የአዲስ አበባ ልጆች ከች በሉ/ፋራዎች እንዳትገቡብን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby HD » Thu Aug 05, 2010 7:47 pm

አቦ ገልብጤ ምናለ ማዙካህ እንዳንተ አይነቱን 10 በወለደች ኖሮ, አመጣሽው ኔሙን አይደል, ይመችሽ የአራዳ ልጅ,እኔማ ስሙ ጠፍቶብኝ በንዴት ጨጓራዬ ሁላ ሊነሳ ነበር :lol:, ምናለሽ ተራ ነው አንድ እግር ካልሲ በስሙኒ ሲሸጥ ያየሁት, ለካ አንቺም ሞክረሻታል? እኔማ አልገዛሁም, ያን ያክል ክራይስስ ውስጥ አልገባሁም ነበር :lol: :lol: ምናለሽ ተራ የሌለ ነገር ቢኖር ''ምንም'' ብቻ ነው :lol: ያለህ ነገር ሁሉ ሄደህ ልትሸጠው ትችላለህ, አሮጌ ማንኪያ, ሹካ, ጠርሙስ, የጠርሙስ ክዳን ለብቻው,የለስላሳ ጠርሙስ የተሸረፈ, የለስላሳ ጠርሙስ ያልተሸረፈ, ነጠላጫማ አንድ እግር, ባለ ሁለት እግር, ባለ ሶስት እግርም አለ :lol: :lol: እነ ጦምኔክስ የስሙኒ ጉርሻ ሳይሆን አይቀርም እንደዚህ ያደለባቸው ይህውልሽ, እንቁላል ያለው ከሆነ ደሞ 30 ሳንቲም ነው አሉ, ስጋና እንቁላል ሁለቱም ኖሮት ሀይለኛ ቡሌ ከሆነና ሰውዬው ደሞ አካፋ የሚያክል እጅ ካለው 50 ሳንቲም ሁላ ይገባል አሉ :lol: :lol: አንዳንዴ ባለ ሀምሳ ሳንቲሙ አንድ ጉንጭ ኮካ ኮላ ሊመረቅበትም ይችላል, ሀፒ ሚል እንደ ማለት ነው :lol:, አንዳንድ ጊዜ ባለ ቡሌው ሰውዬ አውቆ እጁ ላይ ትንሽ ካስቀረ , ደንበኞቹ ደሞ ''ከፍዬ አይደለ እንዴ? እያንዳንዷን ቡሌ ከእጅህ ላይ መጠራረግ አለብኝ'' ብለው የሚበጣበጡ ነፍ ናቸው, :lol: እጅህን ካልላስኩ ብሎ የሚቀውጥም አይጠፋም :lol: አይ ቲንክ እንደነሱ አይነቶቹ ናቸው እዚህ አበሻ ሬስቱራንት ከች ብለው በጥባጭ የሚወጣቸው, ሸዋዬዎችኮ መርኬን የሚያውቋት ዋና ዋና እቃ መሸመቻዋን, እንደ ጣና ገበያ, የልብስ ቡቲኮች, የምግብ ምናምን መሸጫዎችን ነው እንጂ , ውስጧን የምናቃት እኛ የአራዳ ልጆች ነን, :lol: በርበሬ በረንዳ ሄዶ የሚያውቅስ አለ? አንድ እንጀራ በ75 ሳንቲም ገዝታቹ ወደ በርበሬ በረንዳ ከች ካላቹ የመጬ ነው ጠግባቹ የምትመለሱት, እዛ አካባቢ ያለው ግራውንዱ ሁላ በርበሬ ብቻ ነው, መኪኖቹ በርበሬ ለብሰዋል, ወንበሮቹ, የተሰጡት ልብሶች, ስልኮች, ማዳበሪያዎች በጠቅላላ በርበሬ የታጠኑ ስለሆኑ እንጀራዋን ካገኛቹት ነገር ጋር እያስነካቹ ማግበስበስ ነው, :lol: መኪና ባጠገባቹ ሲያልፍ እንጀራቹን ልታጠቅሱ ትችላላቹ, ዛፓ ሲያልፍ ኮፍያውን ማስነካት ትችላላቹ ከዛ እሷን በሀይለኛው ትነፉና ቤት ሄዳቹ ውሀ መጠጣት ነው::
ይመቻቹ, ቡሀላ አካባቢ ከች ይባልለታል :wink: ፒስ
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby ገልብጤ » Thu Aug 05, 2010 8:07 pm

ቅቅቅቅ..HD...ምን አለሽ ተራ ምን የሌለው ነገር አለ ብለሽ ነው..የተጣፈ ፓንት እንኳን ነፍ ነው..2 አይነት ካልሲ ገዝተሽ መዘነጥ ነው እንጂ..የፓንቱማ ነገር አይነሳ እሙሙ መሽፎኛው ቦታ ላይ ያንሶላ ቅዳጅ ተጥፎባት የሆሊውድ አክታሮች የፈረሙባት ነው የሚመስለው..ስለ ቡሌው ደግሞ ደንበኛ ከሆንሽ ላሪፍ ጉርሻ 50 ሳንቲም ከከፈልሽ ኮካ ኮላ በቆርኪ በነጻ ይመረቅልሻል ..

እስኪ ጊዜ ሲኖረኝ ብቅ እላለሁ ...ወደ ጥግራራ ለሽብለል
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ሮዚ... » Thu Aug 05, 2010 10:28 pm

:lol: :lol: :lol: በሳቅ ገደላችሁኝ ነው የሚባለው ጭውቲአቹ አሪፍ ነው እስቲ ቀጥሉበት
ሮዚ...
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 44
Joined: Wed Dec 16, 2009 11:19 am

Postby adegenga_bozene » Thu Aug 05, 2010 11:05 pm

You guys are cracking me up :lol: :lol: :lol:
I'm not good at writing in Amharic..Sorry

U name all these places but how could you forget yesebategna shelewoch? The once who cook nice misir wat and make gabi while havig s e x.
adegenga bozene
adegenga_bozene
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 13
Joined: Mon Nov 01, 2004 7:53 am
Location: ethiopia

Postby ጦምኔው » Fri Aug 06, 2010 4:15 am

adegenga_bozene wrote: yesebategna shelewoch? The once who cook nice misir wat and make gabi while havig s e x.
:lol: :lol: :lol:

አቦ አነፈርከኝ ከምር.......የነሱማ ነገር አይነሳ ነው

እኔ ከሰባተኛ ሰፈር የማልረሳው ስኔፉን ነው :lol: የማይታጠን ነግር የለም.......ቀበርቾ....ጠጅ ሳር: ጡንጅት: ወይራ..በቃ የማይሸት ነገር የለም.....ግራዋ ደሞ የመጨረሻ ነው የሚጠቀሙት.... :lol: አንዳንዴ ከፈረደብህ በዛ በኩል ስታልፍ የእሙሙ እጣቢ ሁላ ሊደፋብህ ይችላል...ሎል.....መቻል ነው.......ተሳስተህ እንኳን እሳደባለሁ ብትል ለዕድሜ ልም የሚሆንህን ስድብ ነው አሸክመው የሚልኩህ...... :lol: ሀሀ....ምናምን የሚገባበት አፍ መች ዝም ይላል ብለህ ነው :lol:

አቦ ይልቅ አንዴ ያጋጠመኝን ልቅደዳቹ.....ከምር ድሮ የመጬ ኔፓ ነበርን....... መኛጢ ስልህ.....እና ማዘር አንድ ቀን የጥቁር ጤፍ ቂጣ ጋግራ ለኔና ለፈላው ብራዘር ትገጨናለች...እኛልሽ የጭቁን ፒሳችንን ቺርስ እያልን እያጋጨን ወደ ተላክንበር ስንሸበለልልሽ የሆኑ ሁለት ጎዳናዎች አየንልሽ.....እና እኔና ብሮ በጣም አሳዘኑን እና ያንን ቂጣ ስንገጫቸው ምን እንዳደረጉት ታውቂያለሽ?..... ሁለቱም አሸተቱት እና መኪና ስር ወረወሩት :lol: ..ዚ ፈኒ ፓርት ኢዝ...የዛን ቀን ነው እኔና ብሮ ሊታዘንልን የሚገባው እኛ እንደሆንን የገባል :lol: :lol: ....ሲሪየስሊ ግን አይ ላቭ ማይ ሴንስ ኦፍ ሂዩመር ከምር.........ለካ ጀለሶች የጳውሎስ ሆቴልን ቡሌ ሲያጣድፉ የምውሉ ወደሎች ነበሩ :lol: ..ምናልባት የጉርሻ ተጠቃሚም ሊሆኑ ይችላል :lol:

የቄራ ልጆች ኡፋቹ ቁርጥ ነው አሉ :lol: ለነገሩ የማትበሉት የበሬ አካል ድምጹን ብቻ ነው አይደል :lol: ሀሀ.....ግን ከምር በጣም የሚገርመኝ አብዛኛው የቄራ ልጅ ሌዘር ልባብ አያጣም ...ቅቅ....እነ HD ቤት እንደውም ድሮ አያትየው የሸመቱት አንድ ሌዘር ነበር......ከፋዘር ወደ መጀመሪያው ልጃቸው እያለ እያለ ሲወርድ ሲዋረድ የመጨረሻው ልጅ HD ላይ ሲደርስ የሰፈሩ ልጆች "ይሄ ለዘር ሳይሆን ለዘር ነው አላሉትም :lol:


እስኪ ደሞ አስለቅሸው ከች እላለሁ..ጠይቆኛል :lol:
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby sarandem » Fri Aug 06, 2010 4:47 am

ጦምኔው wrote: ሀሀ.....ግን ከምር በጣም የሚገርመኝ አብዛኛው የቄራ ልጅ ሌዘር ልባብ አያጣም ...ቅቅ....እነ HD ቤት እንደውም ድሮ አያትየው የሸመቱት አንድ ሌዘር ነበር......ከፋዘር ወደ መጀመሪያው ልጃቸው እያለ እያለ ሲወርድ ሲዋረድ የመጨረሻው ልጅ HD ላይ ሲደርስ የሰፈሩ ልጆች "ይሄ ሌዘር ሳይሆን ለዘር ነው አላሉትም :lol:


:lol: :lol: :lol:
አልተቻላቹም :: የሌዘሩ ነገር እውነት ከሆነ በሬውም ላይ እንዲህ አልቆየም:: መስመር ላይ የሆነ ልጅ አስታወስከኝ:: የቦብ ማርሌ እየሳቀ ጣቱን አግጩ ላይ ያለበትን ቲሸርት ሁሌ ያደርጋል:: ቲሸርቱን ሳይቀይረው ለረጅም ወቅት ከመቆየቱ የተነሳ ሳቂታው ቦብ ፊቱን አጨማዶ አፍንጫውን እነደያዘው ማለት ነው:: ጦሜ x እኔ እንኩን ሳቅሽ የኪራይ ሰብሳቢ ባለሀብት ልጅ እንደሆንሽ ነው::ኤኒዌይ...ኤኒ ሁ ይመቻቹ ::
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby Monica**** » Fri Aug 06, 2010 8:58 am

HD, ጦምኔክስና ሌሎችም አራዶች እንዴት ከረማችሁ?
ቤቱ በጣም አራዳ አራዳ ይሽታል :lol: :lol: :lol: :lol:
HD የቄራ ልጆች ከምር ደስ ይሉኛል.....እንዳትስቅብኝ እንጂ ሁሌ ቄራ ሲባል ፎቶ ሀይሉ የሚባል ፎቶ ቤትጋ የሚቆሙት ጎረምሶች ናችው.....ለከፋችው ደስ ይል ነበር :lol: :lol: :lol: አቤት ትዝታ ገነት ሆቴል ምናምን ስትል ሀይለኛ ትዝታ ውስጥ ከተትከኝ.....ዩ ሲ የመጀመሪያ ቦይፍሬንዴ ከገነት ሆቴል ዝቅ ብለህ ወደከርቸሌ ጠምዘዝ ስትል ነበር እና ከሚክሲኮ ጀምረህ ገነት ሆቴል, ፖፕላሬ ኦል ዘ ዌይ ቱ ቄራ ብዙ ቱዝታዎች አሉኝ!!! አንድ ቀን አጫውታችሁ ይሆናል
HD ዩሲ አንተና ጦምኔው ገልብጤ አማርኛችሁ ፕሮፐር አራዳ ነው....አይ ገስ እንደዛ አይነት አማርኛ እንደገና ካልተፈጠርኩኝ መናገር አልችልም በጣም ነው የሚያስጠላብኝ......አቦ ዛሬ ዶክኮኛል ....ልጠግረር ምናምን ብል ከመልኬ ጋር በፍጹም አይሄድም :oops: :oops:በስድብ አትውስዱብኝና ልክ አፐር ክላስ ኢንግሊሾች እንደወርኪንግ ክላስ ሲያወሩ ማለት ነው :oops: :oops: :oops: ግን እንድት እንደምታስቀኑኝ ስታወሩ ልነግራችሁ አልችልም.....የትም ተወለድ መርካቶ እደግ ወይም ቄራ እደግ ልበል? እንዴት ቦሌ ተወልደሽ ኦልዴርፖርት አድገሽ አራዳነት አትችይም እንዳትለኝ....ከምር እኔ ትምህርት ቤትም እያለሁ ሆነ ሰፈራችን ውስጥ እንደዛ እሚያወራ ስው የለም ለምስክርነት እወዳለሁን ጠይቁት ጎረቤቶች ነበርን ሩዋንዳ.....እና ይቅርታ እንደዛ ስለማላወራ አራዳነቴን አያስቀማኝም አይደል? :lol:
HD በኖርማል አማርኛ ማውራት ከተፈቀደለኝ ልቀጥል? :lol: :lol: :lol: :lol:
ጦምንዬ የለዘሯ ነገር ፍርፍር እስክል ነው የሳቅኩት የሱ ሲገርመኝ ስራንደም ደሞ የቦብ ማርሊን ጨመረለኝ!! :lol: :lol: :lol: :lol:
Yየአራዳ ልጆች በሉ ይመቻችሁ
ሞኒካ ነኝ ከስጢፋኖስ ሜዳ
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ቢጥቅ » Fri Aug 06, 2010 10:24 am

ወይ እናንተ ሰዎች በጣም ታስቃላችሁ ከምር....በጣም የሚመች ክፍል ነው 8) የኔ ሰፈሬ ቦሌ ጃፓን ኤንባሲ አካባቢ ነው:: ሰፈራችን በጣም ጭር ያለ ነው ሁሉም ቤቱ ዝግ ነው :wink:

ለማነኛውም አራዳዎች ጨዋታችሁ በጣምምምምምምምምምምም ደስ ይላል 8) 8)

ቢጥቆ
ቢጥቅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 470
Joined: Sat Sep 12, 2009 3:54 pm

Postby ሀሚሮዝ » Sun Aug 08, 2010 10:15 pm

ኪየፍ ተብሉዋል በሀይለኝኣው የ አራዳ ልጆች ..ሰላም ነው አይደል.. ምነው መርኪየክስን እና ቂየራን ስትዳስሱ ጨርቆስን ላሽ አላችሁት ... በውነት በጥአም ነው የከፋኝ ...ምክንያቱም ስንት አራዳ ያፈራ ነው ሰፈሩ
አንድ ጊዝየ ትዝ የሚለኝ እዛ ሰፈር የሆነ የክፍሊየክስ ልጅ ነጋድየ ቢጥየ ነገር ነው መሰለኝ ከባንክ ሳቢ ይዞ ሲወጥአ ከርቀት ሁለት የራዳ ልጆች ከልመውት ኑረው ትንሽ ራመድ ራመድ እንዳለ ይጋጩት እና ሳቢውን ይረካከቡታል ..ልጁም ምንም የሚያርፈው ጉዳይ የለም አገር አማን ብሎ ብየቱን ይነካዋል .. እብየቱ እንደደረሰ ሳቢዉን ቸክ ሲያደርግ የለም... ከዛም ሲሮጥ ልጆቹ እተጋጩበት ቦታ ከባንክ ብየቱ እምብዛም አይርቅም እና ተመልሶ ማፈላለግ ይጅምራል ...የሚያደርገዉን ምንም አያውቅም ..ይጮሀል ...ይለፈልፋል ..ብቻዉን ከዛም አካባቢዉን ቅውጥ ያደርገው ጅመር ..ፒፕሉም በሁንየታው በጥአም ተግርሞ ከበው ያዩት ጀመር ..ከዛ ለተሰበሰበው ሰው ጮክ ብሎ ሼዋ ደስ ይበልህ .ጎጃም አሩን በላልህ እንዳለ እቦታው የነበረ በሙ በሳቅ ድክም ያሉት
ፒስ
ሀሚሮዝ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Wed Mar 17, 2010 9:06 pm
Location: Milano

Postby ከረዝ » Mon Aug 09, 2010 12:43 am

ጫወታችሁ ይመቻል እኔም ትኔም ሀሳቤን አስባስቤ ምጣሁ
ከረዝ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Mon Aug 09, 2010 12:21 am

Postby sarandem » Tue Aug 10, 2010 10:36 am

ውይ ሞኒክ ለካ የዲታ ልጅ ነሽ ? እኛ ይህንን ሳናቅ ብዙ በጣም ተዳፍረናል:: በከባዱ ይቅርታ ጠይቀናል:: ይገርምሻል እኛ ከሰፈር ...ከጎረቤት የሽሮ ክክ እየዘገንን ሰፈር ያሰለቸን ነበርን:: ሳስበው እነ ጦምኔው... ውቃው ደጉ ዋናው...ከንደዚህ አይነት ስራ ከደመ ንጹህ አይመስሉኝም::
ሀመሮዝ እንደከተበው
ምነው መርኪየክስን እና ቂየራን ስትዳስሱ ጨርቆስን ላሽ አላችሁት ... በውነት በጥአም ነው የከፋኝ ...ምክንያቱም ስንት አራዳ ያፈራ ነው ሰፈሩ

እንዴ ዘ ሰፈረ ጨርቆስ ነሽ እንዴ? ጨርቆስማ እንዴት ይረሳል::
እነ ዘነበ ወላን ያፈራች ጨርቆስ...እንዴት ትረሳለች::
አንቺ ግን ወሬያም ቢጤ ትመስያለሽ:: ራስ ብሩ ሜዳ አጠቐቁረሻል ማለት ነው::

መንገዱ ከመጥበቡ የተነሳ ሰርግ ሲጨፈር ሀይሎጋ ሳይሆን ሰለሜ ሰለሜ ከሚባልለት ሰፈር ነሽ ለካ ፍሬንድ::
ፍሬንድ ጨርቆስ ሰፈር ስታልፍ ማድረግ የሌለብህ ነገሮች ተብለው የተነገሩን እጠቅሳለሁ :wink: መጥተሽ አስተባብይ::
:arrow: ህጻን ልጄ አዳልጦት ከወደቀ ወይኔ ልጄ :!: ካልክ ...አባቱ ተገኘ ተብሎ ባንተ ስለሚላከክብህ የወደቀ ልጅ ስታይ እንዳላየ ዝም ብለህ እንደ ዮሀንስ አራምዴ በስሎው ሞሽን ነው መራመድ ያለብህ::
:arrow: ውይ ይህ ህጻን ያምራል :!: ብትል ጋሼ በስፔሻል ኦርደር በፍጥነት እናደርሳለን የሚሉ ብዙ ቺኮች እንደማታጣ በጎተራ ሙሉ ገብሴ እና በሰጋር በቅሎዬ እወራረዳለሁ :wink:
:arrow: ባለ መኪናም ከሆንክ መኪናህ ላይ ልጆት ጢሎ ቢሉም ክላስክ ማድረግ ያልሰሙትን ኑ ጢሎ በሉ ብሎ መጥራት ስለሚሆን ሙዩት አርገህ መንዳት ነው ያለብህ::

የጨርቆስ ልጆች :twisted: ስቴዲዮም አካባቢ እንዳንደርስ ስለምትቀውጡት ብንናደድባቹም እንወዳቹሀለን:: 8)
እናንተ ደግሞ ጋዴ ገርግዳቹ ክትክት ያለበት
ሙቪ ለመከለም አዲስ ከቴ ..ሲኒማ ራስ ታጠቜቁሩ ነበር:: ሀሚሮዝ መቼም እኛ እንደ እናንተ አንጨክንም በፋራው ዘመን የህንድ ፊልም ለማየት ቼላ...ዲናሬ ወይም ከርክ ሞልተንልሽ ይሆናል...ማን ያውቃል?
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby Monica**** » Tue Aug 10, 2010 10:57 am

ውይ ስራንደም በሳቅ አንፈራፈርከኝ ዛሬ :lol: :lol:
የዲታ ልጅ? አይ ዶንት ኖ ዘ ዴፍኒሽን ኦፍ ዲታ........ግን አይ ሀድ አ ሞደስት አፕብሪንጊንግ በኛ አገር ስታንዳርድ ማለቴ ነው..........እዚህ ስትመጣ ከወርኪንግ ክላስ ፖፕሌሽኑ ጋር እንቁጠርሽ ሲሉ .....እኔ እህትህ የኢትዮጵያ ሜንታሊቲ ስላለኝ እረ ሚድል ቱ አፐር ክላስ ነኝ ብዬ አንድ ስሞን ተጨቃጨኩት አሁን አዎ ወርኪንግ ክላስ ነኝ ብዬ አክሴፕት አድርጌ እኖራለሁ በልቤ ሁሌም ሚድል ክላስ ብሆንም :lol: :lol: አይ ገስ ጥሩ ቶፒክ ላይሆን ይችላልና ይቅር ጉረኛ ምናምን ያስመስላል ድንገት በኢንፊሪየርቲ ኮምሌክስ ሰፈር የሚያደርጉ ስዎች ካሉ ኢቪን ዞ ኢት ኢዝ አ ሀርሽ ሪያሊቲ!!!
ወደጨዋታው ልመለስና ሽሮማ ሳይዘግን ያደገ ልጅ ያለ አይመስለኝም :lol:
ስረግ ላይ ለምንድነው ሰለሜ የሚዘፈነው በሀይሎጋ ፋንታ? :lol: :lol: እግዚአብሄርን ጨርቆስ ሁሌ ለምን እንደመጥፎ ይነሳል ግን ስንትና ስንት አሪፍ ልጆች ያሉበት ሰፈር ነው እኮ !!! :lol: :lol:
ከሁሉም ግን አፌ ጆሮዬጋ እስኪደርስ ድረስ ያሳቀኝ የታችኛው ነው !!!ኡፍፍፍፍፍፍፍ ስራንደም ነፍስህ አይማርም ተንኮለኛ የሆንክ ልጅ :lol: :lol: :lol: ይልቅ እኔ የምፈራው የለገሀር አካባቢ ልጆችን ነው ለምን እንደሆነ ግን እኔንጃ እንደው ተደባዳቢ ነገሮች ይመስሉኛል ከዛ አንስተው እስቴዲየምን አካባቢ ኮንትሮል ያደርጉት ነበር!!!
ስራንደም አይ ላቭ ዩ ማን ዩ ሜድ ማይ ዴይ!!!!
sarandem wrote:


:arrow: ህጻን ልጄ አዳልጦት ከወደቀ ወይኔ ልጄ :!: ካልክ ...አባቱ ተገኘ ተብሎ ባንተ ስለሚላከክብህ የወደቀ ልጅ ስታይ እንዳላየ ዝም ብለህ እንደ ዮሀንስ አራምዴ በስሎው ሞሽን ነው መራመድ ያለብህ::
:arrow: ውይ ይህ ህጻን ያምራል :!: ብትል ጋሼ በስፔሻል ኦርደር በፍጥነት እናደርሳለን የሚሉ ብዙ ቺኮች እንደማታጣ በጎተራ ሙሉ ገብሴ እና በሰጋር በቅሎዬ እወራረዳለሁ :wink:
:arrow: ባለ መኪናም ከሆንክ መኪናህ ላይ ልጆት ጢሎ ቢሉም ክላስክ ማድረግ ያልሰሙትን ኑ ጢሎ በሉ ብሎ መጥራት ስለሚሆን ሙዩት አርገህ መንዳት ነው ያለብህ::

የጨርቆስ ልጆች :twisted: ስቴዲዮም አካባቢ እንዳንደርስ ስለምትቀውጡት ብንናደድባቹም እንወዳቹሀለን:: 8)
እናንተ ደግሞ ሙቪ ለማየት ጋዴ ገርግዳቹ ክትክት ያለበት
ሙቪ ለመከለም አዲስ ከቴ ..ሲኒማ ራስ ታጠቜሩ ነበር:: ሀሚሮዝ መቼም እኛ አንጨክንም በፋራው ዘመን የህንድ ፊልም ለማየት ቼላ...ዲናሬ ወይም ከርክ ሞልተንልሽ ይሆናል...ማን ያውቃል?
[/color]
Yesterday is history, tomorrow is mystery, but today is a gift and that is why they call it the present!!!
Monica****
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3195
Joined: Fri Dec 26, 2003 10:24 pm
Location: 999 Total eclipse st. Venus

Postby ጦምኔው » Tue Aug 10, 2010 2:17 pm

አማን ተኩም አራዶች.......ሳራንደም የሰፈር ልጅ...አይ አንቺ አመጣጣሽው እኮ...ይመችሽ

ሀመሮዝ......የዛፉ ዘንበል ሀገር ልጅ ነሻ :lol: ሰላምከ አባ

የጨርቆሶች ነገርማ አይነሳ......ሲኒማ አዲስ ከተማማ በ 35 ቁጥር አንበሳ መርኬት ከች ይሉልሽና በኤክ ትሪስ የሕንድ ፊልም:: :lol: አስቢው እስኪ በሕንድ ፊልም ርዝመት ሶስቱን በአብድ ቀን መከለም......ዳያስ ሁሉ በሰሀን አስቋጥረው ነው ሲኒማ የሚገቡት ስልሽ :lol:

ሲሊሜ :lol: :lol: :lol:

የጨርቆስ ሰፈር ቤቶች በጣም የተደጋገፉ ከመሆናቸው የተነሳ ለአንዱ ቤት ማገር ማቆሚያ የተመታ ሚስማር ኔክስት ዶር ትሪ ይሰቀልበታል :lol:

እናልሽ ቤቶቹ አንዱ በአንዱ ላይ ተደግፎ ተደግፎ ነው የቆመው እና መጨረሻ ላይ ያሉስ ሰዎች ቤት ነው ጋለል ብሎ በእንጨት ተደግፎ የሚቆመው ( እንደ ፒቲ ጎል ማለት ነው ) :lol: ..እና የዛ ቤት ሰዎች በጣም ነው የሚከበሩት በሰፈር ውስጥ አልኩሽ.......ኤጵ ብለው እንጨቱን ካነሱት የአንድ ቀበሌ ሕዝብ ቤት መፍረሱ አይቀርማ :lol:

የፖፑሌሽኑ ብዛትማ አይነሳ.....ሴንሰስ ሁሉ የራሳቸው አላቸው :lol:

ሀሀ የተሰጣ ሽሮ እየዘገንን :lol: :lol: ...ሳራንደምማ ጥራጥሬ በጣም ከመውደዱ የተነሳ ለዶሮ የተበተነ እንክርዳድ ሁሉ ከዶሮ ጋር እየተሻማ ነበር የሚቆረጥመው :lol: .... አንተ ለነገሩ የተሰጣ ነገር ሁሉ አትምርም ነበር......በፋሲካ ሰሞን እኛ ሰፈር ጉልባን እንደጉድ ነበር ከተሰጣበት የሚጠፋው...... Now I know How :lol:

ና ውረድብን ደሞ :lol:

ፒስ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ያገር ተስፋ » Tue Aug 10, 2010 3:54 pm

ኬፍ ብለናል የአራዳ ልጆች
አቦ ጨዋታችሁ ይመቻል!
ሞንካ የቄራ ልጆች የምትወጂ ከሆነ ትመችኛለሽ ማለት ነው.......ለነገሩ እኔ ሰፈሬ ማሞ ካቻ አካባቢ ነበር ወደ በግ ተራ አካባቢ ግን ብዬ ውሎዬ ቄራ ነበር! ፎቶ ሀይሉ ስትይ በቃ ቦታው ታየኝና ይሄኔ እኔ አንቺም ልንተዋወቅም እንችል ይሆናል አልኩ :lol: :lol: :lol:
አቦ የአዱ ገነት ትዝታ ማለቂያ የለውም! ሳራንዳምና ጦምኔው ክፉኛ ጭውቴያችሁ ሙድ አለው!
ጨርቆስ እኮ ዘመናዊው እሪ በከንቱ ነው ይባላል! ....ጨርቆስ ገብተህ በስላም ከወጣህ እውነትም ጨርቆስ ትወድሀለች ማለት ነው:: :lol: :lol: እነሱ ደሞ ሙድ አያዙብህ በቃ አለቀልህ ማለት ነው!
ያገር ተስፋ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 45
Joined: Wed Apr 27, 2005 11:22 am
Location: ethiopia

Postby HD » Tue Aug 10, 2010 8:39 pm

አምበሳ ጋላቢዎች , የአራዳ ልጆች ኬፍ ነው ? ሞኒካ አንቺ የማጄላን ልጅ ነበርሽ አንዴ ? :lol: :lol: ቦሌ ሩዋንዳ , ሳርቤት , ጨርቆስ , :lol: :lol: ጨርቆስ እኮ በቄራ ልጆች ቁጥጥር ስር ነበረች አታውቁም እንዴ ? የሳሪስ ፍንዴክሶች በላንቻ በኩል አርገው ሲመጡባቹ እኛ አልነበርን እንዴ በሞተር ሳይክልና በአስራ አንድ ቁጥር ከች ብለን የምንከሻከሽላቹ ? ሳራንደም ያልከው መንገድ አሁን ተሰርቶ ጠራ ያለ መንገድ እንደወጣው ሰምቻለው , እድሜ ለዛ እሳት አደጋ ገበያው በእሳት ድራሹ ባይጠፋ ኖሮ ዘላለማቹን ሴሌሜ እያላቹ ነበር የምትኖሩት :lol: ጦምኔክስ ሰላም ነው ? በኤክ ትሪስ የህንድ ፊልም ለማየት እኛም እኮ ወደ መርኬክስ ከች እንል ነበር , :lol: ቺኮቻችንን በ 35 ቁጥር ፈርስት ክላስ (ወንበር ላይ ) አሳፍረን በቼላ ፓስቲ በሻይ አሽረን የህንድ ክንቴ ፊልም አሳይተን ሀይለኛ ሮማንቲክ ዴይ አሳልፈን እንመለስ ነበር , :lol: :lol: አንዳንድ ጀለሶቻችንማ ምናለሽ ተራ ወስደው ሀይለኛ ቡሌ በስሙኒ አስጠልፈው ይመልሷታል , አንዳንዴ ሳናውቀው የክኔክስ ስሜት ከፊልሙ እንወርስና ከአዲስ ከተማ ልጆች ጋር ክንቻ እንገባና ዛባዎች ከች ብለው አንድ ሁለት ጥፊና ቦክስ አቅምሰውን ዴታችንን አድቬንቸረስ የሚያረጉበት ቀንም አለ , :lol: እናታቸውን ልቀፍላቸውና ,
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 9 guests