ሚስትዬዋ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ለማ12 » Fri Dec 21, 2012 2:54 pm

ወዳጀ ወርቅ የማይወጣ ነገር ወግብህን በቁፋሮ ባትገድል የሚሻልህ ይመስለኛል:

ይልቁንስ ሽቀላህን አጠናክረህ ዘመዶችህን ለመርዳት ብትሞክርስ?ከርታታው88 wrote:ጊዜ ጠፋ እባካችሁ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby Gosa » Fri Dec 21, 2012 3:01 pm

ከርታታው88 wrote:ጊዜ ጠፋ እባካችሁ


ወይ ከርታታው! አንከራተትከን እንጂ ምኑን ተንከራተትክ አንተ:: ደግሞ የማይሆን ቦታ ላይ ማቆም ትወዳለህ :lol:
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ከርታታው88 » Fri Dec 21, 2012 7:22 pm

መሀላችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ያስቀመጥኩትን የቢራ ጣሳዬን እየተመለከተች "ቢራ በጣም ትወዳለህ አይደል?" ብላ ፈገግታ አላብሳ ጥያቄዋን ወረወረች:: እኔም ቀበል አደርጉና አይ በጣምም ባይሆን እወዳለሁ: ሌላ ምን መደበርያ አለን ብለሽ ነው ለእኛ ለወንደላጤዎች:: "ወንደላጤዎች ደሞ መደበር ታውቃላችሁ እንዴ በፈለጋችሁበት ጊዜ የፈለጋችሁትን ማድረግ የምትችሉ የባልና ሚስት መተዳደርያ ደምብ የማይመለከታችሁ ተቆጣጣሪ የሌላችሁ....ይህን ነጻነት ይዛችሁ የምን ድብርት ነው የምታወራው" ብላ ስታፋጥጠኝ....አይ ምን መሰለሽ..... ብዬ ለመመለስ ስሞክር አቁዋረጠቺኝና "don't miss understand me በወንደ ላጤነት ቅር... ሚስት አታግባ ማለቴ አይደለም: የsingle ህይወት የexcitement ህይወት ነው ማለቴ ነው:: እኔም ቀበል አድርጌ ልክ ነሽ ግን excitementም ሆነ ሌላው ሌላው ሁሉ ሄዶ ሄዶ ሁሉም እድሜ ይወስነዋል....ልልሽ የፈለኩት ብዬ ለማብራራት ስሞክር አሁንም ቀበል አደረገቺና "ገብቶኛል ልትለኝ የፈለከው:ሚስት በወቅቱ ካልተገባ አፈር አላባሽ እንጂ ውሀ አጣጪ አትሆንም.....ማለትህ ነው አይደል"" ስትል በአባባሉዋ ከት ብዬ ስስቅ....."አየህ እንኩዋን የተናግርክውን ያስብክውን ማወቅ ጀምሬያለሁ" አልቺና እሱዋም እንደ እኔው ሳቁን ተያያዘቺው::
ሳቁ በረድ ሲል...." እስቲ አንድ ነገር ልጠይቅህ.....ለትዳር የምታስባት እስካሁን የለቺህም እንዴ?" የፈራሁት ጥያቄ ነበር:: ጥያቄውን ለመመለስ ጣራ ጣራ ሳይ "ለነገሩ ብትኖርህ ኖሮ ዛሬ ታስተዋውቀኝ ነበር.....ተሳሳትኩ እንዴ? ብላ እራስዋ መለስቺውና ገላገለቺኝ:: ኣረ ምንም አልተሳሳትሺም ልክ ነሽ:: አሁንም አያያዘቺና....."ጥሩ ቁመና አለህ የተረጋጋና ጥሩ ሥራ አለህ:እድሜህም ወጣት ባትባልም ጀማሪ ጎልማሳ ነህ ...ታድያ በሞላ ኮረዳ ምንድ ነው ችግሩ....? ቢራዬን አንስቼ ጎንጭት አልኩና......ምን መሰለሽ ችግሩ ፈላጊና ተፈላጊ አለመገናኘት ነው......አንድ ቀን የልኬን እንደማገኝ ተስፋ አደርጋለሁ..... "በል በል ጨቀጨቁህ አይደል.....ተነስ ምሳችንን እናዘጋጅ" ብላ ልክ እነሚያውቀው ሰው ወደ ኪቺኔ አመራች:: መቼም ስም አይከለከልምና ኪቺን ለበላት እንጂ ነገርዬዋ ሌላ ስም የሚያስፈልጋት ነች:: ከመጥበቡዋ የተንሳ ሁለት ሰው ሳይነካካ መቆም የሚያስችል ቦታ የላትም::
"በል ምንድ ነው የምትፈልገው ምን እንስራ......" ፈጠን አልኩና እረ ሁሉም ተዘጋጅቱዋል ማሞቅ ብቻ ነው....ስላት እንደመገረም ብላ አይን አይኔን ትኩር ብላ እያየች "እኮ ምን ምን ሰርተሀል?" አለቺ....ቆይ አንዴ አሳልፊኝ አልኩና ፍሪጁን ከፍቼ የተሰራውን የስፓጌቲ ሶስና ለጥብስ ያዘጋጀሁትን ሥጋ አውጥቼ አሳየሁዋት:: ትከሻዬን ያዝ አደረገቺና አሁን አይኑዋ አይኔ ላይ እንዳለ ..."ይህን ነው ሁሉም ተዘጋጅቶዋል የምትለው...." ብላ ቀልዳዊ ትችቱዋን በፈገግታ ጣል አደረገቺና ወደ ነበርንበት ክፍል ራመድ ብላ ከላይ ለባስው የነበረውን ሹራብ መሳይ ሸሚዝ አወለቀቺና ከቦርሱዋ ውስጥ አንድ ሻሽ የመሰለ ባለ ቀለም ጨርቅ አውጥታ ጸጉርዋን ወደላይ ሰብሰብ አድርጋ ባወጣቺው ሻሽ ሸፍና ተመልሳ ኪቺን መጣች::
ይቀጥላል
ከርታታው88
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Tue Jan 10, 2006 7:43 pm

Postby የአውራጃው_ሌባ » Sun Dec 23, 2012 9:26 am

ቅቅቅቅ በእንዲህ ዐይነት ጌም እኔም ነበርኩበት በመጨረሻ እህቴን አግብተህ ከኢትዮጵያ አምጣልኝ ልትል ነው አልፉ :roll:
የአውራጃው_ሌባ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 457
Joined: Sat Feb 19, 2005 7:30 am
Location: united states

Postby መስለ መላጣው » Thu Dec 27, 2012 6:23 am

አንዲት ሽፋፋ ጎጃሜ በዳሁ ለማለት ነው ይህ ሁላ ትረካ :lol: :lol: ልክ እኮ የጦር ሜዳ ውሎ አደረከው ሴት አውል
መስለ መላጣው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Wed Jul 28, 2010 10:42 pm

ከርታታው

Postby ናሳ » Fri Dec 28, 2012 11:46 pm

ከርታታው አቦ አንከራትትህ ገደልከን እኮ
ወይ ጨርሰው ወይ ተወው.
የታሪኩ መጨረሻ እንደነ ግምት
1: አልጋላይ እንውጣ
2: ልዳርህ most probably to her family member[/code]
ናሳ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Fri Dec 28, 2012 11:28 pm
Location: Toronto

Postby ለማ12 » Mon Jan 27, 2014 4:01 pm

እረ በሳቅ ፈነዳሁ:
ምን አደርክ ወዳጄ?
https://www.youtube.com/watch?v=iWWf3lc_UpI
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Previous

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests