እንኳን በድጋሚ በሰላም መጡ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Feb 18, 2012 1:33 am

ይበቃኛል

ዛሬ

እየፈረሰ ነው እየተናደ

ነገም ሆነ

የማልደርስበት ተስፋ የጨለመ

አልፈልግም ልለውጠው

ላጠፋው ልበርዘው

ትናንት

ነውና የእኔ

ልጅነቴ

ይበቃኛል

ያጠራቀምኩት ትዝታዬ

ለተረፈው እድሜዬ

ይበቃኛል


አምሀ አስፋው
ሜይ 22, 1995 እ.ኤ.አ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Tue Mar 27, 2012 11:31 am

ማዲንጎ አፈወርቅ

"ኧረ ሰው አለቀ ሰው አለቀ በሏት
እሷ ለታመመ ለሞተም ግድ የላት..........

ትቻት ረስቻት ሆኜ እንደነገሬ
በምን አስታውሻት ሲያመኝ ዋለ ዛሬ......."

ባቲ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Apr 06, 2012 11:35 am

ታላቁ ሙሉቀን መለሰ

ምነው ከረፈደ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Apr 06, 2012 11:46 am

ታላቁ ኤፍሬም ታምሩ

"....የአንቺ ይችላል ወይ እባክሽ አንጀትሽ
የኔ አልችልም ብሏል ሲያጣሽ በናፍቆትሽ...."

አንቺ ልጅ አደራ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Apr 06, 2012 12:31 pm

ክቡር ተሾመ አሰግድ

"ደሜን ባልቋደስ....የኔ አይናማ.....ከወንድም ከህትሽ...የኔ አይናማ
ከአንጀቴም በማዘል....የኔ አይናማ...ባልሆን እንደናትሽ....የኔ አይናማ
ከኔም ሆድ በፍቅር.....ተቀምጠሻል...እንደቀልድ እንደቀልድ..."

የኔ አካል
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby የመረረው. » Fri Apr 06, 2012 11:37 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ታላቁ ሙሉቀን መለሰ

ምነው ከረፈደ


ሙሉቀን መለሰ ትግሬ ነው እንዴ??
----------Oooo---
-----------(----)---
------------)--/----
------------(_/-
----oooO----
----(---)----
-----\--(--
------\_)-
የመረረው.
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 98
Joined: Mon Mar 05, 2012 7:37 pm
Location: USA

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Apr 28, 2012 8:20 am

ህብስት ጥሩነህ

መምጣቴ አይቀርም
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Thu May 03, 2012 8:23 am

አኒ ዲፍራንኮ

OR ELSE WE'RE COMING UP
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby recho » Fri May 04, 2012 7:55 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ክቡር ተሾመ አሰግድ

"ደሜን ባልቋደስ....የኔ አይናማ.....ከወንድም ከህትሽ...የኔ አይናማ
ከአንጀቴም በማዘል....የኔ አይናማ...ባልሆን እንደናትሽ....የኔ አይናማ
ከኔም ሆድ በፍቅር.....ተቀምጠሻል...እንደቀልድ እንደቀልድ..."

የኔ አካል
ወያኔው ጉዋዴ... ለዚህ ዘፈን ያለኝ ፍቅር ቃላት አይገልጸውም .. ጆሲ ጎሳየ የዘፈነውን አይተህዋል ? ከልቡ ዘፋኝ መሆኑን ጎረምሳው አስመስክሮበታል .. በዛላይ በጨዋነት የሰው ዘፈን መዝፈኑን ክሊፑ ላይ ገልጾ አመስግኖታልም ... ከዛ የሙሉቀንን ዘፈን ከዘፈነው ሌባው ልጅ ይሻላል መቸም ..
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri May 04, 2012 11:08 pm

ሠላም recho...ኢ-ወያኔዋ ጉዋዴ :D

ወያኔው ጉዋዴ ... ለዚህ ዘፈን ያለኝ ፍቅር ቃላት አይገልጸውም .. ጆሲ ጎሳየ የዘፈነውን አይተህዋል ? ከልቡ ዘፋኝ መሆኑን ጎረምሳው አስመስክሮበታል


እኔም በጣም የሚስማማኝ ዘፈን ነው.....የጆሲ ቨርዥንም ጥሩ ነው......ልጁ ጥሩ ድምፅ አለው

በዛላይ በጨዋነት የሰው ዘፈን መዝፈኑን ክሊፑ ላይ ገልጾ አመስግኖታልም ... ከዛ የሙሉቀንን ዘፈን ከዘፈነው ሌባው ልጅ ይሻላል መቸም ..


ጨዋነቱ ግን አልገባኝም :wink: ክሊፑ ላይ የተሾመን ዘፈን መዝፈኑን መግለፅ አለመግለፁ ምን ለውጥ እንደሚያመጣ አይታየኝም.....ዘፈኑ የራሱ እንዳልሆነ ሰው ሁሉ ያውቃልና.....ክሊፑ ላይ ከማመስገን በፊት አስቀድሞ የዘፈኑን ባለቤት ማስፈቀድ ይገባ ነበር...ስለዚህ የሙሉቀንንም የዘፈነውም ሆነ ጆሲ ሁለቱም "ሌቦች" ናቸው :D.....ባይሆን እንደጀማሪ ዘፋኝነታቸው የድምፃቸውን አሪፍነት ለማስመስከር የተጠቀሙት አቋራጭ መንገድ ስለሆነ እንለፋቸው በሚለው እንስማማ


recho wrote:
ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ክቡር ተሾመ አሰግድ

"ደሜን ባልቋደስ....የኔ አይናማ.....ከወንድም ከህትሽ...የኔ አይናማ
ከአንጀቴም በማዘል....የኔ አይናማ...ባልሆን እንደናትሽ....የኔ አይናማ
ከኔም ሆድ በፍቅር.....ተቀምጠሻል...እንደቀልድ እንደቀልድ..."

የኔ አካል
ወያኔው ጉዋዴ... ለዚህ ዘፈን ያለኝ ፍቅር ቃላት አይገልጸውም .. ጆሲ ጎሳየ የዘፈነውን አይተህዋል ? ከልቡ ዘፋኝ መሆኑን ጎረምሳው አስመስክሮበታል .. በዛላይ በጨዋነት የሰው ዘፈን መዝፈኑን ክሊፑ ላይ ገልጾ አመስግኖታልም ... ከዛ የሙሉቀንን ዘፈን ከዘፈነው ሌባው ልጅ ይሻላል መቸም ..
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat May 05, 2012 11:51 am

የጠፈር ምርኮኛ

ግማሽ ቀልድ አላውቅም

ሞት እንዲሁ ልሙት በሰኮንድ መቶኛ

እንቅልፍ እንደሬሳ ዘላለም ልተኛ

መንገድ ስጡኝ ሰፊ . . .

ልጉዋዝ ከድፍን አፅናፍ

ልፍጠን እንደብርሀን አለማትን ልለፍ

ፀሃይ ልሁን ፀሃይ

እንደፅርሃ ኣርያም ሁሉንም የሚያሳይ

እሳተ ገሞራ ኣመዱ ረመጡን

ጎርፍ የሳት ጎርፍ ልሁን

ከሲኦል ሚሊየን ሚለየን ነበልባል

መንገድ ስጡኝ ሰፊ . . .

ልሂድ በጨለማ አይን ከማያይበት

ጥቁር ከከሰለው ከጠቆረው ፅልመት

በፀጥታው ቦታ ዘመን ከቆመበት

በዘላለማዊው ባዶ ቦታ ዋሻ

አየር በሌለበት አድማስ መጨረሻ

ልንሳፈፍ ልቃኘው . . .

ለኔ ኮከብ ጠጠር ኩዋስ መጫወቻ ነው

የመሬት ቁራጭ ነኝ ታሪክዋን የምጽፍ

በጥቁር ወረቀት በሰማይ ብራና

ስጉዋዝ እየተሞላሁ በጠፈር ላይ ፋና

ስሄድ እኖራለሁ

ሰማየ ሰማያት እመዘብራለሁ

የተዘጋውን በር እበረግዳለሁ

የሌለ እስቲፈጠር; ዝምታ እስኪነቃ

በትልቅ እርምጃ ከመሬት ጨረቃ

ከጨረቃ ኮከብ; ካንዱ አለም ወዳንዱ

ስጉዋዝ እፈጥራለሁ

በፀሀይ ላይ ጎጆ-ቤቴን እቀልሳለሁ

ከሲኦል ሚሊዮን ቢሊዮን ልቃጠል

ከገሀነም እሳት ሚሊዮን ነበልባል

መንገድ ስጡኝ ሰፊ . . .እጅግ ታላቁ ገብረክርስቶስ ደስታ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat May 12, 2012 12:32 pm

አበስ....ገበርኩ...እቴ

ከአንጀትሽ ላይወጣ.....ከሆድሽ ታምቆ

ልብሽና ልቤ.....አድባር አውጋሩ አውቆ

ነጋሪት ጎስመን.....ክተት አስነግረን

ጦር;ሰይፍ;ጎራዴ.....ዝናር አስደርድረን

እዩን!... እዩን!... ብለን

ላንቆስል ተታኩሰን.....ላንጣጣል ታግለን

እንዲያ ተጯጩኸን.....ፎክረን አቅራርተን

ከፍቅር አውድማ ላይ.....ተገኘን ተጣብቀን

ኤዲያ.....ባክሽ ይብቃን

ደከመን.....ታከተን

ተኩስ ይቁም.....ይስከን

ቆርጦ ላይቆርጥልን.....ችለን ላንሰለች

አንቺን ብሎ ተኳሽ.....ደሞ እኔን ብሎ ሟችአባይ ፍቅሩ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Jun 01, 2012 7:34 am

ጂል ስካት

".......and a freak 'cause that's what I like and I like being what I like and what I like is all a part of what I am"

NOTHING IS FOR NOTHING
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sun Jun 03, 2012 9:44 am

ታላቁ አለማየሁ እሸቴ

ሀይሎጋ ሀይሎጋ ሽቦ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Thu Jun 14, 2012 12:02 pm

በዓለም ላይ ያሉ 4 እውነታዎች

1. በምላስህ ጥርሶችህን በሙሉ በአንድ ጊዜ መንካት አትችልም

2. የመጀመሪያውን እውነታ ካነበቡ በኻላ ጅሎች ጥርሳቸውን በሙሉ ለመንካት ጥረት ያደርጋሉ

3. አሁን እየሳቅክ ነው.....ምክንያቱም አንተም ከጅሎቹ አንዱ ሆነሀል

4. ይህንን ፅሁፍ ለጓደኞችህ ለመንገር እያሰብክ ነው.....ምክንያቱም ብቸኛው ጅል መሆን አትፈልግምና :lol:

ምንጭ.....ጫልቱ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests