መኖር ማለት ምን ማለት ነው ?

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

መኖር ማለት ምን ማለት ነው ?

Postby ጣሴ » Fri Oct 12, 2012 11:24 pm

አይ መኖር ምን ማለት ነው ?
ጣሴ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Wed Dec 29, 2004 4:44 pm
Location: united states

Postby ክቡራን » Sat Oct 13, 2012 1:06 am

ዛሬ ስቲቨንሰን ዩኒቨርስቲ የ 21ኛው ክፍለ ዘመን ትምህርት በቴክኖሎጂ መደገፍን በተመለከተ የሚሰጥ ኮንፍራንስ ላይ ተካፍዬ ነበር:: አንዱ ተናጋሪ እሱ በሚመራው ፕሮግራም ውስጥ እድሜዋ 80 አመት የሆነች ሴት እንዳለችና ከተማሪዎቹ በሙሉ እሷ በጣም ሻርፕ ተማሪ እንደሆነች ነገረን:: እንደውም ፕሬዜንትሺኑ ውስጥ ሪኮሜንድ ያደረገው አንዱ መጽሀፍ የሷ ሪኮሜንዴሽን እንደሆነ ለተሳታፊዎቹ ገለጸ:: ዘ ሞራል ኦፍ ዚ ስቶሪ ..ምንም ነገር ሌት አይደለም:: ይሄ ለኔ ሌት ነው ነው ብለን ካሰብን ያኔ ህይወት ትርጉሟን ታጣለች:: መኖር ማለት ምንድነው ብለን እንጠይቃለን:: ተስፋ ሲሞት የመኖር ትርጉም አብሮ ይሞታል ነው ባጭሩ:: " ተስፋ የመኖር ማግኔት ነው" ነው ባጭሩ ሲጠቃለል:: ክቡራን ነን ስንሆን ዝም ብለን አይደለም:: እንሁን ብለን እንጂ:: :D :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7943
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Oct 13, 2012 1:26 am

ሠላም ታላቁ ክቡራን

በሀሳብህ በከፊል እስማማለሁ.....የመኖር ትርጉሙ "ተስፋ" የሚባል ነገር ይመስለኛል.....ግን ጣሴ የጠየቀውን በደንብ ካየነው "ተስፋውስ" ምንድን ነው :?: "መኖር ማለት....አንፃራዊ ጥሩ ኑሮ መኖር; ታዋቂ መሆን; ለሰው ልጆች መልካም ስራ መስራት; ትዳር መያዝ; ልጅ መውለድ; ከተቻለ ራስን እንደፈለጉ እያዝናኑ; እያበዱ መኖር......ወዘተ ነውን :?: :?: ወይንስ አሁንም "ተስፋ" የሚለው ነገርን አሻሻሎ በሀይማኖት መልክ "ከሞት በኻላ ህይወት" በሚል ተስፋ መፅናናት ነውን :?: :wink:

በዚህም ሆነ በዛ ትሞታለህ..."አፈር ነህና ወደአፈር ትመለሳለህ" :wink: .......ተስፋው ምን ይፈይዳል :?: ስለዚህ የጣሴ ጥያቄ በድጋሚ ላስምርበትና "መኖር ምን ማለት ነው" :?: :?: :?:

ክቡራን wrote:ዛሬ ስቲቨንሰን ዩኒቨርስቲ የ 21ኛው ክፍለ ዘመን ትምህርት በቴክኖሎጂ መደገፍን በተመለከተ የሚሰጥ ኮንፍራንስ ላይ ተካፍዬ ነበር:: አንዱ ተናጋሪ እሱ በሚመራው ፕሮግራም ውስጥ እድሜዋ 80 አመት የሆነች ሴት እንዳለችና ከተማሪዎቹ በሙሉ እሷ በጣም ሻርፕ ተማሪ እንደሆነች ነገረን:: እንደውም ፕሬዜንትሺኑ ውስጥ ሪኮሜንድ ያደረገው አንዱ መጽሀፍ የሷ ሪኮሜንዴሽን እንደሆነ ለተሳታፊዎቹ ገለጸ:: ዘ ሞራል ኦፍ ዚ ስቶሪ ..ምንም ነገር ሌት አይደለም:: ይሄ ለኔ ሌት ነው ነው ብለን ካሰብን ያኔ ህይወት ትርጉሟን ታጣለች:: መኖር ማለት ምንድነው ብለን እንጠይቃለን:: ተስፋ ሲሞት የመኖር ትርጉም አብሮ ይሞታል ነው ባጭሩ:: " ተስፋ የመኖር ማግኔት ነው" ነው ባጭሩ ሲጠቃለል:: ክቡራን ነን ስንሆን ዝም ብለን አይደለም:: እንሁን ብለን እንጂ:: :D :D
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby እቴጌይት » Sat Oct 13, 2012 3:42 am

ጣሴ
አንድ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በስጋ የተለዩ ሰውዬ የመቃብር ሀውልት ላይ ምን ተብሎ ተጽፎ ነበር መሠለህ:-
'በ35 ዓመታቸው ሞተው በ86 ዓመታቸው ተቀበሩ' የሚል:: ሰውዬው ከ35ዓመት ከሞላቸው በኍላ ዶናት ብትሰጣቸው የሚያዩት መሀል ላይ ያለውን ቀዳዳ እንጂ የሚገመጠውን ዶናት አልነበረም:: ይሄንን ታሪክ ባቀረበው ተናጋሪ ትንታኔ መሠረት መኖር ማለት 'keeping your focus on the donut rather than the hole' ነው:: በከፊል የሚያስኬድ ይመስለኛል::
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Oct 13, 2012 4:42 am

ሠላም እቴጌይት

አሁን አስተያየት ብሰጥሽ እንደ አሜሪካ ምርጫ የሚያስቆጣሽ አይመስለኝም :D ለዚህ ርእስ ሙሉ መልስ አለ ብዬ ስለማልገምት ምንም ቢሆን አስተያተሽን ከመስጠት ወደኻላ አትበዪ

'keeping your focus on the donut rather than the hole' ማለት እንደሚመስለኝ ባለህ ላይ እንጂ በሌለህ ላይ አታተኩር ማለት ነው....ስለዚህ ከመኖር ትርጉም ጋር በከፊልስ ቢሆን ምን ያስኬዳል :?:

ለምሳሌ.....አንዱን ደሀ አምስት ሳንቲም ባይኖርህም ጤነኛ ስለሆንክ እሱ ላይ አተኩር ብትዪው ለደሀው የመኖር ትርጉሙ ምንድን ነው :?: እንዲሁም ለአንዱ ሀብታም መሞትህ ባይቀርም የመኖር ትርጉምህ ባለህ ሀብት ላይ ማተኮር ነው ብትዪው ምን ይጠቅመዋል :?:

ምናልባት ሀሳብሽን ሰፋ ላድርገውና.....የመኖር ትርጉሙ....ትርጉሙ ላይ መጨነቅ ሳይሆን መኖሩ ላይ ነው ማለትም ፈልገሽ ከሆነ.....ሳታስቢው ስለተፈጠርሽ ብቻ መኖር; ከዛም መሞት..አፈር መሆን ምን ትርጉም ይሰጣል :?:

ጥያቄው እኔ እንደገባኝ በጣም ሰፊና በጣም ግሩም ጥያቄ ነው.....ባለሽ ላይ አተኮርሽ አላተኮርሽ;በሌለሽ ላይ አተኮርሽ አላተኮርሽ.....የምታስቢውንና የምታልሚውን ሁሉ አገኘሽ;አላገኘሽ....ዞሮ ዞሮ የመኖር ትርጉሙ ምንድን ነው :?: :?: :?: ኧረ ጎበዝ እንተጋገዝ :lol:

እቴጌይት wrote:ጣሴ
አንድ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በስጋ የተለዩ ሰውዬ የመቃብር ሀውልት ላይ ምን ተብሎ ተጽፎ ነበር መሠለህ:-
'በ35 ዓመታቸው ሞተው በ86 ዓመታቸው ተቀበሩ' የሚል:: ሰውዬው ከ35ዓመት ከሞላቸው በኍላ ዶናት ብትሰጣቸው የሚያዩት መሀል ላይ ያለውን ቀዳዳ እንጂ የሚገመጠውን ዶናት አልነበረም:: ይሄንን ታሪክ ባቀረበው ተናጋሪ ትንታኔ መሠረት መኖር ማለት 'keeping your focus on the donut rather than the hole' ነው:: በከፊል የሚያስኬድ ይመስለኛል::
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby እቴጌይት » Sat Oct 13, 2012 6:52 am

ዳግማዊ
የአሜሪካ ምርጫ ላይማ እንኳን ልቆጣ እንደነገርኩህ የኔታን እና ሁል ጊዜ የሚያስፈግጉኝ ከብዙ የአያቴ ተረቶች አንዱን ስላስታወስከኝ ተዝናንቼ አመሰገንኩህ እንጂ ለምን እቆጣለሁ :?:
ስለሕይወት ትርጉም የጠከስኩት የራሴን ትርጓሜ ባይሆንም የደራሲውን ሀሳብ ግን እንደተለምደው ስተኸዋል :wink:
የሚገመጠውን ዶናት ትቶ ቀዳዳው ላይ ማተኮር ከማግኘት እና ከማጣት ጋር የሚገናኝ አይደልም:: ማለት የፈለገው የሕይወት ትርጉሙ ሕይወትን በምታይበት መነጽር ይወሰናል ነው:: መነጽርህ life is full of opportunities worth living ብሎ የሚያሳይህ ከሆነ የሚገመጠውን እያየህ እየገመጥክ ባይጣፍጥም ቢጣፍጥም እያጣጣምክ ሕይወትህን to the fullest ስትኖር.... መነጽርህ ሕይወት ትርጉም የሌለው ባዶ ሂደት ነው ብሎ የሚያሳይህ ከሆነ ደግሞ የሚገመጠውን ሳይሆን ቀዳዳው ላይ አተኩረህ ስታጣጥምና ሳትበላ ቆመህ ባትቀበርም መቆም መሞት ነውና ትሞታለህ ነው የሚለው:: ይኼ ትንታኔው የሕይወትን ምንነት ሙሉ ለሙሉ ይገልፃል አይገልጽም የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው:: የምርጫው ጉዳይ ሳይገባህ ይሄ ከገባህ ግን የኔታን ተመልሱ እላለሁኝ :lol: :lol:

ደህና ቆይ
እቴጌይት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 656
Joined: Sun Sep 23, 2007 10:38 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Oct 13, 2012 7:30 am

እቴጌይት

ስለምላሹ አመሰግናለሁ...ሆኖም :D

እቴጌይት wrote:ዳግማዊ
የአሜሪካ ምርጫ ላይማ እንኳን ልቆጣ እንደነገርኩህ የኔታን እና ሁል ጊዜ የሚያስፈግጉኝ ከብዙ የአያቴ ተረቶች አንዱን ስላስታወስከኝ ተዝናንቼ አመሰገንኩህ እንጂ ለምን እቆጣለሁ :?:


ጎሽ...ዋናው ጉዳይ የአንቺ መዝናናት ነው :D

ስለሕይወት ትርጉም የጠከስኩት የራሴን ትርጓሜ ባይሆንም የደራሲውን ሀሳብ ግን እንደተለምደው ስተኸዋል :wink:


አባባሉን የፃፈው ደራሲ ማን ይሆን :?: :wink:

የሚገመጠውን ዶናት ትቶ ቀዳዳው ላይ ማተኮር ከማግኘት እና ከማጣት ጋር የሚገናኝ አይደልም::


እሺ....ከምን ጋር እንደሚገናኝ ቀጥዪልኝ

ማለት የፈለገው የሕይወት ትርጉሙ ሕይወትን በምታይበት መነጽር ይወሰናል ነው::


ህይወትን የማይበት መነፅር ምንም ሆነ ምን ዶናት መሀሉ ቀዳዳ ነው :wink: አይመስልሽም :?: :lol: :lol:

መነጽርህ life is full of opportunities worth living ብሎ የሚያሳይህ ከሆነ የሚገመጠውን እያየህ እየገመጥክ ባይጣፍጥም ቢጣፍጥም እያጣጣምክ ሕይወትህን to the fullest ስትኖር....


1. ይሄ "መነፅር' የት ነው የሚገዛው :?: :lol: ከመሬት ተነስተሽ እኮ እውነታውን "የዶናቱን ቀዳዳ" የለም ብለሽ ራስሽን እየሸወድሽ "life is full of opportunities worth living" ማለት እንዴት ይቻላል :?:

2. "......የሚገመጠውን እያየህ እየገመጥክ ባይጣፍጥም ቢጣፍጥም እያጣጣምክ ሕይወትህን to the fullest ስትኖር..."

ሀ. ካላይ እንደነገርሽኝ ከሆነ "የሚገመጠውን ዶናት ትቶ ቀዳዳው ላይ ማተኮር ከማግኘት እና ከማጣት ጋር የሚገናኝ አይደልም::" ብለሻል :wink: ታዲያ ማግኘት ሳይኖር ምኑን ትገምጫለሽ :?: :lol:

ለ. የምገምጠው ካልጣፈጠኝማ ምኑን አጣጣምኩት :?: ጭራሽ የገመጥኩት እየመረረኝ ደግሞ ህይወትን "to the fullest" ስኖር ደግሞ አሰብኩትና እውነትም እቴጌይት ሀይለኛ ፈላስፋ ነች አልኩኝ :lol: :lol: :lol:

መነጽርህ ሕይወት ትርጉም የሌለው ባዶ ሂደት ነው ብሎ የሚያሳይህ ከሆነ ደግሞ የሚገመጠውን ሳይሆን ቀዳዳው ላይ አተኩረህ ስታጣጥምና ሳትበላ ቆመህ ባትቀበርም መቆም መሞት ነውና ትሞታለህ ነው የሚለው::


ታዲያ ምን ለውጥ አለው......ዶናቱ ላይ ያተኮረውም "ጣፈጠውም;አልጣፈጠውም" ገምጦ ሞተ......ዶናቱን ትቶ ቀዳዳው ላይ ያተኮረውም ሞተ :lol: :lol: ......ከዚህ በፊት እንዳልኩት በፈለግሽው መንገድ ተርጉሚውና አተኮርሽም አላተኮርሽም; ገመጥሽም;አልገመጥሽም....እስካለሽ ትኖሪያለሽ.....ስትሞቺ ትሞቻለሽ.......ጥያቄው እኮ መግመጥ;አለመግመጥ ሳይሆን የመግመጥ;ያለመግመጥ ትርጉሙ ምንድን ነው የሚል ይመስለኛል :wink:...ሁሉም ህይወትን በፈለገው መነፅር ይየው; ሁሉም እንደመሰለው ይኑር...አሁን እኮ ጥያቄው...."የመኖር ትርጉሙ ምንድን ነው :?: :?: :?:"

ይኼ ትንታኔው የሕይወትን ምንነት ሙሉ ለሙሉ ይገልፃል አይገልጽም የሚለው ሌላ ጥያቄ ነው::


የእኔም ዋና ጥያቄ ይሄ ነበር........ቢያንስ በተዘዋዋሪ መንገድ ከጣሴ ጥያቄ ጋር እንደማይገናኝ ማመንሽ ጥሩ እርምጃ ነው

የምርጫው ጉዳይ ሳይገባህ ይሄ ከገባህ ግን የኔታን ተመልሱ እላለሁኝ :lol: :lol:

ደህና ቆይ


የኔታ ፈረደባቸው :lol: ......የስንት ጊዜያት ልፋታቸው ውጤት "ከሁለት ያጣ ጎመን" ሆንሽባቸው :lol:

ይመችሽ :!:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ክቡራን » Sat Oct 13, 2012 8:49 am

ሰላም ታላቁ ዳግማዊ ጦፍ ባለው ባንተና በኤቴጌይት መካከል መግባት እንኴን አልፈለኩም ነበር ግን ለኔም ጥያቄ ስለቀረበ የራሴን አስተያየት እነሆ በረከት እልሀለሁ:: :D እቺን ጥያቄ እንደጻፍካት ወደ አራዳው ሰፈር ከመውጣቴ በፊት መልስ ጽፌልህ ነበር:: ግን የነበርኩበት ቦታ ኢንተርኔት ኮኔክሽኑ ጥሩ ስላልነበረ ስልከው ሳይን አውት አደረገኝ:: :evil: ብሊቭ ሚ በመንፈስ ተነጥቄ የጻፍኩት ነበር የመሰለኝ ዋ! ምን ያደርጋል ... እዚህ ላይ እኮ ነው እቺ አለም ፌየር አይደለችም የሚባለው:: :D የዚች አለም ፌየር አለመሆን ደሞ የመኖር ትርጉምን ጥያቄ ያጭራል:: እውነትን የሚፈልግ, ጀስቲስ በዚህ አለም ላይ የለም ብሎ ያመነ ይቺ አለም ፌየርነስ እነደ ጎደላት የተረዳ ሰው ህይወት ወይም ኑሮ ምንድናት ብሎ መጠየቁ አይቀርም:: ምናልባት አሁን የምጽፈው እንደ ቅድሙ ክርቲካል ቲንከር ሆኜ ላይሆን ይችላል :D ይችላል:: አርብ ነው ሁሌም የምዝናናበት ቤት ስሄድ የምወዳቸው ሙዚቀኞች ይኖራሉ ብዬ ስገባ ቀይ ላፕ ቶፕ የያዘ አንድ ጎረምሳ መድረኩ ላይ ተሰይሟል...
አስተናጋጇ ስትመጣ.."ምነው" አልኴት
..."ምኑ "አለችኝ
"አርብ እኮ ነው ሙዚቃ የለም እንዴ ?" አልኮአት::
"ዛሬ የለም በዲጄ ነው" አለችኝ::
"ሙዚቀኞቹስ"....??
እንደማታውቅ ሆነችብኝ:: ገፍቼ ልጠይቃት አልፈለኩም:: ሰሞኑን ቢዝነስ ሞቷል ሚከፈሉት ስለሌላቸው አትምጡ ብለዋቸው ይሆናል ብዬ ገመትኩ:: እና ያን መንገድ ሁሉ ድራይቭ አድርጌ እራት ብቻ በላሁና መኪናዬን አስነስቼ ቀኝ ኌላ ወደ ቤቴ :: ሙዴን አጠፋችው ልጅቷ:!!
የኔን እዚህ ላይ ላቁምና ..እስኪ አንተ ወዳነሳሀው ነጥብ ልመለስ እንቅልፌ ሳይመጣ....
ወንድማችን ጣሴ ጥያቄውን አንተ እንዳፍታታህው አልፋታተውም አልበታተነውም:: አንተ የኑሮን ፊሎሶፊካል ትርጉም ይሆናል ማየት የፈለከው...ጣሴ ደሞ ህይወት ውሉ ጠፍቶበት አሰልቺና ተመሳሳይ ሩቲን ሆኖበት የዛ ጭንቀት የወለድው ጥያቄ ይሆናል ዋርካ ፍቅር ላይ ያመጣው:: :wink: እንግዲህ የምናይበት ኮርነር ወይም አፕሮች መልሱን ይወስነዋል ብዬ አስባለሁ:: ህይወት ተስፋ እያደርክ የምትሸጋገርው መሰላል ነው ኢን ፋክት መሰላሉ ተስፋው ራሱ ነው:: ጣሴ መሰላሉ ወድቆበታል:: ባይሆን እመርጣለሁ:: እኔ ራሴ አንዳንዴ ተስፋ ስቆርጥ ህይወት ምነድነው ኑሮስ ምንድነው ?? የምልበት ሁኔታ አለ:: ይሄ የጣሴ ችግር ብቻ አይደለም:: ሁሉም ሰው ላይ በተለያየ ጊዜ ሊከሰት ይችላል መፍትሄው መወደቅ አንዳለ ሁሉ መነሳት እንዳለ ማስብ ነው:: መፍትሄው ያን የተስፋ መሰላል ተንጠላጥሎ መያዝ ነው:: በነገራችን ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ( ማንኛውም አይንት እምነት ሊሆን ይችላል ) ከሚያምኑት ነገር ጋር ሙጭጭ ቃሉ በቀላሉ ተስፋቸው ከጃቸው አይወድቅም:: ምን ለማለት ፈልጌ መሰለህ ዳግማዊ እቺ አለም ላይ ቡዙ ኢንጀስቶች አሏት:: ቡዙ የተዛባና አን ባላንስድ የሆነ ነገር አለ:: በዚህ ፍትህ አልባ ና ኢንጀስቲስ ዎርልድ ኖረን አንተ አንዳልከው አፈር መጨረሻችን አይሆንም:: ይሄ ራሱ ከኢንጀቲስ የከፋ ሌላ ኢንጀስቲስ ነው:: ከሞት በኌላ ህይወት እxትራፖሌት ያደርጋል:: አውቃለሁ አንተ በዚህ ሀሳብ እንደማትስማማ..ለኔ ግን ህይወት በምድር ላይ አታበቃም የሚል እምነት አለኝ:: ያለተከፈለንን የምንከፈልበት ያላግኘነውን የምናገኝበት ወይም ያለአግባብ የዘረፍነውን የምንመለስበት አብሶሊዩት ሩል ኦፍ ሎው ያለበት ሄቨንሊ ክንግደም አለ ብዬ አምናለሁ:: ""ዩሪፕ ዋት ዩሶው..""የሚልው አባባል ሀይማኖታዊ ብቻ አይደለም ዩነቨራስል ትሩዝም ነው:: እንደውም ዩኑቨርስ የሚመራበት ህግ ነው:: ኦኬ እንደዛ ከሆነ ይሄን ህግ የሚያስፈጸም ኪንግደም አለ ማለት ነው:: ያ ተስፋ ነው. እንግዲ ለኔ የኑሮ ማግኔቴ ነው የምለው :: ያ እምነት መኖሬን እንዳከበረው ቢቻል በመልካም ህሊና እንድኖር የሚያድርገኝ ድሪቭን ፓወር ነው:: አንድ ቀን ይከፈለኛል ወይም ደሞ አንድ ቀን እከፍላለሁ በሚል እምነት ስለማስብ ቢበ መልካም ህሊና እንድኖር ምክንያት ይሆነኛል:: መኖሬ ትርጉሙ ይሄ ነው ብዬ አስባለሁ እንጂ በማየው ኢንጀስቶች የመኖር ትርጉም ምንድነው ብዬ ራሴን ከድልድይ ላይ ወርውሬ አላጠፋውም:: ሁሉም የዘራውን ያጭዳልና :: እንግዲህ ይሄ ተስፋ ነው እኔን የሚያኖረኝ:: ይሄ የምነት ተስፋ ከሌለን ህይወት ትርጉም አልባ ናት:: ምን ያህል % እንደሆነ አላውቅም እንጂ ከሚያምኑ ሰዎች ( it really doesn't matter የየትኛው እምነት ተእከታይ መሆንህ ) ይልቅ የማያምኑ ሰዎች የኑሮ ትርጉሙ ምንድነው በሚል ጥያቄ የሚሰቃዩ ይመስለኛል:: ምክንያቱም በዚች ምድር ላይ ያሉ አንፌይር የሆኑ ነገሮች ራሳቸው ተስፋ ሊያስቆርጡቿውና ሁሉም ነገር ምድር ላይ ያበቃል ብለው ስለሚያምኑ:: ይችላሉ:: ህይወት beyond earth የምትቀጥል ከሆነች ግ ያንን ኢንጀስቲስ የምቌቌምበት ሀይል መልካም ተስፋ እሰንቃለሁ:: መኖር ከባድ ቢሆንም እንዳልከፋ መጽናና ይሆነኛል:: እንደ አመለካከታችንና እምነታችን ነው የኑሮና የህይወት ነገር....... ቡዙ አስቀባጠርከኝ:: መልስ መስጠቴ ሳይሆን የሚሰምኝን ና የገባኝን ነው የሰጡኅህ:: አይ ቲንክ በእቴጌይት ዶናት አናሎጂ የኔን ሀሳብ ማየት ይቻላል ዶናቱ ተስፋ ነው:: በመሀል ያለው ቀዳዳ ደሞ ኢሊዩዥን ነው :: ጣሴ ባዶውን ቀዳዳ ብቻ የሚያይ ከሆነ መኖር ምንድነው ቢል አይፈረድበትም:: የዶናቱን ዙሪያ እንዲያይ እመከራለሁ::ሁላችሁም ሰላም እደሩ:: ለሌላው ጊዜ ባርብ ምድር እነደዚህ አይነት ከባድ ጥያቍ አይጠየቅም ታላቁ ዳግማዊ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7943
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Oct 13, 2012 9:45 am

ሠላም ታላቁ ክቡራን

አንተ እንደጠቀስከው የማንስማማበት ሀሳቦች ቢኖሩም በጣም ደስ የሚል አፃፃፍና ድንቅ መልስ :!:

አንተ የኑሮን ፊሎሶፊካል ትርጉም ይሆናል ማየት የፈለከው...ጣሴ ደሞ ህይወት ውሉ ጠፍቶበት አሰልቺና ተመሳሳይ ሩቲን ሆኖበት የዛ ጭንቀት የወለድው ጥያቄ ይሆናል ዋርካ ፍቅር ላይ ያመጣው::


እዚህ ጋርም በድጋሚ በጣም ትክክል ነህ:!: ምናልባት የጣሴ ጥያቄ አንተ እንዳልከው ከሆነ የአንተ መልስ ትክክል ነው......በሰው ጥያቄ ዘባርቄ ከሆነ አንተንም ጣሴንም ይቅርታ እጠይቃለሁ :D

በመጨረሻም የዘባረቅኩትን የግሌ ጥያቄን (የማንስማማባቸውን ሀሳቦች) ለመድገም ያህል.......ለጊዜው ማረጋገጫ የሌለንን የፈጣሪና "ከሞት በኻላ ህይወት" የሚሉትን ጥሩ "ማፅናኛዎች" ለጊዜው ብንተዋቸው; የህይወት ትርጉሙ ምንድን ነው :?: :?: እስቲ አስበው :lol:

አንዱ ፈላስፋ አለ እንደተባለው......"እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ እንኳን; እግዚአብሔርን መፍጠር ነበረብን" ያለው ለዚህ ይሆን :?: :wink:

የእቴጌይትን ዶናት ካነሳኸው ዘንዳ ደግሞ በሌላ ምሳሌ እንየው.....ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች ነገር ግን ቀዳዳውን ሳይሆን ዶናቱን የሚመለከቱ...በእሷ አገላለፅ "መነጽርህ life is full of opportunities worth living ብሎ የሚያሳይህ ከሆነ የሚገመጠውን እያየህ እየገመጥክ ባይጣፍጥም ቢጣፍጥም እያጣጣምክ ሕይወትህን to the fullest ስትኖር ..." የሚኖሩ......አንድ የሚሊየነር ልጅና አንድ የመናጢ ደሀ ልጅ........የሚሊየነሩ ልጅ የቢሊየነር ልጅ አይደለሁም ብሎ "የዶናቱን ቀዳዳ" ሳያይ :wink: ፊቱ የቀረበለትን የሚሊዬነር ልጅነት ዶናቱን በደንብ የሚገምጥ.....ሁለተኛው ደግሞ የመናጢ ደሀ ልጅነቱን "የዶናቱን ቀዳዳ" ሳያይ; ነገር ግን ፊቱ የቀረበለትን የሊስትሮ ሳጥን ይዞ የሚሊዬነሮች ልጆችን ጫማ እያሳመረ ዶናቱን የሚገምጥ :lol: :lol: ሁለቱም ልጆች የሚያዩት በአንድ አይነት መነፅርና የሚገምጡትም "life is full of opportunities worth living" እያሉ ነው......እና ይህ ነው የመኖር ትርጉም :?: ይበልጥ የሚያስቀው ደግሞ ሁለቱም ደግሞ ይሞታሉ......አሁንም በድጋሚ ለሁለቱም 'የመኖር ትርጉም ምንድን ነው :?:" :lol: :lol:

አክባሪህ
ክቡራን wrote:ሰላም ታላቁ ዳግማዊ ጦፍ ባለው ባንተና በኤቴጌይት መካከል መግባት እንኴን አልፈለኩም ነበር ግን ለኔም ጥያቄ ስለቀረበ የራሴን አስተያየት እነሆ በረከት እልሀለሁ:: :D እቺን ጥያቄ እንደጻፍካት ወደ አራዳው ሰፈር ከመውጣቴ በፊት መልስ ጽፌልህ ነበር:: ግን የነበርኩበት ቦታ ኢንተርኔት ኮኔክሽኑ ጥሩ ስላልነበረ ስልከው ሳይን አውት አደረገኝ:: :evil: ብሊቭ ሚ በመንፈስ ተነጥቄ የጻፍኩት ነበር የመሰለኝ ዋ! ምን ያደርጋል ... እዚህ ላይ እኮ ነው እቺ አለም ፌየር አይደለችም የሚባለው:: :D የዚች አለም ፌየር አለመሆን ደሞ የመኖር ትርጉምን ጥያቄ ያጭራል:: እውነትን የሚፈልግ, ጀስቲስ በዚህ አለም ላይ የለም ብሎ ያመነ ይቺ አለም ፌየርነስ እነደ ጎደላት የተረዳ ሰው ህይወት ወይም ኑሮ ምንድናት ብሎ መጠየቁ አይቀርም:: ምናልባት አሁን የምጽፈው እንደ ቅድሙ ክርቲካል ቲንከር ሆኜ ላይሆን ይችላል :D ይችላል:: አርብ ነው ሁሌም የምዝናናበት ቤት ስሄድ የምወዳቸው ሙዚቀኞች ይኖራሉ ብዬ ስገባ ቀይ ላፕ ቶፕ የያዘ አንድ ጎረምሳ መድረኩ ላይ ተሰይሟል...
አስተናጋጇ ስትመጣ.."ምነው" አልኴት
..."ምኑ "አለችኝ
"አርብ እኮ ነው ሙዚቃ የለም እንዴ ?" አልኮአት::
"ዛሬ የለም በዲጄ ነው" አለችኝ::
"ሙዚቀኞቹስ"....??
እንደማታውቅ ሆነችብኝ:: ገፍቼ ልጠይቃት አልፈለኩም:: ሰሞኑን ቢዝነስ ሞቷል ሚከፈሉት ስለሌላቸው አትምጡ ብለዋቸው ይሆናል ብዬ ገመትኩ:: እና ያን መንገድ ሁሉ ድራይቭ አድርጌ እራት ብቻ በላሁና መኪናዬን አስነስቼ ቀኝ ኌላ ወደ ቤቴ :: ሙዴን አጠፋችው ልጅቷ:!!
የኔን እዚህ ላይ ላቁምና ..እስኪ አንተ ወዳነሳሀው ነጥብ ልመለስ እንቅልፌ ሳይመጣ....
ወንድማችን ጣሴ ጥያቄውን አንተ እንዳፍታታህው አልፋታተውም አልበታተነውም:: አንተ የኑሮን ፊሎሶፊካል ትርጉም ይሆናል ማየት የፈለከው...ጣሴ ደሞ ህይወት ውሉ ጠፍቶበት አሰልቺና ተመሳሳይ ሩቲን ሆኖበት የዛ ጭንቀት የወለድው ጥያቄ ይሆናል ዋርካ ፍቅር ላይ ያመጣው:: :wink: እንግዲህ የምናይበት ኮርነር ወይም አፕሮች መልሱን ይወስነዋል ብዬ አስባለሁ:: ህይወት ተስፋ እያደርክ የምትሸጋገርው መሰላል ነው ኢን ፋክት መሰላሉ ተስፋው ራሱ ነው:: ጣሴ መሰላሉ ወድቆበታል:: ባይሆን እመርጣለሁ:: እኔ ራሴ አንዳንዴ ተስፋ ስቆርጥ ህይወት ምነድነው ኑሮስ ምንድነው ?? የምልበት ሁኔታ አለ:: ይሄ የጣሴ ችግር ብቻ አይደለም:: ሁሉም ሰው ላይ በተለያየ ጊዜ ሊከሰት ይችላል መፍትሄው መወደቅ አንዳለ ሁሉ መነሳት እንዳለ ማስብ ነው:: መፍትሄው ያን የተስፋ መሰላል ተንጠላጥሎ መያዝ ነው:: በነገራችን ላይ እምነት ያላቸው ሰዎች ( ማንኛውም አይንት እምነት ሊሆን ይችላል ) ከሚያምኑት ነገር ጋር ሙጭጭ ቃሉ በቀላሉ ተስፋቸው ከጃቸው አይወድቅም:: ምን ለማለት ፈልጌ መሰለህ ዳግማዊ እቺ አለም ላይ ቡዙ ኢንጀስቶች አሏት:: ቡዙ የተዛባና አን ባላንስድ የሆነ ነገር አለ:: በዚህ ፍትህ አልባ ና ኢንጀስቲስ ዎርልድ ኖረን አንተ አንዳልከው አፈር መጨረሻችን አይሆንም:: ይሄ ራሱ ከኢንጀቲስ የከፋ ሌላ ኢንጀስቲስ ነው:: ከሞት በኌላ ህይወት እxትራፖሌት ያደርጋል:: አውቃለሁ አንተ በዚህ ሀሳብ እንደማትስማማ..ለኔ ግን ህይወት በምድር ላይ አታበቃም የሚል እምነት አለኝ:: ያለተከፈለንን የምንከፈልበት ያላግኘነውን የምናገኝበት ወይም ያለአግባብ የዘረፍነውን የምንመለስበት አብሶሊዩት ሩል ኦፍ ሎው ያለበት ሄቨንሊ ክንግደም አለ ብዬ አምናለሁ:: ""ዩሪፕ ዋት ዩሶው..""የሚልው አባባል ሀይማኖታዊ ብቻ አይደለም ዩነቨራስል ትሩዝም ነው:: እንደውም ዩኑቨርስ የሚመራበት ህግ ነው:: ኦኬ እንደዛ ከሆነ ይሄን ህግ የሚያስፈጸም ኪንግደም አለ ማለት ነው:: ያ ተስፋ ነው. እንግዲ ለኔ የኑሮ ማግኔቴ ነው የምለው :: ያ እምነት መኖሬን እንዳከበረው ቢቻል በመልካም ህሊና እንድኖር የሚያድርገኝ ድሪቭን ፓወር ነው:: አንድ ቀን ይከፈለኛል ወይም ደሞ አንድ ቀን እከፍላለሁ በሚል እምነት ስለማስብ ቢበ መልካም ህሊና እንድኖር ምክንያት ይሆነኛል:: መኖሬ ትርጉሙ ይሄ ነው ብዬ አስባለሁ እንጂ በማየው ኢንጀስቶች የመኖር ትርጉም ምንድነው ብዬ ራሴን ከድልድይ ላይ ወርውሬ አላጠፋውም:: ሁሉም የዘራውን ያጭዳልና :: እንግዲህ ይሄ ተስፋ ነው እኔን የሚያኖረኝ:: ይሄ የምነት ተስፋ ከሌለን ህይወት ትርጉም አልባ ናት:: ምን ያህል % እንደሆነ አላውቅም እንጂ ከሚያምኑ ሰዎች ( it really doesn't matter የየትኛው እምነት ተእከታይ መሆንህ ) ይልቅ የማያምኑ ሰዎች የኑሮ ትርጉሙ ምንድነው በሚል ጥያቄ የሚሰቃዩ ይመስለኛል:: ምክንያቱም በዚች ምድር ላይ ያሉ አንፌይር የሆኑ ነገሮች ራሳቸው ተስፋ ሊያስቆርጡቿውና ሁሉም ነገር ምድር ላይ ያበቃል ብለው ስለሚያምኑ:: ይችላሉ:: ህይወት beyond earth የምትቀጥል ከሆነች ግ ያንን ኢንጀስቲስ የምቌቌምበት ሀይል መልካም ተስፋ እሰንቃለሁ:: መኖር ከባድ ቢሆንም እንዳልከፋ መጽናና ይሆነኛል:: እንደ አመለካከታችንና እምነታችን ነው የኑሮና የህይወት ነገር....... ቡዙ አስቀባጠርከኝ:: መልስ መስጠቴ ሳይሆን የሚሰምኝን ና የገባኝን ነው የሰጡኅህ:: አይ ቲንክ በእቴጌይት ዶናት አናሎጂ የኔን ሀሳብ ማየት ይቻላል ዶናቱ ተስፋ ነው:: በመሀል ያለው ቀዳዳ ደሞ ኢሊዩዥን ነው :: ጣሴ ባዶውን ቀዳዳ ብቻ የሚያይ ከሆነ መኖር ምንድነው ቢል አይፈረድበትም:: የዶናቱን ዙሪያ እንዲያይ እመከራለሁ::ሁላችሁም ሰላም እደሩ:: ለሌላው ጊዜ ባርብ ምድር እነደዚህ አይነት ከባድ ጥያቍ አይጠየቅም ታላቁ ዳግማዊ:: :D
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ክቡራን » Sat Oct 13, 2012 3:00 pm

GM ታላቁ ዳግማዊ 8) ይሄ ጉዳይ ጥሩ ቡና ያስፈልገዋል:: ገና መንቃቴ ነው :: :D አንተ የምትጠይቀው ጥያቄም የኔም ነው:: አንተ እንዳስቀመጥከው ሁሉን ነገር በንጽጽር ካየነው እጊዚአብሄር ተሳስቷል እንዴ ? ወደሚለው ልንሄድ እኮ ነው:: እኔ እዚህ ውስጥ የለሁም:: እኔን ተወኝ:: :D እኔ እንደውም ይቺ አለም የነዚህ ሁሉ ኢንጀስቲሶች ውጤት ስለሆነች ጀስቲስ ያለበት አለም አለ ብዬ ማመኔ ነው ==> እግዚብሄር አለ ብዬ እንዳምን የሚያደርገኝ:: የኢነጀስቲስ ውጤት ነው የጀስቲስ አለም መኖርን ጀስቲፋይ የሚያደርግልኝ:: ሌላው ደሞ እኮ የዚች አለም ምስቅልቅልነት የተፈጠረው ወይም ባንተ ምሳሌ ሊስትሮ ጠራጊ ብላቴናና የቢሊየነር ልጆች የተፈጠሩት በሰው ሰልፊሽነት ( ራስ ወድድነት ገብጋባነት) የተፈጠሩ እንጂ እጊዚአብሄር እንዲህ እንድነለያይ ፈልጎ አይደለም:: የሱ ፕላን እንዳልሆነ መጽሀፍ ይናገራል:: "" እጊዚአብሄር ምድርን ፈጠረ ሁሉም መልካም እደሆነ አየ::"" በፍጠረት መጽሀፍ ላይ ይህን ይላል ቃሉ:: ይህ የምድር ሀብት ኢኩሊ ዲስትሪቡትድ ቢደረግ ድሀና ሀብታም አይኖርም ነበር:: ኪንግደም ኦፍ ሄቨን ኦን ዚ ኢረዝ ሀፕፐነድ ያደርግ ነበር:: ክርስቶስ ያንን ሄቨንሊ ኦርደር የጀመረበት ጊዜ ነበር:: "ሁለት ያላቹ አንድን ስጡ::" ይሄ ለሄቨንሊ ኦርደር ቤዚክ ፋክት ነው:: ግለኝነት እንዳይኖር ! ሀብታም ና ድሀ እንዳይኖር የሚያግድ ስራት ከራሱ ሀዋርያቶች ጀምሮ ወደ ህዝቡ ለማስረጽ እንዲሁም ራሱንም ምሳሌ በማድረግ ያሳይ ነበር ሰው ግን ሁሉም አጌነስት ጎዶስ ሎው ሪቢሊየን ስለሚያደርግ...( ለምን እንደዛ እነደሚያደርግ ራሱ አንድ ጥያቄ ነው ) አለማችን የሰማይና የምድር ያህል ተራርቃለች:: አንዳንዴም እግዚአብሄር በማን ሳይድ ነው ያለው ብለህ እንድትጠይቅ ሁሉ ያደርግሀል:: ግን ያም ሆኖ ተስፋዬንና እምነቴን በግዚአብሄር ላጣ አልፈልግም ቡዙ የእጊዚአብሄር ነገሮች ም ባይገቡኝም at the same time የሰው ሞቲቪም ባይገባኝም:: ግን ሁላችንንም ወይ የምንካስበት ( እኔን ልብ ይሏል :D ) ) ወይ ህሊናችን አታድርጉ ያለንን ነገር አድርገን ህሊናችን ዳኛ ሆኖ የምንከሰስበት አንድ ሄቨንሊ ኦርደር አለ እላለሁ:: እኔም ዲክ ቼኒም ራምስፊልድም በዚች ምድር ላይ አብረን ኖረን በዚች ምድር ላይ ማብቃት የለብንም:: ይሄማ ከኢንጀስቲስ የከፋ ኢንጀስቲስ ነው... ኖ ዌይ! :D እረ አባክ ጣሴ የምትባል ሰው ተመልሶልኛል በልና እኔን ገላግለኝ:: :D :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7943
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሓየት11 » Sat Oct 13, 2012 4:05 pm

እሰይ እዚህ ቤት ለኛ የሚሆን የሚመጥነን ወግ ተጀምሮልኛልሳ :wink:

ሰላም ነው ፈላስሞች ... እንዲውም ኑሮ የመረረው ጣሴ :D

እስኪ የኔን የህይወት ፍልስፍና ደግሞ እዚሁ የዋርካ ግድግዳ ላይ ለመርገው::

ህይወት ወጥ ትርጉም ያላት አይመስለኝም:: ... ራሷን ችላ የምትገለጽም አይመስለኝም:: ስለሆነም ይመስለኛል ... ሰዎች የህይወትን ትርጉም ከመግለጽ ይልቅ ... የመኖራቸውን አላማ ወደ መግለጽ የሚያደሉት:: ... በራሷ ልትቆምም ... ልትተረጎምም ስለማትችል መሰለኝ... እሰከዛሬ ድረስ ... የሰው ልጅ ለህይወቱ ትርጉም ለመስጠት ሲሞክር ... በዚህ ምድር ከመኖሩ አላማ ጋር በማያያዝ የሆነው:: ... አላማ ደግሞ እንደየ ሰው ግለሰባዊ አስተዳደግና ማህበራዊ ባህል እምነት ወዘተ የሚተረጎም ነው:: ...

በእግዜር የሚያምኑት ... የመኖራቸው አላማ... ከዚህ ለጥቆ ያለውን ... ፍጹም ህይወት/ኢተርናል ላይፍ/ ... ወራሽ ለመሆን ስለሆነ ... ምድራዊ ህይወታቸው የሚተረጎመው ... የእግዜር ፍቃድና ፍላጎት ከማሟላት ... እንዲውም ህገ እግዛቤርን ሳይጥሱ ... ይችን ምድራዊ "የመፈተኛ ህይወት" ... እንደነገሩ መኖር ነው:: ...

ለማያምኑት ደግሞ እንዲሁ ... ህይወታቸውን ... የመኖራቸውን ትርጉም ... የሚገልጹት ... በሚኖሩባት የህይወት ዘመን ለመተግበር በያዙት ... የህይወት ግብ ነው:: ... አንዳንዱ ለሌላ ኖሮ መሞትን እንደ አልቲሜት ግቡ ይወስደዋል:: ... ለምሳሌ የመሀይም-ሊቋ እናቴ :D ... ሌላው ሲምፕል ላይፍን ... ኡደቷን ተከተሎ ... ወልዶና ዘምዶ ... ዘሩን ተክቶ ማለፍ ... እንደ የህይወት ግቡ ያየዋል:: ... ይህ አይነት አላማ ... ትንሽና እርባና/ትርጉም የለሽ ቢመስልም ቅሉ ... የሰው ልጅ ህይወት ሳስተይን እንዲያደርግ ... የተፈጥሮን ህግ ጠብቆ ... መሄዱ ቀላል ነገር አይደለም:: (ጌዎች ካላችሁ ቅር እንዳይላችሁ ... ወራጅ አለ በሉ :lol: ) ::

ለሌላው ደግሞ ዛሬን በተገኘው አጋጣሚ ፈታ ብሎ መኖር ... የህይወት ትርጉሙ ነው:: ... ስለ ነገ አይጨነቅም:: ... ነገር ግን ይቺን ህይወቱን በጣም ይወዳታልና ... ያለችውን ህይወት (ቆይታውን) ለማጣጣም ይተጋል:: ... ህይወትን ሲወድ ሞትን ይፈራል ... እና ሞት ሳይቀድመው በፊት ... አጭሪቷን ቆይታውን ማጣጣም እንዳለበት ደጋግሞ ራሱን ያሳምናል:: ... ሺ አመት አይኖር ... የሚባል ተረት ... የምንሰማው ከእንደዚህ አይነት ወገን ነው:: ...

ስቲል ለሌሎች ደግሞ ህይወት በዓላማ የምትገለጽ ቢሆንም ቅሉ ... ዋነኛ ዓላማዋ ከቁጥጥራችን ውጪ ነው ... ብለው ስለሚያምኑ ... ህይወት ባመጣችው ጅረት አብሮ መፍሰስን ... እንደ የመኖር ትርጉም ይወስዱታል:: ... ራሷ መርታ ... የምታደርሳቸው አልቲሜት ዴስቲኔሽን ኢዝ ዘ ቬሪ ሪዝን ፎር ሊቪን:: ...

እና ምን ለማለት ነው ... ስለ ህይወት ወጥ የሆነ ትርጉም አንጠብቅ ... ለማለት ነው:: ... ትርጉም የምንሰጣትና የምንነፍጋት ራሳችን ነን --- እንደ ግለሰብ:: ...

****

ይህን ያክል ካልን ዘንዳ ... ስለራሳችን ደግሞ እናውራ::

ለኔ የህይወት ትርጉም በዋናነት ... ከጅረቷ ጋር አብሮ መፍሰስ ... መትመም ... ነው:: ... ይሄን ሁላ የህይወት መንገድ ስጓዝ ... በኔ ዕቅድና ፕላን አልነበረም:: ... ኦፍኮርስ ... በልጅነቴ የመኖሬ አላማ ምን እንደሆነ ... ህይወት ራሷ ክሉ የሰጠችኝ ይመስለኛል ... ለምሳሌ በፍላጎት/ዲዛየር አማካኝነት:: ... (ልክ ከኔ የተሻሉ ሌሎች ዕድለኞችን ... ልዩ ታለንት እንደሰጠቻቸው ማለት ነው ... ላይክ ዘፋኝ ... ዘፍኖ የሌሎችን ህይወት የሚቀይረው አይነት ... ወይም ደግሞ በዜማው ፍቅርን የሚሰብክ ... የሰላምን ፍሬ የሚዘራው አይነት) ... :: እና የኔም ህይውት የሆነ ክሉ በልጅነቴ ስላሳየችኝ ... እዛች ቦታ ላይ ለመድረስ ... እውተረተራለሁ:: .... በሌላ አነጋገር እዛች ቦታ ላይ መድረስና ህልሜን እውን ማድረግ ... የመጨረሻው የህይወት ግቤ ሲሆን... የመኖሬን ትርጉም የምለካውም ... ያቺን አላማ በማሳካትና ባለማሳካት ... ህልሜን በመጨበጥና ባለመጨበጥ ... ይሆናል ማለት ነው:: ... በመሆኑም እዛች ቦታ ላይ እስከምድረስ ድረስ ... ህይወቴ ለኔ ትርጉም ያላት ያህል ይሰማኛል:: ... አንዳንዴ ባልጠበቅኩት መንገድ ... ህይወት ኮምፓሷን ብታዞርብኝም ... በዛች በዞረችብኝ አቅጣጫም ... የመጨረሻዋ መድረሻዬ ላይ ለመድረስ ... አዲስ ቅየሳ ... አዲስ መንገድ ... አዲስ ጉዞ ላስነካው እችላለሁ:: ... በእርግጥ በዚህ መልኩ ነው ... አሁን ያለሁበት ቦታ ድረስ ... ልዘልቅ የቻልኩት:: ... በዚሁ መልኩም እቀጥላለሁ::


http://youtu.be/JXdhHn8L65o

ሓየት
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby recho » Sat Oct 13, 2012 4:49 pm

እስቲ ሴታሴትዋ ሪቾ ታውራ ዛሬ ... :D

ሂወት ምንድነው ? የሂወት ትርጉም ሊገባን የሚችለው መኖር እንደማንችል ወይንም በጣም የምወደው ሰው መኖር እንደማይችል እና እኛ ግን አሁንም እስትንፋሳችንን ሊነጥቀን የሚታገል ነገር እንደሌለ ስናውቅ ነው .. ያኔ የኒወት ትግጉም በድነንብ ይገባናል ...ግን ሂወት የምንለው በዚህ ዝባዝንኪያም አለም ላይ የምኖረውን ብቻ ነው ወይንስ ከዚያ ማንም ሄዶ ካልተመለሰበት አለምምም ሂወት አለ ብለን ተስፋ አድርገን ለምኖረው ወይንም ተመልሰን ውሻ ወይንም ድመት ሆነን እንወለድና ሂወት ይቀጥላል ብለን ዘርግተን እንደምናየው ቀጣይና የማያቆም ኡደትን ነው ሂወት የምንለው ? ስለየትኛው ሂወት ነው እያወራን ያለነው ?

መኖራችንን አፕሪሼት ለማድረግ መጀመሪያ አለመኖር ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ዲፋይን ማድረግ አለብን ብዬ አምናለሁ .. አለመኖርን የማያውቅ ሰው ስለመኖር ምን ያውቅና ነው መጀመሪያ ህይወትን እንዲህናት እንዲያ የሚለው? ሂወትን የሚያጣፍጠው ሞት ነው ..ሞትን የማያውቅ ሰው ጨካኝ , አረመኔ እንዲሁም በማይረባ እሳቤ ጭንቅላቱን ያጨቀ ሞኝ ተላላ ሰው ነው .. ይቅርታ ሰዎችዬ.. መኖርን ለማወቅ መጀመሪያ መሞት ምን እንደምመስል ማየት ይኖርብናል .. ከዛ የሂወት ጣፋጭነት ... እስካለን ድረስ አንዳችን ላንዳችን ሂወት መቀጠል መደጋገፍን እንማራለን .. ውስጣችን ያለውን ራስ ወዳድ , እብሪተኛ እና ስግብግብ ሰውነታችንን ሳንገድል የሂወትን ትርጉም ለመረዳት መጣር በራሱ የሚያተርፈን ውጥረትን ብቻ ነው .. እንግዲህ ይሄንን ለመረዳት ወይንም ሪቾን መሆን ካለዛም በሪቾ የሚወት መስመር መጉዋዝ ይኖርብናል ... ያ ደግሞ አይቻልም ... ስለዚህ ሁላችን የየራሳችንን ሞት መሞትና የየራሳችንን የሂወት ዴፊኒሽን መያዝ ይኖርብናል ማለት ነው ...

ዛሬ ላይ ስልጣን አለን .. ዛሬ ሙሉውን የራሳችን ነው . ጥሩም , መጥፎም ልናደርግበት እንችላለን ... ያ ነገን ሊያስተካክል ይችል ይሆናል .. አይችልምም ይሆናል ምክኒያቱም ነገ መኖሩን ማን አወቀ? ገና ለገና ነገን ለማስተካከል ሲጣር ዛሬን መኖር መቆም አለበት? ከጥፋቶች ሁሉ ጥፋት... ለመኖር ስንዘጋጅ .. ስንዘጋጅ .. ስንዘጋጅ ....ሳንኖር እናልፋለን .. ሂወት ዝግጅት አያስፈልጋትም.. የሚመጣውን እንደየ አመጣጡ እያስተናገዱ ማለፈ ነው .. በአንድ ወቅት ከእድሜዬ እና ልረዳው ከምችለው በላይ የሆኑ ነገሮችን አየሁ .. ያንን የልጅነት ጭንቅላቴ መርሳት አቅቶት በትላንትና ላይ እኖር ነበር .. እና ሂወቴ ላይ ትልቅ መሀተም ያላቸው አንዲት ሴት ጨዋታ አጫወቱኝ ..

Code: Select all
ሪቾ ገጠር ሄደሽ ስለማታውቂ ወይንም እዛ አካባቢ ያለውን የሂወት ትርጉሞች አታውቂም ..ከአረም አራሚ ገበሬ አንድ ትልቅ ቁምነገር እንማራለን ... አረሙን እየነቀለ ወደፊት ይጉዋዛል .. ወዳልታረመው ሰብል .. በመሀል ዞር ቢል ከሰብሉ መሀል ያልነቀለው አንድ ትልቅ አረም አየ .. ያንን ለመንቀል ግን አልተመለሰም ... ምክኒያቱም ... አረሙን ለመንቀል ከተመለሰ ሂወት ያላቸውን ሰብሎቹን የመርገጥ ፖሲቢሊቲ አለ .. ያንን አደጋ ላይ መጣል ስላልፈለገ አረሙ እንዳለ ሆኖ ለሰብሎቹ ሂወትን ሊሰጥ ወደደ .. ሂወት እንደዛ ናት ..


በዛን ዘመን ለነበረ ጭንቅላቴ ይሄ ብሂል በውነቱ ምንም ማለት አልነበረም .. መነጫነጬን አላስተወኝም .. ግን አሁን ላይ ሆኜ ሳየው ፊታችንን ያዞርነው ወዴት ነው ? ወደሚታረመው አረም ወይንስ አርመን ወዳለፍነው ሰብል .. ወደስህተታችን ወይንስ ልናስተካክል .. ስህተትን ልናርም ወደምንችልበት አቅጣጫ .. ያ ነው ለኔ የመኖር ትርጉም .. መኖር ማለት ነገሮችን የማስተካከያ እድል ማግኘት ነው .. ወደፊት ማየት .. ያንን እድል ማግኘት .. ያንን እድል ማግኘት ደግሞ ምን ያክል መታደል መሆኑን የምናውቀው ወደፊት መሄድ እየፈለጉ ነገሮችን ማስተካከል እና ያሉትን የሂወት ስንክሳሮች እየነቀሉ ጣፋጩን ሂወታቸውን ማስተካከል የሚችሉበትን እድል እየናፈቁ ግን አንድ ስንዝር መራመድ እንደማይችሉ አውቀው በሀዘን ያሉትን ስናይ ነው ...

ከጥቂት ሰአታት በፊት ከጉዋደኛዬ ጋር በቴክስት ሜሴጅ በጣም ያናደዳትን የስራ ባልደረባዋን በተመለከተ ስናወራ ነበር ... መሀል ላይ ግን ያልጠበኩት ዜና ሰማሁ .. ያ ትላንትና ስራዋን እንድትጠላ ሲያስጨንቃት የነበረው ሰውዬ ስራ ቦታው ላይ ዛሬ አልተገኘም ... ያ ለኔና ለጉዋደኛዬ ፈኒ ዜና ነበር .. ኦ ጌታዋን የተማመነች በግ ላትዋን ደጅ ታሳድራለች ነበር ያልነው ... ግን ሂወታችን በማን ቁጥጥር ላይ ናት ? ማነው ሂወታችንን እንደፈለገ የሚሰጥና የሚነሳን? የስራ ባልደረባዋ አፓርትመንቱ ውስጥ ሞቶ ተገኘ! ደውሎ ስራ እንደማይመጣ ምክኒያቱም እየሞተ ስለሆነ የሚናገርበትን እድል አላገኘም .. ሂወት ምንድናት ? መኖር ምን ማለት ነው ? ዛሬ ላይ ብቻ እርግጠኛ ነን .. ነገ የዚህ አለም ስዎች እንሁን አንሁን አናውቅም .. ሶ ሌትዝ አፍ ፈን ..! በተቻለ አቅም ሁሉ ጥሩ እንሁን .. አካባቢያችን ያሉ ሰዎች ሂወታቸውን በኛ የተነሳ መልካም ከሆነላቸው እንዳድርገው .. አፍተር ኦል .. ሂወታችኝ የኛ አይደለችም ... !

መልካም ሰንበት ...
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ሓየት11 » Tue Nov 06, 2012 3:41 pm

እንደኔ ሁሉ ድህነት የሰለቸው ... ህይወት ትርጉም አልባ የሆነችበት ... ምቀኛው ጣሴ :) ... ይችን ቤት በርግዶ የት ጠፋ? ... ተመነጠክ እንዴ አንተ? ... :o

ዎርዝ ሪዲን ስለሆነ አመጣንላችሁ ወዲህ ... አንብቡት ... ትዕዛዝ ነው :roll: :lol:

Dreams: the 12 steps

by Paulo Coelho

When Joseph Campbell created the expression “follow your blessing,” he was reflecting an idea that seems to be very appropriate right now. In “The Alchemist,” this same idea is called “Personal Legend.”
Alan Cohen, a therapist who lives in Hawaii, is also working on this theme. He says that in his lectures he asks those who are dissatisfied with their work and seventy-five percent of the audience raise their hands. Cohen has created a system of twelve steps to help people to rediscover their “blessing” (he is a follower of Campbell):


1. Tell yourself the truth
Draw two columns on a sheet of paper and in the left column write down what you would love to do. Then write down on the other side everything you’re doing without any enthusiasm. Write as if nobody were ever going to read what is there, don’t censure or judge your answers.

2. Start slowly, but start
Call your travel agent, look for something that fits your budget; go and see the movie that you’ve been putting off; buy the book that you’ve been wanting to buy. Be generous to yourself and you’ll see that even these small steps will make you feel more alive.

3. Stop slowly, but stop
Some things use up all your energy. Do you really need to go that committee meeting? Do you need to help those who do not want to be helped? Does your boss have the right to demand that in addition to your work you have to go to all the same parties that he goes to? When you stop doing what you’re not interested in doing, you’ll realize that you were making more demands of yourself than others were really asking.

4. Discover your small talents
What do your friends tell you that you do well? What do you do with relish, even if it’s not perfectly well done? These small talents are hidden messages of your large occult talents.
Begin to choose
If something gives you pleasure, don’t hesitate. If you’re in doubt, close your eyes, imagine that you’ve made decision A and see all that it will bring you. Now do the same with decision B. The decision that makes you feel more connected to life is the right one – even if it’s not the easiest to make.
Don’t base your decisions on financial gain

The gain will come if you really do it with enthusiasm. The same vase, made by a potter who loves what he does and by a man who hates his job, has a soul. It will be quickly sold (in the first case) or will stay on the shelves (in the second case).

7. Follow your intuition
The most interesting work is the one where you allow yourself to be creative. Einstein said: “I did not reach my understanding of the Universe using just mathematics.” Descartes, the father of logic, developed his method based on a dream he had.

8. Don’t be afraid to change your mind
If you put a decision aside and this bothers you, think again about what you chose. Don’t struggle against what gives you pleasure.

9. Learn how to rest
One day a week without thinking about work lets the subconscious help you, and many problems (but not all) are solved without any help from reason.

10. Let things show you a happier path
If you are struggling too much for something, without any results appearing, be more flexible and follow the paths that life offers. This does not mean giving up the struggle, growing lazy or leaving things in the hands of others – it means understanding that work with love brings us strength, never despair.

11. Read the signs
This is an individual language joined to intuition that appears at the right moments. Even if the signs point in the opposite direction from what you planned, follow them. Sometimes you can go wrong, but this is the best way to learn this new language.

12. Finally, take risks!
The men who have changed the world set out on their paths through an act of faith. Believe in the force of your dreams. God is fair, He wouldn’t put in your heart a desire that couldn’t come true.

Source
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests