by recho » Thu Jun 06, 2013 12:17 am
ኦ ጋይስ ለምኑ ነው ግን ኮንግራው? ላይፌን ፊገር አውት ስላረኩ ? ፍቅር ከሁሉ እንደሚበልጥ ስለደረስኩበት? ለምኑ? ለሁሉም ቢሆን አመሰግናለሁ ..
ሓዩ አይጦ ሰላም ነው? ከምርን አላሳቀኝም, አላዝናናኝም, አላስደነቀኝም, ወይንም አልገባኝም :lol: የሆኑ ሰዎች ሲደንሱ አየሁ :lol: ሚስ ያረኩት ምኑን ነው
ከተሰጠኝ ነገር ሁሉ አምላኬን ስለ ፍሪ ዊል አመሰነዋለሁ ... በነጻነት ልንኖር በነጻነት የፈልግነውን ሆነን ልንኖር እግዜር ፈጥሮናል .. በራሳችን ሂወት ላይ የመሰለንን ውሳኔ ልንወስን .. መሆን የምንፈልገውን ነገር በነጻነት እንድንሆን ተፈጥረናል ..የሂወታችን ኢንጂነሮች ራሳችን እንጂ የጉዋደኛ ወይንም የቤተሰብ አካላት ወይንም እንደው የምንወደው ወይ የምናደንቀው ሰው የሂወት ተሞክሮ አይደለም .. የአራሴን ጥፋቶች አጠፋለሁ .. የራሴን ውድቀቶች እወድቅና ከራሴ ውድቀት እማራለሁ .. የሚጠቅም ከመሰለኝ ደግሞ ከጉዋደኛዬ ውድቀት እማራለሁ .. ያንን ለማድረግ ግን ሂወቴን የምመራበት ትልቁ መመሪያዬ የራሴው ጭንቅላት እንጂ የሌሎች ጋጋታና ጫጫታ አይደለም .. አዎ አሁንም ቢሆን I am the master of my soul.! አለቀ! የሂወት ውሳኔያችን ላይ ጣልቃ ሲገቡ, ሲወስኑ ሲዋሰኑ, ሲመክሩና ሲያማክሩ የምናገኛቸው ሰዎች መጀመሪያ የራሳቸው ሂወት ስኬት ሲታይ ወደማጥ እያዥቆለቆለ, ፍሬን እንደሌለው መኪና አቅጣቻቸውን ስተው ቁልቁለቱን በፍጥነት ሲወርዱ ሲታዩ .. ፍጥነታቸው ከማሸነፍ ጋር ተምታቶባቸው አውቀው ሳያውቁ ... ይሄ ነው ህመሜ .. አዎ አሁንም .. I am the captain of my fate,! አይዞን .. ከምር አይዞን .. ሁላችን ሂወታችንን እናስኬድበት ዘንድ አንድ አይነት ተደርጎ እንመራበት ዘንድ የተጻፈልን መጸሀፍ የለም .. የራሳቸውን ሂወት መመሪያ ነው ቅዱስ መጸሀፍ አርገው የሚያነበንቡልን .. የራሳችንን ሂወት በራሳችን አቅጣቻ .. በተሰጠን እድልና በተጻፈልን አካሄድ እንሂድበት .. አንድ ማስተር ማይንድ አይምራን .. አሁንም ቢሆን I am the captain of my fate, I am the master of my soul.! በዚህም እኮራበታለሁ! ኦ ልክ ነው .. ሞኝ ወድቆ .. ብልጥ ግን ከሰው ውድቀት ይማራል የተባለው .. ትክክል ነው .. ሲወድቁ ሳይ እንዳልወድቅ እጠነቀቃለሁ .. ሁሉን አላውቅም .. ከነሱ ሂወት እማራለሁ .. እነሱን ከጣላቸው ጉርጉዋድ እንዳልገባ ጠርዜን እይዛለሁ .. ግን ግን .. በፍጹም .. እንደው በፍጹም የሂወቴን መሪ ከራሴ ሌላ ለሌላ ሰው አላስጨብጥም .. እንደው ምን ሲደረግ ... I am the master of my soul.! ኦ የግጥሙ ይዘት ከላይ ከተቀበጣጠረው ጋር ሊያያዝም .. ላይያያዝም ይችላል ... የገባው ልብ ይበል ..
Out of the night that covers me,
Black as the pit from pole to pole,
I thank whatever God may be,
For my unconquerable soul.
In the fell clutch of circumstance,
I have not cried nor winced aloud,
Under the bludgeoning of chance,
My head is bloody but unbowed.
Beyond this place of wrath and tears
Looms but the horror of the shade,
And yet the menace of the years
Finds and shall find me unafraid.
It matters not how straight the gate,
How charged with punishments the scroll,
I am the captain of my fate,
I am the master of my soul.
William Earnest Henley, 1875
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1