ቅዳሜ ከሰዐት ...

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ቅዳሜ ከሰዐት ...

Postby ሙዝ1 » Sat Sep 29, 2012 1:23 pm

ሰላም ወገኖች .... ቀደምቶቹም ... ዘመኔን ተጋሪዎችም ... ተከታዮችም ....
ያኔ እንዲህ እንዳሁኑ ኑሮ በግራ በቀኝ እኔን መካከል ጋር አድርጋ ሳትወጥረኝ ቀኖች ሁሉ ቀን ነበሩ ... ... ቀንነትም ነበራቸዉ ... እሁድን ለኳስ ሜዳ .... ቅዳሜን ለብድ ሜዳ ... ባንልም .... ከሰኞ እከ አርብ በትምህርት ቤት --- ለነገሩ የኔ ዘመን ጥሩ ነበር መሰለኝ የምንማረዉ በፈረቃ ስለነበረ ግምሽ ቀን ነዉ ትምህርት ቤት የማሳልፈዉ ... ቀሪዉ ግማሽ ቀን በጥናት ... ምናምን ያልፋል ... ታዲያ ምንም ነገር ማስታወስ የማልፈልግባት ቀን ብትኖር ቅዳሜ ከሰዐት ነበርች ... .... እንደ አዝማሪዉ ይደገም ቅዳሜ ባልልም .... ለቅዳሜ ከሰዐት በሗላ ግን ከፍተኛ ፍቅር ነበረኝ ...

የኔና የቅዳሜ በፍቅር መዉደቅ ጊዜዉ ሲሰላ በኛ አቆጣጠር በ1980ዎቹ አጋማሽ እድሜዬ በ20ዎቹ ዙሪያ ላይ ነበር ... ... ያ ወቅት ምን ያክል የምኞትና የምኞቱም ምህዳር በጣም ጠባብ ... ... ከስኒከርና ከጂንስ .... ስኒከርና ጂንሱንም ለምንም ሳይሆን ለነ ሪቾ መታያ ... ከዛ በላይ ምን ነበር? ... እርግጥ ነዉ ምን መሆን ትፈልጋላችሁ ተብለን ስንጠየቅ የምንለዉ አናጣም ... ያልነዉን ለመሆን ግን ትዝ የሚለኝ ስትራቴጂክ እቅድ አልነበረንም ... በቃ እንሆናለን .. ... መሆን ለምንፈልገዉ የምከፍለዉ ጊዜ ... ሀሳብ ...ግን ለነ ሪቾ የምከፍለዉን ያክል አልነበረም ... ....

ታዲያ በዛ ዘመን ቅዳሜን የምንወዳት ለምን ይሆን? እስኪ ወጣትነታችሁን ሀረር አካባቢ ያሳለፋችሁ እጃጩን አዉጡ? ... የጥናት ቤት እና ሀረርጌ በወጣትነት በደንብ ይታወቃሉ ... ... ቅዳሜ ካንዱ ጀለሳችን የጥናት ቤት እንከትማለን ... ያንን ጀለሳችንን ስንመርጥ በመልኩ አይደለም ... .... ያ ጀለሳችን ሰፈር ዉስጥ ባለዉ ጉልቤነትም አይደለም ... ያ ጀለሳችን ምርጥ የሰፈር ኳስ ተጨዋች መሆን አይጠበቅበትም ... ብቻ ሱፐርሶኒክም ትሁን አርቴች ቴፕ ልትኖረዉ ይገባል ... ... ካለችዉ ይመረጣል ... ... ሁሉም ከየቤቱ ለዕለቱ የካሴት መዋጮ ያደርጋል ... የሚመለስ ነዉ ታዲያ :wink: ...

ጥናት ቤቷ መሽሞንሞን የምትጀምረዉ ከጠሗቱ 4 ሰዐት አካባቢ ነዉ ... ርግጠኛ ነኝ በዛ ሰዐት ቡና የሚያፈሉ እንስቶች እቤታቸዉ ሁነዉ ... ወይ ገላቸዉን እየተጣጠቡ ነዉ አልያም ድርያቸዉን ከእናቶቻቸዉ የሰረቁትን ሽቶ እየነሰነሱ ነዉ :wink: .. .. .... ፍራሹ ይራገፋል ... ቤቱ ይጠረጋል ... ይወለወላል .... አንሶላ ...ይነጠፋል ... ትራስ ---- ሀሀሀሀ ሀረር የትራስ ሀገር ነች ,,, የቡና ረከቦት ቦታዉን ይይዛል .... የቅዳሜ ዉበቷ ከዛ ይጀምራል .. ሀረር ከተማዉ? አላችሁ? .... ወደ ሀረር አራተኛ አልያም ሸዋበር ይኬዳል ... ከአካባቢዉ ከመጡ የኦሮሞ ማህበረሰቦች ... ሚጬዮ .... አዮ ... ሜቃ ቢቴ .... ሜቃ ጉጉራ ምናምን እየተባባልን ... ... ጫታችንን ሸማምተን እንመለሳለን ... ... የእለቱ ዲጄ ይመረጣል ... ... የእለቱ ሹፌር (ጫት አቀባይ) .... የእለቱ ቡና አፍሊ ... ሽር ጉድ .... ከሰል ለማቀጣጠል .... ሽር ብትን ... ከዚህ ሁሉ ወከባ በሗላ ሁሉም ቦታ ቦታዉ ይዞ ይጀመራል ... ... አንዳንዴ ሙድ ስንይዝ እንመራረቃለን ... ... ይጨጫሳል .... እጣኑ ሰንደሉ ... የቡናዉ ጭስስስስስ ... ህምምም ቡና እኮ የሚጠጣዉ በአይንም ጭምር ነዉ ... ሲፈላ ሲያዩት ደስ ይላል ... ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests