ጓዶች እንኳን ለመስከረም 2 የአብዬት በአል አደረሰን

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ጓዶች እንኳን ለመስከረም 2 የአብዬት በአል አደረሰን

Postby ገልብጤ » Tue Sep 11, 2012 11:18 pm

ውቃው ስንተኛው የአብዬት በአል ነው ግን :?:

ጓደ መንግስቱ ሀይለማሪያም የኢሰፓ ማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የኢፌድሪ ጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዉቃው » Tue Sep 11, 2012 11:47 pm

ጓድ ገልብጤ

እንኳን ደረስን !
አብዮቱ ካስቀመጠውን ማስረጃዎች መካከል ለ39ኛ ጊዜ በድምቀት የሚከበረውን በዓል "ከየካቲት 1966 ጀምሮ የተፈጸሙ ክንውኖች " ከሚለው ሰነድ ላይ አለፍ አለፍ እያልኩ ለማቅረብ እገደዳለሁ ::

የካቲት 20...
በፊውዳል አቋም የተገነባው የአክሊሉ ሀብተወልድ ካቢኔ በህዝቡ የንቅናቄ ግፊት ወደቀ ::

ሐምሌ 1 ....
የጦር ኃይሎች አስተባባሪ ኮሚቴ 13 ነጥቦችን የያዘ የ"ኢትዮጵያ ትቅደም"ን ዓላማዎችን ገለጠ ::

ነሀሴ 16
የቤት ኪራይ እንዳይጨምር ውሳኔ ተሰጠ ::

መስከረም 1 1967
በበጎ አድራጎት ስር የነበሩት ድረጀቶች በመንግስት ቁጥጥር ሰር ዋሉ :: የጦር ሓይሎች ደርግ በእንግሊዛዊው ጆናታን ድምብልቢ የተነሳውን የወሎን የረሀብ እልቂት በቴልቪዥን ንጉሡና ህዝቡ እንዲመለከተው ጠየቀ ::

መስከረም 2 1967
ኃይለስላሴ ከስልጣን ወረዱ :: የንጉሡን ፈላጭ ቆራጭነት ብቻ አጠንክሮ የኖረው የ1948 ህገ መንግስት ታገደ :: በፊውዳልና በጉልተኞች መደበ የተመሰረተው ፓርላማ ተዘጋ :: የአዲሲቱ ኢትዮጵያ ይወጭ መመሪያ ወጣ ::

መስከረም 5
ደርጉ ርዕሰ ብሄር ሆነ :: የሊቀመንበሩ ስልጣንና ተግባር ተገለጸ ::

መስከረም 21
የቀንጦት መኪናዎች ወደሀገር ወስጥ እንዳይገቡ ተከለከሉ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby recho » Wed Sep 12, 2012 3:49 am

ውቄክስ ቅቅቅቅቅቅ ከምር ዩ አር ማይ ሂሮ ማሪያምን !!!!! የፖለቲካ ትምርትን ሽምድድድ ያረከው ለፈተና ብቻ አልነበረም እንደዚህ እንደገልብጤ ... :lol: :lol: :lol: :lol: ቆይ ግን ደርግ ራሱ ምን ማለት ነው ? :lol:

ከጙዋድ መንግስቱ አይለማሪያም ቆራጥ አመራር ጋር ወደፊት ! መልካም የአቢዩት በአል ! :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ገልብጤ » Wed Sep 12, 2012 1:59 pm

ጙዋ


ጓዶች ..እዩዋቸው እነዚህ የአድሀሪ ቅጥረኞች አማርኛችንን ሲያበላሹ ..ጓ..ን..ጙዋብሎ የሚጽፍ የውስጥ አድሀሪ ነው ...ነው..
ደርግ ራሱ ምን ማለት ነው


አያቹ እነዚህ አድሀሪወች ደርግ ማለት እንኳን በቅጡ ያማያውቁ
..ደብድብ

..ርገጥ

..ግዛ

ይህ ማለት ሆኖ ሳለ እነዚህ የአድሀሪ ቅሪቶች ስለደርግ ማወቅ ይፈልጋሉ

ስላዳመጣቹኝ በኔ እና ባብዮቱ ስም አመስግናለሁ
ኢትዮጵያ ትቅደም
አድሀሪ ይወድማል
የኢሰፓአኮ ተልእኮ ይሳካል
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዉቃው » Wed Sep 12, 2012 9:00 pm

ጓድ ሪቾ

ደርግ ማለት የተመካካሪዎች ስብስብ ....መማክርት ....ማለት ነው :: ልብ ብለሽ እንደሆነ መስከረም 5 1967 ..ንጉሡን ተክቶ ርዕሰ-ብሄር የሆነው ደርጉ ነው :: ውሳኔዎች የሚስጡት በጋራ ነው ...እጅ በማውጣት ! ልዑል ራስ አስራተ ካሳ ይገደሉ ..እጅ ይወጣል ..ይገደሉ ነው :: ያው በኋላ አብዮት ልጆቿን እንክት ቅርጥፍ ቅርጥፍጥፍ አርጋ በልታ ጓድ ሊቀመንበሩ በብቸኝነት ብቅ እስኪሉ :: ኢሀዲግም እንዲሁ ነው :: ብዙው ነገር በምክር ቤቱ ይወሰናል :: ለዚህም ነው ፋጡማ ሞተች... ከበደ ሞተ... የተባለው :: የመጀመሪያው ደርግ በዘር ማጥፋት የተከሰሰው ..ኮሌክቲቭ ሊደር ሺፕ አሰራሩ ስለነበረና ሁሉንም ስላስጠየቀ ነው ...ተብሏል ::

በዓሉ አሁንም በድምቀት እየተከበረ ነው ::

አብዮታዊት ኢትዮጵያ ወይም ሞት !
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Postby ደጉ » Thu Sep 13, 2012 8:43 am

recho wrote:.... ቆይ ግን ደርግ ራሱ ምን ማለት ነው ? :lol:

ሪች ደርግ ማለትንገልብጤ አስቀምጦልሻል... :D ደርግ ደግሞ "ነበልባል" እሚባል ጢር ነበረው...

ነ = ነፍስን
በ= በጠብ መንጃ
ል= ልትገድል
ባ= ባትገድል
ል= ልትገደል
...ምናልባት ውቃው ስለ ነበልባልም ያስረዳሽ ይሆናል ... :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4414
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby recho » Thu Sep 13, 2012 3:03 pm

ዉቃው wrote:ጓድ ሪቾ


አብዮታዊት ኢትዮጵያ ወይም ሞት !
:lol: :lol: :lol: :lol: መንጌ ብያየው ይቺን ለስርአቱ ባለህ ታማኝነት ሽልማት ታገኝ ነበር .. ምን ያረጋል የተጠለለባትንም አገር አተራምሶ አሁን ወደገጠር ደግሞ ተሰዶዋል አሉ .. ይሄስ ምን ያክል እውነት ነው ? :lol: :lol:

ደጉ :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ዉቃው » Tue Oct 09, 2012 9:49 pm

ጓዶች

ተዋርካ ለመጥፋት ባላስብም በብዙ የግል ጉዳዮች መደራረብ የተነሳ መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ ::

በፌስቡክ ያላችሁ ጓዶችን ከኔ ሳጥን ጠራርጎ ያስወጣው የጠፋው ስልኬ አዲስ ባለቤት መሆኑን እንድታውቁት ይሁን ::

አብዮቱ በትንንሽ ቀልባሾች እንደማይሰናከል በዚህ አጋጣሚ አረጋግጣለሁ :: ፒስ !
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests