የአዲስ አበባ ልጆች ከች በሉ/ፋራዎች እንዳትገቡብን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Re: የአዲስ አበባ ልጆች ከች በሉ/ፋራዎች እንዳትገቡብን

Postby ገልብጤ » Mon Aug 02, 2010 11:08 pm

ኣሸወይና wrote:
HD wrote:ኬፍ ተብሏል , የአራዳ ልጆች እንዴት ናቹ ? በየቤቱ ከምንቀላውጥ ለምን የራሳችንን ቤት ከፍተን ጭውቴውን አናዳራውም ? ምን ይመስላቿል ? አንዳንዴም ቡሌ ይዛቹ ብቅ ማለትም አይከፋም , በተለይ የመርኬክስ , ፒያሳ , ካሳንችስ , ቄራ ,ሳሪስና , አራትኪሎ ልጆች እዚህ ከች ብትሉና ብንቀውጠው ምን ይመስላቿል ?
ብንዝናና ምን ይልሻል ወይ ወይ ..
ወይ ..
ብንጫጫስ ምን ይልሻል ወይ ወይ ..

ወይ

ይመቻቹ
አቦ ይመችሽ ያራዳ ልጅ!ዉነትሽን ነዉ!የሰዉን ቤት ዉስጥ ገብተን ከምድረ ሸዋዬ የየክፍለ ሀገሩ ልጆች ጋራ ከምንጨቃጨቅ የራሳችን ቤት ይሻለናል!!
ኣቦ ይሄ ጨጉዳ የሚሉት ጴንጤ አቴንሽን ዲሀይድሬሽን ስላለበት በትልቁ ኢግኖር እንግጨዉ!!ከፋራ ዕና ከዕሳት አደጋ መኪና ቢያንስ 500 ሜትር መራቅ ነዉ!!

ኣሸወይና ከአራት ኪሎ!!የዱሮዉ ጃንሚዳ


ቅቅቅቅ አሼ ዋሽሽ እኮ ..ጃንሜዳ ነኝ ነው ያልሺው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1744
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ገልብጤ » Mon Aug 02, 2010 11:14 pm

ገልብጤ wrote:እሺ አራዶች አማን ናችሁ !!!

እኛ ደህና ነን ...ሽቀላ በዝቶብን ጠፈተን ነበር አሁን ከች ብለናል..አሁን ደከም ስላለን ብዙም አንጽፍም

እስኪ.እዮባ..የሚባለውን giga ..የብብቴን ጸጉር እንደናቱ ---- ሙልጭ አድርጎ ይላጨልን
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1744
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby HD » Tue Aug 03, 2010 3:13 am

የአራዳ ልጆች መጣሁላቹ
ሩማችንን ስታዩ ከች ከች ያላቹ
እንደ ኮካ ኮላ ቁጭ ቁጭ ያላቹ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ እንደምን አላቹ
እኔ ከናንተ ናፍቆትና ሀሳብ በስተቀር አማን ነኝ :wink:
ሸዋዬዎች እናንተስ? ደህና ናቹ ወይ? ለመሆኑ ይሄ የወሊድ መቆጣጠሪያ ለሸዋዬዎች ተዳርሷል የሚባለው ውሸት ነው ማለት ነው? ምነው እንደዚህ በዛቹ? ዋርካን የሸዋዬ መፈልፈያ አርጋቿት ዱቅ አላቹ እንዴ? :lol: በስማም አቦ ይመቻቹ ለማንኛውም, እናንተ ባትኖሩ እኛ በማን እንቀልድ ነበር? :?:? አኒዌይ ፒስ ነው አይደል? እንዴት ነው ዊኬንዱን እንዴት አሳልለፋቹት? አሼ ሰላም ነው? ወይኔ የአራዳ ልጅ, ለካ አንቺም የኔ እጣ ደርሶሽ ነበር? መምሬ አብደላ አልክ :lol: :lol: ክላስ ያለው ኔም ነው የሰጣቿቸው, ሌላ ደሞ ምን እናረግ ነበር መሰለሽ አሼ, እዛ መካነ እየሱስ የሆነ በዐል ምናምን ሲኖር በቃ አለ አደለ መንፈሳዊ መስለንልሽ ምናምን ቡሌ ጠለፋ እንሰማራለን, ከዛ እዛ እንገባልሽና ጸልየን ምናምን ሀይለኛ ቡሌ እንጠልፍና ወደ ቤታችን እንመለሳለን:: ቆይ መጣሁ የቡሌ ነገር ሲነሳ ሞረሞረኝ :lol:
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby HD » Tue Aug 03, 2010 4:25 am

አይ ቡሌ ,, ተጠለፈ ነው የሚባለው ,, የአራዳ ልጆች ይህውላቹ ቡሌ እንጠልፋለን ,ቺክ እንጠልፋለን , አውሮፕላን እንጠልፋለን , ስልክ እንጠልፋለን , ዋርካንም እንጤልፋታለን ,, ሸዋዬዎች :lol: :lol: አሼ እዛ አራት ኪሎ አካባቢ ሸሌዎች ነፍ ናቸው አይደል? እንዴት ነው አንቺ ፒምፕ ምናምን ለመሆን አልሞከርሽም ነበር? ቄራ አካባቢ ብዙ ባይኖሩም ጌጃ ሰፈርና አብነት አካባቢ ግን ነፍ ናቸው,, እነ ጨምጬክስና One-Nowን እዛ ብናቀምሳቸው ኖሮ በነጋታው እዚህ ዋርካ ላይ መተው ''ሸሌ የነጫቹ እንሰብሰብ'' ብለው ሩም ይከፍቱ ነበር :lol: :lol: እኔ ግን ጥሎብኝ ሸሌ መንጨት አይመቸኝም, የሸዋዬ ችኮች እያሉ ከሸሌ ጋር ምን አበጣበጠኝ? ጌጃ ጌጃ የሆኑት ወንዶች እኮ እኛን የጠመዱን አንድም ቺኮቹን እንደ ቡና ስለምንቆላቸው ነው,, አቤት ሸዋዬ ለመጥበስ ያልገባንበት, ያልደረሰብን የለም እኮ, :lol: ማርያምን,, አንድ ግዜ አንዱ ጀለሳችን የሀብታም ልጅ ላይ ተለከፈላቹ,, ቤተሰቦቿ ደሞ የመጬ ሀርደኛ ከመሆናቸው በላይ ገገማ ነገር ናቸው,, እኛ ታድያ በቃ ጀለሳችንን ለመርዳት ሚሽን ጀመርንላቹ,, ልጅቷን ከሱ ጋር ለማጣበስ,, እናም የመጀመሪያው ታክቲክ የነበረው ልጁን በቃ አለ አይደለ የሆነ ያለው ሞጃ ነገር ማስመሰል ነበረብን,, ከዛ መጀመሪያ መርኬክስ ሄድንና ሀይለኛ ሀይለኛ ሰልባጅ ሌዘር,ሰዐት,ሱሪ, ሾዳ ምናምን ገዛንለትና ልጁን የቦሌ ልጅ አስመሰልነው,, የሚቀጥለው ስልታችን ደሞ እንደምንም ብለን ልጁ በሁዋላ እከፍላቿለው ስላለን እዛ ግቢ ውስጥ ትንሽዬ ሩማቸውን እንዲከራይ ረዳነው,, ከዛማ እላቿለው ልጁ ገና እጁ ሳትገባ ሞተላት አልኳቹ,, እኛ የነገርነውን አንዳንዴ ይረሳና የሌለ ነገር መቀባጠር ጀመረ,, ምንድነው የምትሰራው ሲሉት ''አዲስ ምሩቅ ኢንጂኔር ነኝ, ቤተሰቦቼ ውጪ ናቸው'' ምናምን እያለ ጥግረራውን ጀመረ,, ደሞ ከሁሉም የሚያደክመው እኮ ለማዙካው አዳማ የአበባ ምርት እርሻ ውስጥ ስራ አግኝቻለው ብሏቸው እሳቸው ልጁ ከተሸበለለ ጀምሮ ቀን እየቆጠሩ ነው :lol: :lol: ደሞዝ ለመብላት ማለት ነው :lol: :lol: ከዛ ልጁ የስሜት ነገር ሆኖበት አንድ ቀን ሳያስበው ሰራተኛቸውን ግቢ ውስጥ ውር ውር ስትልበት ጠርቶ አስገባና ደከለላቹ, አቤት ውርደት,, ዘስፔንስ ላረጋቹ ነው እውነተኛ ታሪክ ስለሆነ ማለት ነው እናቴ ትሙት :lol: :lol: መጣሁላቹ,, አንተ One-Now ደህና ነህ? ምናባህ ነው እዚህ እየመጣህ ጽሁፍ የምትደጋግመው? ልጁ ያደገው በጨዋ ደምብ ዳዊት እየደገመ ስለሆነ ነው,, :lol: አትፍረዱበት,, በሉ ነጋቲ ቡላ
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby እዮባ » Tue Aug 03, 2010 4:35 am

አዱ ገነት ተወልዶ ማደግ እራሱኮ አንድ ጸጋ ነው :wink: ለማንም ያልተሰጠ ጸጋ
A+T ርኛ

MY THINKING IS CLEAR, MY SPEECH IS CRYPTIC.
እዮባ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 906
Joined: Sat Jun 20, 2009 3:30 am
Location: In the state of peace

Postby Monica**** » Tue Aug 03, 2010 8:30 am

HD ስላም ይሄ ቤት ሞቅ ሞቅ ብሎ የለ እንዴ!!!!
አሁንም ሁለቱም ስፈሮቼ አልተጠሩም......... እና ኦልድ ኤርፖርትና ሩዋንዳ ኤምባሲ አካባቢ አራዳ የለም ማለት ነው ከኔ በቀር? :lol: :lol: :lol: :lol:
እንደው የአመቱን ገብሬል እንክዋን ለማክበር ብስራተገብሬል ብቅ ብለህ አታውቅም?
ወይም የ I.C.S ገርሎችን ለማሳደድ ብቅ አላልክም?
ስለቦሌስ ይቅር እንዴት ኦልድ ኤርፖርት ይረሳል??? :oops: :oops: :oops: :oops:
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ቆንጂት08 » Tue Aug 03, 2010 11:44 am

ግን ያዲስ አበባ ልጅ አሮጚቶችን ይመለከታል ?ኤጭ የኩታሮች ቤት ምን ልሰራ መጣሁ........
ቆንጂት08
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 887
Joined: Wed Dec 19, 2007 3:49 pm

Postby Monica**** » Tue Aug 03, 2010 12:09 pm

ቆንጂቴ እረ ተይ አሮጊት የአዲሳበባ ልጅ የለም አሉሽ እንዴ? :lol: :lol: :lol: :lol:
እኔን በበኩሌ ይመለከተኛል የፈለገ የሙዝ አያት ብሆንም, :wink:
ቆንጂት08 wrote:ግን ያዲስ አበባ ልጅ አሮጚቶችን ይመለከታል ?ኤጭ የኩታሮች ቤት ምን ልሰራ መጣሁ........
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby HD » Tue Aug 03, 2010 7:36 pm

ሞኒካ ሰላም ነሽ? እኔኮ በቃ ከፍቷት ነካችው ብዬ መንገዱን ጨርቅ ያርግልሽ ልል ነበር,, እንኳን ተመለስሽ አቦ!! የሩዋንዳና I.C.S አካባቢ ልጅ ነበርሽ እንዴ? እንዴታ እዛማ ብዙ ሂስትሪ አለን:: የሩዋንዳ አካባቢ ነገር በተለይ ዞሬ ዞሬ ማንሳቴ አይቀርም ነበር, የሱማሌ መዐት በለው ነው የሚያስብለው,, :lol: :lol: እዛ ሰፈር ስትሄጂ ታክሲ ነጂውም ሱማሌ ነው, ወያላውም ሱማሌ ነው, ትራፊኩም ሱማሌ ነው,,ተሳፋሪውም ሱማሌ :lol: :lol: :lol:ወላሂ ነው የምልሽ እዛ ስንሄድ ሞቃዲሹ እንሂድ ብለን ነው የምንነሳው,, በተለይ ከሁሉ የሚገርመኝ አስር ጀለሳሞች ሆነው ሰርክል ሰርተው ምናምን ዱቅ ይሉና ዲስኩር ሲጀምሩ ነው :lol: :lol: አስሩም እኩል ያወራሉ ማን ማንን እንደሚሰማ አይታወቅም,, :lol: :lol: በዛ ላይ አንዳንዴ ሊደባደቡ ነው ምናምን እንልና በቃ ልናይ ብድግ ብድግ ስንል ለካ እነሱ ቻው እየተባባሉ ነው :lol: :lol: አይ ቲንክ ሩቅ ቦታ የሚሄድ ጀለሳቸው ከሆነማ ቦክስ ሁላ አለ አሉ :lol: :lol: እዛ ሰፈር ያለውን ቦሌ ሚካኤል ታውቂዋለሽ አይደል? እዛ ያሉት ቄሶች ሁላ ሱማሌዎች ናቸው አሉ :lol: :lol: ''ወሪያ እንደምን አደራቹ'' ብለው ነው የማታ ትምህርት የሚጀምሩት:: እኔ እዛ ሰፈር የምሄደው በብዛት ወደ ውጪ ስልክ ለመደወል ስል ብቻ ነበር,, ድፍረታቸውና ችሌያቸው እንደምታውቂው የመጬ የተራቀቀ ነው,, ሸዋዬዎች ከሰፈር ሰፈር የሚደውሉበትን ኮይን እኛ አሜሪካ ደውለንበት እንመለሳለን:: I.C.Sማ ከሰፈሬ ቄራ በጣም ቅርብ ስለነበረ እዛ አካባቢ ኤቭሪ ደይ ነበር የምሄደው ማለት ትችያለሽ,, አቤት ግቢው ሲመች,, ግን ምን ያረጋል እዛ የሚመጡ ቺኮች በመኪና ስለሚመጡ እኛ ደሞ ግቢ የሚያስገባን ስለሌለ ብዙ ጊዜ እነሱን መጥበስ የመጬ ይከብዳል:: እነስን ከመጥበስ በቆሎ እየጠበሱ ለአንድ አመት መሸጥ ይቀላል አልኩሽ:: ብስራተ ገብሬልም አንዳንዴ እንሄድ ነበር,, እዛ በር ላይ ቆመሽ እኮ ስለ ማርያም ስለ ገብሬል ካልሽ በአንድ ቀን መቶ ብር ምናምን ነው የምትሽሪው,, ስለዚህ እዛ አካባቢ ያሉ ለማኞች ወደ ልደታ አካባቢ ሲመጡ ለየኔቢጤዎች ኮይን ምናምን ይበጥሱላቸዋል,, እውነቴን እኮ ነው,,እዛ ሰፈር የሚበዙት ግን መካነየሱስ, ቃለ ህይወት ምናምን ቸርቾች ናቸው,, እዛ ያሉት ፓስተሮች ደሞ ሀመር ምናምን ነው የሚነዱት :lol: :lol: ሀመራቸውን ሀይድሮሊክ ያስገጥሙለትና ጎማው ደሞ ባለ ሪም ምናምን ነው አልኩሽ,, አንቺ ግን ምንድነው የድሮ አውሮፕላን ማረፊያ ምናምን እያልሽ የሰፈሩን ሙድ የምትዘጊው? እናቴ ትሙት ልክ አይደለሽም,, እራሱ የዛ ሰፈር ልጅች ቢሰሙሽ እንደዛ ስትዪ ስለ ምን እንደምታወሪ አይገባቸውም :lol: :lol: ሳር ቤት, ብስራተ ገብሬል, I.C.S, S.O.S ምናምን ነው የሚባለው ,, ለማንኛውም ይመችሽ አቦ :wink: :wink: ቆንጂት ሰላም ነሽ? ቆንጂት ወይም ደሞ በአራዳ ቋንቋ ባርቢ ገርል :lol: :lol: አይዞሽ በባከነ ሰዐት የምትኖሪ ከሆነም ምንም ጣጣ የለውም ከጩጉዳ ጋር እናጣብስሻለን ዋናው መምጣትሽ ነው
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby HD » Tue Aug 03, 2010 8:20 pm

ዑዑዑፍፍፍፍፍፍፍ,, ዛሬ ጎፈሬያችን ሹርባ ይሰራለታል ተብሏል,, እዚህ ውስጥ ጸጉር መስራት የምትችሉ?? እስኪ እጃቹን ወጣ ወጣ አርጉ,, ቂጣቹን ፈንደድ ፈንደድ :lol: :lol: ሸዋዬዎች ሰላም ናቹ? አዳዲስ አራዶች ተጨምረውልኝ አሁንማ እንደ ልቤ ነው የምሳፈጣቹ,, ዘይ ጋት ማይ ባክ :wink: አንተ One-Now አለህ? እስኪ ደሞ ስለ ድሮው የኔና ያንተ ታሪክ ልደስኩር,, ትዝ ይልሀል ያኔ ለቡሄ? እኛ ሆያሆዬ ልንጨፍር እናንተ ቤት ስንመጣ? አንተ ሆያሆዬ አትጨፍርም ነበር ,, እህትህ ለእንቁጣጣሽ አበባየሁሽ ልትጨፍር ስትወጣ አንተን ይዛ ትወጣ ነበር,, የሰፈሩ ሰው ''ልጃገረዶች መጡ'' እያሉ ኮይን ምናምን ሊሰጧቹ ሲወጡ አንተን አይተው እንደዛ እንድልደከሙብህ,, :lol: :lol: አንተ የአዱ ገነታችን አሰዳቢ,, አዲስ አበባን የቆረቆሩት ዘመዶቼ ናቸው አልሽ,, እሺ የእቴጌ ጣይቱ የልጅ ልጅ :lol: :lol: ልዑል ሸዋዬ :lol: :lol: ግርማዊነቶ,,አንተ የሰራተኛ አጫዋች,, 24/7 ቤት ውስጥ ተዘግቶብህ እኛ ውጪ በሰፈራችን ጭውቴውን ስናደራው አንተ በቀዳዳ ስትቃኝ :lol: አሁን አንተ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ ትላለህ? ካንተ እንደወረደ ጨምጫሚ ይሻላል አቦ,, እሱ እንኳን ባይሆን ቆቅ እያባረረ, ፍየላቸውን እየነጨ ስሜቱን እያረካ ምናምን ነው ያደገው,, ጨምጬክስ ሰላም ነው? አይ ጨምጬክስ ይሄ ሰውዬ እኮ አቦ በናትሽ በጠበጠን,, ፍየላቹን አውሰውና እስኪ ስሜቱን ያርካ,, ኤድስ የለባትም አደል? :lol: :lol: እናቱነኝለትና ይሄ ሙሽሪት አቋም,, ዛሬ በናታቹ የመጬ ጠሮብኛል, ጭቅጭቅ አምሮኛል :lol: እስኪ ወደ አንዱ የአበሻ ሬስቱራንት ሄጄ ወደ በሁዋላ እቧጨቃለው,, እንጀራዋ ቀጠነች,, ወጥ ጨምሩልኝ ምናምን እያልኩ አለ አይደል የጭቅጭቅ ጥማቴን እወጣለው,, እኛ አበሾች እኮ ግን የጭቅጭቅ ሱስ አለብን :lol: :lol: እናቴ ትሙት,, ይሄ ነገር ታድያ አራዶችንም ሆነ ሸዋዬዎችን ይመለከታል,, ድሮ እኛ ሰፈር የነበሩ አሮጊቶች እንዲሁ ጭቅጭቅ ሲያምራቸው ወደ ሰፈራቸው ያለ ሱቅ ይሄዱና ''የተከፈተ ኦሞ ሸጥክልኝ'' , ''የተቦረቦረ ሳሙና ነው'' , ''ቃርያው በደንብ አያቃጥልም'' እያሉ ባለሱቁን ሲነዘንዙት ይውላሉ,, ብታዩ እኮ ሆን ብለው ለጭቅጭቅ ተዘጋጅተው ነው የሚሄዱት,, ታድያ እዛ ሰፈር ያሉ ሸምሱዎች ምናምን በቃ ሱቅ የሚሸጥ ሲቀጥሩ ጭቅጭቅ የሚችል ምናምን ነው የምቀጥሩት,, የጭቅጭቅ ነገር ሲነሳማ እኮ አቤት እዛ ጌጃ ሰፈር እያለሁ የነበረው ጭቅጭቅ :lol: :lol: እንደምታውቁት የኛ ሰው አብሮ መብላት እንደሚወድ ሁሉ አብሮ ማራትም ይወዳል,, :lol: የጋራ ሽንትቤት ነው ያለው ለማለት ነው :lol: ታድያ ሽንት ቤቱ የሞላና መመጠጥ ያስፈለገ ጊዜ ነው ጦርነት ከች የሚለው,, አዋጥተው ስለሚከፍሉ አልኳቹ በቃ ''እኔ ሶስት ቀን ብቻ ነው ያራሁት'' :lol: :lol: ምናምን እያሉ ላለመክፈል ሲጨቃጨቁ ይውላሉ,, አንዳንዴ ''አንቺ ባራሽው እኔ ልክፈልልሽ'' ሲባባሉማ በቃ ድክም ነው የምንለው አልኳቹ,, በተለይ አንድ የሆኑ ግቢማ መዝገብ አዘጋጅተውላቹ ሽንትቤት በተኬደ ቁጥር ይመዘገባል :lol: :lol: በሉ መጣሁ እኔም ልሂድና ልጨቃጨቅ,, ኮስተር ብዬ ሄጄ ነው የምጨቃጨቀው,, ሌሎቻቹም እንዲሁ ስትረስ ያለባቹ አንዳንዴ ጭቅጭቅ ጥሩ ነው,, ሂዱና ተጨቃጨቁ :lol:,, አንተ One-Now አንተም ሂድና ሰራተኛቹን ጨቅጭቅ,, :lol:
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby HD » Tue Aug 03, 2010 8:22 pm

እረስቼው,, አንቺ ቆንጂት,, ነይና እስኪ ስለ ጭቅጭቅ ንገሪን :lol:
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby ቆንጂት08 » Tue Aug 03, 2010 9:02 pm

አይ ሞኒክ አንቺ የሙዝ አያት ስትሆኝ እኔስ የራስታው,የአውራጃ ሌባው አያት ከማን አንሼ በሉ እነ hd ባዳዲስ ያራዳ ቃላቶች እንዳያዋክቡኝ እንጂ ምንም ዘመኑ ቢረዝም እኔ የነ ራስታው አያት ብዙ ጨዋታ አለኝ ታዲያ ሞኒክ አደራ ላስፎገር ስል አንቺ ሹክ በይኝ .....
ቆንጂት08
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 887
Joined: Wed Dec 19, 2007 3:49 pm

Postby ቆንጂት08 » Wed Aug 04, 2010 7:28 am

hd ግን ጭቅጭቅ ካልክ ብል ልጨቅጭቅህ እዛ ዋርካ ፈገግታ ላይ በጀመርከው ታሪክ 6 ጊዘ አልክና ስለ7ኛው ሳታወራ አንጠልትለሀው ጠፋህ ግን 7ኛው ላይ ምን ሆነ ልትል ነው ኮንዶሙ ተበጠሰ ወይስ ሴትዮዋ አረገዘች?ነው ቪያግራው የሰውየውን ልብ ጽጥ አርጎት እላይዋ ላይ ሞተ ለማለት ነው እዚ ያለሁበት ሀግር ስንቶእንድሚያጋጥማቸው
ለማንኛውም የጨጉዳን ግብዣ ድብዚ እንዳውም ችማግሌውን አትልየ ወስጅባት ተናዳ በዛው ጠፍታለች የባስውን የጭጉዳን ከሰማችማ በቃ ለሂወታም ሊያስፈራ ነው
ቆንጂት08
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 887
Joined: Wed Dec 19, 2007 3:49 pm

Postby ካለድ » Wed Aug 04, 2010 8:14 am

HD የስፈሬ:ልጅ:ስላም:ነው:እኔም:ቄራ:ነው:ተወልጄ:ይደኩት:እስኪ:እንደ:ጉድ:ቅደድ:ስለ:ስፈራችን
ካለድ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 599
Joined: Sat Jan 06, 2007 4:11 pm

Postby Monica**** » Wed Aug 04, 2010 9:42 am

HD ስላም ያራዳ ልጆች በሙሉ
እንዴት ናችሁ??? እኔና ጨጉዳ እንዳልኩህ ብዙ ትዝታ አለን ተወልደን ያደርግነው ሱዳን ቦርደር ላይም ቢሆን :wink:
HD የወሎ ስፈር ጨዋታህ በሳቅ ብዛት እምባዬ ጠብ እስኪል ነው የሳቅኩት የሶማሌዎቹ ነገር ግፈኛ :lol: :lol: :lol:
ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ታውቂዋለሽ ወይ ነው ያልከኝ??? ኦፍኮርስ በሚገባ አውቀዋለሁ የምወደው አባቴ ድንጋይ የተንተራስባት ቦታስለሆነች ልዩ ፍቅርና ከበሬታ አለኝ......በጣም ከቤተክርስቲያኑ ጋር ኮኔክሽኔን ለማሳወቅ ያህል ሚካኤል ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ስው መቀበር ከተከለከለ ብዙ አመታቶች አልፈዋል የተቀበሩትንም እያወጡ ከግቢው በታች ያለው የቀብር ቦታ ላይ መልስው ቀብረዋችዋል!!!! ላክሊ አባቴ ግን ቤተክርስስቲያኑ ግቢ ውስጥ ነው ቤት ውስጥ ያረፈው ግቢ ውስጥ መቅበር ከተከለከለ በህዋላ..... እና አዲስ ገና እግሬ ሲገባ አባቴን አይቼ ወደዚህም ስመጣ እሱን ተስናብቼ ነው እና ሚካኤል ምን ያህል ለኔ ልቤ ውስጥ እንዳለ ጉራዬን ለመንዛት ያህል ነው :lol: :lol: :lol:
እና አሁን ቄሶቹ ሶማሌዎች ናችው ነው የምትለኝ ወይስ ሶማሊኛ ተናጋሪዎች ናችው :lol: :lol: :lol: ለነገሩ እኔም የሶማሌው ፖፕሌሽን መብዛት ግርም ይለኛል.....እዛ ስፈር የማውቃችው ስዎች በሙሉ ትልቁን ቤት ለሶማለዎች አከራይተው ስርቪስ ውስጥ ይኖሩ ነበር አሁን አሁን ግን ማንም ለሶማሌ ማከራየት አይፈልግም ሁሉ ነጭ ተከራይ ፈላጊ ነው :lol: :lol: :lol: :lol:
የዛሬን አያድርገውና ወሎ ሰፈር ምርጥ ስዎች የሚኖሩበት ምርጥ ስፈር ነበር....አሁንማ እልም ያለ ቢዝነስ ሴንተሮች በዝተዋል!!! እኔ ልጅነቴን እዛ ስፈር ላሳልፍ እንጂ የጉርምስና ዘመኔ ብስራተገብሬል ነው ያሳለፍኩት እና ልዩ የሆነ ኮኔክሽን አለኝ......ባልወለድበትም ልክ እንደተወለድኩበት ሆኖ ነው የሚስማኝ.....ግርም የሚለኝ ነገር ከቴሌው አለፍ ብለህ እስከብስራተገብሬል ድረስ የነበረው ሜዳ ከትልቅነቱ የተነሳ እራሱን የቻለ አገር ነበር የሚመስለኝ......አሁን አሁን ሳየው ታብሌት የምታክል ሜዳ እንዴት ሆኖ ነበር እንደዛ ሂውጅ የሚመስለኝ?? :lol: :lol: :lol:
አንድ የሚቆጨኝ ነገር ሁሌ ሳርቤቱጋ ስደርስ ወርጄ ውስጡ ምን እንደሚመስል ባለማየቴ እናደዳለሁ እስኪ ሌላ ጊዜ ስሄድ አየዋለሁ......የአዱ ገነት ትዝታ በቀላሉ አይለቅም
የብስራተገብሬሉ ለማኞችም ቀላል አላሳቀችኝም :lol: :lol: :lol: :lol: $100.00 እንደሚስጥ ባውቅ ኖሮ እኔም እለምን ነበር :lol: :lol:
ደሞ ቄራ ቅርብህ ከሆነ የቡልጋሪያ ኤምባሲ( የድሮው) ወይም ጎተራ አካባቢ ልጅ ነህ ማለት ነው??? የቄራ ልጆች ደስ ይሉኛል አራዳነታችው :wink:
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 9 guests