የአዲስ አበባ ልጆች ከች በሉ/ፋራዎች እንዳትገቡብን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby Monica**** » Wed Aug 04, 2010 9:53 am

ቆንጂትዬ አዱ ገንተን የፈጠሯት አያቶች ናችው እኮ እምዬ ሚኒሊክ ቅድም ቅድም አያቶች :lol: :lol: :lol:
አንቺ የሁለት ልጅ አያት ነሽ? እኔ የሙዝነት እንጀራ አያት ነኝ"!!!እሱና ሀሪከን ግን ከዋርካ ላይ እንዲህ ቫኒሽ ያድርጉ????
ቆንጂት08 wrote:አይ ሞኒክ አንቺ የሙዝ አያት ስትሆኝ እኔስ የራስታው,የአውራጃ ሌባው አያት ከማን አንሼ በሉ እነ hd ባዳዲስ ያራዳ ቃላቶች እንዳያዋክቡኝ እንጂ ምንም ዘመኑ ቢረዝም እኔ የነ ራስታው አያት ብዙ ጨዋታ አለኝ ታዲያ ሞኒክ አደራ ላስፎገር ስል አንቺ ሹክ በይኝ .....
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby One-Now » Wed Aug 04, 2010 4:10 pm

HD wrote: እዛ ታድያ ድንገት ካፍሽ አምልጦሽ እናትህ እንዲህ ትሁን ካልክ በቃ አለቀልህ, ''እንዴ እምዬን እናቴን?'' ብሎ በያዘው ዱላ ድራሽህን ያጠፋዋል, አንድ 2 አመት ከሆናቸው በሁዋላ ግን እሱ ራሱ እናትህን ልብዳት እያለ ሲሳደብ ትሰማዋለህ


ላንተ አራድነት ይሄ ነው አይደል? አስተዳደገ ብልሹ የመንደር ልጅ መሆንክን እያረጋገጥክልን ነው. ለእናቶች ክብር የማትሰጥ ሰው ነህ. እናት የለህም እንዴ?

ከጥሩ ቤተሰብ የመጣንና በስነስርአት ተኮትኩተን ያደግን የአዲስ አበባ ልጆች እንዳንተ በብልግና አንጨማለቅም. ብልግናን እንጸየፈዋለን እንጂ አንኩራራበትም. "የአራዳ ልጅ ነኝ" እያልንም ጉራ አንቸረችርም. የክፍለሀገር ልጅ ምናምን እያልንም የሰውን ክብር አንነካም. ሰውን በሰውነቱ እናከብራለን እንጂ ከገጠር መጣ ብለን አንንቅም: አንሳደብም.

"የሀብታም ልጅ: የቅልጥጤ ልጅ" እያሉ ድሮ መንገድ ዳር ቆመው እየተሳደቡ አላስወጣ አላስገባ ከሚሉን ስራፈት ዱርዬዎች አንዱ እንደሆንክ ይሰማኛል. አልጠላህም. ስለደረሰብህ የአስተዳደግ ብልሹነት ግን አዝንልሀለሁ.

ካሰብክበት ደግሞ አሁንም ራስህን ማሻሻል ትችላለህና የተሰትካከለ አመለካከት ያለው ሰው ለመሆን ሞክር. ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰውነቱ ሰው ነው. ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሰው ነው. ከገጠር መጣ ብለህ ኢትዮጵያዊን የምትንቅ ከሆነ ማንነትህ የተምታታብህ ግለሰብ ነህ. ከገጠር ጋር ግንኙነት ያለው አንድም ዘመድ የለህም ማለት ነው?

አንድ ነገር ስለራሴ ልንገርህ: አዲስ አበባን ከቆረቆሩ ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ጋር የምዛመድ ሰው ነኝ ብዬ በፍጹም አልኩራራም.

ይበቃሀል
One-Now
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Tue Jul 27, 2010 1:49 pm

Postby HD » Wed Aug 04, 2010 6:33 pm

ሞኒካ አማን ነው? ኬፍ ተብሏል,, ጭውቴውን አሁን ከች አረግሽው አይደል? ቆንጅት :lol: :lol: የጀመርኩትን ቀልድ እዛው ሄጄ እጨርስላቿለው,, ልብ አንጠልጣይ ነው አይደል? :lol: :lol:, ካለድ የሰፈሬ ልጅ ስላም ነው ወይ? የቄራ ልጅ ነህ ለካ? አቦ ይመቸን, እስኪ የየት አካባቢ ልጅ እንደነበርክ ንገረን, ማለትም ቄራ ምኑ ጋር,, የቄራ አራዶች መለያችን የነበረው ያው ሁላችሁም እንደምታውቁት ሞተር ሳይክላችን ነው :lol: :lol: , በዛ ሞተር ስንት ቢዝነስ ይሰራበት ነበር መሰላቹ,, በተለይ በተለይ ከቄራ ግቢው በሬ ደንብሮ ከፈረጠጠ ያው ሁሉም ሰው እኛን ወደ መማጸን ይገባ ነበር,, አንተ One-Now ትዝ አይልህም አንድ ጊዜ በሬው ፈርጥጦ እንደ ስፔን ትርዒት በቀንዱ ያነሳህ ጊዜ? እናማ በቃ ጀለሶቻችን ሞተሮቻቸውን ብድግ ብድግ ያደርጉና በሬውን መያዣ ወጥመድ አላቸው, እንደ የቮሊቮል መረብ አይነት ነገር ማለት ነው,, ከዛ ሁለት ሞተሮች ሆነው በሬውን ይይዙታል,, ከዛ ታድያ የቄራ ድርጅት በትንሹ ሀምሳ ብር ይከፍላቸዋል ለዛ ማለት ነው,, ብዙ ጊዜ እኔ ሞተር አልነዳም ነበር,, የኔ ዋናው ስራ በሬ ማስደንበር ነው,, :lol: :lol: አንዳንዴ አለ አይደለ ኮይን ሲጠርብን አውቀን በሚስጥር እናስደነብረውና እኛው እንደገና ይዘን ብር እንቀበል ነበር :lol: :lol: ቄራ ሰፈር የሚገርማቹ ከጌጃ ሰፈር መርኬክስ ምናምን ሲነጻጸር የመጬ ጠራ ያለ ሰፈር ነው,, በተለይ ከሁሉ የሚመቹት ከገነት ሆቴል አካባቢ የሚወጡት የሽመልስ ሀብቴ ሀይስኩል ቺኮችና እዛ ቄራ ጋር ያለው ትምሮ ቤት ስሙ ጠፋኝ,, እንዳውም ቀይ ከላይና ከስር አረንጓዴ ነበር መሰለኝ የሚለብሱት,, ኤኒዌይ እነሱን ማሳደድ ማለት በቃ የመጬ ነበር የሚመቸው,, ካለድ እስኪ ስለ ቄራ ብዙ እንቀዳለን ወደ ሞኒካ ሰፈር ሩዋንዳ አካባቢና ወሎ ሰፈር ምናምን ይውራለት,, አንቺ ሞኒካ ለካ ሱማሌዎቹን አንቺም ታውቂያቸዋለሽ? አቤት ስነስርዐት, ለቡሄ ምናምን ደሞ ሆያ ሆዬ እንደሚጨፍሩ ታውቂያለሽ አይደል? እነሱ ገንዘብ የሚገኝበት ቦታ ላይ ሁሉ አሉ,, ዘይ ዶንት ጊቭ ኤ ፋክ,, :lol: :lol: አንድ እዚህ ያለሁበት የሚኖር ሱማሌ አለ,, እንዳውም እሱ የተወለደው እዛ ሱማልያ ስለሆነ ቦሌ የኖረው ለጥቂት ጊዜ ነው,, እና አሁን በቃ ሆያ ሆዬ እያለ ሙድ ይይዝብኛል :lol: :lol: አንዳንዴ የለማኞቹን ኮፒ እያረገ ''ስለግዛቤር'' ሲል የመጬ ነው ድክም የሚያረገኝ,, እኔ ግን አለ አይደለ የገባው ነው እልና ሙድ አልይዝበትም,, እዛ ሰፈር ያሉት ቄሶች ሱማሌዎች ናቸው ያልኩሽ ሲሉ የሰማሁትን ነው :lol: :lol: አይ ቲንክ ሙድ እየያዙባቸው ነው :lol: :lol: ደሞ በሁዋላ ከዋርካ ጀነራል እንደ ጉንዳን በሰልፍ መተው እዚህ እንዳይቀውጡት :lol: :lol: እዛ ሰፈር ስትሄጂ የሞቃዲሹ ቶክስ ምናምን ሁላ ያስተጋባል አሉ,, :lol: :lol: እዛ ከሚካኤል ጀርባ ያለውን የቃለ ህይወት ነው ምናምን ሀይስኩልስ አታውቂውም? ፐርፕል ነገር የሚለብሱት? አቤት እዛ ያሉት ቺኮች :roll: እንዴት እንደሚመቹ አልኩሽ,, እነሱን ለመጥበስ ሲል አንዱ ጀለሴ የትምሮ ቤታቸውን ዩኒፎርም ከአንዱ ፍንዴክስ ላይ ገዛ :lol: :lol: ማታ ማታ ሲለቀቁ በቃ እሷን ገድግዶ ይሸኛቸዋል ምናምን አልኩሽ,, ቡሀላ ታድያ ጥያቄ ማብዛት ጀመሩ,, ክፍልህ የት ነው ምናምን ፎንቃ ያዛቸው መሰለኝ ,, :lol: :lol: እዛ ሳር ቤጥ ደሞ :lol: :lol: የትኛውን ሜዳ ነው የምትይው? እዛ ሰፈር ያለ ሜዳ ደሞ ብዛቱ በስማም,, የፈረስ ግልቢያ, የጎልፍ, የኳስ, የግጦሽ ሜዳ ደሞ ለፈረሶቹ, :lol: :lol: ፈረሶቹ የሚጸዳዱበት ደሞ ሌላ እራሱን የቻለ ሜዳ :lol: :lol: እዛ ሰፈር እኮ ሜዳ በሜዳ ነው,, አንድ ግን የሆነ ግብዳ ሜዳ ነበር ልክ ሳርቤት እጥፍ እንዳልሽ ቡሀላ ግን ሜድሮክ ከች አለና አሳጠረው :wink: አንድ ቀን እኔና ጀለሶቼ ኮይን ጠረረብንና እዛ ሀብታም ሰፈር ሄደን ትንሽዬ የተቆፋፈረች ሮድ ነበረች እሷን ጠጋግነን ምናምን በቃ የሚያልፉ ሸዋዬዎች የመጬ ነው ያሻሩን አልኩሽ,, የሚገርምሽ እኮ ቄራ ውስጥ ስንት የተበላሸ መንገድ ነው ያለው, ግን እኛ ብስራተ ገብርኤል ድረስ ሄደን እንሰራለን :lol: አንድ ጊዜ በተለይ የማልረሳው እዛ ያየሁት ግብዴ ውሻ ነው,, በስማም እንደዛ አይነት ውሻ እዚህ መጥቼ እራሱ አንድ ጊዜ ነው ምናምን ነበር ያየሁት ቆይቷል :lol: :lol: ያን ለታ እኔና ጀለሴ ብር ሁላ አስይዘናል እኔ ውሻ ነው ብዬ እሱ ደሞ ድብ ነው ብሎ :lol: :lol: ሌላኛው ጀለሳችንማ ከቄራ ያመለጠ በሬ ነው ብሉ ሞተር እስከማስጠራት ሁላ ደርሶ ነበር :lol: :lol: :lol: እስኪ የጠዋት መክሰስ ቡሌ ጠልፌ ልምጣ ,, :lol: :lol: ይመቻቹ,, አንተ One-Now እናትህን ዋናው የጅኒ አለቃ ይውቃትና ምንድነው እዚህ እየመጣህ የምትገነፍለው?
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby ትርዛ » Wed Aug 04, 2010 10:23 pm

እኔስ እንደው ወደእስራኤል ስመጣ አይሮፕላን ለመሳፈር መጣሁበት እንጂ ተአዲስ አበባ አይደለሁም:: :lol: :lol: :lol: እንደው እዚያ ወሎ ለያውም ጦሳ ተወልዳ አድጋ "ጀሚላ ተቸርችር ጉዳና" ስትል አለማፈሯ ነው የሚገርመው:: :lol: :lol: :lol: ወርቅነህ ና ና መልስ ስጥ አንት ሉጢ
ትርዛ ነኝ (የነፍሴ ደስታ)
ትርዛ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 78
Joined: Fri Apr 09, 2010 10:10 pm

Postby ጦምኔው » Wed Aug 04, 2010 10:29 pm

ቄራ ሰፈር የሚገርማቹ ከጌጃ ሰፈር መርኬክስ ምናምን ሲነጻጸር የመጬ ጠራ ያለ ሰፈር ነው
:shock:

ኧረ ገደላ :!: ዝም ስንል እኛንም ከጌጃ ጋር ልትጠርቡን ነው እንዴ ፍሬንድ?.... አሁን ቄራ ሰፈር ከኛ ሰፈር የሚበልጠው በምንድነው አባ?.......እንዴ እኛ እኮ ቄራዎችን ሱሉልታ ሙቭ አድርገን ሁላ እንቦንሳቹዋለን :lol:........አሁን ቄራ ሰፈር ነው?...... ቄራ ሲባል ወደ ጭንቅሌዬ ከች የሚለው ስጋ ነው....ሙክት.... እና ደግሞ ኮርማ..... በዛ ላይ ደሞ ስኔፉ.... :lol: HDያ አትዋሺና እናንተ ሁላ ኳስ ለመጫወት ስትሄዱ አፍንጫቹን ቤት አይደል እንዴ ዱቅ የምታደርጉት?. :lol:..... ሚኪያልን ከምሬን እኮ ነው...... ይልቅ ቄራዎች በጣም የምትታወቁት ጩቤ በመሳል ነው...... ቄራ አድጎ ጩቤ የሌለው ልጅ ያለ አይምስለኝም......ገና ስትወለዱ ሁሉ ማዘሮቻቹ በጡት ፋንታ ጩቤ እና ሞረድ አይደል እንዴ የሚፖሽሯቹ ? :lol: :lol: በደቦ መካነት ምናምን ነው ሆቢያቹ ሁላ....ግራ ቂጡን ያልተወጋ የቄራ ልጅ አለ እንዴ? :lol:...ስልሽ መርኬን እና አካባቢዎቿ በጣም ነው የምነሠዳባቹ......እንጠጥርባቹዋለን ስልሽ አባቱ :!:

ይልቅ ጭውቴሽ ተመችቶኛል....አቦ አደራሪው...... ይመችሽ ያራዳ ልጅ.....እኛም ሲመቸን ከች ብለን እንቀዳለን......

ሞኒክ አሪፏ.....አብሽር ብለናል እናቱ....አራድኛሽ ሰላም አለው ....10/10.....ሀሀሀ. :lol:

ፒስ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby HD » Wed Aug 04, 2010 11:23 pm

ጦምኔክስ ሰላምን ነው ወይ? እንዴ? ለካ የመርኬክስ ልጅ ነሽ? ሙድ ለመያዝ ለመያዝማ በመርኬክስ ልጆች ሙድ መያዝ ማን ያቅተዋል ብለሽ ነው,, :lol: ግን አለ አይደለ አውክዋርድ እንለዋለን, መርኬክስ እና ቄራ ሲነጻጸሩ እኮ ቻይናና ጅቡቲ ማለት ናቸው, :lol: :lol: ትዉጡናላቹ እኮ እናቴ ትሙት :wink:, አየሽ እኔ ለማለት የፈለኩት ሳኒቴሽን ምናምን ለማለት ነው,, ጩቤማ የሌለው የቄራ ልጅ ጥርስ የሌለው አምበሳ ነው የሚባለው,, :lol: :lol: የስኔፉ ነገርማ ስለለመድነው ለኛ ምንም አይመስለንም, ደሞ እንዳልኩሽ እኔ ወደ ቄራ ሙቭ ያረኩት ካደኩ በሁዋላ ነው, ጌጃ ሰፈር ነች ያሳደገችኝ :lol: ለመሆኑ ጦምኔክስ ከየትኛው ''ተራ'' ነሽ? :lol: :lol: ያው እንደምታውቂው መርኬክስ የተከፋፈለችው በጠቅላላ ''ተራ'' በሚባሉ ሰፈሮች ነው :lol: :lol: ሱማሌ ተራ,ቦምብ ተራ, ሸክላ ተራ,ሸራ ተራ,ብቅል ተራ,ጎማ ተራ,ሸማ ተራ, በስማም ስንት ናቸው :lol: :lol: እኛ ሰፈር ያለችን ያቺው በግ ተራችን ብቻ ነች, :lol: :lol:
ለማንኛውም ይመችሽ ጦምኔክስ አቦ, ከች እያልሽ እስኪ ልቀቂብን
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby HD » Wed Aug 04, 2010 11:25 pm

ትርዛ እረስቼው ,, ዌልካም ቱ ዘ አራዳ ተራ :lol: :lol:
ጭውቴውን ከች አርጊልን እንጂ ከቤርሙዳም ብትሆኚ ጣጣ የለውም ::
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby ዋናው » Wed Aug 04, 2010 11:35 pm

ጦሜx እዚች ቤት ውስጥ ያንተን ስም ሳላይ አልገባም ብዬ'ኮ ነው ኢግኖር የገጨዉት... ዛሬ ጉግል ጥሎኝ ከች ብል አጋቹ ብዬ ምጥት...
እኔ'ምለው ግን አሁን ባዱገነት ርዕስ ስር መርኬን 'ሚያስንቅ ሠፈር ተነሣ ሲባል የ6ኪሎ አውልትና የጎርጊስ አውልት ተቃቅፈው አያለቅሱም....?
ጦሜx የቄራ ቺኮቹ ሳይቀር'ኮ ጥርሳቸዉን በጩቤ ነው 'ሚፍቁት በአሲድ ነው ሚጉመጠመጡት... እኛ መርኬዎች ለፍቅር እንጂ ለገጀራ ጊዜ የለንም ... ለማንኛዉም ግን እቺ ቤት አንዳንድ ሸላይ ቀደዳ አላት...
ከዚህ ሠፈር ወግ ጋር ሚመሳሰል ሙድ አላት::

ፍቅር ጀባ ነው ያለው እሪኩም ካሜራዉን እየወለወለ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
ዋናው
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2806
Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
Location: ሕልም ዓለም

Postby ገላጋይ-1 » Thu Aug 05, 2010 1:45 am

HD wrote:ዑዑዑፍፍፍፍፍፍፍ,, ዛሬ ጎፈሬያችን ሹርባ ይሰራለታል ተብሏል,, እዚህ ውስጥ ጸጉር መስራት የምትችሉ?? እስኪ እጃቹን ወጣ ወጣ አርጉ,, ቂጣቹን ፈንደድ ፈንደድ :lol: :lol: ሸዋዬዎች ሰላም ናቹ? አዳዲስ አራዶች ተጨምረውልኝ አሁንማ እንደ ልቤ ነው የምሳፈጣቹ,, ዘይ ጋት ማይ ባክ :wink: አንተ One-Now አለህ? እስኪ ደሞ ስለ ድሮው የኔና ያንተ ታሪክ ልደስኩር,, ትዝ ይልሀል ያኔ ለቡሄ? እኛ ሆያሆዬ ልንጨፍር እናንተ ቤት ስንመጣ? አንተ ሆያሆዬ አትጨፍርም ነበር ,, እህትህ ለእንቁጣጣሽ አበባየሁሽ ልትጨፍር ስትወጣ አንተን ይዛ ትወጣ ነበር,, የሰፈሩ ሰው ''ልጃገረዶች መጡ'' እያሉ ኮይን ምናምን ሊሰጧቹ ሲወጡ አንተን አይተው እንደዛ እንድልደከሙብህ,, :lol: :lol: አንተ የአዱ ገነታችን አሰዳቢ,, አዲስ አበባን የቆረቆሩት ዘመዶቼ ናቸው አልሽ,, እሺ የእቴጌ ጣይቱ የልጅ ልጅ :lol: :lol: ልዑል ሸዋዬ :lol: :lol: ግርማዊነቶ,,አንተ የሰራተኛ አጫዋች,, 24/7 ቤት ውስጥ ተዘግቶብህ እኛ ውጪ በሰፈራችን ጭውቴውን ስናደራው አንተ በቀዳዳ ስትቃኝ :lol: አሁን አንተ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ ትላለህ? ካንተ እንደወረደ ጨምጫሚ ይሻላል አቦ,, እሱ እንኳን ባይሆን ቆቅ እያባረረ, ፍየላቸውን እየነጨ ስሜቱን እያረካ ምናምን ነው ያደገው,, ጨምጬክስ ሰላም ነው? አይ ጨምጬክስ ይሄ ሰውዬ እኮ አቦ በናትሽ በጠበጠን,, ፍየላቹን አውሰውና እስኪ ስሜቱን ያርካ,, ኤድስ የለባትም አደል? :lol: :lol: እናቱነኝለትና ይሄ ሙሽሪት አቋም,, ዛሬ በናታቹ የመጬ ጠሮብኛል, ጭቅጭቅ አምሮኛል :lol: እስኪ ወደ አንዱ የአበሻ ሬስቱራንት ሄጄ ወደ በሁዋላ እቧጨቃለው,, እንጀራዋ ቀጠነች,, ወጥ ጨምሩልኝ ምናምን እያልኩ አለ አይደል የጭቅጭቅ ጥማቴን እወጣለው,, እኛ አበሾች እኮ ግን የጭቅጭቅ ሱስ አለብን :lol: :lol: እናቴ ትሙት,, ይሄ ነገር ታድያ አራዶችንም ሆነ ሸዋዬዎችን ይመለከታል,, ድሮ እኛ ሰፈር የነበሩ አሮጊቶች እንዲሁ ጭቅጭቅ ሲያምራቸው ወደ ሰፈራቸው ያለ ሱቅ ይሄዱና ''የተከፈተ ኦሞ ሸጥክልኝ'' , ''የተቦረቦረ ሳሙና ነው'' , ''ቃርያው በደንብ አያቃጥልም'' እያሉ ባለሱቁን ሲነዘንዙት ይውላሉ,, ብታዩ እኮ ሆን ብለው ለጭቅጭቅ ተዘጋጅተው ነው የሚሄዱት,, ታድያ እዛ ሰፈር ያሉ ሸምሱዎች ምናምን በቃ ሱቅ የሚሸጥ ሲቀጥሩ ጭቅጭቅ የሚችል ምናምን ነው የምቀጥሩት,, የጭቅጭቅ ነገር ሲነሳማ እኮ አቤት እዛ ጌጃ ሰፈር እያለሁ የነበረው ጭቅጭቅ :lol: :lol: እንደምታውቁት የኛ ሰው አብሮ መብላት እንደሚወድ ሁሉ አብሮ ማራትም ይወዳል,, :lol: የጋራ ሽንትቤት ነው ያለው ለማለት ነው :lol: ታድያ ሽንት ቤቱ የሞላና መመጠጥ ያስፈለገ ጊዜ ነው ጦርነት ከች የሚለው,, አዋጥተው ስለሚከፍሉ አልኳቹ በቃ ''እኔ ሶስት ቀን ብቻ ነው ያራሁት'' :lol: :lol: ምናምን እያሉ ላለመክፈል ሲጨቃጨቁ ይውላሉ,, አንዳንዴ ''አንቺ ባራሽው እኔ ልክፈልልሽ'' ሲባባሉማ በቃ ድክም ነው የምንለው አልኳቹ,, በተለይ አንድ የሆኑ ግቢማ መዝገብ አዘጋጅተውላቹ ሽንትቤት በተኬደ ቁጥር ይመዘገባል :lol: :lol: በሉ መጣሁ እኔም ልሂድና ልጨቃጨቅ,, ኮስተር ብዬ ሄጄ ነው የምጨቃጨቀው,, ሌሎቻቹም እንዲሁ ስትረስ ያለባቹ አንዳንዴ ጭቅጭቅ ጥሩ ነው,, ሂዱና ተጨቃጨቁ :lol:,, አንተ One-Now አንተም ሂድና ሰራተኛቹን ጨቅጭቅ,, :lol:


:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

ወይ HD በሳቅ ገደልከኝ.... ምንም እንኩአን በአንተ አባባል ሸዋየ ብሆንም....

በነገራችን ላይ እኔ ደግሞ ከሚያኮሩኝ ነገሮች አንዱ አድስ አበባ ያለመወለደ ነው ... ከምር...

አንተ ግን ማነህ? የማውቅህ መሰለኝ... አስተማማኝ? ጃንሚዳ?.... ቀጥል ጫወታውን... :lol:
ገላጋይ-1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Fri Aug 25, 2006 5:43 pm

Postby ኤልሳ* » Thu Aug 05, 2010 1:59 am

የድሬን ልጆችንስ ምን ትሉ ይሆን?:twisted:
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

Postby ጨምጫሚ » Thu Aug 05, 2010 2:54 am

HD wrote: ልዑል ሸዋዬ :lol: :lol: ግርማዊነቶ,,አንተ የሰራተኛ አጫዋች,, 24/7 ቤት ውስጥ ተዘግቶብህ እኛ ውጪ በሰፈራችን ጭውቴውን ስናደራው አንተ በቀዳዳ ስትቃኝ :lol: አሁን አንተ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ ትላለህ? ካንተ እንደወረደ ጨምጫሚ ይሻላል አቦ,, እሱ እንኳን ባይሆን ቆቅ እያባረረ, ፍየላቸውን እየነጨ ስሜቱን እያረካ ምናምን ነው ያደገው,, ጨምጬክስ ሰላም ነው? አይ ጨምጬክስ ይሄ ሰውዬ እኮ አቦ በናትሽ በጠበጠን,, ፍየላቹን አውሰውና እስኪ ስሜቱን ያርካ,, ኤድስ የለባትም አደል? :lol: :lol:

ቼዲ ተው አንተ እንደዚ አይነት እርጥብ የሊስትሮ ቀልድ እርግፍ አርገህ ተወው አላልኩህም ከሰው ጋር ያጋጫል ስንት ጊዜ ነው የመከርኩህ እንደቄራው ጥንባት ለምደህው መተው አስቸገረህ መሰለኝ :lol: :lol: :lol: :lol:
አባትህ ደህና ናቸው ግን ይሄን ምትልክላቸው ዶላር መቼም በቢራና በጠጅ ነው ሚጨርሱት ከዛ የተረፈውን ሴተኛ አዳሪ በመንጨት በዚ ኑሮ በተወደደበት ዘመን :lol:
ጨምጫሚ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1075
Joined: Sun Sep 20, 2009 6:44 am

Postby HD » Thu Aug 05, 2010 2:55 am

እቧ? :shock: መርኬዎች ምንድነው ጋንግስተር ሆናቹብና አቦ, ጦምኔክስ ምነው ጡሩምባውን ነፋህላቸው እንዴ? እናንተ ግን ተዉ አትገፋፉኝ, እኔ በመርኬ ሙድ አልይዝም, መርኬ ላይ ሙድ የሚይዝ መጨረሻው አያምርም እናቴ ትሙት, መርኬዎች ግን ምንድነው ቄራ ላይ ያለባቹ? እኛ ሳንጃችን መለያችን, ስጋችን ኩራታችን, ሽቷችን የውጭ ምንዛርያችን ነው እኮ አቦ, እኔ በመርኬ ላይ አልሻፍድም, ሽምብራ አሳ በጤና ተብሏል, ደሞ ጩቤ ለፍቅር አይሆንም ያለው ማነው? ቾኮቻችንን ሂዱና ጠይቋቸው ምን ምን እንደምናረግ በጩቤያችን, :lol: :lol: ኤኒዌይ አዳዲስ ብቅ ብቅ ያላቹ የአራዳ ልጆች አማን ነው? ዋናው, ኤልሳ (ፈገግታ አንዳንዴም ጥሩ ነው),ጦምኔክስ ሰላምታዬ በቄራ ላዳ ታክሲ ከች ይበልላቹ, መርኬዎች ግን ስለ ፍቅር እያወራቹ ለምን ሀርድ ትቦጭቃላቹ? የቦምቤይን የሚያክል ህዝብ ቢኖራቹ የምንፈራቹ መሰላቹ እንዴ? ለምንድነው ፒስ የማታወርዱት? ብሄረ ጽጌ ባሉት ዝንጀሮዎች ይዣቿለው ፒስ አውርዱ, አሁን የጋራ ጠላቶቻችን ሸዋዬዎች እያሉ ? መርኬክሶች ግን ከምር በውይይት ታክሲ አይደል እንዴ ከቦታ ቦታ የምትንቀሳቀሱት? በዛ የተሳፈረ ሰው እኮ ሹፌሩ ፍሬን በያዘ ቁጥር መሳሳም ነው, :lol: እኔ እዛ ላይ ከተሳፈርኩ አሪፍ ቀሽት ልጅ ፈልጌ ከሷ ፊለፊት ነው የምቀመጠው :lol: በፍሬን እያሳበብኩ ለመለመጥ :lol: ሙሽራ ሁላ የሚወጣው እኮ በውይይት ታክሲ ነው አሉ, :lol: :lol: እዛ ከሸራ ተራ ትንሽ ዝቅ ብሎ ያለው ምን ተራ ነበር? ስሙ ጠፋኝ, እዛ ከች ብዬ አንድ ቀን አንድ ግር ካልሲ በስሙኒ ሲሸጥ አይቻለው አቡነ አረጋዊን, ሰልባጅ ማንክያና ሹካ በአስር አስር ሳንቲም ሲሸጥ እራሱ አይቻለው, እኛስ ቺኮቻችንን ስጋ ቁርጥ, ክትፎ, ጥብስ, ምናምን እያበላን ነው የምንደክላቸው, እናንተ እዛ በስሙኒ አንድ ግብዴ ጉርሻ ቡሌ አሽራቿቸው አይደል እንዴ የ50 ብር የምትነጯቸው? :lol: :lol: እኔ ሙድ አልይዝባቹም እንጂ ስንት እቀድ ነበር, :lol: መርኬክሶች ግን ይመቻቹ, እኔ መርኬን ከፓሪስ በላይ ነው የምወዳት, እዛ ገብቶ እኮ ግርግሩን ማየት እራሱ ሰንሴት ከማየት ይበልጣል, ከሁሉ የሚመቸኝ ግን ሸዋዬዎችን እንደ ቴኒስ ኳስ ስትጫወቱባቸው ነው, አንተ ካለድ, ናና አግዘኝ, አሁን አስራ አምስት ሆነው ይመጣሉ :lol: ብቻዬን አልችላቸውም :lol: ይመቻቹ የአራዳ ልጆች ግን ከምር, እስኪ ከች በሉ ደሞ.........የቄራ ሽቶ ለቺኮቻቹ እልካለው,, አንተ ጨምጫሚ ስለም ነው? ጫት በሙዝ እየነፋህ ለምን እዚህ ትወራጫለህ? :lol: :lol: የሊስትሮን ቀልድ ማናናቅሽ ነው? ሊስትሮ ሲቀልድ እኮ የሚኒሊክ ሀውልት ሁላ ይስቃል አሉ,, ሳቅ በሳቅ ኪኪኪኪኪ
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby ጦምኔው » Thu Aug 05, 2010 6:59 am

ዋንቾ ከባድ ጀለስ...አማን ነሽ አባቱ?.....አቦ ዋርቃ ፍቅር ጭውቴ ጭውቴ ልትሸት ነው መሰለኝ......

ስማ እንጂ......ሀሀ የሐውልቶቹ አነፈረኝ አባ.. :lol: ....ሰማሽው ዛዳውን.........የስሙኒ ጉርሻ ምናምን ሲል...ጀት ፊት HD ያችን ጉርሻ ቢቀምስ አሳይለም ይጠይቅ ነበር የመርኬ ልጅ ለመሆን :lol: ... ከምር ግን የሱ ጉርሻ ነገር አይገርምም?......አንዳንዱማ ሲያጎርስ አንድ በያይነቱ እጁ ላይ ያዘዘ ነው የሚምስለው :lol:..... ቢወድቅብህ ዶሮ ጠባቂ ሁላ ሊያደርግህ ይችላል........ዶሮ ሲባል ዶሮ ተራ ትዝ አለኝ :lol:........ አይ አዲስ አባ.....በዶሮ ራሱ ስንት ስያሜ አላት እኮ.....ዶሮ ተራ.....ዶሮ ማነቂያ........ ቄራ ታዲያ በሬ ማነቂያ መሆኑ ነው ? :?: :lol: ..........

ስማ እንጂ አውቶቡስ ተራ ጌጃዎች ከች ሲሉ ከልመሀቸው ታውቃለህ?......እንደ ግመል በሰልፍ ነው የሚሄዱት......አንዱ ነቃ ያልው ከተሜው ነው መሰለኝ የሚመራቸው ከፊት.....ከመናሕእሪያው ወጥተው ሲሻገሩ አልኩህ ሀምሳውም እስቂያልቁ አያቋርጡም :lol: .......... እንዴ ክላክስ አይደለም ምድረ ሾፌር ሁላ ወጥቶ ኡ ኡ ቢል ስልህ :lol:...እኛማ ጮቤ ነበር የምንላቸው...... ከኃላቸው ሄደን " ጮቤ ረገጥክ" ስንላቸው አልኩህ በቃ እየዘለሉ... እየተሽከረከሩ የረገጡትን ጮቤ ይፈልጋሉ :lol: :lol:

አንዱ ጮቤ እኮ ነው እኛ ሰፈር ከች አለልሽና ያው ሊሸቃቅል ነገር ላቦሮዎች ከኪሱ አንዲት ክር ብቅ ብላ ነገር ይከልሙልሻል....እናልሽ ያው ጌጃ ሳቢ የሚቋጥረው በክር ነው ይሉልሽና ያንን ክር እየተከተሉ ሲስቡ ሲስቡልሽ አንድ ቱባ ክር ምናምን ይጠመጥሙልሻል.... ኔፓ......ማታ ያ ጌጃ ቤቱ ገብቶ ሱሪውን ሲያወልቅ ሚስቱ የሰራችለት የዳንቴል ፓንት የለም :lol:

ስማ አንጂ የቄራው.......የሱማሌዎቹ ቄሶች ጭውቴሽ ይደለል.... :lol: ... ለሱማሌ ቤት ማከራየት ስትል...ልክ ቤት ያከራሀቸው ቀን ግድግዳ ነው አሉ የሚሰረስሩት....የስልክ መስመር ፍለጋ :lol:... አንዱ እኛ ሰፈር ሸኪ ሱቅ የሚባል ሱቅ ነበረልሽ....እና ጠዋት ጠዋት እየሄደልሽ አንዱ ሶማሌ ስልክ ይደውላል......እና ሸባው ሰውዬውን በቀን በቀን ሲከልሙልሽ እና አንዳንዴም ቲፕ ምናምን ሲለቅባቸው አመኑትና ራሱ ዳያል እንዲያደርግ ይፈቅዱለታል.....ያ ሶማሌ ለካ አልኩሽ ዘመዶቹ ሁሉ በሀገር የሉም መሰለኝ ወይም ደሞ አስጨርዳጅ ምናምን ነው መሰለኝ ያልደወለበት ሀገር የለም......እና ዕልም አላለም!!......ሸኪው በቃ ከቴሌ ቢሉ ከች ሲልላቸው ካርታ የለውም እንጂ ATLAS ነው የመሰላቸው :lol: ያልተነሳባቸው በሽታ የለም.... ቶንሲል ደም ማነስ ቁርጥማት ውልቃት ምናምን :lol: ......እና በቃ የሰፈር ሰው ዕርዳታ ምናምን ሰብስቦ ነው የከፈሉት ( ከምሬን ነው)...ከዚያ በኃላማ በቃ ሸባው ሱማሌ ቀርቶ ራሳቸው ራሱ ስልክ ሲደውሉ ራሳቸውን አያምኑትም :lol:

አንዱ ደሞ እኛ ሰፈር አባቱ ቤቢ ፊያት ነበራቸው........አይ ቤቢ ፊያት......አታፍርም እኮ እሷም ሰው ጭና ስትሄድ :lol: እና ልጁን አባትየው መንዳት ያስተምሩታል......እና ያው መንጃ ፍቃድ ያወጣና ታክሲ መንዳት ይጀምራል.......እና ጀለስ " ታክሲ ስነዳ ጋቢናውን ብቻ የምነዳ እየመሰለኝ ተቸግሬያለው አላለኝም? :lol:

አቦ እስኪ ደሞ ይደቀስለት...... ፒስ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby HD » Thu Aug 05, 2010 6:53 pm

ቱፍ ቱፍ ቱፍ :!: :!: :!: የአራዳ ልጆች እንዴት ናቹ? ጦምኔክስ አቦ ይመችህ, :lol: :lol: የአውቶብስ ተራውን ጭውቴ እኮ መጀመሪያ ከች ላረገው ብዬ ነበር :lol: :lol: እንዳውም ትንሽ እንደጻፍኩ ምድረ ሸዋዬ በታንክ በBM በቦምብ ምናምን ታጥቀው ከች አይሉ መሰለሽ? አሁንማ እኛ ከተባበርን የታባታቸው ጭውቴውን እናደራባቸዋለን, :lol: :lol: ጦምኔክስ, የዳንቴሉ ነገር አቦ ድክም ነው ያደረገኝ, አንተ ቅንጭላት ራስ :lol: :lol: ከሁሉ ግን ድክም የሚያረገኝ ሲቃለዱ ነው :lol: :lol: በዱላ አናት ለአናት እየተባባሉ ቀልድ? :lol: :lol: ደሞ አዱ ገነት ከች ብለው ትንሽ ኮይን ምናምን ካጠራቀሙ መጀመሪያ ፐርቼዝ የሚያረጉት ሞባይል ነው :lol: :lol: እሷን ይዘው ፎቶ ይነሱና አገራቸው ይልካሉ :lol: :lol:, ሱማሌዎች ከነሱ ጋር ሲነጻጸሩ እኮ የመጬ የገባቸው ናቸው, ስልክ መጥለፍ ምናምን እንደ ሱማሌ የተካነ የለም, አንድ ግዜ እኛ ሰፈር አንድ ቤት እስከነ ግቢው ምናምን አስራ አምስት ሆነው ተከራዩና ከዛ ሳይነቃባቸው ከጎረቤት ያለውን የስልክ መስመር ጠልፈው ወደቤታቸው ቀጠሉት, :lol: :lol: ከጎረቤት ያሉት ሼባ ሁለት ቺኮች ነበራቸው አልኩሽ ደሞ, ቺኮቹ የመጬ ቀሽት ናቸው, እና የቴሌ ሂሳብ ከች ሲል አንድ ሺ ብር :lol: :lol: ሼባው በንዴት ልጆቻቸውን ከቤት ሁላ ሊያባርሯቸው ደርሰው ነበር, ቡሀላ በሚቀጥለው ወርም እንደገና ሴም ቲንግ, :lol: ''በቃ አሁንስ መረረኝ'' ይሉና ስልኩን አስቆረጠውልሽ አልከፍልም ብለው ፍርድ ቤት እየተከራከሩ እያለ, ወር ሞልቷቸው እንደገና ሌላ የሺ ምናምን ብር መጣላቸው, ለካ ሼባው ያስቆረጡት መስሏቸው ላይኑ ግን ስቲል ሱማሌዎቹ ጋር ጎረቤት ይሰራል, በቃ አልኩሽ ሰውዬው በዛች ሶስት ወር ከስተው ምናምን አልኩሽ :lol: :lol: ቡሀላ አንድ የተረገመ የሰፈራችን ሸምሱ ባለሱቅ ነበረ, እሱ እንዴት አርጎ ነቄ እንዳለ አላውቅም ሄዶ ለሼባው ነገራቸው ቡሀላ ምድረ ሱማሌ ተከርቸም ገባልሽ :lol: :lol: እኔ ግን መርኬክስ አንድ ግዜ ያየሁትን እስከመቼም አልረሳውም :lol: እናቴ ትሙት, :lol: አንድ የፔፕሲ መኪና ሙሉ ሳጥኖችን ጭኖ መርኬክስ ላይ ሲሄድ መኪናው እየሄደ እኮ ነው :shock: ከሁዋላ ተንጠልጥለውልሽ ሳጥኑን ያወርዱልሻል, ያው የመርኬ ሮድ ደሞ የተጨናነቀ ስለሆነ መኪናው ስፒድ አልነበረውም እና በቃ ሰዉ ዝም ብሎ ያያል አልኳቹ :lol: :lol: አይ የናንተ ግፍ, እዛ ሱማሌ ተራ ደሞ አንድ መኪና ፓርክ አርጋቹ ብትሄዱና ከ30 ደቂቃ በሁዋላ ከች ካላቹ መኪናዋን እስኬለተኗን ብቻ ነው የምታገኟት :lol: :lol: በዛ ላይ ሱሪ የገዙ መስሏቸው እቤት ሲሄዱ አሮጌ ጆንያ ተጠቅልሎ የሚያገኙ ሸዋዬዎች ነፍ ናቸው :lol: :lol: ይመቻቹ አቦ,, እመለሳለው,, ቄራን ደሞ ለቀቅ አርጉ,, :lol: እናታቹን ልቀፍላትና :wink:
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby ገልብጤ » Thu Aug 05, 2010 7:23 pm

ዋውውውውውው..ገዳይ ጨውቴ እኮ ነው..የድሮ አራዶች አቦ ይመቻችሁ...

HD...የስሞኒ ካለሲ ገዛሁ ያልሽው ከምናለሽ ተራ ነው. :D :D :D ..በረከተልሽ ግን
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests