........መደበሪያ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby recho » Tue Aug 14, 2012 3:47 am

-...- wrote:recho ሩሜትሽ እንደዛ ስታማርጥ ምነው አንቺ በሶ ጨብጠች ነበር የምትኖሪው ? እንደሷው ማማረጥ ነበረብሽ :: If you can't beat them join them. አመለጠሽ ስንት የኑሮ ተሞክሮ :: አሁን ያ ወልጋዳ በትዳር ጠፍሮሽ ቁጭ አልሻት :: ቀናሁበት ያላማረጠች አግኝቶ ::
:lol: :lol: :lol: የመረጥኩትን አጊኝቼ ነበር ገጦ .. ለዛ ነው .. አንዳንዴ እኮ አትሩጥ አንጋጥ ነው .. በሮጠ በመረጠ መሰለህ ? :P
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ገልብጤ » Tue Aug 14, 2012 4:39 pm

-...- wrote:recho ሩሜትሽ እንደዛ ስታማርጥ ምነው አንቺ በሶ ጨብጠች ነበር የምትኖሪው ? እንደሷው ማማረጥ ነበረብሽ :: If you can't beat them join them. አመለጠሽ ስንት የኑሮ ተሞክሮ :: አሁን ያ ወልጋዳ በትዳር ጠፍሮሽ ቁጭ አልሻት :: ቀናሁበት ያላማረጠች አግኝቶ ::


ኧረ አንተ ሰውዬ ተው እንጂ ሪቾ...እኔን ኮ ዌይቲንግ ሊስት ውስጥ አስቀምጣኛለች .....እና ምንድነው የምትለው ከሷ የፈለከውስ ምንድን ነው..ኧረ በፈጣጤ አይሆንም
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ጦምኔው » Tue Aug 14, 2012 8:38 pm

ሪች @ ጂሰስ :D :D :D

አቦ ጨማምሪበት! ሩም ሜትሽ ሙድ አላት ከምር! She sounds like fun! Can I have her digits?? :D
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby recho » Tue Aug 14, 2012 9:05 pm

ጦምኔው wrote:ሪች @ ጂሰስ :D :D :D

አቦ ጨማምሪበት! ሩም ሜትሽ ሙድ አላት ከምር! She sounds like fun! Can I have her digits?? :D


አይይይ ጦምን ከሪቾ የተጠጋ ምን ጤና አለው ብለህ ነው .. ሺ ኢዝ ሀፒሊ ሜሪድ :lol: :lol: :lol:


ሺ ኢዝ .. ኤቭሪ ናው ኤንድ ዜን አንድ የምትሰራው ነገር አታጣም... ሶ ፋይናሊ ዊ ጋት ኢን ቱ አግሪመንት ሶስት ወር ዴት ላታደርግ እና ፊገር አውት ልታረግ ላይፍዋን በሪቾ ገገማዋ መካሪነት እና ተሳካልኝና ተወች .. አንዱን ሳምንት ዲፕረስድ ሆነች .. ሁለተኛውን ተረጋጋች ... ከምርዋ ዴዲኬትድ ሆና ላይፍዋን ማስተካከል ጀመረች... ከምር አም ሶ ፕራውድ ኦፍ ህር ... እና ሶስቱ ወር አለፈ .. አሁን ከባር ሳይሆን ከስራ ቦታዋ ላይ (የቀድሞ አለቃዋን :lol: ) ዴት ማድረግ ጀመረች .. ወዲያው አብረው አልሰከሩም .. ወዲያው ልብስ አልወለቀም ረጋ ቀዝቀዝ ያለ ሪሌሽንሺፕ .. ታዲያ ስፕሪንግ ላይ ሮድ ትሪፕ ታሰበና ሁለቱ አብረው ሄዱ .. አንድ ነገር ያየሁት ሺ ወዝ ሶ ሶ ሶ ኤክሳይትድ .. ግን ይሄንን ታደርጋለች ብዬ አልጠበኩም .. አኮርዲንግ ቱ አዲሱ ቦይፍሬንድ ሻወር ወስዶ ሲወጣ .. በሩን ሲከፍተው ተሽቀንጥራ ወደውጥ ወደቀች .. ፈጽሞ እርቃንዋን ነበረች እና ግማሽ አካልዋ መሬት ግማሹ ስቲል ሀንጊንግ በበሩና በመሬቱ መሀል አንንገትዋ ተቆልምሞ ማለት ነው .. አይ ቲንክ ወደጎን ነው የወቀችው .. በጭንቅላትዋ ቆማ እያለ :lol: :lol: :lol: በጣም ደንግጦ አር ዩ ኦኬ? ዋት ዌር ዩ ዱዊንግ? :lol: :lol: ከወደቀችበት መሬት ቁጭ ብላ አይንዋን ቁልጭ እያረገች .. ሶ ሶሪ .. አይ ወዝ ሶ ኤክሳይትድ ... አይ ዶንት ኖው ውሀት ቱ ዱ .. ዚስ ኢዝ ማይ ፈርስት ታይም ዛት አይ ስቴይድ ፎር 3 መንዝ ዊዝ አውት ዴቲንግ .. :lol: :lol: :lol: ትምርት ነው ለኔ .. ይቺን ልጅ እግዜሩ ጠብቆኝ እንጂ .. 6ወር እንድትቆይ ብመክራት ኖሮ ጸጸቱ መቼም አይወጣልኝ ነበራ :lol: :lol: ማን ያቃል በመስኮት ትዘል ይሆናል .. አይ ላቭ ያ ቼስ .. አይ ዊሽ አማርኛ ማንበብ ብትችል ኖሮ :lol: :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ጦምኔው » Tue Aug 14, 2012 11:54 pm

:lol: ተገለባባጯን ነዋ የዳራቹለት :lol: ፑር ሀዝባንድ !

ይመቻት በራሁባት!

አንዱ ጀለሴ የነገረኝ ስለ ሩም ሜቱ:: ሁሌ ጠዋት ከስራ አድሮ ሲመጣ ፍሪጅ ውስጥ ያስቀመጠውን ማካሮኒ አያገኘውም ሩም ሜቱ በልቶበት እየሄደ :lol: በጣም ተማርሮ ነው የነገረኝ:: ያም ብቻ ሳይሆን ምንም ዓይነት ቡሌ ሰርቶ ማግኘት የለም:: በዛ ላይ ሸኖ ቤታቸው በጣም ይደብራል:: ቁጥር ሁለትን ለማድረግ ሁሉ ስትገቢ ሶፍት ከቤትሽ (ከሩምሽ) ይዘሽ ነው የምትሄጂው:: ሸር ማድረግ የለም:: ሳሙና ሁሉ ቤድ ሩም ነው የሚቀመጠው :lol:

ይጨማመራል እስኪ ብሶቱ.....እየጠጣቹ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby እንሰት » Wed Aug 15, 2012 2:42 am

ሀ ሀ አሪፍ ጨዋታ ጀምራችሁዋል:: የኔዎቹ ጋር ድራማ የለም::

ከድንቅ ያገኘሁትን ግን ላካፍላችሁ

የደባል ሩም ሜትስ ኑሮ
አብሮ መኖር መተሳሰብን ይጠይቃል። ብዙ ዓይነት ጸባይና ልምድ ያለን ሰዎች ከሌላ ሰው ጋር ስንኖር
ከጸባያችንም ሆነ ከልምዳችን መቀነስ ሊኖርብን፣ በተቻለ መጠንም ተግባብተንና ተሳስበን አንዱ የራሱን ጥቅም ብቻ ሳይመለከት ልንኖር ግድ ይለናል። ከሥራ ስንወጣ ናፍቆን የምንመጣበት ፣ በሰላም
አረፍ የምንልበት ቤት ሊኖርን ያስፈልጋል፡ ለዚያ ደግሞ የአንድ ሰው ሳይሆን የሁለት ሰው ጥረት ግድ ይላል።

ብ ዙዎቻችን እዚህ አሜሪካ አሁን የምንኖረው ዓይነት የደባል ኑሮ በአገራችን አልኖርንም። አገር ቤት
የምናውቀው ተከራይ አንድ ግቢ ከመሆኑ በቀር ራሱን ችሎ ሰርቪስ ቤት ወይም ትንሽ የተሰራች ቤት ተከራይቶ የሚኖር ነው።

እዚህ አገር ከመጣን በኋላ ግን በአንድ ጣሪያ ፣ ከመኝታ ቤት በስተቀር ሁሉን ነገር በጋራ እየተጠቀሙ መኖርን ጀምረናል። ይህ ሲሆን ታ ዲ ያ ከ ለ ተ ያ የ የአገ ራ ች ን ክ ፍ ል እንደመምጣታችን መጠን፣ አስተሳሰባችንም፣ አመለካከታችንም፣ የአኗኗር ዘይቤያችንም የተለያየ እንደመሆኑ መጠን አብረን ስንኖር
የሚገርሙ በርካታ ነገሮች ያጋጥሙናል።

በውጭ የሚመስለን እና በውስጥ ያሉበትና የሚኖሩበት የሚናገሩት ብዙ ልዩነት አለው። ራሳችንን እንደመስታወት እንድንመለከትና እንማማር ዘንድ ይህ ጽሁፍ ቀርቧል። በዚህ ታሪክ የቀረቡት ታሪኮች እውነተኛ ሲሆኑ የባለታሪኮቹ እና የቦታ (የአፓርትመንት) ስሞች ግን ተቀይረዋል። መልካም ንባብ።
*************
ዮናስ እዚህ አትላንታ በቻታው መንታው አፓርትመንት ላለፉት ሁለት ዓመታት ኖሯል። አፓርትመንቱ ለሃይዌይ 85 የቀረበ በመሆኑና ስለተመቸው የመውጣት ሃሳብ የለውም ፣ አንዱ ሩም ሜት ሲወጣ፣ ሌላ እያስገባ በመኖር ላይ ይገኛል። ከስድስት ወር በፊት አብሮት ይኖር የነበረው ደባሉ የተለየ ጸባይ እንደነበረው ዮናስ ይናገራል። “አንዲት ፍቅረኛ አለችኝ እና አልፎ አልፎ ቤቴ ትመጣለች፣ ሁለት ዓመት ያህል አብረን ቆይተናል። አንድ ቀን እቤት መጥታ በኔ ላፕቶፕ Iሜይሏን ማየት ፈልጋ ከፈተችው።

ስትከፍተው ያጋጠማት ነገር ያልጠበኩት ነበር። የወሲብ ዌብ ሳይት ተከፍቶ፣ ርቃናቸው ስክሪኑ ላይ አፈጠጠባት። ለሁለት ሳምንት ያህል ዘግታኝ በመከራ ነበር የተግባባነው፡ እሷ፣ ቤት ቁጭ ብዬ የፖርን ፊልም ሳይ የምውል ነበር የመስላት፣ ነገሩ ግን ሩም ሜቴ፣ ልጠቀምበት እያለ ፣ ለካ ክፍሉን ዘግቶ እሱን ሲያይ ነው የሚውለው፣ የሚገርመው የራሱ ላፕቶፕ አለው፣ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ለምን በኔ ላፕቶም መጠቀም እንደፈለገ የሚገርም ነው። ከዚያ ወዲያ አንድ ወር ስጥቼ አስወጣሁት” ብሏል።
**************
ብዙዎች ስለ ደባሎቻቸው የሚያቀርቡት አቤቱታ “የራሳቸውን ጥቅም ያስቀድማሉ (አድቫንቴጅ
ይወስዳሉ) የሚል ነው፡ በዚሁ አፓርትመንት የምትኖረው ማርታ ከነዚህ ውስጥ አንዷ ነች። እሷ
እንደምትለው ከአንዲት ጓደኛዋ ጋር የአንድ ዓመት ሊዝ ፈርመው አብረው ተከራዩ። “የሚገርመው ነገር
ጓደኝነታችን አንድ ላይ ስለምንሰራ በመሆኑ ጥሩ ልጅ እንደሆነች ነው የማወቀው፣ ለካ ከውጭ ማወቅ
እና አብሮ መኖር የተለያዩ ናቸው .. ይህችው ጓደኛዬ ፣ የመጀመሪያ ቀን እዚያ ቤት ስንገባ፣ አብረን ክሮገር ሄደን ፍሪጁ የሚችለውን ያህል ምግብ ገዛን። ከዚያ ወዲህ አሁን ስድስት ወር ሆነን፣ እሷ የምግብ መግዛትና ማብሰል ነገርን ትታዋለች። መቼም ቤቱ ባዶ ሲሆን ዝም አልል አያልኩ የምግብ ነገር የምገዛው እኔ ፣ የምሰራው እኔ ። በግል ጸባይዋ ጥሩ ልጅ ናት፣ ግን ቤት ውስጥ ሥራ በመከፋፈልና ምግብን በተመለከተ ጉዳይ ዜሮ ነች። ውጭ ግን ሁሉም የሚያወቀው የምንዋደድ ጓደኛሞች መሆናችንን ነው .. አሁን ሊዛችን ባለቀና በወጣሁ እያልኩ ነው” ስትል ብሶቷን ትናገራለች።
*************
ሩም ሜቶች አብረው ሲኖሩ፣ አስቀድመው ድርሻቸውን በግልጽ ሊነጋገሩ እንደሚገባ አማካሪዎች ይናገራሉ። መተሳሰብ አስፈላጊ ነው። በተለይ በምግብ ማብሰል ጉዳይ የተወሰኑት ብቻ ሲጎዱ ይታያል። ምግብ ማብሰል የማይችል፣ ቢያንስ ግሮሰሪ መግዛት ይኖርበታል። አሜሪካ አገር ምግብ ርካሽ ነው፣ በዚያ ግምት ውስጥ መግባት አያስፈልግም። ተራ ገብቶ አንድ ሳምንት አንዱ፣ ሌላውን ሳምንት ሌላው ምግብ መስራት ወይም አንድ ላይ እየተጫወቱ ተጋግዞ መስራት ያስፈልጋል። በኛ ባህል አብሮ መብላት የተለመደ በመሆኑ የግድ መተሳስብ ይኖርብናል። ከዚያ ሲያልፍ ግን ነገሩ አስከፊ ይሆናል። ሰለሞን አደረግኩ ያለው ያንን መሆን የሌለበትን ነገር ነበር።
“የምኖረው ስፕሪንግ ቼዝ አፓርትመንት ነው። እዚያ እያለሁ፣ ሩም ሜቴ የትም ዞሮ መጥቶ ያገኘውን መብላት እንጂ፣ ተሳስቶ እንኳን ስቶቭ ለኩሶ አያውቅም፣ በኋላ ግን ምርር ሲለኝ፣ የራሴን ፍሪጅ ገዛሁና መኝታ ቤት ውስጥ አደረኩት፣ አሁን እየሰራሁ የማስቀምጠው መኝታ ቤቴ ነው፣ ውሃም እንኳን ገዝቼ አልጋዬ ሥር ነው የማስቀምጠው፣ በሬን ስለምቆልፍ ትንሽ አርፌያለሁ፣ ሊዛችን ሊያልቅ ሶስት ወር ነው የቀረው፣ እስከዚያው እንዲሁ እቆያለሁ” ነው ያለው።
*****************
ፍቃዱ እና ሚሚ በፍቅረኝነት ሶስት ዓመት ከቆዩ በኋላ ለመጋባት በማሰብ ቤት ገዙ፣ ቤት የገዙት በሁለቱም ስም ነው። ነገር ግን ለጋብቻ ሳይበቁ ተጣሉ። ሁለቱም ቤቱ ውስጥ ስማቸው አለና፣ ትቶ መውጣቱን ወዲያው መወሰን አልቻሉም፣ ከቤቱ ሶስት መኝታ ቤት ውስጥ አንዳንድ ተከፋፍለው እንደ ሩም ሜት መኖር ጀመሩ፡ ሚሚ ስትናገር “ሁለት ሥራ ስለምሰራ ብዙም አላገኘውም፣ በውጭ ግን መጣላታችንን ብዙም ሰው አያውቅም፣ ቤቱ ዋጋ ካወጣ መሸጥ እንዳለብን ብነግረውም ገና አልተስማማንም፣ ነገር ግን የቀድሞ ፍቅረኞች ያሁን ደባሎች ሆነን መኖር ጀመርን፡፡ የሚገርመው እኔን ለማስቀናት እያለ የማያመጣቸው የዚህ አገር ሴቶች የሉም፣ እነሱ ከፍላቸው ሲጯጯሁ እኔ ቤት ከሆንኩ ሙዚቃዬን በጣም ከፍቼ አጮኸዋለሁ .. በዚህ ሁኔታ እስከመቼ እንደምኖር ባላውቅም፣ አጅግ አስቸጋሪ ህይወት ውስጥ ነኝ .. በክሬዲቴ ፈርጄ
ትቼው የምወጣ ግን ይመስለኛል .. እንጃ!” ስትል በሃዘን ተናግራለች።
**************
ፍቅረኛን ቤት ማምጣት ብዙዎች ሩም ሜቶችን የማያግባባ ነገር ነው። ሁሉም የሚኖረው የራሱን ህይወት ቢሆንም አብረው እስካሉ ድረስ መግባባት እንደሚያስፈልግ ደግሞ ይታወቃል። ሌክ ሾር አፓርትመንት የምትኖረው ሙሉ ወርቅ ስለዚህ ጉዳይ በራሷ ያጋጠማትን እንዲህ ስትል ትናገራለች “እኔ የማወቀው ወንድ ፍቅረኛውን ቤቱ ሲወስድ እንጂ፣ ሴቷ ወንዱን ቤቷ ድረስ ስታመጣ አይደለም፣ - ምናልባት ተሳስቼ ይሆናል - የኔ ሩም ሜት ደግሞ ፍቅረኛዋን ማምጣቷ ሳያንስ ፣ የሚሆኑት ነገር ሁሉ እኔ በቤቱ የሌለሁ ዓይነት ነው፣ መታ ቤታቸው የሚያደርጉት ነገር ሁሉ እኔ ክፍል በደንብ ይሰማል፣ ሰአት አይመርጡም፣ በዚያ ሁኔታ እኔ መኖር ስላልቻልኩ፣ በገባሁ በሁለተኛው ወር ትቼ ወጣሁ” ነው ያለችው።
*************
ለብቻ መኖርና አብሮ መኖር የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ቤታችን የምናርፍበት ቦታ በመሆኑ ለሌላው ማስብ ተገቢ ነው። ገረመው ያጋጠመው ሩም ሜት ግን ከዚህ ለየት ይላል። “ካሬጅ Oክስ የሚባል አፓርትመንት
ውስጥ እየኖርኩ ሳለ፣ ከሥራ ደክሞኝ ስመጣ፣ የሚያጋጥመኝ የሰው መዓት ነው፣ ሩሜቴ ባጋጣሚ ባለብዙ ጓደኞች ነው፣ ነገር ግን ያ ማለት 24 ሰአት ቢራ እየጠጡ ቤቱን ቀውጢ ሲያደርጉ መዋል ተገቢ አይደለም፣ ያ ሁሉ ጎረምሳ ሳሎኑን ሞልቶ እየተንጫጫ ክፍሌ ገብቼ ማረፍም ሆነ ኪችን ሆኜ ምግቤን መስራት አልቻልኩም፣ አንዳንድ ጊዜ እሺ ፣ ግን ቤታችን በየቀኑ የጎረምሶች መናኸሪያ መሆን ያለበት አይመስለኝም፣ በዚህ ሁኔታ አብረን መኖር ስላልቻልን፣ ያስገባሁት እኔ ነኝና አስወጣሁት፣ አሁን ውጭ ስሜን ማጥፋት ትልቅ ሥራው አድርጎታል” ሲል የደረሰበትን ይናገራል።
***************
የአላምረው ደግሞ ለየት ይላል .. “የኔ ሩም ሜት የሚገርም ነው፣ ካልሲውን ሲንክ ውስጥ ያጥባል፣ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ ስለው ቲቪ ለማየት እንዲመቸኝ ነው፣ ይላል . . አጥቦ የሚያሰጣው የምንቀመጥበት ወንበር ላይ ነው፣ ክፍሉ - አልጋው ሳይቀር በወረቀቶችና በማይረቡ እቃዎች የሞላ ነው፣ ጽዳት የሚባል ነገር አያውቅም፣ የበላበትን ሰሃን ወዲያው ቀርቶ በሳምንትም ዝም ካሉት አያጥብም። ቤት ውስጥ ከሚመጡ እንግዶች ጋር በግድ ፖሊቲካ ካላወራ አይሆንለትም፣ ቶሎ ብሎ የማን ደጋፊ ናችሁ? ማለት ይቀናዋል። እኔ ጋ የሚመጡ ሰዎች ዘና ብለው ከኔ ጋር መጫወት አይችሉም፣ እቤት ካለ በሁሉም ነገር ጣልቃ እየገባ፣ ነገሩን ሁሉ ወደ ፖሊቲካ እየወሰደ ረፍት ይነሳናል። ሁለታችንም ሊዝ ፈርመናልና የሚቀጥሉትን አራት ወራት
መቀጠል አለብኝ -ምርጫ የለኝም፣ ከዚህ በኋላ ግን ብችል ለብቻዬ ብኖር እመርጣለሁ” ሲል የራሱን አጋጣሚ ይናገራል፡
******************
“ምንም ሱስ የለብኝም ብላ አስገባኋት ..” የምትለው ደግሞ ትርሃስ ነች፡ ትርሃስ ጂሚ ካርተር አካባቢ የገዛቸውን ቤት ክፍያ እንዲረዳት ሩም ሜት አስገባች። ታዲያ ሱስ የለብኝም ያለችው ሴት ፣ ለካ ሺሻን እንደ ሱስ አልቆጠረችውም ፣ ትርሃስ ትቀጥላለች .. “ አንድ ቀን ከሥራ ስመጣ ቤታችን በጭስ ተሞልቶ የቃልቻ ቤት መስሏል፣ እሷም በስስ ቀሚስ ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ ሺሻዋን ትለዋለች፣ እኔ ደግሞ የሺሻም ሆነ የሲጋራ ጭስ አለርጂክ ነኝ፣ ምንም ሳትነግረኝ፣ ለዚያውም ሳሎን እንዲህ ማድረጓ አበሳጨኝ፣ ዛሬ እንዲህ ያደረገች ነገ የምታመጣው አይታወቅም ብዬ አስወጣኋት .. “ ብላለች።

ከላይ በተጠቀሱት ችግሮች ውስጥ መፍትሄውንም እንዳያችሁ ተስፋ እናደርጋለን። የተሰማችሁን ጻፉልን።
ከድንቅ መጽሄት።
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እህምም » Wed Aug 15, 2012 10:13 pm

:lol: ሬች you have the best stories. እረ ጨምሪ...
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby ጦምኔው » Tue Aug 21, 2012 10:16 pm

PM Meles Zenawi may your soul rest in peace. There are so many things that has been done during your terms (21 years that is). Among them were milestone ones like keeping AU headquarter in Addis and starting the "Hidase Gideb". There also are bad things like the 2005 election, human right violation and refusing freedom of speech and press. However, you are gone now and I don't think you have ever had a peacefull moment in your earthly life. You had been in struggle for 17 years and then leading your party and the country for 21 years. It sound very harsh for me. I do respect you as a gentle man and as an intelectual. I do admire your strength in staying to fullfill your goal standing still for so long unlike many of our opposition leaders. I do wish your kids to get strength since you are a father because I cannot imagine how i feel if I lose my dad. R.I.P.
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ጦምኔው » Sat Aug 25, 2012 1:33 am

ከኛ ሰፈር ተነስተው ወደ ፒያሳ ዎክ ላድርግ ቢሉ አንድ መጽሀፍ ሊወጣው የሚችል የሰዎች ታሪክ ያያሉ:: ለምሳሌ ልክ ከኛ ቤት ወጥተው ፊትዎትን በር ላይ እየታጠቡ አባባ ሽመልስን ይከልሟቸዋል ቀይ የሹራብ ኮፍያቸውን ደፍተው: የብርጭቆ ቂጥ የመሰለ: አንዱ እጀታ የተሰበረ እና በገመድ ከጆሯቸው ጋር ጥፍር ተደርጎ የታሰረ መነጥራቸውን አድርገው ውዳሴ ማርያማቸውን ከዓይናቸው የአንዲት ጣት ያል አርቀው ለማንበብ ሲታገሉ ያያሉ:: በየመሀሉ በር ላይ ተቀምጦ ጸሀይ የሚሞቀውን ትልቁን ልጃቸውን ሽብሩን በከዘራቸው ቀወር እያደረጉ "ኪሪያላይሶን በል" ሲሉት ያደምጣሉ::

ከሳቸው ቤት አጠገብ ወይዘሮ አበሩ ትላንትና የዘፈዘፏትን አንዲት የነተበች ነጠላቸውን እንዳትቀደድባቸው "እሹሩሩ" እያሉ ያሿታል:: አስተሻሸታቸው መሳቀቃቸውን ያሳያል:: አስር ጊዜ ወደ ጋሽ ሽሜ ታላቅ ልጅ እያዩ "ሆ! " ይላሉ እርስዎአን እያዩ "እኚህ ሰውዬ ጤናም የላቸው እንዴ?" በሚል አስተያየት::

በአንድ ጆግ ውሀ ፊትዎትን ታጥበው ግማሹን የኛን ጊቢ ታሪክ በኍላ አያለሁ ብለው ወደ እኛ ቤት ገብተው ልብስዎትን ለባብሰው ሲወጡ ጥለውት የገቡት እንቅስቃሴ እንዳለ ሆኖ ሌሎች ተጨማሪ ክስተቶች ተጨማምረው ያገኛሉ:: (የኛን ጊቢ ታሪክ እመለስበታለሁ)

ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby recho » Sat Aug 25, 2012 1:35 am

የያዝከኝ ጉንፋን የመለስን ቀን ይስጥህ ... እየዞርኩ እየተራገምኩ ነው ሶሪ ጦምን ቢለቀኝ ፈርቶ :cry:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ጦምኔው » Sat Aug 25, 2012 1:45 am

recho wrote:የያዝከኝ ጉንፋን የመለስን ቀን ይስጥህ ... እየዞርኩ እየተራገምኩ ነው ሶሪ ጦምን ቢለቀኝ ፈርቶ :cry:


ይስጥህ!!! (ግራ እጅ ወደላይ) :!:

BTW ጀግና አይሞትም!! የተባለው ፉከራ ለጉንፋንሽም ይሰራል ማለት ነው?? ይቅርታ ግራ ግብቲንግ ብሎኝ ነው :lol:
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ዉቃው » Sun Aug 26, 2012 6:17 pm

ፕሬዚደንቱ እና ወይዘሪት ሊዊንስኪ ተከታትለው ወደ ፕሬዚደንቱ የግል ማጥኛ ክፍል ገቡ :: ወዲያ ከንፈር ለከንፈር ይሞጫሞጩ ጀመር :: የጃኬቷን ቁልፎች በቀስታ ፈታቻቸው : ቀጥላም የጡት መያዣዎች አላቀቀች :: ፕሬዚደንቱም ጡቶቿን በእጆቹ ከፍ አርጎ እንደልቡ ይሞጨሙጫቸው ጀመር ::

እንደ ወይዘሪት ሊዊንስኪ ገለጻ ከሆነ " ዛሬ ውበቴ ላይ ብቻ አትኩሮ ያወራ ጀመር :: ጡቶቼን ብቻ ሳይሆን እሙሙዬንም በጆቹ ይነካካብኝ ጀመር ::" የሆነ ጊዜ ላይ ፕሬዚደንቱ ሲጋሩን በወይዘሪት ሊዊንስኪ እሙሙ ከተተውና ከዛ አውጥቶ ወደ አፉ በመክተት " በጣም ይጣፍጣል " አላት ::

At one point, the President inserted a cigar into Ms. Lewinsky's vagina, then put the cigar in his mouth and said: "It tastes good."

ውርስ ትርጉም ከስታር ሪፖርት
ለመጀመሪያ ጊዜ በአባ ዉቃው
ከዋሽንግተን ዲሲ
በአጭር የተቀጨው ረጅሙ ጉዟችን !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1038
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ዉቃው » Sun Aug 26, 2012 6:23 pm

ማሳታወሻ -:- ከላይ ያለው ሐተታ የተጻፈው ስለ ፕሬዚደንት መ /አ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሳይሆን ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ነው ::

አመሰግናለሁ
በአጭር የተቀጨው ረጅሙ ጉዟችን !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1038
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby sarandem » Sat Sep 01, 2012 7:48 am

ሰላም ብለናል ለዚህ ቤት ታዳሚዎች:: ዘጌ..ጌች.. ደጉ ..ሙዝ..ሪች.. ጛድ ውቃው..ሌሎችም
ወይ ጦምን ስንት ጉድሽን አነበብኩት:: እነዛ ፍሬንዶች ያ ሁሉ እንቁላል መሬት ላይ አስቀምጠው ያቀረቡልሽ ልትታቀፊው ነው :?: :lol:
sarandem
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 674
Joined: Tue Jul 11, 2006 8:59 am
Location: Nomad Cafe

Postby recho » Sat Sep 01, 2012 4:53 pm

sarandem wrote:ሰላም ብለናል ለዚህ ቤት ታዳሚዎች:: ዘጌ..ጌች.. ደጉ ..ሙዝ..ሪች.. ጛድ ውቃው..ሌሎችም
ወይ ጦምን ስንት ጉድሽን አነበብኩት:: እነዛ ፍሬንዶች ያ ሁሉ እንቁላል መሬት ላይ አስቀምጠው ያቀረቡልሽ ልትታቀፊው ነው :?: :lol:
ወየው ሳራንደም መጣ :lol: በማሪያም በገመድ ከዋርካው ጋር እሰሩልኝ ... እኔ ስለማልችለው ነው .. ምነው አንተ ይሄንን ያክል ... ነውርም አይደል እንዴ? ቢያንስ ቢያንስ ለቅሶ እንኩዋን አትደርስም ? በሀዘን እንዴት እንጨካከናለን አንተ ? :)
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests