ደሜን....

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ደሜን....

Postby ሳምራውው33 » Thu Oct 18, 2012 8:17 am

ውጤቱን ስለማውቅ ጠልቄ መርምሬ
ወጊ ሹል መሆንዋን ከቁብ መች ቆጥሬ
ስጋዬን ሊቀደው ደምስሬን ሊበሳ
ሀኪሙ ሰውዬ ስለት ሲያመጣ::

መርፌውን ስደደው አስገባው በክንዴ
ደሜን ቀድተህ ውሰድ አኑረው በዘዴ
የነብስ እስትንፋሴ ቅንጣቢ አካል ነው
ቆሞ ለመሄዴ ምሰሶ ማገር ነው::
ድንገት ለተጎዳ ደሙ ለፈሰሰ
ሊሞት ለሚያጣጥር እስትንፋስ ላነሰው
የኔ እስትንፋስ ገብቶ የሱን እንዲያግዘው
ውሰድልኝ ደሜን በክብር አስቀምጠው ::

ሀብትና ንብረት የሌለው ሰው ከሚሰጣቸው ስጦታዎች የከበረው ደም መስጠት ነው :!: :!:

Give blood save life .
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest