........መደበሪያ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ጦምኔው » Tue Aug 07, 2012 2:25 am

ከሀገር ቤት የመጣ ቡሌ ተጠልፎለት የጀበና ቡና በሉባንጃ ጢስ እየታጠንን ተቀምቅሞለት በምቾት እና በምርቃና የተጻፈ:: :D ኤዲት እያደረጉ እንዲያነቡ ይጠየቃሉ::

አይ ቅምቀማ.....ባለፈው ሀገር ቤት ለቫኬሽን ተመርሾለት የአዱገነት አሪፎች (ታናናሽ ብራዘሮችንም ጨምሮ) አይ አሳሳባቸው.....አይ አመጣጠጥ:: የማይጠጡት ነገር ጥይት ብቻ ነው እኮ:: እኔ ትዝ ይለኛል ለመጀመሪያ ጊዜ ቅምቀማ የተጀመረለት ኮልፌ ሀይ ስኩል ሶቶ ከተባለ በኍላ ነው:: ትምሮ ቤታችን አጥር አልነበረውም:: ዙሪያው በር ነው ስልህ:: እና ልክ ጫካውን አልፈህ ስትወጣ ቦዛ ቤቶች አሉ:: እዛ ነው የመጀመሪያውን ቦዛ የቀመከምነው:: እና ከትምሮ እየተፎረፈ አንዳንዴም ለላይብረሪ ብሬክ ይሳብለት ነበር:: ቦዛ ይጠጣለታል ሽልጦ AKA CD በሚጥሚጣ ይጎረስለታል:: በ ዱ ቂቅ ብለህ በእግር ከልኳንዳ እስከ ሰፈር (ኳስ ሜዳ ማዞሪያ) በቸርኬ ያለ ድካም ይገባለታል::

ጠንከር ያለ ቅምቀማ የተጀመረለት ኮሌጅ ነው:: ሳቢውም ከች ሲል በቃ ድራፍት ተጀመረለት:: ከዛ ቢራ (ያው ለዓመት በዓል ወይም ዕቁብ ሲደርሰን) አፎርድ ስናደርገው ቅንዳንዴ ይቸለስበታል:: በዛ ዘመን ቺኮቹን ራሱ ግሪን ሀውስ ወይም አንዱ ካፕል ሀውስ ይዘሀቸው ስትሸበለል ካንተው እኩል ድራፍታቸውን ቀምቅመው እኩን ፏ ብለው ሳቅ በሳቅ ሆነው አንተንም ሀፒ ገጭተውህ "ያሰብኩት ተሳካ...." እየዘፈንክ ወደ ቤት:: አንዳንዶቹ ጸዳ አሉ የሚባሉትም ግፋ ቢል ትንሿን ጉደር በኮካ ምጥጥ አድርገው የብላክ ሌብል ያህል ጡዘው ይመቹካል::

አሁን ልክ ከአሙካ ሄጄለት ከብራዘሮች ካር ስወጣለት አባቱ ይህንን የቅምቀማ ስም እንደ ዘር ማንዘራቸው እስከ ሰባት ቤት ድረስ ይጠሩልሀል:: እኔን ብዙ ያውቃል ብለው ሲጠብቁኝ እኔ ፍሬንዳቹ ፍጥጥ:: ኧረ ፍጥነት:: የመጬ ግርሞ:: ቺኮቹማ በቃ አይቻሉም አባቱ:: ኢንቨስትመንት በለው አንዷ ቺክ ላይ ስፔንድ የምታደርገው:: ማታ እንውጣ ምናምን ብለክ ፕሮፖስ ካደረክ የጸጉር ቤ: የጥፍር መሰሪያ: የሳውና ባዝ: ከነጀለሶቿ ትቀፍልሀለች:: በዛ ላይ ማታ ወይ መኩ ካልያዝክ ወይም ያው ላዳ ይዘህ ካላመጣሀት ምንም እንደማይሰጥህ እርግጠኛ ሁን:: እና ክለብ ይዘሀቸው ስትሄድ አጃቢ አያጡም:: ያንተው ሀላፊነት ናቸው:: እና ይሄ በ 17 የተባዛ ቤንጃሚን ሲከሳ ሲከሳ እያየህ አንተም አብረህ ትከሳለህ :lol: ወዲያው ለሶሶት አንድ ኪሎ ቁርጥ ከግማሽ የፍየል ጥብስ ጋር ጥጥት አድርገው በላዩ ላይ አምቦ ውሀ በኮካ ደፍተውበት ቁልጭ ቁልጭ ይሉብሀል:: አንተ ኮይኑን ትመታውና ኦቨር መውጣቱን ልትሰርዘው ስታስብ ብድግ ብለው መንገድ ይጀምራሉ::

ቅምቀማ ቤት ገብተውልህ በቃ ሰምተህ የማታውቀውን ጡጢ ስም ጠርተው ይጦዙና አባው ፈጤ ብለህ እያየካቸው ተበታትነው አንተ ያንተዋን ብቻ ይዘህ ለማታውቃቸው ጎረምሶች የቀሩትን ቺኮች አሟሙቀህ አስረክበህ ትሸበለላለህ:: አሪፍ ሆነህ ካልተገኘህማ እንደ ገልብጤ ከፈዘዝክ ሁልሉም እያየካቸው አንድ በአንድ እየቀነሱ ልክ እንደ አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች መዝሙር ዜሮ ይቀራል ብለህ ቤትህ ገብተህ አንድ ለአምስት ታስለቅሳለህ :lol:

አቦ አስረዘምኩት መሰለኝ ..የሆነ የዳግማዊን ፖስት አስመሰልኩት.. :lol: ሪቾ መቼም እንደማታነው የታወቀ ነው....

ፒስ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Tue Aug 07, 2012 5:25 pm

ጦማር...
ጠቃሚና አዝናኝ....ኢንፎቴይመንት ነው ያበረከትሽልን..... ያው ከሰሞኑ ..አለ አይደል በ 2013 ( በኢትዮ አቆጣጠር) ይኬድለታል ተብሏል....

ባይዘዌይ...ሳራንደምን ካገኘከው ሰላም በልልኝ.... በጣም ጨዋታ የሚያርፍ ልጅ ነበር!!
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ኤልሳ* » Tue Aug 07, 2012 7:22 pm

ጦምኔው wrote: ከፈዘዝክ ሁልሉም እያየካቸው አንድ በአንድ እየቀነሱ ልክ እንደ አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች መዝሙር ዜሮ ይቀራል ብለህ ቤትህ ገብተህ አንድ ለአምስት ታስለቅሳለህ :lol: [/i]


:lol: ይሄ የመጨረሻ ያስቃል...አብልተህ... አጠጥተህ... አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች እያልክ ወደ ቤትህ ከገባህ... አልተረፍክም... :lol: ሼም አፍ ዩ :lol:
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

Postby ኤልሳ* » Tue Aug 07, 2012 7:31 pm

ዘጌ_ዘጋንባው wrote: ከሰሞኑ ..አለ አይደል በ 2013 ( በኢትዮ አቆጣጠር) ይኬድለታል ተብሏል....

:lol:
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

Postby Gosa » Wed Aug 08, 2012 2:23 am

ጦምኔው wrote:አይ ፋሲካ....ድሮ ቀረ!! ይሄ ድሮ ቀረ የሚል አባባል በቃ ለመደብን አይደል? ምኑ ይሆን ድሮ የቀረው? ምን ያልቀረ አለና?.....ፈላ እያለን ያው እኛ ሰፈር ያደገ ሰው ያውቀዋል:: ልጅነት በጭቁን መንደር ሙድ አለው:: አንዴ ትዝ ይለኛል ለእኔና ለፈላው ብራዘር (ያው ታናሽ ነው) ፋዘር ኮምፕለተ ነው የገዛልን-የካሽሚር:: የኔ አረንጌአዴ ነበር (መስከረም 2 ነው ያስመሰልኩት) ለብራዘር ደሞ ኔቪ ብሉ (ደማቅ ሰማያዊ? ).....በጣም የሚያምረው ኮምፕሊቱ (2 ፒስ) የሚሰፋው ሸራ ተራ ነው:: ገበሩ የሻማ ነው (እዚህ ጋር "ያሻማ ቡሬ ቲያን" ያስታውሷል) እና የኔ ገበሩ ወይን ጠጅ ነበር:: ያው ሸሚዝ ተሸመተለት ከ ተክልዬ (ትሪፍት ስቶር ዘኢቲዮ):: ሾዳው አይነሳ:: :lol: አንድ ሰሞን መጥቶ የነበረ ጫማ ትዝ ካላቹ...ለነገሩ አሁንም ከማርኬት አልጠፋም መሰለኝ:: የፕላስቲክ ሾዳ ነው በቆዳ ጫማ ሙድ የተሰራ ማሰሪያ ሁሉ አለው:: ያው ማች አይደል የኔ አረንጓዴ የታናሽ ደሞ ቢጫ ነበር: እናማ በቃ ያው the night before አልነጋ ሁሉ ብሎን ለብሰነው ነው ያደርነው:: :lol: አይ እሱ ጫማ:: ከወራት በኋላ መርገጫው አላልቆ Moon Walk ነበር የምንሄደው:: መጨረሻ ላይ በጠዋት ጤዛ በረጠበ ድንጋይ ታግዞ አፍርጦ ሰበረን እንጂ:: true story! true story).

አቦ ፋሲካ በና ልጅነት ዘመን ቀረ:: ምሳ ከተበላለት በኋላ ትልቁ ብራዘር እኔን: ታናሼን እና የመጨረቻውን ብራዘር ይዞን ያዝናናን ነበር:: ብሔርው ጽጌ...ሐምሌ 19.....ምን ያልሄድንበት መናፈሻ :: ታላቅ ብራዘርም ድሮ ቀርቷል በቃ!!!

ይቀጥል ይሆናል........

:D :D :D ወዳጄ ጦምኔው:: እዉነትም ይሆን ልቦለድ ብቻ ነገሩ ከራሴ ታሪክ ጋር ተመሳስሎብኝ እንዴት እንዳሳቀኝ ልነግርህ አልችልም:: እኔ ለብሔረ ጽጌ አልታደልኩም የክፍለ ሀገር ልጅ ስለሆንኩ:: ግን የገጠሩ ሜዳውና ጫካውም ያው መናፈሻ አይደል... ትዝታ ቀሰቀስክብኝ :(
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ጦምኔው » Thu Aug 09, 2012 11:48 pm

ዘጌው... :D 2012 በኛ.....አባቱ የዛኔማ እንጃልሽ...የላይኛው ይሁንሽ :lol: ስሚ እንጂ ዘጌው..ባለፈው የተሸበለልሽለት ጊዜ ምን አጋጥሞሽ ነበር ረጋርዲንግ ቺኮቹን እና ቅምቀማ ?? እስኪ ዘይሪን!!

ሳራንደም ከች ይላል ሰሞኑን.....ጥሪው ተልኳል

ኤልሲ....ዘይገርም ነው እኮ! እውነት ነው ግን ከምን ፍጥንጥን ካላልሽ ቺኮቹ እኛ በዲያስፖራ ቺኮች የለመድነውን ይዘን ስንሄድ እነሱ ኪሏቸው ጨምሯል ስልሽ....ሊጋቸው ሀይ ነው:: ታይዋለሽ ከተሸበለልሽ :lol:

ጎሳ ሰላም አለቃ:: ያ ካሽሚር በጊዜው ሙድ ነበረው:: እስኪ አንቺም ትዝታሽን ጣል አድርጊው ሞሽሪና.....
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

:-)

Postby ደጉ » Fri Aug 10, 2012 10:15 am

.... ጦምኔው ቅቅቅቅቅ እምጠጣ ቢሆን ልክ እንደ አንተ ነበር እምጀምረው ነበር ማለት ነው..? እስኪ ያመለጠኝን ሁሉ አንብቤ እመለስበታለሁ.. :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4552
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby -...- » Fri Aug 10, 2012 12:13 pm

ይችን በአማርኛ ተርጉሞ ለሚያቀርብልኝ ወሮታውን እከፍላለሁ ::

ጦምኔው wrote:ከሀገር ቤት የመጣ ቡሌ ተጠልፎለት የጀበና ቡና በሉባንጃ ጢስ እየታጠንን ተቀምቅሞለት በምቾት እና በምርቃና የተጻፈ:: :D ኤዲት እያደረጉ እንዲያነቡ ይጠየቃሉ::

አይ ቅምቀማ.....ባለፈው ሀገር ቤት ለቫኬሽን ተመርሾለት የአዱገነት አሪፎች (ታናናሽ ብራዘሮችንም ጨምሮ) አይ አሳሳባቸው.....አይ አመጣጠጥ:: የማይጠጡት ነገር ጥይት ብቻ ነው እኮ:: እኔ ትዝ ይለኛል ለመጀመሪያ ጊዜ ቅምቀማ የተጀመረለት ኮልፌ ሀይ ስኩል ሶቶ ከተባለ በኍላ ነው:: ትምሮ ቤታችን አጥር አልነበረውም:: ዙሪያው በር ነው ስልህ:: እና ልክ ጫካውን አልፈህ ስትወጣ ቦዛ ቤቶች አሉ:: እዛ ነው የመጀመሪያውን ቦዛ የቀመከምነው:: እና ከትምሮ እየተፎረፈ አንዳንዴም ለላይብረሪ ብሬክ ይሳብለት ነበር:: ቦዛ ይጠጣለታል ሽልጦ AKA CD በሚጥሚጣ ይጎረስለታል:: በ ዱ ቂቅ ብለህ በእግር ከልኳንዳ እስከ ሰፈር (ኳስ ሜዳ ማዞሪያ) በቸርኬ ያለ ድካም ይገባለታል::

ጠንከር ያለ ቅምቀማ የተጀመረለት ኮሌጅ ነው:: ሳቢውም ከች ሲል በቃ ድራፍት ተጀመረለት:: ከዛ ቢራ (ያው ለዓመት በዓል ወይም ዕቁብ ሲደርሰን) አፎርድ ስናደርገው ቅንዳንዴ ይቸለስበታል:: በዛ ዘመን ቺኮቹን ራሱ ግሪን ሀውስ ወይም አንዱ ካፕል ሀውስ ይዘሀቸው ስትሸበለል ካንተው እኩል ድራፍታቸውን ቀምቅመው እኩን ፏ ብለው ሳቅ በሳቅ ሆነው አንተንም ሀፒ ገጭተውህ "ያሰብኩት ተሳካ...." እየዘፈንክ ወደ ቤት:: አንዳንዶቹ ጸዳ አሉ የሚባሉትም ግፋ ቢል ትንሿን ጉደር በኮካ ምጥጥ አድርገው የብላክ ሌብል ያህል ጡዘው ይመቹካል::

አሁን ልክ ከአሙካ ሄጄለት ከብራዘሮች ካር ስወጣለት አባቱ ይህንን የቅምቀማ ስም እንደ ዘር ማንዘራቸው እስከ ሰባት ቤት ድረስ ይጠሩልሀል:: እኔን ብዙ ያውቃል ብለው ሲጠብቁኝ እኔ ፍሬንዳቹ ፍጥጥ:: ኧረ ፍጥነት:: የመጬ ግርሞ:: ቺኮቹማ በቃ አይቻሉም አባቱ:: ኢንቨስትመንት በለው አንዷ ቺክ ላይ ስፔንድ የምታደርገው:: ማታ እንውጣ ምናምን ብለክ ፕሮፖስ ካደረክ የጸጉር ቤ: የጥፍር መሰሪያ: የሳውና ባዝ: ከነጀለሶቿ ትቀፍልሀለች:: በዛ ላይ ማታ ወይ መኩ ካልያዝክ ወይም ያው ላዳ ይዘህ ካላመጣሀት ምንም እንደማይሰጥህ እርግጠኛ ሁን:: እና ክለብ ይዘሀቸው ስትሄድ አጃቢ አያጡም:: ያንተው ሀላፊነት ናቸው:: እና ይሄ በ 17 የተባዛ ቤንጃሚን ሲከሳ ሲከሳ እያየህ አንተም አብረህ ትከሳለህ :lol: ወዲያው ለሶሶት አንድ ኪሎ ቁርጥ ከግማሽ የፍየል ጥብስ ጋር ጥጥት አድርገው በላዩ ላይ አምቦ ውሀ በኮካ ደፍተውበት ቁልጭ ቁልጭ ይሉብሀል:: አንተ ኮይኑን ትመታውና ኦቨር መውጣቱን ልትሰርዘው ስታስብ ብድግ ብለው መንገድ ይጀምራሉ::

ቅምቀማ ቤት ገብተውልህ በቃ ሰምተህ የማታውቀውን ጡጢ ስም ጠርተው ይጦዙና አባው ፈጤ ብለህ እያየካቸው ተበታትነው አንተ ያንተዋን ብቻ ይዘህ ለማታውቃቸው ጎረምሶች የቀሩትን ቺኮች አሟሙቀህ አስረክበህ ትሸበለላለህ:: አሪፍ ሆነህ ካልተገኘህማ እንደ ገልብጤ ከፈዘዝክ ሁልሉም እያየካቸው አንድ በአንድ እየቀነሱ ልክ እንደ አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች መዝሙር ዜሮ ይቀራል ብለህ ቤትህ ገብተህ አንድ ለአምስት ታስለቅሳለህ :lol:

አቦ አስረዘምኩት መሰለኝ ..የሆነ የዳግማዊን ፖስት አስመሰልኩት.. :lol: ሪቾ መቼም እንደማታነው የታወቀ ነው....

ፒስ
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Postby ገልብጤ » Sat Aug 11, 2012 9:29 pm

ጦምኔው እኛ ወደ ሽገር ስንሄድ የሰንበቴ ቤት ደጅ ነበር የምንጠናው ,,እሙሙም ያው በርካሽ ዋጋ 4ኪሎ እስከ ሾላ ነፍ እኮ ነበር ለዛውም በ3 ብር ሾርት....በነዲጎኔ እና ጌታ ዘመን ግን በብር ከሀምሳ 2 ቀን አዳር ትነጨበት ነበር ...ለዛውም የታጠነ ቀሚሳቸው ስር ውሽቅ የምትለው ከሰል ማደጃ ታውቃት የለ ...ቂቂቂቂቂቅ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ጦምኔው » Sun Aug 12, 2012 9:08 pm

"ሳትናከስ መለበጥ አትችልም?" አልሽኝ እኔ እነዛ እንቡጥ ጽጌሬዳ የመሰሉ ከናፍርትሽን ጎርሼ ስሜትሽን ልገዛ ስጣጣር እየገፈተርሽኝ:: እንደነከስኩሽ አልታወቀኝም:: "ምናልባትም እንደ ኩበት ደርቀው የተሰነጣጠቀው ከንፈሬ ቆርጦሽ እንዳይሆን" ስልሽ ግራና ቀኝ ጆሮ ግንዴን በሁለት እጆችሽ ይዘሽ እያገላበጥሽ ካየሽኝ በኍላ ከንፈሬን በእጆችሽ መዳደሱን ጀመርሽ:: "ኣ ኣ....ጥርስና ከንፈርማ መለየት አያቅተኝም" ብለሽ እየተመናቀርሽ መንገድሽን ጀመርሽ::

ባለፈው ደግሞ ተረከዜ እየተሰነጣጠቀ አስቸገረኝ:: አንዳንዱማ ስንጥቅ ቼላ ይደብቃል ብለሽ ምርር ብለሽ ስታለቅሺ ሰምቼ ዕቁብ ገብቼ ቆንጂት ኮንጎ ገዛሁልሽ:: ሁለት ሳምንት ከዘነጥሽበት በኍላ ለቁራሌው ሸቀልኩት ብለሽ ነገርሽኝ:: ለምን ብዬ ብጠይቅሽ ጩሎ ከምናለሽ ተራ ሰከንድ ሀንድ ቋ ቋ ጫማ እንደገዛልሽ ነገርሽኝ:: እርር ድብን ብዬ ተናደድኩና ቤቴ ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ::

እንዲሁ ደሞ የዛሬ ወር ገደማ ጩሎ ያንን የጠፈርተኛ የሚያክል የጀርባ ቦርሳውን አንግቦ: ካራቴ ጫማውን በጥቁር ፒትልስ ዝንጥ ብሎ: በእጁ የሀይላንድ ውሀ ዕቃ ይዞ (ቧንቧፍሬሽ) እየጠጣ አንቺም ወገቡ ላይ ጥምጥም ብለሽ ዎክ እያደረጋቹ ሰፈር አግኝቼሽ እንደ መናደድ ስል "ሆድዬ ጩሎ እኮ ማለት ወንድሜ ነው:: ንጹህ ወንድሜ ነው:: ከፈለክ ያንተም ወንድም ይሆንሀል::" ብለሽ አንቺ በግራ እኔ በቀኝ የጩሎ ወገብ ላይ ጥምጥም ብለን ወደ ፒያሳ ዎክ ስናደርግ ሀብተ ጊዮርጊዝ ድልድይ ጋር የትምሮ ቤት ልጆች ከልመውኝ "ወገባም" እያሉ ነው የሚሰድቡኝ ስልሽ ሳቅሽብኝ::

እንደማፈቅርሽ ደጋግሜ ነገርኩሽ:: አንድ ቀን አብረን ለምን አናድርም ስልሽ ከትከት ብለሽ ሳቅሽና የት እንደምናድር ጠየቅሽኝ:: ለምን እንደጠየቅሽ ግራ ገባኝ:: የምትቀልጂም መሰለኝ:: "እናንተ ዕቃ ቤት ነዋ!" ስልሽ ድጋሚ ሳቅሽና ጩሎ እዛ እንደሚያድር ነገርሽኝ:: ተበሳጭቼ ሄድኩና ማምሻውን ዕቃ ቤታቹ ውስጥ አጮልቄ ሳይ ጩሎ እና አንቺ መለመላቹን ስትኮራኮሩ አየኍቹ:: እንዳለየ አሳለፍኩልሽ::

ሶስት ወር ጠብቅሽ እና "ቀረብኝ እኮ" አልሽኝ:: "ምኑ" ብዬ ስጠይቅሽ ብስጭት ብለሽ "እንዴት ምኑ ትለኛለህ? ፔሬዴ ነዋ" ብለሽ በዓይኖችኝ እያሽሟጠጥሽ ተሽኮረመምሽ:: "ኧረ አይመልሰው" አልኩና በሆዴ ፔሬድሽ ሊቀርበት የቻለበትን ምክንያት ማሰላሰል ጀመርኩ:: ወዲያውኑ ግን ወ ጭንቅላቴ የመጣው ብቸኛ ምክንያት የጩሎ ኩርኮራ ብቻ ነው::

ስለዚህ በቃሽኝ::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ጌታ » Mon Aug 13, 2012 3:25 pm

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ድሮም መክሬሃለሁ ትብቃህ!!!
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3120
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ጦምኔው » Tue Aug 14, 2012 2:05 am

ሰላምከ ጌች:: አልሰማ ብዬ .....

እኔና ፈላው ብራዘር አብረን ነበር አንድ አልጋ ላይ የምንደቅሰው:: እኔ ከላይ በራስጌው እርሱ ከታች በግርጌው:: እና ያው አንድ ብርድልብስ ነበር ሼር የምናደርገው:: የሰው ትንፋሽ ይደብረኛል በጣም:: እና ከብራዘር ጋር ብርድልብሱን ስንለብስ እኔ በበጉ በኩል ነበር ሁሌ የምለብሰው (የደብረ ብርሀን ስኩዌር ብርድልብስን ያስታውሷል):: ያእ ፕራይቬሲ እንዳቅሚቲ መሆኑ ነው እንግዲህ::

እኛ ቤት በጣም ብዙ ነገር ነበር ሼር እያደረግን ያደግነው:: ዩኒፎርም ሁሉ ሼር እናደርግ ነበር:: ጠዋት እኔ ተምሬበት ስወጣ እሱ ከሰዓት ትምሮ ቤት በሩ ላይ ይጠብቀኝና ደርቦ ይገባል:: ስፖርት ስንማር ማልያ እና ቁምጣ ለቤተሰቡ አንድ ነበር የተገዛልን:: እሱን እየተቀያይርን ነው የኖርነው::

በዚህ መሀል ግን አንድ ትልቅ ነገር ተምረንበታል:: ፍቅር እና ተካፍሎ መኖርን:: በተጨማሪም በትንሹ መኖር ችለንበታል:: ባለህ ነገር ማደር ትልቅ ነገር ነው:: በዛ ላይ አንድም ቀን ማጣቴ ተሰምቶኝ አያውቅም:: ሁሌም ደስተኛ ነበርኩ:: አሁንም እዚህ የባዕድ ሀገር ይሄው ከቤተሰቤ የተማርኩት በጋራ አምሮ መኖር ከማውቀው ሰው ሁሉ ጋር በፍቅር እና በመተሳሰብ አብሬ እንድኖር ረድቶኛል:: እጄ ሞልቶ የሚናፍቀኝ ያ ያሳለፍኩት ትንሽ ሕይወት ነው::

አብዛኛው የአዲስ አበባ ሕዝብ ከዚህ የተለየ ታሪክ ያለው አይመስለኝም:: አትሊስት እኔ የማውቃቸው እና በዙሪያዬ የነበሩ ቤተሰቦች ያንን ነው የኖሩት:: ከቤተሰብ አልፎ ከጎረቤቶቻችን ጋር ተሳስበን ተከባብረን ተካፍለን ነው የኖርነው:: ያ ወርቃማ ጊዜ ነበር::

እዚህ ሀገር ግን እንደሚሰማው ሰዉ ምን እንደሚነካው እንጃ አብሮ ተሰስቦ መኖር አቅቶታል:: እኔ ዕድለኛ ሆኜ እዚህ ሀገር ከመጣሁ ከስፖንሰሮቼ ቤት ከወጣሁ በሁዋላ እስካሁን አንድ ሩም ሜት ነው ያለኝ:: ወንድሜ ማለት ነው:: ከ 6 ዓመት በላይ አብረን ነው ያለነው:: ከሩም ሜት ይልቅ ቤተሰባዊነታችን ይልቃል:: ጉአደኞቻችን የጋራ ናቸው:: አንዳችን ለአንዳችን አስበን ሁሉን ነገር ተካፍለን እየተቆጣጣን እየተመካከርን አለን:: እኔ እንደገባኝ ያ የኖርኩት ትንሽ በቤተሰቦቼ የተከበበ የኑሮ ልምድ ረድቶኛል::

በትምህርት ቤት የማውቃቸው ጓደኞቼ ከሩም ሜት ጋር በተገናኘ በጣም ብዙ ልምዳቸውን አካፍለውኛል:: አብዛኛው የሚያማርራቸው ነው:: ያለቀሱ ሁሉ አሉ:: :lol: እስኪ በዚህ ጉዳይ ያጋጠመንን እናውራው:: ጥሩ መማማሪያ ይሆነን ይሆናል::

ፒስ!
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby recho » Tue Aug 14, 2012 2:54 am

ማይ ሩሜት ..

ዘ ስዊተስት ገርል ኤቨር .. ብቻ ያንን የሚተጣጠፍ መብመንጃዋን ማውጣትዋ ነው እንጂ .. አሪፍ ልጅ ነበረች .. 9 ወር ኖርንና ያው መቸም መለያየት አይቀር ተለያየን .. አሁን ግን በጣም ጉዋደኛዬ ናት .. የማልረሳው ነገራችን ምግብ መቀላቀል አልቻልንም ምክኒያትም እኔ ሽሮ ነው መብላት የምወደው እስዋ ደግሞ እንጀራ ከአያያዙ ጀምሮ አትችልበትም.. በዛላይ የቅንጦት ምግብዋ ነው .. አበሻ ሬስቶራንት አዲስ የጠበሰቻቸውን ለማሳየት የምትወስድበት እንጂ ቁዋሚ ምግብ ሲሆን አታውቀውም .. ግን የፈለኩትን ኩክ ባደርግ ቢበዛ ቆማ ከዛ ምን ይገባል ..እሱ ምንድነው እያለች እንደትንሽ ልጅ ታደርቀኛለች እንጂ ምንም ከፍቶዋት አታቅ (አንዳንዶች ነጫጭቦች የአበሻ ምግብ ይገማናል የሚሉትን ያስታሱልኝ እንግዲህ .. ) ታዲያ አንድ ቀን እኔም ሽሮዬን እሱዋም ማሽ ፖቴቶ በግሬቭዋ እያወጋን በላንና እኔም ሽሮዬን በምሳቃዬ በትንሽዋ ወጡን ብቻ .. እሱዋም ለነገ ምሳዋ ግሬቪውን ለብቻ ማሽፖቴቶዋን በሌላ አርጋ ተኛን.. ጠዋት በተደናበረ አይንዋ ቀድማኝ የወጣችው እስዋ ናትና ምሳዋን ይዛ ሄዳለች ..እኔም ያልምንንም መጠራጠር የመክደኛውን እንኩዋን ክዳን ቀለም መቀየር ሳላስተውል ግሬቪዬን ይዤ ወደስራ ሄድኩ ... ምሳ ሊደርስ አካባቢ ቴክስት አገኘሁ .. ሪቾ ሶሪ ስዊቲ አይ ሀቭ ዮር ሽሮ ወጥ . ዶ ዩ ቲንክ ኢት ዊል ቢ ኦኬ ኢፍ ዩ ኢት ግሬቪ ዊዝ ኢንጀራ ኤንድ አይ ዊል ትራይ ማሽ ፖቴቶ ዊዝ ሽሮ ሎል ሲሪ አጌን .. ላቭ ዩ .. ዊል ሜክ ኢት አፕ ቱ ዩ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:

የሩሜት መጥፎ ትዝታ የለኝም ... አሪፍ አሪፍ ግን ጥሩ አሉኝ .. አረፍ እያልኩ ከተፈቀደልኝ እመለሳለሁ .. ጦምን እንዳልከው እዚህ አገር ሼር አርጎ መኖር ምናምን ፈጽሞ የማይታሰብ ነው .. ቤተሰባዊ ኑሮን እንዴት እንዳልኖሩት አላቅም .. የግድ መቸገር እየልብህም ቤተሰብ ሼር አርጎ መኖርን እንዲያስተምርህ .. ፍቅርን ካላወቅክ ከባድ ነው .. !!!

ሰላም :)
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby recho » Tue Aug 14, 2012 3:32 am

በሌላ ጊዜ ...

አጅሪ አርብ አርብ ማታ አዳዲስ ወንድ ይዛ ትመጣና ቅዳሜ ጠዋት ስሙን የማላቀው ሰውዬ ቁርስ ሊሰራ ይንደፋደፋል ... እና አይ ወዝ ሶ ታየርድ ኦፍ ስትሬንጀር ዎኪንግ ኢን ዘ ሀውስ አንቺ ልጅ እረፊ ብዬ ተነጫነጭኩ .. እህእ እኔኮ ሀበሻ ነኝ .. ፈራለሁ :lol: ተዚያነ .. ልጅት ይቅርታ ይቅርታ አለችና ለተወሰኑ ቅዳሜዎች ቤት ውስጥ ያደረም አርብ ማታም የተንጎዳጎደም የለም .. በኔቤት .. ለካ ጨዋታው ሌላ ነው ... ግን አሪፍ ምን አገባኝ .. እኔ ከስራ ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ባለው እመጣለሁ ከስራ ( ማታ ስለምሰራ አርብ ) ስለዚህ አጅሬው ከዛ በፊት ይወጣል ... እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም .. ሶ ያንን አርብ ለታ ቤታችን አካባቢው ጭር ብሎዋል .. ኦ አልገባችም ማለት ነው እያልኩ ድራቭ ዌዩ ላይ ደረኩ .. ማንም የለም .. እና ሪቾዬ ወደ መስታወቱ በር ቀረብ ብዬ ሳላንኩዋኩዋ ጎረቤት ሳልረብሽ ... ውሾች ሳላስጮህ በር ልከፍት ጥረት እያደርኩ ድንገት ቀና ስል ቡም!!! ጩህቴን አቀለጥኩት ... :lol: እየቀለድኩ አይደለም .. በመስታወቱ ውስጥ አይ ሲ ጂሰስ .. !!! ጸጉሩ ለሁለት መሀል ላይ ተከፍሎ ወደሁዋላው የወረደ .. የለበሰው አይታየኝም ወይንም እኔ ለማየት ጊዜም አልነበረኝ .. ጺሙ ልክ እንደ እየሱስ ብለን የምናየው ስእል መሀል ላይ ክፍተት ያለው ሆኖ ደስ የሚል ... አይኖቹ ትንንሽ .. ብልጭ ብልጭ የሚሉ .. ልዩነቱ ይሄኛው ጂሰስ ፈርቶ ይቁለጨለጫል ... ሩሜቴ በሩን በርግዳ ሶሪ ሶሪ እያለች ወደውስጥ ስታስገባኝ .. ኦፕስ ጂሰስ እኛቤት መጥቶ ነው ለካ ... ትንሽ ቀደም ብየ ስለመጣሁ ነው እንጂ ያየሁት ለካ አጅሪት ቴክኒክ ቀይራ ቀደም አርጋ ታስወጣለች .. ዌል ፋይን ዊዝ ሚ .. እኔ ያልኩት ጠዋት ቡና ላፈላ ስነሳ ቤትኪራይ የማይከፍል ሰው ቤትውስጥ ማየት አልፈልግም ነው .....ስረጋጋ ዋይ ዲድ ዩ ስክሪም ላክ ኢትዝ ዘ ኢንድ ኦፍ ዘ ዎልድ ገርል ? አለ ጂሰስ :lol: :lol: የሪቾ መልስ .. አር ዩ ፋኪንግ ኪዲንግ ሚ .. ያይ ቶውት አይ ሲ ጂሰስ ... ሊወስደኝ የመጣ ሁሉ ነው የመሰለኝ :lol: እየቀለድኩ አይደለም .. አይ ቶውት አይ ሲን ጂሰስ !!!! :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby -...- » Tue Aug 14, 2012 3:46 am

recho ሩሜትሽ እንደዛ ስታማርጥ ምነው አንቺ በሶ ጨብጠች ነበር የምትኖሪው ? እንደሷው ማማረጥ ነበረብሽ :: If you can't beat them join them. አመለጠሽ ስንት የኑሮ ተሞክሮ :: አሁን ያ ወልጋዳ በትዳር ጠፍሮሽ ቁጭ አልሻት :: ቀናሁበት ያላማረጠች አግኝቶ ::
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests