እንኳን አደረሳችሁ መባባል ቀረ?

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

እንኳን አደረሳችሁ መባባል ቀረ?

Postby ሙዝ1 » Wed Sep 26, 2012 8:18 am

ሄይ ነገደ ዋርካዊያን ይላል ተድልሽ ....
አማን ናችሁ? ምንድን ነዉ ነገሩ? ድሮ ድሮ ዋርካ አይደለም ለእንቁጣጣሽና ለመስቀል .... ለሚስቶች ቀን ... ለአለቆች ቀን ምናምን እንኳን አደረሳችሁ እንባባል ነበር? ምን ነዉ መድረሱ ሁሉ መድረስ አይደለም ያላችሁ ይመስላል ... የሆነዉ ይሁን ምን ይደረጋል ... ያዉ እኔም እንደወጉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ የማስታዉሳችሁ የጥንቶቹ .... ...
ሪችዬ
ዋናዉ
ዉቃዉ
ሀሪከን
ማህደረ
ሞኒካ
ፉፊ
እድላዊት
ጦጣዉ
ቆንጅቶች (የዋርካዋም የእስራኤሏም)
ደጉ
ጌታ
ፓኑ አባ ፈርዳ
ሽማግሌዉ
ትህትና2
ትትና
ስዋቭ
ናደዉ ጣሰዉ
ብሩክይርጋ
ቤቲ
ሚሚ
ዲያና
.......... ........... .............
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሾተል » Wed Sep 26, 2012 10:52 am

በክብርነታችን ሆነን ስማችን ባይጠቀስና ከድሮዎቹ አባላቶች አንዱ እንደነበርን ይቀራል ብለን የማንጠረጥረው ጉዳይ ቢሆንም የጥንቱ ሙዝ እንኩዋን አብሮ ለብርሀነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሰን እላለሁ::

ምን ይደረግ ተረሳን::ለከብቶቻችን ስንል ከተኛን ብዙ አመት ሆኖናል::አጥንታችንን የከሰከስነው ደማችንን ያፈሰስነው ያ ሁሉ የሞትንለት ከብቶችን የማገድ ተጋድሎ በነ ሙዝ ተረሳ......

ይሁን እስቲ.....ቅቅቅቅቅቅቅቅ

ዋው...የዛሬ አመት ኢትዮዽያ ነበርን.....በቃ አንዲትም ሳትቀር የቀረጽናትን ቪድዮ በትዝታ ወዳገራችን ይወስደን ዘንድ እሱን እንመልከት::

መልካም የመስቀል በአል

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ሙዝ1 » Wed Sep 26, 2012 12:04 pm

ሾተል wrote:ምን ይደረግ ተረሳን::ለከብቶቻችን ስንል ከተኛን ብዙ አመት ሆኖናል::አጥንታችንን የከሰከስነው ደማችንን ያፈሰስነው ያ ሁሉ የሞትንለት ከብቶችን የማገድ ተጋድሎ በነ ሙዝ ተረሳ......

ምን ይደረግ ተረሳህ :lol: ቂቂቂ ... ያዉ ከከብቶችህ ጋ ዋርካ ፖለቲካ አካባቢ መመላለስ ከጀመርክ በሗላ የዋርካ ፍቅር አባልነትህን ተነጥቀሀል ... ያቋቋምኩትን ምናምን ብሎ ነገር የለም ,,,, ተባራሀል .... ቢህንም ቢሆንም .... እነዛ አሪፍ የዋርካ ፍቅርና ቻት ሩም ትዝታዎቻችን ሁሌም ጎላ ብለዉ አሉ ... እነ ዝክረ ወሲብ .... :wink:

ዋው...የዛሬ አመት ኢትዮዽያ ነበርን.....በቃ አንዲትም ሳትቀር የቀረጽናትን ቪድዮ በትዝታ ወዳገራችን ይወስደን ዘንድ እሱን እንመልከት::

በጉጉት እየጠበቅን ነዉ ... ምናልባትም እኔንም ቀርጸኸኝ ይሆናል :lol: ቂቂቂ ... ለነገሩ አንተ በፓስፖርትህ ቅድሚያ ተሰጥቶህ ወደ መካከል ሄደህ ይሆናል ... እኔ ከህዝቡ ጋ እየተጋፋሁ በቅርብ ርቀት ለማየትም ስንጠራራ ነበር አይደለም ለመቅረጽ :wink:

መልካም የመስቀል በአል

ሾተል ነን

መልካም በዐል ላንተም .... ክብርነትዎን ባለማስፈራችን ይቅርታ እንጠይቃለን :lol:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሾተል » Wed Sep 26, 2012 1:00 pm

ሙዝነት ምን ሆነ መሰለኽ?ባለፈው ሀምሌ መጨረሻ አካባቢ ሮም ውስጥ አመታዊ የኢትዮዽያ ስፖርት ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የአበሻ ፌስቲቫል ነበር::መቼም በየሄድኩባቸውና በስደት በኖርኩባቸው አገራት የሆነ የሙከራ አሻራ ጥዬ ቦታ በመቀየሬና እዚህም የቀዘቀዝኩበት አገር ያው በማደርጋቸው ሙከራዎች ሚጢጢ ስም ቢኖረኝም በአበሻው ዘንድ ደግሞ በዚህ ለከት በሌለው የእጅ አፌ በምለቀልቀው የማያውቀኝና ያላነበበኝ አበሻ ቢኖር ባየሁዋቸው ነገሮች ጥቂት ነው::

እና ይኽ በእንዲህ እንዳለ ሮም ለስፖርት ፌስቲቫሉ ሄጄ ነበርና በቃ አብላጫው በፎቶ ያውቀኝ ስለነበር ሳልፍ የሚጠቃቀሰውን እንተወውና የሚወደኝ የሚጠላኝ የሚያደንቀኝ የሚረግመኝን ሁሉ በፍቅር አግኝቼያቸው እኔ ባላውቃቸውም በነሱ ግፊት አጠገቤ መጥተው ስማቸውን ሳይነግሩኝ (የነገሩኝም አሉ ) እጅ ለእጅ ተጨባብጠን ስለ ሳይበር ዋርካና ስለፓልቶክ ወክ እያደረግንም ቁጭ ብለንም እንዲሁም ቆመን ያወጋንበት ጊዘ ነበር::የሚያደንቁኝ አድናቆታቸውን በአካል የለገሱኝ.....የሚጠልኝ ደግሞ ከማደርጋቸው ድርጊቶች እንድቆጠብ በፍቅር የመከሩኝ.....እንዲሁም ይኼ ያምርብሀል ይኼንን ተወው ያሉኝ ብዙ ቀናዎችን ያገኘሁበትና የተዋወቅኩበት ጊዜ ነበር::

ታድያ የገረመኝ ከአድናቂዎቼና የሚጠሉኝ መሀል ሁለት ነገሮች ይዞ የቀረበኝ አንድ እዚሁ እኔ ከምኖርበት አገር ጎረቤት የሚኖር ልጅ ያለኝን አልረሳም::

"ሾተል ከሚያደንቁምህ እንዲሁም ከሚጠሉህም መሀል አንዱ ነኝ::ጽሁፎችኽና ግልጽነትህ ያስደስተኛል::ብዙም ከጽሁፎችኽ ተምሬያለሁ.....ነገር ግን ምናለ እነዚህ ፖለቲከኞችን ከመጨፍጨፍ ብትታደግ?ባንተ ጽሁፍ ስንቶቹ እየተለወጡ እንደሄዱ ታውቃለኽ?ምንም የምትጽፈው ነገር ጥሩና እውነት ያለው ቢሆንም በቃ ፖለቲከኖችን አትጨፍጭፋቸው::በምንም ይሁን በምን ይኼ የወያኔ መንግስት መውረድ አለበት::ምንም ተቃዋሚ የሚባሉት በስህተት የተገነቡ ቢሆንም ይኼንን መንግስት መጣል ስላለብን እነሱን ለቀቅ አድርገኽ ለምን ስለወያኔ መጥፎነት አትጽፍም?......" ወዘተ ያለኝን ነገር እግዚአብሄርን ነው የምልህ አልረሳውም::

ታድያ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ካለው ተቃዋሚ......አባይ ሊገነባ ነው ሲባል አይገነባም ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ለሚወጣ ከብት ሁላ.....ድርጅታችን የፍትህ የአንድነት ነው ብለው ሲያበቁ የትግራይን ህዝብ ሲሰድቡ ለሚውሉ ከብቶች......የግልገል ግቤ ግንባታ ላይ የሆነች 15 ሜትር ታክል ቦታ ላይ አደጋ አጋጧት ስትደረመስ እልልልልል የሚል ከብት የቁርጥ ቀን ጅል.......ውሸታምነታችን ብታውቁም እኛ ስለምናውቅላችሁ አንጎላችሁን ስቱንና እኝ እያሰብን ገንዘባችሁን እያለብን ቀፈታችንን እንሙላ ለሚሉ አራሙቻዎች ወዘተ ተረፈ እንዴው እውነት አገሬን የሚወድ ከሆነ እያየሁ ዝም ልበል?

ለዚህ ነው ከምወደው ስነጽሁፍ,ዋርካ አምድን ትቼ ይኼንን ቢታጠብ የማይጠራ ከብት ሽንፍላን ሁላ ጥቆማ ልጠቁመው ብዬ በዛው ፖለቲካ ሩም ገብቼ የእግር እሳት ሆኜባቸው ያለሁት::
እውነት ምንም ጊዜ እውነት ስለሆነ ያንን ያየነውን ደግሞ ካልመሰከርንና ከብቶች ከታገዱበት እያመለጡ ሲወጡ መንገዱን ካላሳዩዋቸው ምኑን አገር ወዳድነት ይኖራል?

ለዚህ ነው ዋርካ ፍቅርንና ስነጽሁፍን ትቼ ከበሰለና በጥበብ ከተሞላ እንዲሁም ቀልድና ብዙ የሚያዝናኑ ነገሮች ካሉበት አምድ ለጊዜው እራሴን አግልዬ እዛ ከምድረ ---- ጋር የምውለውና መቼም ወደ ዋርካ ፍቅር ተመልሼ ዝክረ ወሲብ ሩም የጀመርኩዋቸውን የብድ ዳያሪዎቼን እጨርሳለሁ::

የዛኔ የድሮ ፍሬንዴ እንዳንተ ያሉትም አትረሱኝም::

ሳናስበው ዋርካ ፖለቲካ ሆነን ከብት አጋጅ እረኛ ሆነን::እድገት በፍጥነት ይሏል እንደዚህ ነው::

በል የሆነች ቀጠሮ ቢጤ አለችኝ::ወደዛች ልሂድ::

በነገራችን ላይ ባለፈው አመት ዳመራን ያሳለፍኩት አዲስ አበባ ሳይሆን አዋሳ ነው::ባይገርምህ ከአዲሱ አመት ጀምሮ እስከፋሲጋ ድረስ እንዲሁም የግንቦት ልደታን የገጠሩን አከባበር ሳይቀር በቪድዮ ቀርጬ ይዣለሁ::ሲመቸኝ አገር ለናፈቀው ዩ ትዩብ ላይ እለጥፍለታለሁ::

የጥምቀት በአልንማ የለሊቱን ማህሌት ሳይቀር ነው እንቅልፍ በአይኔ ሳላይ ሙሉውን ስቀርጽ የነበረው::አቤት አሁን ሳየውማ እንዴት ደስ ይለኛል መሰለኽ::ከባህሎቼ አንዱ በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል::ወረቡ....የቅኔው ዘረፋ....ማህሌት አቁዋቁዋሙ.....እረ ስንቱ?

አሁንም በድጋሚ መልካም የመስቀል በአል ላንተ ለወንድሜም ለመላው የዋርካ ተሳታፊዎችም ይሁን::

ለክብርነታችንም ይሁን::

አሜን

ሾተል ነን......... ወይኔ አረፈድን...ቻው ቻው
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ቂቅ » Wed Sep 26, 2012 1:44 pm

ሾተል ያገር ሰው እውነትም ሞኝ ነክ :lol: ፈርስት ራስክን እንደ ታዋቂ ጸሀፊ መቁጠርህ ሰከንድ ከኔ የሚማር ይኖራል ብለህ ማስብክ :lol: ቃላትን መደርደር ለመለስ መዘመር መብትህ ቢሆንም ነጥብህ ግን አንኳርነት የለውም ብሮ :roll: ዋርካ ውስጥ አስተማሪ የሚባሉት በጣም ጥቂት ናቸው:: ከሀይማኖትና ታሪክ አጠቃላይ ኢትዮጵያን ሰፋ አድርጎ ከማዬት በዕውቀት የታገዘ ጽሁፍ ጽፎ ያነበብሁት እናመስግንሀለን የተባለውን ሲሆን ፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮችን ደግሞ ናፖሊዮን የተባለው (አንትሮፖሎጂስት ይመስለኛል) ከወያኔዎች ደግሞ ተቃውሞውን ወያኔነቱን ቢያንስ እጂግ በጣም በሚያስጠላ መልኩ ባልሆነ መንገድ የሚጽፍ ስልኪ ናቸው:: ሐየትም ወያኔነትን ውስጡ ቀርቅሮ (መሀል ላይ ያለ ቢመስልም) ስድብ ያበዛል ሀይማኖትንና ኦርቶዶክስን ይሳደባል እንጂ ትንሽ የሚቀመስ አይጠፋውም:: ሌሎቹም እነ ተድላ ጎበዞች ናቸው:: አንተማ ምን የሚነሳ ነገር አለህ? እውነቴን ነው ሾተል :lol: የዋህ እንደሆንህ አይካድም ግን አገብጋቢ ቢጤ ነህ :lol:

ሾተል wrote:ሙዝነት ምን ሆነ መሰለኽ?ባለፈው ሀምሌ መጨረሻ አካባቢ ሮም ውስጥ አመታዊ የኢትዮዽያ ስፖርት ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የአበሻ ፌስቲቫል ነበር::መቼም በየሄድኩባቸውና በስደት በኖርኩባቸው አገራት የሆነ የሙከራ አሻራ ጥዬ ቦታ በመቀየሬና እዚህም የቀዘቀዝኩበት አገር ያው በማደርጋቸው ሙከራዎች ሚጢጢ ስም ቢኖረኝም በአበሻው ዘንድ ደግሞ በዚህ ለከት በሌለው የእጅ አፌ በምለቀልቀው የማያውቀኝና ያላነበበኝ አበሻ ቢኖር ባየሁዋቸው ነገሮች ጥቂት ነው::

እና ይኽ በእንዲህ እንዳለ ሮም ለስፖርት ፌስቲቫሉ ሄጄ ነበርና በቃ አብላጫው በፎቶ ያውቀኝ ስለነበር ሳልፍ የሚጠቃቀሰውን እንተወውና የሚወደኝ የሚጠላኝ የሚያደንቀኝ የሚረግመኝን ሁሉ በፍቅር አግኝቼያቸው እኔ ባላውቃቸውም በነሱ ግፊት አጠገቤ መጥተው ስማቸውን ሳይነግሩኝ (የነገሩኝም አሉ ) እጅ ለእጅ ተጨባብጠን ስለ ሳይበር ዋርካና ስለፓልቶክ ወክ እያደረግንም ቁጭ ብለንም እንዲሁም ቆመን ያወጋንበት ጊዘ ነበር::የሚያደንቁኝ አድናቆታቸውን በአካል የለገሱኝ.....የሚጠልኝ ደግሞ ከማደርጋቸው ድርጊቶች እንድቆጠብ በፍቅር የመከሩኝ.....እንዲሁም ይኼ ያምርብሀል ይኼንን ተወው ያሉኝ ብዙ ቀናዎችን ያገኘሁበትና የተዋወቅኩበት ጊዜ ነበር::

ታድያ የገረመኝ ከአድናቂዎቼና የሚጠሉኝ መሀል ሁለት ነገሮች ይዞ የቀረበኝ አንድ እዚሁ እኔ ከምኖርበት አገር ጎረቤት የሚኖር ልጅ ያለኝን አልረሳም::

"ሾተል ከሚያደንቁምህ እንዲሁም ከሚጠሉህም መሀል አንዱ ነኝ::ጽሁፎችኽና ግልጽነትህ ያስደስተኛል::ብዙም ከጽሁፎችኽ ተምሬያለሁ.....ነገር ግን ምናለ እነዚህ ፖለቲከኞችን ከመጨፍጨፍ ብትታደግ?ባንተ ጽሁፍ ስንቶቹ እየተለወጡ እንደሄዱ ታውቃለኽ?ምንም የምትጽፈው ነገር ጥሩና እውነት ያለው ቢሆንም በቃ ፖለቲከኖችን አትጨፍጭፋቸው::በምንም ይሁን በምን ይኼ የወያኔ መንግስት መውረድ አለበት::ምንም ተቃዋሚ የሚባሉት በስህተት የተገነቡ ቢሆንም ይኼንን መንግስት መጣል ስላለብን እነሱን ለቀቅ አድርገኽ ለምን ስለወያኔ መጥፎነት አትጽፍም?......" ወዘተ ያለኝን ነገር እግዚአብሄርን ነው የምልህ አልረሳውም::

ታድያ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ ካለው ተቃዋሚ......አባይ ሊገነባ ነው ሲባል አይገነባም ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ለሚወጣ ከብት ሁላ.....ድርጅታችን የፍትህ የአንድነት ነው ብለው ሲያበቁ የትግራይን ህዝብ ሲሰድቡ ለሚውሉ ከብቶች......የግልገል ግቤ ግንባታ ላይ የሆነች 15 ሜትር ታክል ቦታ ላይ አደጋ አጋጧት ስትደረመስ እልልልልል የሚል ከብት የቁርጥ ቀን ጅል.......ውሸታምነታችን ብታውቁም እኛ ስለምናውቅላችሁ አንጎላችሁን ስቱንና እኝ እያሰብን ገንዘባችሁን እያለብን ቀፈታችንን እንሙላ ለሚሉ አራሙቻዎች ወዘተ ተረፈ እንዴው እውነት አገሬን የሚወድ ከሆነ እያየሁ ዝም ልበል?

ለዚህ ነው ከምወደው ስነጽሁፍ,ዋርካ አምድን ትቼ ይኼንን ቢታጠብ የማይጠራ ከብት ሽንፍላን ሁላ ጥቆማ ልጠቁመው ብዬ በዛው ፖለቲካ ሩም ገብቼ የእግር እሳት ሆኜባቸው ያለሁት::
እውነት ምንም ጊዜ እውነት ስለሆነ ያንን ያየነውን ደግሞ ካልመሰከርንና ከብቶች ከታገዱበት እያመለጡ ሲወጡ መንገዱን ካላሳዩዋቸው ምኑን አገር ወዳድነት ይኖራል?

ለዚህ ነው ዋርካ ፍቅርንና ስነጽሁፍን ትቼ ከበሰለና በጥበብ ከተሞላ እንዲሁም ቀልድና ብዙ የሚያዝናኑ ነገሮች ካሉበት አምድ ለጊዜው እራሴን አግልዬ እዛ ከምድረ ---- ጋር የምውለውና መቼም ወደ ዋርካ ፍቅር ተመልሼ ዝክረ ወሲብ ሩም የጀመርኩዋቸውን የብድ ዳያሪዎቼን እጨርሳለሁ::

የዛኔ የድሮ ፍሬንዴ እንዳንተ ያሉትም አትረሱኝም::

ሳናስበው ዋርካ ፖለቲካ ሆነን ከብት አጋጅ እረኛ ሆነን::እድገት በፍጥነት ይሏል እንደዚህ ነው::

በል የሆነች ቀጠሮ ቢጤ አለችኝ::ወደዛች ልሂድ::

በነገራችን ላይ ባለፈው አመት ዳመራን ያሳለፍኩት አዲስ አበባ ሳይሆን አዋሳ ነው::ባይገርምህ ከአዲሱ አመት ጀምሮ እስከፋሲጋ ድረስ እንዲሁም የግንቦት ልደታን የገጠሩን አከባበር ሳይቀር በቪድዮ ቀርጬ ይዣለሁ::ሲመቸኝ አገር ለናፈቀው ዩ ትዩብ ላይ እለጥፍለታለሁ::

የጥምቀት በአልንማ የለሊቱን ማህሌት ሳይቀር ነው እንቅልፍ በአይኔ ሳላይ ሙሉውን ስቀርጽ የነበረው::አቤት አሁን ሳየውማ እንዴት ደስ ይለኛል መሰለኽ::ከባህሎቼ አንዱ በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል::ወረቡ....የቅኔው ዘረፋ....ማህሌት አቁዋቁዋሙ.....እረ ስንቱ?

አሁንም በድጋሚ መልካም የመስቀል በአል ላንተ ለወንድሜም ለመላው የዋርካ ተሳታፊዎችም ይሁን::

ለክብርነታችንም ይሁን::

አሜን

ሾተል ነን......... ወይኔ አረፈድን...ቻው ቻው
ቂቅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 144
Joined: Wed Aug 08, 2012 4:41 pm
Location: Saturn

Postby ሙዝ1 » Wed Sep 26, 2012 3:40 pm

ሀይ ሾተል ....
ዋርካ ፖለቲካ ላይ የምትጽፋቸዉን በአብዛኛዉ አነባለሁ .... ተመሳሳይ አቋም የያዝንባቸዉም ሀሳቦች ቀላል አይደሉም ... ሶሪ ቱ ሰይ ዚስ ..... እንደ ዲያስፖራ የጠላሁት ማህበረሰብ የለም .... ሁሉንም ማቀላቀሉ አስቸጋሪ ቢሆንም የሆነ የሚጎላቸዉ መሰረታዊ ነገር እንዳለ ይሰማኛል ... በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ በማጠላሌ .... የሆነዉ ሁኖ ግፋበት .... ያየኸዉንና እዉነት መስሎ የታየህን አቋም ይዘህ መተጋተግ ነዉ ... ማን ይፈራል ሞት ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Re: እንኳን አደረሳችሁ መባባል ቀረ?

Postby recho » Wed Sep 26, 2012 9:17 pm

ሙዝ1 wrote:ሄይ ነገደ ዋርካዊያን ይላል ተድልሽ ....
አማን ናችሁ? ምንድን ነዉ ነገሩ? ድሮ ድሮ ዋርካ አይደለም ለእንቁጣጣሽና ለመስቀል .... ለሚስቶች ቀን ... ለአለቆች ቀን ምናምን እንኳን አደረሳችሁ እንባባል ነበር? ምን ነዉ መድረሱ ሁሉ መድረስ አይደለም ያላችሁ ይመስላል ... የሆነዉ ይሁን ምን ይደረጋል ... ያዉ እኔም እንደወጉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ የማስታዉሳችሁ የጥንቶቹ .... ...
ሪችዬ
.
ሙዝራስ የኔ ጠማማ ... ከዋርካዊያን በሙሉ አንደኛ ስሜ ስለተጠራ የተሰማኝን ደስታና ኩራት በመጀመሪያ እገልጻለሁ :lol: :lol: እንኩዋን ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳቹ .. እኛ ያው በጥግረራ አሳልፈነው እሁድ ስለህነ ደመራ የምንደምረው እናንተም ጋር እንደዛው መስሎኝ ነው እንጂ በአሉስ አልተረሳም ... ደግሞ ምናባህ ለአዲስ አመት እንኩዋን አደረሳቹ ብዬ የለ እንዴ? :lol: :lol:

መልካም በአል ተመችቶዋቹ ነገ ለምታከብሩት ...በጥግረራ ለምታከብሩት እሁድ እንገናኝ ደመራ ላይ :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ስርርር » Wed Sep 26, 2012 9:37 pm

:D ሪቾ!

ዝርዝሩ ውስጥ አለመጠቀሴ ቢያስተዛዝበንም..... እኔም አለሁ ለማለት ነው:: ዋርካውያትና ዋርካውያን እንክዋን ለመስቀል በአል አደረሳችሁ

ስርርር ትግራዋይ
ስርርር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 733
Joined: Fri Mar 05, 2010 8:00 pm

Postby ገላጋይ-1 » Wed Sep 26, 2012 10:58 pm

ወይ ሙዝዝዝ,

የነ መደደ ስም ሲጠራ እኛ የዱሮዎቹ ተረሳን ... :?
ገላጋይ-1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Fri Aug 25, 2006 5:43 pm

Re: እንኳን አደረሳችሁ መባባል ቀረ?

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Sep 27, 2012 10:41 am

ሙዝ1 wrote:ሄይ ነገደ ዋርካዊያን ይላል ተድልሽ ....
አማን ናችሁ? ምንድን ነዉ ነገሩ? ድሮ ድሮ ዋርካ አይደለም ለእንቁጣጣሽና ለመስቀል .... ለሚስቶች ቀን ... ለአለቆች ቀን ምናምን እንኳን አደረሳችሁ እንባባል ነበር? ምን ነዉ መድረሱ ሁሉ መድረስ አይደለም ያላችሁ ይመስላል ... የሆነዉ ይሁን ምን ይደረጋል ... ያዉ እኔም እንደወጉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ የማስታዉሳችሁ የጥንቶቹ .... ...
ሪችዬ
ዋናዉ
ዉቃዉ
ሀሪከን
ማህደረ
ሞኒካ
ፉፊ
እድላዊት
ጦጣዉ
ቆንጅቶች (የዋርካዋም የእስራኤሏም)
ደጉ
ጌታ
ፓኑ አባ ፈርዳ
ሽማግሌዉ
ትህትና2
ትትና
ስዋቭ
ናደዉ ጣሰዉ
ብሩክይርጋ
ቤቲ
ሚሚ
ዲያና
.......... ........... .............
ጥሬው ሙዝ ...እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ ከነሙሉ ቤተሰብህ በሰላም አደረሰህ!

ሌላው ምንም እንኳን ደረጃዬ ወርዶ በ 13ኛነት ብጠቀስም ብትረ መንግስቱም ከ11 ወደ 0 ወርዷል እያል በመጽናናት አልፈነዋል ...ለማንኛውም እንደ ጉራጌ አገሬ መግባት ባልችልም ወጣ ብዬ ቢራዬን መጋት አያቅተኝምና ..ወደ ቢራ ቤቴ ሹልክ ልበል ::
በድጋሙ መልካም የመስቀል በአል ለሁላችሁም!
ፓኑ አባ ፈርዳ
ፕራግ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ሙዝ1 » Thu Sep 27, 2012 12:50 pm

ሪቼዬል የኔ አስቀያሚ ሁሌም'ኮ አንደኛዬ ነሽ ...
እንዴ ስርር አንተ'ኮ ከሶስተኛዉ የዋርካ ጄነሬሽን መካከል ነህ ...

ገሌክስ ከባድ ጀለስ ... አቤት የያኔዉ የጦርነት ዉሏችን :lol: ምድረ ዋርካዊያንን እናሳብድ ነበር አይደል? ...

ፓኑ አባ ፈርዳ የቢራዉ ባላባት (የጃርሶዉ ባላባት መባልህ ቀረ አይደል?) .... ... ስማኝማ የአቡቹን ቀጣይ ታሪክ በጉጉት እየጠበኩ ነዉ ... የሱ ልጅ ነገር እንዴት አይምሮዬ ዉስጥ እንደተቀረጸ አትጠይቀኝ ... ሁሌም ጎጃም ስሄድ ከእናሮ ጀምሬ እስከ ጎሀጽዮን ድረስ ሽማግሌ ካየሁ እየቆምኩ ስለ አቢቹ የማልጠይቀዉ ሰዉ የለም ... ...

ሁላችሁም በድጋሚ መልካም በዐል ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Re: እንኳን አደረሳችሁ መባባል ቀረ?

Postby ድክሞ » Thu Sep 27, 2012 3:05 pm

ሙዝ1 wrote:ሄይ ነገደ ዋርካዊያን ይላል ተድልሽ ....
አማን ናችሁ? ምንድን ነዉ ነገሩ? ድሮ ድሮ ዋርካ አይደለም ለእንቁጣጣሽና ለመስቀል .... ለሚስቶች ቀን ... ለአለቆች ቀን ምናምን እንኳን አደረሳችሁ እንባባል ነበር? ምን ነዉ መድረሱ ሁሉ መድረስ አይደለም ያላችሁ ይመስላል ... የሆነዉ ይሁን ምን ይደረጋል ... ያዉ እኔም እንደወጉ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ የማስታዉሳችሁ የጥንቶቹ .... ...
ሪችዬ
ዋናዉ
ዉቃዉ
ሀሪከን
ማህደረ
ሞኒካ
ፉፊ
እድላዊት
ጦጣዉ
ቆንጅቶች (የዋርካዋም የእስራኤሏም)
ደጉ
ጌታ
ፓኑ አባ ፈርዳ
ሽማግሌዉ
ትህትና2
ትትና
ስዋቭ
ናደዉ ጣሰዉ
ብሩክይርጋ
ቤቲ
ሚሚ
ዲያና
.......... ........... .............

መልካም በአል ብንረሳም :) :) :) :) :) :)
selam
ድክሞ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 147
Joined: Tue Mar 21, 2006 10:52 am
Location: adis

Re: እንኳን አደረሳችሁ መባባል ቀረ?

Postby recho » Thu Sep 27, 2012 3:19 pm

ድክሞ wrote: መልካም በአል ብንረሳም :) :) :) :) :) :)
ቢረሳ ቢረሳ ድክሞን ይርሳ ? :lol: :lol: :lol:

ሙዝራስ .. :lol: ሚ ኢዝ ኩርቲንግ አሁን ...
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ሓየት11 » Thu Sep 27, 2012 3:42 pm

ቅቅቅ ... ማንን ነው መደዴ ያልከው በናትህ ... ልወቀው እስኪ ጠቀስቀስ አድርጋቸው... ቅቅቅ

ይገርማል እኮ ...

ለእንኳን አደረሳችሁም ... ከሰው ሰው ሲመርጡ ... ዋይ እነዚህ ... ጉዳሞች :lol: ... ደግነቱ ሌላኛው ስሜ ተጠርቷል ... ቅቅቅ

ገላጋይ-1 wrote:ወይ ሙዝዝዝ,

የነ መደደ ስም ሲጠራ እኛ የዱሮዎቹ ተረሳን ... :?
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ሙዝ1 » Thu Sep 27, 2012 4:38 pm

ድኬ ቂቂቂ ... ከምር ግም እኔ እና አንተማ ተለያየን'ኮ .... ለአዲስ አመት እንኳን ተዘጋጋን .... ይሁን እስኪ .... በል ጊዜ ካለህ እኔ በሽ ነኝና ደዉልና ጉልበታችን አጠፍ ... ብርጭቋችንን ጠበቅ አድርገን እናዉጋ ...

ሀየት .... ሀሀሀ ... ከምርህ ነዉ? ምክንያት የለኝም ግን በፍጹም አልጠብቅም በዛ መልኩ ... :lol:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests

cron