'' ሲለን ድክም ነበር የምንለው በል መጣሁ ቡሀላ አካባቢ ከች እላለው, ከች በኮሮኮንች, እነዚህ ኒገሮች እየጠሩኝ ነው, ጀለሶቼ ሆነዋል አዚህ ደሞ እናታቸውን ልቀፍላቸውና :lol:
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby HD » Thu Jul 29, 2010 1:37 am

እኔ HD ባለጎፈሬው ወንድማቹ , ዋርካን በሊዝ የነጨኋት ብራዘር ስለ ሸዋዬዎች ምን ታዘብኩላቹ መሰላቹ , :arrow: ፖለቲካ ይወዳሉ , :lol: :lol: ስባተ ልክስክስ, በስማም በወልድ ለመንፈስ አራዳ ,አሀዱ ጀለስ አሜን, እንዴ???? እስከዚህ ድረስ? :roll: ዋርካ ውስጥ ፖስት ከተደረጉት ጉዳዮች አብዛኛዎቹ ፖለቲካ ሩም ውስጥ ናቸው ገብሬልን , የአራዳ ልጆች እስኪ አሁን ዋርካ ፍቅር የሚል ፎረም እያለ ሰው ሁሉ ፖለቲካ ፎረም ሄዶ ሲቧጨቅ እውነት የአራዳ አምላክ አይታዘብም? ሸዋዬዎች እግዜር ይይላቹ, ዋርካ ፍቅርን የመሌ ጸጉር አስመሰላቿት, ምናለ እዚህ ከች ብላቹ አራድነት በትንሽ በትንሹ በማንክያ እያጎረስን ብናስተምራቹ? እናንተ ደሞ ሸዋዬነትን በጃቹ ብታጎርሱን? አዱ ገነታችን መቼስ የኛ ብቻ ሳትሆን የናንተም ናት ታድያ ምናለ ስለሷ ብናወጋ? እኛ አዲስ ስለገባልን ትሮሊይ የኤሌክትሪክ ባስ ብናጫውታቹና እናንተ ደሞ አዲስ ስለገቡላቹ ባጃጆች ብትቀዱልን? አሁን ማን ይሙት ሞኒካ በባጃጅ ሄደሽ አታቂምና ነው? ጭጉዳ በባጃጅ ሲያንሸራሽርሽ እንደነበር እነ እማማ ወለተ ወሬ ሲያወሩ ያልሰማን እንዳይመስላቹ, ሰምተናል :!: ሸዋዬዎች ግን እውነት ኢንተርቴይኒንግ አታውቁበትም, አሁን እኛ ባጃጅ ቢገባልን ኖሮ, የባጃጅ እሽቅድድም, ወፍራም ሴት በባጃጅ አሳፍሮ ዳገት የመውጣት ውድድር, ምናምን እያዘጋጀን አደገኛ የገቢ ምንጭ እናረጋቸው ነበር, ግን ምን ያረጋል እዚህ ከች ብላቹ እንኳን አይዲያ አትሰበስቡም, ቀሽሞች, በሉ ወክ አድርጌ ልምጣ, እድሜ ለዛች ነጭ እሷን ከጠበስኩ ጀምሮ ማታ ማታ የሷን ውሻ ለማናፈስ ስንል ወክ በወክ ሆነናል, ደሞኮ ውሻዋ የሚበላው ብዛቱ, አቤቱ አምላኬ ሳፋ ሆድ አትስጠኝ አለ ሸምሱ, ሀብታም ለመሆን እኮ ነው :lol: , እናማላቹ ይሄ ውሻዋ በቀን የሚበላውን ጨምጫሚ በዛች ሆዱ በሳምንት አይጨርሳትም, ጨዋታን ጭውቴ ያመጣዋል አሉ አንድጊዜ አንዱ ሸዋዬ ምን ሆነ መሰላቹ, ዲቪ ደረሰውና እዚህ ከች ብሎላቹ ስፖንሰሮቹ ፈነገሉት መሰለኝ አፓርትመንት ተከራይቶ እስከነ ልጆቹ ሲኖር pet food store የሚል ያይና ሲገባ ምግቦቹ የመጬ ርካሽ ሆኑበት ከዛ የሸዋዬ ነገር ነቄ ሳይል የታሸጉ ሀይለኛ ሀይለኛ ቡሌዎችን ገዝቶ ለልጆቹ ሲወስድላቸው እነሱ ደሞ በቃ የታሸገ ምግብ ብለው ተመችቷቸው ምናምን ሲኮመኩሙ ቆዩላቹና አንድ ቀን ሰውዬው ማለትም አባታቸው ለጓደኛው እዚህ በጣም ርካሽ ምግብ ይሸጣል ብሎ , :lol: :lol: ደሞኮ አያፍርም ለሰው ሁላ ይጠቁማል, ከዛ ለጀለሱ አሳይቶት የውሻና ድመት ምግብ መሆኑን ሲነግረው ሰውዬው እዛው ለቀቀው አሉ :lol: :lol: , እና ሸዋዬዎች ምግብ ስትገዙ ለሰው መሆኑን አረጋግጡና ግዙ, እመለሳለው ጨቀጨቀን ብላቹ ደሞ እንደ ጀበና ግንፍል እንዳትሉ, ይመቻቹ
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby የፎካ ልጅ » Thu Jul 29, 2010 2:05 am

እዮባ wrote:የፎካው ልጅ ሰላም ነው ብሮ, ዋርካ ፍቅር ላይ ካሉት ጥቂት ኢንተርቴይነሮች አንዱ ሊሆን ይችላልና እባካቹ አናት አናቱን እያላቹ እንዳታባርሩት, ድክም የሚያረግ ፍንዳታ ነው :lol:


ልክ ነህ እዮባ እኔም ከጻፍኩ በኍላ ደብሮኝ ነበር ለምን እንደዛ እንደጻፍኩ
ዋርካ አውሬ ያረግሀል ያገኘኸውን ሁሉ ተናከስ ተናከስ ይላል :lol:
የፎካ ልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 454
Joined: Fri Jul 17, 2009 3:46 pm

Postby ጨምጫሚ » Thu Jul 29, 2010 7:26 am

ሸዋዬ ነገር ነህ አንተ ራስህ ምን መቶ ጊዜ ሸዋዬ ሸዋዬ ትላለህ ምን ሸዋዬ ምትባል ልጅ ፍቅር ይዞህ ነበር መሰለኝ::
ሸዋዬ ፊት :lol: :lol:

ሸዋዬ.... ጎንደርዬ አይሻልም :lol: :lol:
ጨምጫሚ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Sun Sep 20, 2009 6:44 am

Postby ጨምጫሚ » Thu Jul 29, 2010 7:40 am

HD wrote: :lol:, የምታውቅ ከሆነ ደሞ እዛ ያሉ ቆምጬዎች የሚተዳደሩት በመሸከም ነው, እና ሴልፎን የመጣ ሰሞን እንጠራቸውና ''ሞባይል ትሸከማለህ?'' ስንለው ''አዎ ምን ያህል ከባድ ነው? የት ነው ያለው?'' ሲለን ድክም ነበር የምንለው በል መጣሁ ቡሀላ አካባቢ ከች እላለው, ከች በኮሮኮንች, እነዚህ ኒገሮች እየጠሩኝ ነው, ጀለሶቼ ሆነዋል አዚህ ደሞ እናታቸውን ልቀፍላቸውና :lol: [/color]

አሁን ይሄ ምን ቀልድ መሆኑ ነው በናትህ
አለማወቅ እኮ ያለ ነው ምንም ሚያስቅ ነገር አለው አሜሪካ ነው ያለሁት ነው ያልከው አንተ አሜሪካ መጀመሪያ መጥተህ መንገድ መሻገር አቅቶህ ስትደናበር አልነበር እንዴ ስፖንሰሮችህ እንደህጻን ልጅ እጅህን ይዘው
አደለም እንዴ ያስተማሩህ ባሜሪካ ስታንዳርድ ያለምንም ጥርጥር አንተ መጀመሪያ ስትመጣ ለፈረንጆቹ ቆምጬ ማለት ነህ ቅቅቅቅ :lol: :lol: :lol:
ጨምጫሚ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Sun Sep 20, 2009 6:44 am

Postby ትፍስህት-ጥ » Thu Jul 29, 2010 7:41 am

አንድ ነገር

እውነተኛ አራዳ አራዳነቱን አይናገርም በድርጊት እንጂ.....

ላይክ "አራዳ አይቸኩልም እንድሚባለው"

ኤችድዬ አዲስ ነገር ነሽ መስለኝ ለፍርንጁ ሀገር ?!
Life is the journey b/n what you are and who you meant to be. ____________ unknown.
ትፍስህት-ጥ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 8
Joined: Wed Jan 25, 2006 12:25 am
Location: On the HWY of meant 2 BE!!

Postby One-Now » Thu Jul 29, 2010 1:57 pm

HD wrote: እዛ ታድያ ድንገት ካፍሽ አምልጦሽ እናትህ እንዲህ ትሁን ካልክ በቃ አለቀልህ, ''እንዴ እምዬን እናቴን?'' ብሎ በያዘው ዱላ ድራሽህን ያጠፋዋል, አንድ 2 አመት ከሆናቸው በሁዋላ ግን እሱ ራሱ እናትህን ልብዳት እያለ ሲሳደብ ትሰማዋለህ


ላንተ አራድነት ይሄ ነው አይደል? አስተዳደገ ብልሹ የመንደር ልጅ መሆንክን እያረጋገጥክልን ነው. ለእናቶች ክብር የማትሰጥ ሰው ነህ. እናት የለህም እንዴ?

ከጥሩ ቤተሰብ የመጣንና በስነስርአት ተኮትኩተን ያደግን የአዲስ አበባ ልጆች እንዳንተ በብልግና አንጨማለቅም. ብልግናን እንጸየፈዋለን እንጂ አንኩራራበትም. "የአራዳ ልጅ ነኝ" እያልንም ጉራ አንቸረችርም. የክፍለሀገር ልጅ ምናምን እያልንም የሰውን ክብር አንነካም. ሰውን በሰውነቱ እናከብራለን እንጂ ከገጠር መጣ ብለን አንንቅም: አንሳደብም.

"የሀብታም ልጅ: የቅልጥጤ ልጅ" እያሉ ድሮ መንገድ ዳር ቆመው እየተሳደቡ አላስወጣ አላስገባ ከሚሉን ስራፈት ዱርዬዎች አንዱ እንደሆንክ ይሰማኛል. አልጠላህም. ስለደረሰብህ የአስተዳደግ ብልሹነት ግን አዝንልሀለሁ.

ካሰብክበት ደግሞ አሁንም ራስህን ማሻሻል ትችላለህና የተሰትካከለ አመለካከት ያለው ሰው ለመሆን ሞክር. ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰውነቱ ሰው ነው. ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሰው ነው. ከገጠር መጣ ብለህ ኢትዮጵያዊን የምትንቅ ከሆነ ማንነትህ የተምታታብህ ግለሰብ ነህ. ከገጠር ጋር ግንኙነት ያለው አንድም ዘመድ የለህም ማለት ነው?

አንድ ነገር ስለራሴ ልንገርህ: አዲስ አበባን ከቆረቆሩ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ጋር የምዛመድ ሰው ነኝ ብዬ በፍጹም አልኩራራም.

ይበቃሀል
One-Now
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Tue Jul 27, 2010 1:49 pm

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests