........መደበሪያ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ጦምኔው » Wed May 09, 2012 9:17 pm

recho wrote:
እህምም wrote::lol: ጦምንሻ you just made my day. የዋርካ አዲክሽኔን ልታስመልሰው ነው መሰለኝ.
ኦ ማይ ጋድ!!! :arrow: :arrow: እ ህ ህ ም !


I know. Welcome back lil girl :lol:
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ጦምኔው » Wed May 09, 2012 10:10 pm

ኤለመንተሪ ተየማርኩት የካቲት 23 መሳለሚያ ነው:: መሳለሚያ አዲስ አበባ ውስጥ ያለ ሰፈር ነው ለማታውቁት የስቴት እና የቦሌ ልጆ :lol: በጣም ብዙ ነገሮች ተምሬበታለሁ ያንን ትምህርት ቤት:: ሶስተኛ ክፍል እያለሁ (ያኔ ነው እንግዲህ እንግሊዝኛ መማር የጀመርነው በኛ ባች) እና አንድ ምንባብ ነበር:: "Almaz is listening to a radio" ምናምን የሚል ነገር:: እሱን አንብቤ ክፍል ውስጥ በተማሪዎች ፊት የእንግሊዝኛ አስተማሪያችን አስር ሳንቲም ሸልመውኛል:: የዚያን ቀን ከትምሮ በሗላ ተንበሻበሽንበት:: :lol:

የመንግስት ትምህርት ቤት ስለነበር መጽሀፍ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ተውሰን በዓመቱ መጨረሻ ላይ ነበር የምንመልሰው:: አምስተኛ ክፍል እያልን ነው ትዝ ይለኛል:: እኔና አንድ ጓደናዬ ነበርን አብረን የተዋስነው:: (በቂ መጽሀፍ ስለሌላቸው አንድ መጽሀፍ ለሁለት ነበር የሚሰጡን) :lol: ከቀበሌ ሁሉ መዋሻችን ላይ ማህተም አስመትተን ነው (Prrof of residence መሆኑ ነው) አማርኛ መጽሀፋችንን ተውሰን በዓመቱ መካከል ላይ አካባቢ ጠፋብን:: ያው የጭቁን ልጆች ስለነበርን በዓመቱ መጨረሻ ላይ ቤት መጽሀፍ የሚገዛልን የለም:: ስለዚህ we gotta do something አልን እና እኛም ያው ዕረፍት ሰዓት ጠበቅን እና የአንዱን ልጅ አማርኛ መጽሀፍ ለመጥነው:: ልጁ ዓይጤ ይባላል:: እና ያንን መጽሀፍ ወደ አንድ ወር ጀለሴ ቤት ደብቀን የቤት ስራ ስንሰራበት ቆየን እና ከወር ምናምን በሗላ አሁን ብናመጣውም አያውቀውም ብለን ይዘነው መጣን:: በአማርኛ ክፍለ ጊዜ እየተማርን አይጤ የዛን ቀን እኛ አጠገብ ተቀመጥ:: ልክ መጽሀፉን ሲያየው አወቀው እና "እንዴ መጽሀፌ! ይሄማ የኔ ነው" ብሎ ቀወጠው:: እኛም ያው የሌባ አይነ ደረቅ ገገምን የኛ ነው ብለን:: ከዛ አይጤ "እንደውም ባለፈው ለታህሳስ ገብርኤል ከጀለሶቼ ጋር የድግስ ምሳ እኛ ቤት ስንበላ ቀይ ወጥ የነካው ምልክት ገጽ 71 ላይ አለ" ብሎ ገልጾ ወጡን አወጣው:: መጽሀፉንም ወሰደው እና ከጀለሶቹ ጋር ወደቤት ሰዓት ላይ ወገሩን:: :lol:

I love የመንግስት ትምህርት ቤት ላይፍ::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ደጉ » Thu May 10, 2012 8:47 am

ጦምኔው wrote:.... እሱን አንብቤ ክፍል ውስጥ በተማሪዎች ፊት የእንግሊዝኛ አስተማሪያችን አስር ሳንቲም ሸልመውኛል:: የዚያን ቀን ከትምሮ በሗላ ተንበሻበሽንበት:: :lol:...

.... :D ጦምኔው የስጡዋችሁ ገንዘብ"ኮ እስከ አመቱ መጨረሻ ያዝናናችሁ ነበር...አያይዙን ብታውቁበት ;) ጨዋታህ ግን ብዙ ነገር አስታወሰኝ ....መሳለሚያንም ሳላውቀው አወኩት ...:)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4458
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby እህምም » Thu May 10, 2012 8:43 pm

recho wrote:
እህምም wrote::lol: ጦምንሻ you just made my day. የዋርካ አዲክሽኔን ልታስመልሰው ነው መሰለኝ.
ኦ ማይ ጋድ!!! :arrow: :arrow: እ ህ ህ ም !


ሬች!!! እንዴት ነሽ ቆንጆ ? it's been ages አይደል. hope all is well :)

ጦምንሻ: who you callin little አንተ? fyi አንቱ መባል ጀምሬያለሁ :P
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Postby recho » Thu May 10, 2012 9:20 pm

እህምም wrote:
ሬች!!! እንዴት ነሽ ቆንጆ ? it's been ages አይደል. hope all is well :)
ብቻ ... በጣም ጠፋሽ .. በሌላው ቻናል ቼክ አረኩሽ ... ዊ አር ጉድ ሂር .. አንቺስ? አይበቃም አትመለሺም ? ዙረታም :lol: ሚስድ ያ
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ጦምኔው » Thu May 10, 2012 9:46 pm

ደጉሸት ይኸውልህ እኛ ሰፈር ብዙ ታሪክ አለ ሎል:: መሳለሚያ ብዙ ያልተጻፈ ታሪክ አላት:: "መሳለሚያ: ያልተጻፉ ድርሰቶች" ሁሉ ብዬ መጽሀፍ ሳልጽፍ አልቀርም አባ:: በቅርብ ቀን ጠብቅ:: :lol:

ኤህምምሻ አንቺ ስታድጊ እኮ እኛ እያረጀን ነው ሎል:: So, you still lil በኛ ዓይን:: ደሞ ለማደግ አትሩጪ....ትደርሺበታለሽ:: :lol: It really is great to see you back on warka. በይ ጣፍ ጣፍ አድርጊ::

Recho ጥፊ አማረኝ:: :lol:
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby እምቢ ለሀገር » Fri May 11, 2012 8:33 pm

ጦምኔው ሰላም ብያለሁ :!: ""ጦምኔው"" ማለት ግን ምን ማለት ነው :?:...እስኪ አባ አማርኛ (የ11ኛ ክፍል አማርኛ መምህሬ) ያስተማሩኝን ""የቃላት አተረጓጎም ስልቶች"" በመመርኮዝ ""ጦምኔውን"" ልፈታታው:-
1=ጦ...ምኔው(ጦ(ፊደል) ምኔው)
2=ጦም...ኔው(ጦም(ጾም) ኔው(በወሎዎች አነጋገር=ነው)
3=ጦምኔው(ም.ሳ=ዘንድሮ እንደ ጉድ ጦምኔው(በወሎ ዘይቤ)
4=ጦምኔ..ው(ጥሞና ጠሞነ ጠሟኝ ጠሟኙ....ጦምኔው(ልክ ጉልበተኛውን ጉልቤ ጉልቤው እንደ ምንለው))
ይመስለኛ የስምህ ትርጉም በተ.ቁ 4 ዙሪያ ያንዣብባል::
አይ አባ አማርኛ.... :!: ለአማርኛ ቋንቋ ት/ት መምህሮቻችን የነበረን ንቀት...ይቅር.. አይነሳ::ለእንግሊዘኛ ለፊዚክስ እና ለሂሳብ...መምህራን ትልቅ አክብሮት ነበረን::
አባ አማርኛ..የ11ኛ ክፍል አማርኛ መምህሬ...በት/ቤታችን ውስጥ በሚደርስባቸው ንቀት ይመስላል ብቸኛ ሰው ነበሩ::ከመምህራንም ሆነ ከተማሪዎች ጋር ከስራ ውጭ ሲነጋገሩ አታያቸውም:: ከት/ቤት ውጭ አግኝተህ የእግዜሩን ሰላምታ ብትቸራቸው ወይ ፍንክች አባ አማርኛ::ሁሌም ፊታቸውን እንደ ኮሰኮሱት ነው:: የምንንቃቸውን ተማሪዎች ፈተና ላይ ጠብቀው ወጥ በወጥ ካደረጉን በኍላ የፈተና ወረቀቶቻችን በሚመልሱልን ጊዜ ያኔ..አባ አማርኛ..ግዳይ እንደጣለ አንበሳ ጅንን ብለው ከመቅስፈት ታይታ የምትጠፋ የፈገግታ ብልጭታ ያሾፉሀል:: እኔ ነኝ ያለ ጐበዝ ተማሪ ቢደረደር የአባ አማርኛን ከ60ው ፈተና 50 ቤት አይገባትም::ከ100 80 ቤት መግባት በመርፌ ቀዳዳ እንደመሽሎክ ይቆጠራል::
ክፍል ውስጥ ጥያቄ ተጠይቀህ ስትመልስ በስተት ከአፍህ የእንግሊዘኛ ቃላት ካመለጡህ.... ጦሜው አለቀልህ :!: ""አንተን ብሎ የቅኝ ገዥዎችን አፍ አዋቂ"" ""ትለብሰው የላት ትከናነበው አማራት"" ""ና........ውጣ :!:""............
አባ አማርኛ የአማርኛ ቋንቋ ክቡር ዘበኛ ነበሩ:: ""አማርኛችሁ እኮ እየሞተ ነው::ቋንቋው ከሚሞት እናንተ ድፍት ብትሉ ይሻላል :!: አማርኛ እኮ ውብ ቋንቋ ነው ምጡቅ ነው::የማንነት መገለጫችሁን በቅኝ አታስገዙት :!:"" ምርር ብለው ከሚናገሯቸው ንግግሮች አንዳንዶቹ....
""በአማርኛ ማውራት እና ድንጋይ መወርወር በጥብቅ የተከለከለ ነው :!: "" የሚል ማስጠንቀቂያ በቅጥር ግቢያቸው በልበ-ሙሉነት ወደ ሚያስተጋቡት ቅምጥል የግል ት/ቤቶች....አባ አማርኛን በምናቤ እወስዳቸው እና ጨርቃቸውን አንድ በአንድ እየጣሉ ሲያብዱ ሳይ በስመ-አብ ወወልድ....ብየ ምናቤን እዘጋለሁ::
በል እስኪ ጦምኔው........

እምቢ ለሀገር ነኝ
ከጐንደር
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat May 12, 2012 6:35 am

እምቢ ለሀገር wrote:ጦምኔው ሰላም ብያለሁ :!: ""ጦምኔው"" ማለት ግን ምን ማለት ነው :?:...እስኪ አባ አማርኛ (የ11ኛ ክፍል አማርኛ መምህሬ) ያስተማሩኝን ""የቃላት አተረጓጎም ስልቶች"" በመመርኮዝ ""ጦምኔውን"" ልፈታታው:-
1=ጦ...ምኔው(ጦ(ፊደል) ምኔው)
2=ጦም...ኔው(ጦም(ጾም) ኔው(በወሎዎች አነጋገር=ነው)
3=ጦምኔው(ም.ሳ=ዘንድሮ እንደ ጉድ ጦምኔው(በወሎ ዘይቤ)
4=ጦምኔ..ው(ጥሞና ጠሞነ ጠሟኝ ጠሟኙ....ጦምኔው(ልክ ጉልበተኛውን ጉልቤ ጉልቤው እንደ ምንለው))
ይመስለኛ የስምህ ትርጉም በተ.ቁ 4 ዙሪያ ያንዣብባል::


ለዛቢስ ቀባጣሪ.......መቀባጠሩን ትተህ ፊትህ ላይ የሚያንዣብቡትን ዝንቦች እሽ በል :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ጎተራ® » Sat May 12, 2012 7:12 am

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:
እምቢ ለሀገር wrote:ጦምኔው ሰላም ብያለሁ :!: ""ጦምኔው"" ማለት ግን ምን ማለት ነው :?:...እስኪ አባ አማርኛ (የ11ኛ ክፍል አማርኛ መምህሬ) ያስተማሩኝን ""የቃላት አተረጓጎም ስልቶች"" በመመርኮዝ ""ጦምኔውን"" ልፈታታው:-
1=ጦ...ምኔው(ጦ(ፊደል) ምኔው)
2=ጦም...ኔው(ጦም(ጾም) ኔው(በወሎዎች አነጋገር=ነው)
3=ጦምኔው(ም.ሳ=ዘንድሮ እንደ ጉድ ጦምኔው(በወሎ ዘይቤ)
4=ጦምኔ..ው(ጥሞና ጠሞነ ጠሟኝ ጠሟኙ....ጦምኔው(ልክ ጉልበተኛውን ጉልቤ ጉልቤው እንደ ምንለው))
ይመስለኛ የስምህ ትርጉም በተ.ቁ 4 ዙሪያ ያንዣብባል::


ለዛቢስ ቀባጣሪ.......መቀባጠሩን ትተህ ፊትህ ላይ የሚያንዣብቡትን ዝንቦች እሽ በል :lol: :lol: :lol:


:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: የዝንብ አየር ማረፊያ አለ ክበበው ገዳ እሱን አይቶት ይሆናል::
©ጎተራ ባጫ ከድድ ማስጫ
ጎተራ®
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Mon May 07, 2012 10:17 pm

Postby እምቢ ለሀገር » Sat May 12, 2012 6:15 pm

ሰላም የቤቱ ከፋች እና ዘጊ ጦምኔው :!:

ወዳጀ ቤትህ ከመደበሪያነት ወደ መሰዳደቢያነት ከመቀየሯ በፊት አንድ በላት....

እኔ እዚህ ቤት የመጣሁት ወገቤን ለማሳረፍ ነበር::ግን አልሆነም....እባክህ ውሾችን አባርልኝ....

እምቢ ለሀገር :!:
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

Postby ጦምኔው » Sat May 12, 2012 6:16 pm

ያገር ሰው ስሜን እኮ ተነተንከው ነው የሚባለው:: ሀሀ የስሜ ትርጓሜ እንደዚህ ነው ለካ? ጭውቴህ ተመችቶኛል:: አማርኛ አስተማሪዎችማ ፈን ነበሩ:: እኔ የማልረሳው አንድ ግርማ የቢባል አማርኛ ቲቸር ነበረን ሀይስኩል ስንማር:: የሚያስቀው ፓርት ያው ሰውዬ አራተኛ ክፍል እያለን እርሻ ያስተምረን ነበር:: ጎመን: ጽድ: ካሮት:....ኧረ ምን ያላስተከለን ነገር ነበር:: እንዴት አድርጎ በየት አቋራጭ ገብቶ ከእርሻ ወደ አማርኛ እንደተዛወረ ታሜ ገለታ ይወቀው:: ታዲያልሽ እርሻ ሲያስተምረን በዓመቱ መጀመሪያ ላይ የግድ 50 ሉክ ደብተር እንድንገዛ እና በደንብ አድርገን በካኪ እንድንለብደው ያስገድደናል:: ለእርሻ እኮ ከ 16 ሉክ ቢዛ ቢል 32 ሉክ በላይ ማንም የገዛ የለም:: እሱ በቃ የመጬ አሪፍ አይደል ያንን ደብተር ስማቹን ብቻ ጻፉበት ከዛ ሌላ ምንም ነገር ቢጻፍበት እርሻን ትወድቃላቹ ስላለን እናም በቃ ተስማምተን ያቺን የእርርሻ ደብተር ተንከባከብናት:: ክፍል በመጣን ቁጥር ምንም አያጽፈንም:: ልክ እርሻ ክፍለ ጊዜ ሲሆን ከክፍል ያስወጣን እና ያሳርሰናል:: አትክልቶቹን:: ያንን አትክልት ታዲያ ያው ለመሳለሚያ ቅርብ ነን አላልኳቹም እየወሰደ ይቸበችበዋል ለነጋዴዎቹ:: አባው ሐይለኛ ሰው ነው ስልሽ:: ታዲያ ያቺ እርሻ ደብተር ዓመቱ ሲያልቅ ይታረማል ብሎ ሰበሰበው:: የሚታረመው የሰራነው የቤት ስራ ሳይሆን ደብተሩን በንጽህና መያዝ አለመያዛችን ነው:: :lol: ታዲያ ያንን ደብተር በቃ ወሰዶ አስቀረው:: አልመለሰውም::

አንድ ቀን ታዲያ አንድ ዘመዴ ቤት ተልኬ ወደ 08 ቀበሌ ስሄድልሽ አባው ለካ ሰፈሩ እዚያ ነው:: የዘመዶቼ ጎረቤት ሆኖ አላገኘውም! ካዝኔ ሲነግረኝ አባው የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ቢጤ አለችው በሩ ላይ እና ያንን የእርሻ ደብተራችንን ለካ ምንም ሳያፅፍ በንጽህና አስይዞ አመቱን ሙሉ የሚያቆየው ወድዶ ሱቋ ውስጥ ሊቸበችበው ነው:: እንደ ካዝኔ አባባል ሰውየው በጣም ጥሩ ከመሆኑ የተነሳ መስከረም ላይ ደብተሮቹን በካኪ እየለበደ ነው ለሰፈሩ ሰው የሚቸበችበው:: የሰፈሩ ሰው ደሞ ያው የመለበጃ ላለማውጣት በወረፋ ነው አሉ የሚሸምቱት:: :lol:

ታዲያ ግርምሽ አማርኛ አስተማሪ ሆና ከች ስትትልሽ ሀይስኩል (ኮልፌ) ዘይገርም ብለን ነበር:: ሰውዬው ግን ያው ያቺን የደብረን ለብዱ ታሪክ ይደግማል ብለን ስንጠብቀው የባህሪ ለውጥ አምጥቶ ነው መሰለኝ 4ኛ ክፍል ያላጻፈንን ለማካካስ እስኪመስል ድረስ ቅዳሜ ቅዳሜ ሜካፕ እየጠራ አምስት እና ስድስት ክፍል ኖት ሲያስደቀድቀን ከረመ እልሻለሁ::

አይ ግርምሽ...ያቺ ላዳው ምን ደርሳ ይሆን? (ላዳ ነበረችው ደሞ በንም እንደገዛት ይጣራና ረፖርት ይቀርባል) :lol:

ፒስ
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ጦምኔው » Sat May 12, 2012 6:31 pm

ዳግማዊ እና ጎተራ (R) ሰላም ሰላም ጓዶች:: ጭውቴ እስኪ አመጣጡ:: ይህቺ የፍቅር ቤት ናት እና እንፋቀርባት:: :lol:
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ጌታ » Tue May 15, 2012 6:26 pm

ጦምን ያራዳ ልጅ አሪፍ መደበሪያ ቤት ከፍተሃል:: በዚህ ዘመን እንዲህ ዓይነት ቀሽት ጭውቴ ቤት ዘጋምባው ባመት ሁለቴ ብቅ ሲል ብቻ ነው የሚታየው:: እባካቹ ከዘጌው ጋር አልፎ አልፎ ብቅ እያላቹ ዋርካ ፍቅርን ነፍስ ዝሩባት::
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby -...- » Tue May 15, 2012 6:32 pm

ጌታ wrote:ጦምን ያራዳ ልጅ አሪፍ መደበሪያ ቤት ከፍተሃል:: በዚህ ዘመን እንዲህ ዓይነት ቀሽት ጭውቴ ቤት ዘጋምባው ባመት ሁለቴ ብቅ ሲል ብቻ ነው የሚታየው:: እባካቹ ከዘጌው ጋር አልፎ አልፎ ብቅ እያላቹ ዋርካ ፍቅርን ነፍስ ዝሩባት::


እሺ አዲሳባ እንዴት ነበር ? ስልኪን አነጋግረኸው ብትሄድ ኖሮ ይህኔ የ500 ካሪሜትር መሬት ባለቤት ሆነህ ነበር :: አምጣልኝ ያልኩህን አመጣህልኝ ? ረሳሁት እንዳትለኝና የቀረችህን 3 ጥርሶች እንዳላወልቅልህ !
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Postby recho » Tue May 15, 2012 6:53 pm

ጦምኔው wrote: ሰውዬው ግን ያው ያቺን የደብረንለብዱ ታሪክ ይደግማል ብለን ስንጠብቀው የባህሪ ለውጥ አምጥቶ ነው መሰለኝ
:lol: :lol: :lol: :?: :?: :?: እንዴ :!:

ጌታ :twisted: :evil: :twisted: :evil: :twisted: :roll:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests