ከሀገር ቤት የመጣ ቡሌ ተጠልፎለት የጀበና ቡና በሉባንጃ ጢስ እየታጠንን ተቀምቅሞለት በምቾት እና በምርቃና የተጻፈ:: :D ኤዲት እያደረጉ እንዲያነቡ ይጠየቃሉ::
አይ ቅምቀማ.....ባለፈው ሀገር ቤት ለቫኬሽን ተመርሾለት የአዱገነት አሪፎች (ታናናሽ ብራዘሮችንም ጨምሮ) አይ አሳሳባቸው.....አይ አመጣጠጥ:: የማይጠጡት ነገር ጥይት ብቻ ነው እኮ:: እኔ ትዝ ይለኛል ለመጀመሪያ ጊዜ ቅምቀማ የተጀመረለት ኮልፌ ሀይ ስኩል ሶቶ ከተባለ በኍላ ነው:: ትምሮ ቤታችን አጥር አልነበረውም:: ዙሪያው በር ነው ስልህ:: እና ልክ ጫካውን አልፈህ ስትወጣ ቦዛ ቤቶች አሉ:: እዛ ነው የመጀመሪያውን ቦዛ የቀመከምነው:: እና ከትምሮ እየተፎረፈ አንዳንዴም ለላይብረሪ ብሬክ ይሳብለት ነበር:: ቦዛ ይጠጣለታል ሽልጦ AKA CD በሚጥሚጣ ይጎረስለታል:: በ ዱ ቂቅ ብለህ በእግር ከልኳንዳ እስከ ሰፈር (ኳስ ሜዳ ማዞሪያ) በቸርኬ ያለ ድካም ይገባለታል::
ጠንከር ያለ ቅምቀማ የተጀመረለት ኮሌጅ ነው:: ሳቢውም ከች ሲል በቃ ድራፍት ተጀመረለት:: ከዛ ቢራ (ያው ለዓመት በዓል ወይም ዕቁብ ሲደርሰን) አፎርድ ስናደርገው ቅንዳንዴ ይቸለስበታል:: በዛ ዘመን ቺኮቹን ራሱ ግሪን ሀውስ ወይም አንዱ ካፕል ሀውስ ይዘሀቸው ስትሸበለል ካንተው እኩል ድራፍታቸውን ቀምቅመው እኩን ፏ ብለው ሳቅ በሳቅ ሆነው አንተንም ሀፒ ገጭተውህ "ያሰብኩት ተሳካ...." እየዘፈንክ ወደ ቤት:: አንዳንዶቹ ጸዳ አሉ የሚባሉትም ግፋ ቢል ትንሿን ጉደር በኮካ ምጥጥ አድርገው የብላክ ሌብል ያህል ጡዘው ይመቹካል::
አሁን ልክ ከአሙካ ሄጄለት ከብራዘሮች ካር ስወጣለት አባቱ ይህንን የቅምቀማ ስም እንደ ዘር ማንዘራቸው እስከ ሰባት ቤት ድረስ ይጠሩልሀል:: እኔን ብዙ ያውቃል ብለው ሲጠብቁኝ እኔ ፍሬንዳቹ ፍጥጥ:: ኧረ ፍጥነት:: የመጬ ግርሞ:: ቺኮቹማ በቃ አይቻሉም አባቱ:: ኢንቨስትመንት በለው አንዷ ቺክ ላይ ስፔንድ የምታደርገው:: ማታ እንውጣ ምናምን ብለክ ፕሮፖስ ካደረክ የጸጉር ቤ: የጥፍር መሰሪያ: የሳውና ባዝ: ከነጀለሶቿ ትቀፍልሀለች:: በዛ ላይ ማታ ወይ መኩ ካልያዝክ ወይም ያው ላዳ ይዘህ ካላመጣሀት ምንም እንደማይሰጥህ እርግጠኛ ሁን:: እና ክለብ ይዘሀቸው ስትሄድ አጃቢ አያጡም:: ያንተው ሀላፊነት ናቸው:: እና ይሄ በ 17 የተባዛ ቤንጃሚን ሲከሳ ሲከሳ እያየህ አንተም አብረህ ትከሳለህ :lol: ወዲያው ለሶሶት አንድ ኪሎ ቁርጥ ከግማሽ የፍየል ጥብስ ጋር ጥጥት አድርገው በላዩ ላይ አምቦ ውሀ በኮካ ደፍተውበት ቁልጭ ቁልጭ ይሉብሀል:: አንተ ኮይኑን ትመታውና ኦቨር መውጣቱን ልትሰርዘው ስታስብ ብድግ ብለው መንገድ ይጀምራሉ::
ቅምቀማ ቤት ገብተውልህ በቃ ሰምተህ የማታውቀውን ጡጢ ስም ጠርተው ይጦዙና አባው ፈጤ ብለህ እያየካቸው ተበታትነው አንተ ያንተዋን ብቻ ይዘህ ለማታውቃቸው ጎረምሶች የቀሩትን ቺኮች አሟሙቀህ አስረክበህ ትሸበለላለህ:: አሪፍ ሆነህ ካልተገኘህማ እንደ ገልብጤ ከፈዘዝክ ሁልሉም እያየካቸው አንድ በአንድ እየቀነሱ ልክ እንደ አስር አረንጓዴ ጠርሙሶች መዝሙር ዜሮ ይቀራል ብለህ ቤትህ ገብተህ አንድ ለአምስት ታስለቅሳለህ :lol:
አቦ አስረዘምኩት መሰለኝ ..የሆነ የዳግማዊን ፖስት አስመሰልኩት.. :lol: ሪቾ መቼም እንደማታነው የታወቀ ነው....
ፒስ