ገልብጤ ( የራሄል እምባ )

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ገልብጤ ( የራሄል እምባ )

Postby ገልብጤ » Wed Oct 24, 2012 8:46 pm

እናንተ ምእመኖች የዚህ ቤት አላማ ካዲስ አድማስ እና ካንዳንድ ቦታ ኮፒ እየተደረገ የሚመጣ ነው ..አላማችን እናንተን ማስደሰት ነው ....
አይናማወች ካላቹ ብዬ ነው ቀለሙን ደመቅ ያደረኩት


እንደተጠበቀ ነው፡፡
የኦሪት ልብ እንዳይኖር፡፡

ይሔ ህግ ግን … ያልተገደበ ነው … (በእኔ ህሊና) ሰው ያወጣውን ሰው የመጣስ መብት አለው…! ህግ ህግ ሆኖ የሚቀረው ስንስማማበት ብቻ ነው፡፡ ያልተስማሙበት ህግ … የህጉ አካል ነው ከተባለ ሊሆን ይችላል፤ (የሰፈረ) እንጂ የሆነው እንዲሆን የሚሆነው ሊሆን ግድ ስለሆነ፡፡
ሐዲሱ ይስማማናል፣ … ከፍተኛ መስዋዕት ስላስከፈለ … ከመፍጠር ማዳን ልቋል፡፡ ወደን … መርጠን የላዩን ጠንቅቀን እናስከብራለን… የስሩን ባናስከብረውም አንንቀውም፡፡ የላይኛውን መንገድ ስለዘጋ!!!
እባቢቱን ለሚከተል … ፍርሃቱ የፈጠረበትን ለገዛ አምሳሉ (ለሁሉም ለማይሆን) ለሚንበረከክ አተርፍ ባይ አጉዳይ ቆሞ ለሚሳብ፣ እየሄደ ለማይደርስ፣ በያዘው ለማይረካ፣ የጨበጠው ለሚሟሟበት አዳም… ቀድሞ ህልሙን ካልፈታ፣ ተልኮውን ካለወቀ፣ ከንፈሩ ምስጋናን ከከለከለች … ወየውልህ ትለዋለች … የገዛ ነፍሱ … ለሚሻርና ለሚያልፍ ስም ልባችን ላይ ጣኦት አንትከል፡፡
***


“አይኔ አይንሽን ሲያየው የሚያለቅሰው ለምንድን ነው?”
“እንጀራ አባቱ ስለሆንክ”
“የእንጀራ አባቱ…? ወይስ የፍቅር አባቱ?”
“እሺ የአይን አባቱ፡፡” አይኗን ሳምኳት፤ ባያምሩም አያስጠሉም፡፡ የደስ ደስ እንጂ ውበት የላቸውም፤ የደስ ደስነቷ ውበት ስለሆናት ውበት ምንድን ነው? … ፊቷ አይገፈትርም … ርህራሔዋ ትኩስ ቅቤ የተቀባ እንጐቻ ነው፡፡ ሳቋ ስስ የብርሃን መጐናፀፊያ ነው የሚመስለው፤ ዐይኗ በሙካሽ የተጠለፈ ምርጥ መባ ትመስላለች፤ ጭልጭል እያለችም ታጓጓለች፡፡ ነጠላ ለብሳ ቤተ ክርስቲያን ስትሔድ እምትመለስ ስለማይመስለኝ … አብዝቼ እፀልይ (እለምን) ነበር …
“አባት ሆይ ስታበጃትም ፍቅር አብዝተህባት ነውና ስትነሳም ስታርፍም በምስጋና የተሞላች የመላዕክት ክንፍ የመሠለች ፍጥረትህን ለእኔ ስትል የመናኝ ልብ አትስጣት!” (አብዝቼ እለምን ነበር)፡፡ ስስታምነቴ በ’ሷ ላይ ብሷል፡፡
ወንድሞቿ ከኩርኩም ጋር ምክር ለገሱኝ “ብትደርስባት … በማንኛውም መልኩ አብረሃት ብትሆን ጥርስህን ኪስህ ውስጥ እንከትልሃለን” አሉኝ፡፡ ማን ወላቃ ሆኖ ይቀራል፣ (የድሮ አራዳ ይመስል)
እየደወድኳት ራቅኋት … ብርቃትም ቀረበችኝ … ተደብቃ ታገኘኛለች … እኔ ስጋቱ ስላስጨነቀኝ በጣም ይሸክከኝ ነበር፤ እንዲያም ሆኖ ያላደረገችልኝ ያላስደረገችኝ ነገር የለም … ከእነሱ ቤት ጀርባ መደዳውን እንጀራ የሚሸጡበት ሰፈር ሁለት ጊዜ አዲስ ምድጃ ከነወጡ ሰርቄ፣ ድስቱንም ምድጃውንም ለቆሬ ሸጬ ብሔረ ፅጌ ወስጄ ኮምኩሜአታለሁ፡፡ እሷ ከቤት እያመጣች ያልፖሸርነው እቃ የለም፡፡ የምር ምስራቅን ሐጢያትም እየሠራሁ እወዳታለሁ፡፡ ሁሌም አስባታለሁ … “ነይ” ባልኳት ቁጥር ትመጣለች … “ሒጂ!” ብዬ ማስቀረት ግን አልቻልኩም … እቺ ፍንጭት ድምቡሽቡሽ … ልቤን እንደሞላችው አለች፡፡
***
ከላይ የተፃፈው ትዕዛዝ (በደማቅ እሣት) የማይሻር የማይለወጥ እንደሆነ ልቦች ያውቃሉ … እያወቁም ያጠፋሉ፤ አጥፍተውም “ምህረት” የሚሉ ጥቂቶች ናቸው … ለዛውም ደጅ ለማያሐጠና ልመናና ምህረት … ለአንድ ትንሽዬ ልብ … ትንሽዬ ልብ በቂው ነው፡፡ ይሔንምም እናውቃለን አውቀንም ለመፈፀም እያቅማማን እንገኛለን፡፡ አይናችን ከአዕምሮአችን ጋር የተቀያየመ ይመስል … ባለመመልከት መሀል እያየ አያይም … ደልዳላው ገደል፣ ውኃው ጠጠር፣ ሥጋው ቅጠል፣ ሊሆንብን እየሆነ ይመስላል፡፡
***
ፀሐይዋ አመለኛ መካን የመንደር ሴት ይመስል ትጠብሳለች፡፡ ያለ ምክንያት ያፋሽመኛል፡፡ አሁን … አምስት ደቂቃም አይሞላኝ ከቤቲ ጋር ኪሪያዚስ ብቻዬን ሁለት ጎጆ ኬክ እንደውኃ ፉት ብሎ ከመጣሁ፤ አናቱ ላይ ማኪያቶ ያለ ስኳር ደረብ አድርጌበት … እና … ሆዴ ግን ምንም ያየም የቀመሠም አይመስልም፡፡ በርጫ ከተውኩ ዛሬ ሃያ አንድ ቀኔ ነው … ታዲዎስ እና አዲስ ለመወስወስ ሞከሩ ሞከሩ … አልሞክራትም … አልኳቸው! ተስፋ ግን አልቆረጡም … እስከ አሁንም የተሸወድኩት ይቆጨኛል … ያ ባሪያማ ሱሱ እላዩ ላይ ቤቱን ሠርቶበታል … ከወንድዬ ጋር ሆኖ የገዛ አልጋቸውን ከተሠቀለበት አውርዶ ሸጦ ቅሞበታል … አሁንም እነ አይኖም ምድር ቤት ተቀምጠው እየቃሙ ነው …፡፡ አብሬአቸው መጫወት እፈልግ ነበር … ግን መወስወሴ ስለማይቀር ይብራብኝ፡፡
እቺን ፀሐይ ብጠላትም ቤት ውስጥ ማንበብ ብቻ ሥለደበረኝ … እነ አጅዋ በረንዳ ላይ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ወጭ ወራጁን እከልማለሁ፡፡ የተጨበጨበለት የሽንት ቤት ፍሳሽ ፊት ለፊቴ ያለከልካይ ይንጐማለላል፣ ሽታውን ሁላችንም የሰፈር ልጆች ምርጫ ስለሌለን ለምደነዋል … ዋው! አንድ ቀን እኔና ሐይልዬ … ወደ ዘጠኝ ቤቶች ይሆናሉ አዋጡና እናሰራው ብለን ብር ሠበሠብን … ያለ ከልካይ ተምነሽነሽንበት፤ ከዛ እኛው በረጅም እንጨት ጐርጉረን ለአንድ ሳምንት እፎይ ካስባልነው በኋላ ተመልሶ ገነፈለ (አንዳንዴ አዲስ ጀበናም ይመስለኛል) አሁን ሁሉም ስለሠለቸው ያለከልካይ ይወርዳል … /ጤናችንን እንጠብቅ በሚባልበት ዘመን/ በዚህ በጠራራ ፀሐይ እኔና እሱ ተፋጠን እሱ ይወርዳል እኔ ተቀምጫለሁ፤ እነ ድባቤ አጥር ስር … እንደ ጐራዳ የደስ ደስ ያላት ልጃገረድ እምታምር ጥላ አለች፡፡ እዛች ጋር ሔጄ ለመቀመጥ ሳስብ … ትላትን ማታ ያቺን ፍንጭት የውኃ ድፎ ዳቦ የመሠለች ድንቡሽ … የቆርቆሮውን ተገን አድርገን ሳሩ ላይ ተንጋለን … የሳምኳት አሳሳም … ዋው ባይነጋ ብዬ ተመኝቼ ነበር …፡፡ ከንፈሯ የገብረትንሣኤን ቦክሠኛ ኬክ ይመስል ጣፋጭ ነው፤ በርከት ያሉ ከንፈሮችን ከሷ በኋላም በፊትም ስሜያለሁ … የምስራቅ ግን ጐመን በስጋ ከአይብ ጋር ነው (ኬክነቷ እንዳለ) ቴዲ አይቶኝ ቢሆን ኖሮ … እንደቴዘር ስልክ እንጨት ላይ ሰቅሎ ይጠልዘኝ ነበር፡፡ አንድ እሁድ ማታ ጥጓን አስደግፌ ፊልሜን ስሰራ … ከነ ጩኒ ቤት ዘቢባ ውኃ ደፋችብኝ … ወይ ፍንክች! የጋለን ልብ ውኃ ሊያቀዘቅዘው? ሞኟን ትፈልግ፡፡ (ሌላ ቀን ግን ዘቢባን ሰራሁላት … ሰክራ ስትመጣ ጠብቄ አታልዬ ሐይልዬ ጋር አሳደርኳት… ስጠይቀው ሲያበናት አደረ… በድርጊቴ ተደስቶ ሙሉ ቀን ስፖንሰር አደረገኝ)
እንደ ጅል ቦታዋን እያየሁ ሳቅሁ … (ከከንፈር ግን አልዘለልኩም)
***
ወጣትነት ጉብዝና ነው … የህሊናም የጡንቻም … የመብረር ጊዜዋ እንደደረሠ እርግብ ትር … ትር ያሻዋል፣ ጡንቻው እጃችን ላይ ነው … ማስተዋሉን ግን ፍለጋ ይጠይቃል፤ ያማረ ሁሉ አያምርም! ሥሜት እውነት አይደለም … ማሰብ ወደ መንገዱ ይወስዳል እንጂ ግቡ ራሱ አይሆንም፡፡ እርግጥ ግብ ያለ ውጥን ባዶ የንብ ቀፎ ነው… አውራው ከሌለ ሌሎች መች ይኖራሉ (የንቦች ባህሪ እንዲህ ነው ‘አውራ’ ይሻሉ!) ወጣት መሆንም በራሱ ስሌት ነው … አንዳች ነገር ይነዳል … ያንደረድራል … አይን ያማረውን በጉልበቱ ለልቡ ማቀበል ይፈልጋል … አይን የምላስን ያህል ያጣጥማል … ይሔ እንግዲህ ትኩስነት የሚፈጥረው ክስተት ነው፡፡
***
እቺን ይወዳል መረቁ-ወይኔ መበላት … አይኔ ተርገበገበ… በጣም ቆንጅዬ ልጅ ናት … “ዘምባባ” እድሜዋን አይደለም፤ ለምለምነቷን ነው … ወይ ግሩም! እንዲሁ ተፈጥሮ እንደምታዳላ በዚህች ጣዝማ በመሠለች ቆንጆ ማወቅ ይቻላል፣ ረጅሙ ቁመቷ ላይ ረጅሙ ቀሚሷ አብሯት የተፈጠረ ነው የሚመስለው (የቺክ ደረጃ መዳቢዎች ቢቋቋም ምናለበት … ሴቶችን እንዲሁ አይቼ መመዘን እችላለሁ) መስቀያው አይደለ የልብስ ውበቱ … ቆማ ተነስንሳለች … ወንዳታ ኢትዮጵያ… አንድዬ እንኳን እዚች አገር ላይ ፈጠረኝ (አወዳይ አወዳይ የመሠሉ ልጃገረዶች ሞልተዋል) እንደውኃ ይፈሳሉ … እኛ በምን እንፈስ…?
ቋሚ የፍቅር ጓደኛ ባይኖረኝም የአይን ርሃቤን አዱ ገነት የአራዶች እናት ሸገር ላይ እወጣለሁ … (ለመሴሠን ግን አይደለም) ሠላጣ ሠላጣ የመሠሉም … ቶሎ “ዳይጀስት” የሚሆኑ “ቺኮች” ለጉድ ሞልተዋል፤ ሳላስበው ቆምኩ… እቺ ዘምባባ የመሠለች የእንስቶች እንስት (የምድር) ልቤን ባለበት ገተረችው፡፡
“አቦ ይመችሽ … እግዜርን ቀሽት ነሽ እሺ” እንደሚጥም ፉጨት ውበቷን ነገርኳት “ቁመትሽ ሎጋ ነው የኔ አለም ሰንደቅ ያሰቅላል ሆድዬ … የተባለው ላንቺ ነው…”
የኔንም ልብ እኮ ሠቀልሽው…? ውይ ማማር! ለስላሣ ከሀር የተሠራ ውኃ ሰማያዊ ቀሚስ ለብሳለች … ከላይ እስከ ታች እንደማይዘጋ የአምልኮ በር ሁሉም ነገሯ ይታያል … ብርሃን ይመላለስባታል … የተጫማችው ስስ ሸበጥ ከማማሯ የዘለለ … ጣቶቿን ለእይታ አጋልጦታል … ውይ ውይ የእግር ጣት … ቁርጥምጥም አድርገን ሲጥ ሲጥ እንደምናደርጋት የበከል ሥጋ ለአይን ምግብ ናቸው … ሳልዳብሳቸው ይለሠልሳሉ …
(ምናለ እኔን እየተጫማች በሔደች) የተረከዟ አቀማመጥ ራሱን ችሎ ወገበ ቀጭን ሞንዳላ ዳሌ የምትጣቀስ ቆንጅዬ ልጃገረድ ይመስላል፡፡ ውይ አምላኬ ከመቼ ጀምሮ ነው ግን እንዲህ ቀሚስ በተውለበለበ ቁጥር ነፋስ ሆኜ የቀረሁት…?! ጉረኛ እኮ ነኝ … ደረቴን አየር ሞልቼ ተጠጋኋት … “ይመችሽ አቦ …” ልቤም ይመችህ …! ቆንጆ ማን ይጠላል … እቺ ዘንጣፋ ወደነ ይጌ ሠፈር ቀስ እያለች ሔደች … ተከተልኳት … “ኮሮኮንቹ እንዳያምሽ … ከስር እኔ ልሁንልሽ…?” ዝምታ ነው መልሷ … ይሔ የቀትር ጠራራ ፀሐይ ለልቤ ድፍረት እና ሙቀት ሆነኝ እንጂ ምንም ያህል አልተሠማኝም፤ (እውቀት ቢሆነኝ ምናለበት) ውበቷ ጥላ ሆኖኛል … ርችት የመሠለችን ቆንጆ ተሞዳሙጄ ካበሠልኩ፣ ልቤን በድምቀቷ ካደመቀችው ብደምቅላት ምናለበት …፤ ከኋላዋ ስከልማት ጣት የምታስቆረጥም ሥንግ ቃሪያ ነው የምትመስለው፤ በጨዋ ደንብ እንደደረሠ ጐረምሳ እያፏጨሁ እያወራሁ ሳላስጠጣ እየተከተልኳት ነው፡፡ ከበስተኋላዋ የማየው የሠርከስ ትርኢት ልቤን ውኃ እንደሸረሸረው ቀይ አፈር እያንሸራተተው ነው፡፡ ለጉድ ትወዛ.ወ..ዘ.ዋ.ለች፤ (ህዝብ ለህዝብን አስታወሠኝ) እኔም ልቤም ለጉድ ተወዛወዝንላት፡፡
***
ህሊና እየራቀን ይመስለኛል … ልባችን ወይራ መሆን ይጠበቅበታል … ስስ ከሆነ ጀንፎ ያስፈልገዋል… ለዛውም የብረት፡፡ እምንመራው እና እሚታዘዘን ሥሜት ከሌለን ፈረስን ያለ ኮርቻ ያለ ልጓም መጋለብ ነው፤ … ሁሉም ተሠጥቶናል ግን ሁሉም አይጠቅመንም፤ እንዲጠቅመን የምንፈልገውን ነገር እንጠቀምበት እንጂ አይጠቀምብን፡፡
***
ራስህን ለምን ታዘብከው አትበሉኝ እና ራሴን ታዘብኩት፤ የሔዋኖች ውበት ለሷ ብቻ የተሠጠ እስኪመስል ቀናሁባት … ጠረኗ tasty ነው… ቦታውን አስውባዋለች፤ በርሃውን ልቤን ለጊዜውም ቢሆን ድርቀቱን በአይን ልምላሜ ታድጋኛለች፣ …(አዳሜ በጥቁር መነፅር የአይኑን ማረፍያ ጋርዶ ማንም ስለማይሾፈው በልቡ … ሥንት ቦታ ይሾፍራል መሠላችሁ)
አገጮ ጠቀሠኝ … ፌስታሉን በጀርባው አንጠልጥሎ በሽራፊ ከልሞኝ በባዶ ሜዳ ምራቁን ዋጠ… በታጣ ምራቅ፤ እነዛ የሰፈራችን ቆንጆ ነን ባዮች በአይን ጠረባ ዘርጥጠዋት አለፉ … በልባቸው እኮ “ስታምር” ብለዋል … ችኮች ደማቸው እስኪረጋ በቆንጆ ችኮች ጭው ብለው ሲቀኑ አይጣል ነው፡፡ እቺ ዘንባባ ጥላ ቦታ ላይ ስትደርስ ውበቷ ጐላ … ወይኔ ሰውዬው … “የኔ እመቤት … እእ… አጠገብሽ ስደርስ ፀሐይዋ በውበትሽ ቀንታ አፍራ ነው መሠለኝ ተደበቀች፣ ጉልበትሽ ስር የተንበረከከች ነው የሚመስለው… እባክሽ ምህረት አድርጊላት…?...እ…” ዞራ ለማየት ተጠየፈችኝ “በጣም ውብ ልጅ እኮ ነሽ … ምነው አመሠግናለሁ አይባልም?” ዝምታዋ ከውበቷ ጋር አብሮ የተፈጠረ ይመስላል … “ለነገሩ ተይው … አንቺን የመሠለች የውቦች ውብ … ከማውራት በልቧ የምትመሠክረው ይጥማል፣ አይደል እንዴ የኔ አበባ…? እኮ እውነትሽን ነው… ዝምታም ለእንዳንቺ አይነቷ ቋንቋ ነው”
እንዲህ አይነት ምላስ ከየት አመጣሁ … ግራ ገባኝ … ልጅቷ ግን ልጅ ናት፡፡ “ለሆነው ላልሆነው ነገር እያወራሽ እንዲደክምሽ አልፈልግም … ልቀፍሽ እንዴ…?” በሆዷ ስትስቅ ታወቀኝ “ይገርማል ቁመናና ዛላ አሉ … ጥላ ላይ ሳይሽ ደግሞ በማታ መሬት ላይ እንደተበተኑ ከዋክብት … ታንፀባርቂያለሽ … እርግጠኛ ነኝ ስለውበትሽ ከእኔና ከእናትሽ በስተቀር ማንም አልነገረሽም፡፡ እማዬ ትሙት እናትሽ እንኳን ወለዱልኝ…”
***
ሌጣው ፈረስ የልቡ አይን እየደከመ ሽምጥ እየጋለበ ነው፤ ጥልቀት ወዳለው ገደል፡፡ ተከታዩ የሚያስከትለው ይሆነው አይሆነው ሚዛንን የመሠለ ህሊና የተነጠቀ ይመስል ለስሜት ተንበርክኳል፤ ወደፊት መመልከት የቆሙበትን መርሳት ማለት አይደለም … ተገልጦ የሚነበብ ህይወት ቋንቋውና ታሪኩ ጥዑም ነው፣ ህይወት ነጠላ ሰረዝ ናት … አካፋይ ሥትሆን … ድርብ ካደረግናት ደግሞ ህግጋቷን ትፈፅማለች፤ ተልዕኮ … የሌለው ማንነት ማህፀን ውስጥ የሞተ ሽል ነው… ያ የአባቱ ሀጢአት ርግማን የሆነበት፡፡ የእናት ሆድማ ተልዕኮው ያልተጓደለ ነው፡፡ ለራስ ጊዜ መስጠት ለህይወት መነበብ ነው፤ እምንፈሠው ከገዛ የልባችን ምንጭ ከሆነ … ለሌሎች ደራሽ ወንዝ መሆን የለብንም፡፡
***
“ባይገርምሽ ጉንጭሽ ላይ ያሉት ስርጉዶች … የእናት እቅፍ ነው የሚመስሉት … ስታወሪ እኮ ከኪስሽ ገንዘብ አልወስድብሽም … ተጫወቺ … ጭውቴሽ የውሮ እናት ቤትን እርጐ ካስናቀ እሸልምሻለሁ…እሙ… ግን … አንቺን ለመጥበስ ልደራጅ እንዴ…?”
ድምፅ ሳታወጣ ሳቀች “አዎ የኔ ማር … እንደሱ ነው… ሳቂ ሳቂ እኔ እከፍልልሻለሁ፤ በደንብ ሳቂ … አትሣቀቂ …” የማን አባቱ አኞ ነው እንደምትል ተሥፋ አደርጋለሁ፡፡
“እሙካዬ … እምትሔጂበት ድረስ እየዘፈንኩ ብሸኝሽ ቅር ይልሻል… እ…? ተወዳዳሪ ስለሌለ እሚያሸንፈኝ አይኖርም… ካንቺ በቀር … እ…የኔ ዘንባባ …? አይ ሲ… አንቺን የመሠለች እህት አለችሽ አይደል?” ወየው መዘላበድ! ወየው መቀላመድ! ድሮም ሥሜቱ የነዳው ወንድ እንዲህ ነው…! “ምነው ልቤ? ምነው ምነው … እኔ ብሸወድ አንተ ትሳሳታለህ…?! … “እ… ማለቴ…” “እ… ማለትህ!” ብትለኝኮ … ኤድያ… አጉል የቃላት ትራስ ለሴት ልጅ መሞዳሞጃ ምንም ሙድ የላቸውም፡፡ በተለይ በተለይ እቺን ለመሠለች ቆንጆ፡፡ ከላይ ካልተሠጠ ማን የራሱን አብስሎ በላ!… የእናት ጣት የፈተፈተው ፍትፍት የመሠለች ደመግቡ… “እሙካ ከየትና የት አብረን እንደመጣን አስበሻል… እየተከተልኩሽ እንደሆነ ያወቅሽ አልመሠልሽኝም … እ… እሙ… የኔ ዘንባባ… የኔ ዘንጣፋ … ኧረ ለሞራሌ እንኳ ትንፍሽ በይ…? በእናትሽ…? … ተይ ይቆጭሻል… ወይ ሳቂልኝ…? እሺ በጥፊ በይኝ እና ልመለስ…?” ዞራ አየችኝ … አይኗ ስር የተኳለችው ኩል ሥሥነቱ አዲስ የተሠራ የቀለበት መንገድ ይመስላል፤ ቆመች፡፡
ቆምኩ፡፡
የራሱ እንዲወደድለት የሚፈልግ የሌሎችን መውደድ አለበት፤ ምነው ልቤ? ፈራህ እንዴ? … ለምን አትፈራ …፤ አዳም ሞኙ እስከመቼ ነው እንዲህ ቆንጆ እየተከታተለ እንደ ውኃ የሚፈሠው … ማነው ውብ ሴት እየተከተለ ከመነሻው በቀር መድረሻው ላይ የደረሠ?!...
“የኔ ቆንጆ … ካሰብሽው ሠላም ድረሺ … የዚህን ያህል አምላኬን ቢሆን የተከተልኩት … የለመንኩት እንዲህ እንዳንቺ መልስ አይነፍገኝም ነበር…”
አስተያየቷ ቋንቋው ተደበላልቋል … አይተረጐምም … “
“እሺ ስጪኝ…?” አቋቋሟ ያምራል … እጇን ለቡጢ ጨበጠች … ኩስትርናዋ ቀለም ያልተቀባ አዲስ ቤት አይነት ነው፣ መቆጣት አትችልበትም …
“ስምሽን ነው ሌላ አይደለም” ሳቀች … ድምፅ ነበረው … ግርማ ይፍራሸዋ በጣቱ እንደሚያዋራው ፒያኖ ይርበተበታል … ሳቋ ከምታቃጥለው ፀሐይ በላይ ደማቅ ነው፡፡
“የምሬን ነው ሸልሚኝና ልመለስ?” ልመናዬ ደረቅ እንደሆነ ገባኝ … እንደ ዘመኑ ኮሜዲ ፊልም የላይ የላይ እንጂ ከልብ አይደለም፤ ግንባሯን ቅጭም አደረገች … አተኩሬ ተመለከትኳት … ገጿ ውኃ ጥም ይቆርጣል፡፡
የውኃ ድር ናት … ተበተበችኝ … በጠራራ ፀሐይ እርጥብ ፈገግታ … ለጨበጣት ሙልጭ … ለረገጣት ዘጭ …፤ ትንፋሽ ሰበሰብኩ … እግዜር ምስክሬ ነው … ሥም የወጣላት የአንድ ክፍለ ከተማ ሰዎች ተሠብሥበው ተወያይተው መሆን አለበት … ለዚህች ወለላ ሔዋን የቁንጅናም፣ የርጋታም፣ የደስደስም መገለጫ ሥም … “ቻው ውኃዬ … እኔ ፈሠሥኩ … ከቻልሽ ቅጂኝ …”
እየሳቀች … ነካችው፡፡
ነካሁት … እየተገረምኩ፡፡
***
ዐይን ውበት አይቶ ሲከተል … በቀን ይመሻል፡፡ ልብ ሚዛን ካበጀ … ቆንጆ በጠዋት አረጀ፡፡ የላይኛው ህግ ሲከበር … የስሩ ከተናቀ እንዲህ ፈሠው መቅረት አለ፡፡ ከመዝገብ መሠረዝም፡፡ አለምን ያልናቀ አለም ትንቀዋለች፤ መከተል አይደለም ትርጉሙ… የሚከተሉትን ማመን ነው … ማመን ብቻም በቂ አይደለም … የዘንባባ ዛፍ ላይ ብርቱካን አይበቅልም፡፡ የሆነው ካልሆነው እንዲሆን ማኳኋን ከንቱነት ነው!፡፡
ፀሐይዋን ማለፍ ይቻላል፡፡ እምንቀመጠው ለአይናችን ሳይሆን አይናችንን ለህሊናችን መቀመጥ አለበት … ወጣትነት ያስጨበጥነውን ይሠጠናል … አጥንታችን ሲጠነክር … ለእርጅና ዘመናችን ስንቅ ይሆናል … ለዘርና፣ ብኩንነት የምንይዘው እኛው ነን፡፡ ህግ ሁሉ ህግ አይደለም! ፍቅር ግን ህግ ይሆናል፡፡ የኦሪት ልብ አያስፈልግም፡፡
Last edited by ገልብጤ on Sun Nov 11, 2012 5:16 pm, edited 5 times in total.
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby Gosa » Fri Oct 26, 2012 2:08 pm

ገልብጤ!!
በጣም ተደሰትኩበት:: ሌላም በዚህ ደራሲ የተጻፈ ካለ (የራስህ ድርሰት ከሆነም) አስነብበን::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ገልብጤ » Fri Oct 26, 2012 3:12 pm

Gosa wrote:ገልብጤ!!
በጣም ተደሰትኩበት:: ሌላም በዚህ ደራሲ የተጻፈ ካለ (የራስህ ድርሰት ከሆነም) አስነብበን::


እኔም ተመችቶኝ ነው ውደዚህ ያመጣሁት

ስማ እንጂ ያንተን ጸባይ ( ገጸ ባህሪ) ይወክላል መስለኝ ድርሰቱ...
የራስህ ድርሰት ከሆነም


በልሾተል እንዳይሰማህ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby Gosa » Fri Oct 26, 2012 3:38 pm

ስማ እንጂ ያንተን ጸባይ ( ገጸ ባህሪ ) ይወክላል መስለኝ ድርሰቱ


ቅቅቅቅቅቅቅ እኔ መች ከገዳም ወጥቼ አውቅና :: እንኳን እንደዚያ አይነት ሰው ልሆን....እንደዚያ አይነት ህልም እራሱ ባይ አየሁ ብዬ አላምንም:: ያውም ተከትያት
እሙካዬ … እምትሔጂበት ድረስ እየዘፈንኩ ብሸኝሽ ቅር ይልሻል… እ… ? ተወዳዳሪ ስለሌለ እሚያሸንፈኝ አይኖርም…
ልላት? ኖ!ኖ!ኖ!ኖ! ቅቅቅ:: አላወቅከኝም ቅቅቅ::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ገልብጤ » Fri Oct 26, 2012 3:58 pm

ስማ እንጂ ጽጌን ልጎዝጎዝልሽና ሂጅብኝ ብለህ አልነበር እንዴ የምትጀነጅናት .....አይ ሰው የልቡን አድርሶ ላጥ ነው ...ቅቅቅቅቅ
አይ መሬት ላይ ያለ ሰው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby Gosa » Fri Oct 26, 2012 4:19 pm

ገልብጤ wrote:ስማ እንጂ ጽጌን ልጎዝጎዝልሽና ሂጅብኝ ብለህ አልነበር እንዴ የምትጀነጅናት .....አይ ሰው የልቡን አድርሶ ላጥ ነው ...ቅቅቅቅቅ
አይ መሬት ላይ ያለ ሰው

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
ከምር አላልኳትም:: አንተ ራስህ ማለት የነበረብኝን እየሞላህልኝ ነው መሰለኝ የምታነበው ቅቅቅቅቅቅ:: በጣም ከደፈርኩኝ
"ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ ጥሩ አይደለምና" ብሎ እግዚአብሔር ሔዋንን ላዳም ፈጠረለት ብዬ ነው የምጀምረው: ክርስቲያን ብትሆንም ባትሆንም:: ጽግዬንማ ሙቪ ስናይ ነበር'ኮ ....ረስተሀል ግድየለም
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ገልብጤ » Sat Oct 27, 2012 10:38 am


የሰንበት ትምህርት ቤቱ ወጣቶች አንድ የሚያከብሩት ወጣት አለ፡፡ ዮሴፍ ይባላል፡፡ ልክ እንደ ትልቅ ካህን እሱ የሚለው ለእነሱ ሁልጊዜ ትክክል ነው፡፡ የሰንበት ትምህርት ቤቱ መርሐ ግብር እንዳለቀ ወንዶች ሴቶችን መሸኘት ግዴታ ያለባቸው ይመስል በየሴቶች መንደር ይታያሉ፡፡ ጨለም ካለ እና ደፈር ካሉ ሴቷ ትከሻ ላይ እጃቸውን ጣል ያደርጋሉ፡፡ ትንሽ ድፍረት ያላቸው ሴቶች ከሆኑም የእነሱም እጅ ሸኚው ወገብ ላይ ያርፍና አጋርነቱን ያሳያል፡፡ የአንድ ክብሪት እሳት ብቻውን ቤት አቃጥሎ አያውቅም፡፡ ግን ለቃጠሎው ዋና መነሻ ከክብሪቱ በቀር ማን ሊሆን ይችላል? ብዙዎች ለዘላለም በእግዚአብሔር ፊት ለማገልገል ምኞት ነበራቸው፡፡ ግን በማወቅም ባለማወቅም ክብሪቱን ጫሩት፡፡ ቆይቶ ተስፋቸው ተቃጠለ፡፡ ሴቶቹም እንዲሁ በእግዚአብሔር ፊት በክብር ሊያገቡ ከራሳቸው ጋር ጥብቅ መሀላ ነበራቸው፡፡ መሀላው የፈረሰ ቤቱ የነደደ ቀን ይመስላቸዋል፡፡ እነሱ ክብሪት እንደጫሩና እንዳያያዙት አያውቁም፡፡


ዮሴፍ ከዚህ ነፃ ነው፡፡ ነፃነቱን ከክርስትናው ይልቅ ተፈጥሯዊው ትዕቢቱ ሰጥታዋለች፡፡ ወንዶቹ እንዳይስቱ ይመክራል፡፡ ሴቶቹ ከማይሆን ሰው ጋር እንዳይገጥሙ ይመክራል፡፡ ብዙ ሴቶች የፍቅር ደብዳቤ ይጽፉለታል፡፡ ግድም መልስም እንደሌለው ጓደኞቹ ሲያውቁ ግራ ይጋባሉ፡፡ በእነዚህ ሁሉ ሴቶች መሐል ሳይደናቀፍ የሚያልፍ እሱ ማነው? ሴቶች ዝጋታም ብለው የሚሸሿቸው አይነት ወንድ አይደለም፡፡ ተጫዋች ነው ብለው የሚደፍሩትም አይደለም፡፡ ይሄ ልዩ ባህሪው ነው፡፡ አንድ ቀን ይሄን ባህሪውን የሚያናውጽ ነገር ተከሰተ፡፡ ቀኑ ሚካኤል ነው፡፡ ከቅዳሴ ሲወጣ ከሚያውቃቸው ሴቶች ጋር አንዲት ጥቁር እንግዳ አብራ ቆማለች፡፡ ብዙ ሰዎች እንደሚሉት አይነት ልቡ ክው ሲል ይታወቀዋል፡፡ ከተፃፉለት የፍቅር ደብዳቤዎች ውስጥ ቀይ እስክርቢቶ ያደማቸው ብዙ የልብ ስዕሎች ትዝ አሉት፡፡ ለትርጉማቸው ከዚህ የተሻለ ቅፅበት የለም፡፡ጠይም ናት ቀጭን፡፡ ውበት ማለት ጠይም….ቀጭን መሆን ነው ተብሎ ቢታወጅ እንኳን ከዚህ በፊት ብዙ ጠይም ቀጭን ሴቶች ያውቃል፡፡ አይ ሰይጣን ነው፡፡ ብሎ አሰበና “… አሃ ሰይጣን ከዚህ በፊት የት ነበር? ተዋወቁ፡፡ የልቡ ምት በእጁ ወደ እሷ እንዳያልፍ የሰጋ ይመስል ቶሎ እጁን ሰበሰበ፡፡ በቅርበት ሲያያት አገጯን ለሁለት የተከፈለ የሚያስመስል መስመር አለባት፡፡ ይሄ ልዩ ነገሯ ነው ቢባል እንኳን እሱን ቀርቦ ከማየቱ በፊት ነው ልቡን አንዳች የሰነጠቀው፡፡ልጆቹ እንግዳዋን ይዘው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ እያያቸው እሷ እሱ ውስጥ ቀርታ ልቡን ስታንኳኳ እና በስንጥቁ ለመግባት ስትፍጨረጨር ይሰማው ነበር፡፡ያን ቀን ሌላ ዮሴፍ ሆነ፡፡ ኮስታራ፤ ዝምተኛ…….ሰንበት ተማሪው ሁሉ የበለጠ መጨመቱ ነው ብሎ ችላ አለው፡፡ ቤቱ ሲገባም አዲሷ እንግዳ መኝታ ክፍሉ ውስጥ አይኑ በዞረበት ትዞራለች፡፡ ሊያባራት አቅም ያንሰዋል፡፡ የታየችው ግድግዳ ላይ አፍጥጦ ብዙ ሰዓት ከመቆየቱ የተነሳ የዐይኑ ኃይል ግድግዳውን አለመብሳቱ ግንበኛውን ያስመሰግናል፡፡ማንበብ….መቀደስ….መዘመር….. ከባድ ሆኑ፡፡ከባድ የጭንቅ ሳምንት አለፈ፡፡ ብዙ ሴቶች ፍቅር ያዘን ሲሉት በውስጡ ስቋል፡፡ ለእሷ እንዴት ብሎ ፍቅር ያዘኝ ይበላት? ክብሩን ከዚህ በላይ እሹሩሩ ማለት ግን አልቻለም። የት ያግኛት? ያመጧት ሴቶች አድራሻ ወዴት ነው? እያለ ሲጨነቅ ስልኩ ጠራ ፡፡“ሃሎ”“ዮሴፍ?”ዝም፡፡ ከዚህ በፊት ድምፅዋን ሰምቶት ባያውቅም እሷ መሆኗን ወዲያው አወቀ፡፡“ሄሎ” አለች ድጋሚ መልስ ስታጣ“አቤት ማን ልበል?” ኩራቱ እየተናነቀው“ማርታ ነኝ ባለፈው ቤተ ክርስቲያን ተዋውቀን….” እስከ ህይወቷ ፍፃሜ የተሰጣትን ወኔ ያለ ይሉኝታ ዘረገፈችው፡፡“እሽ እንዴት ነሽ?” ልቡ ደም እየረጨ ሳይሆን ደም እያፈሰሰ ድው…ድው…እያለ ምንም ያልመሰለው መስሎ መለሰ፡፡እሷም የዘረገፈችውን ይሉኝታዋን “እ….አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ….” በማለት ሰበሰበች፡፡“ለምን ተገናኝተን አናወራም?” አለ እሱ እንደምንም። ትንሽ ብትዘገይ የትም ስልክ ቁጥሯን ፈልጎ እንደሚደውል እያሰበ፡፡“እሽ” አለች፡፡ተገናኙ፡፡ ጥግ ይዘው ሲያወሩ ሰንበት ተማሪ ሁሉ እንደ ልማዱ እየመከረ ነው ብለው ልብ አላለቸውም፡፡ ሁለቱም ለምን እንደተገናኙ ያውቃሉ፤ ግን ሾላ በድፍን አውርተው ተለያዩ።በሚቀጥለው ቀን እሱ ሰበብ አዋጣ፡፡ “ትናንት ስላወራነው ነገር በደንብ የሚያብራራ መጽሐፍ አገኘሁ የት እንገናኝ ላውስሽ ነበር…” ተገናኙ፡፡ሾላው ዛሬም እንደተደፈነ ነው፡፡እንደገና በቀጣይ ቀን……..ሁለቱም ልብ ውስጥ ፍቅር ተተክሎ ስር እየሰደደ እየሰደደ….ሄደ፡፡ዮሴፍ እሷን አግብቶ ለመኖር ቆረጠ፡፡ ቀጥታ እንዴት ይጠይቃት? ተፈጥሯዊ ኩራቱ ይፈታተነዋል፡፡አንድ ቀን እንደተለመደው በድፍኑ ሲያወሩ ሲያወሩ…ማርታ ድንገተኛ ጥያቄ አመጣች፡፡“አንዲት ሴት ዲያቆን ለማግባት ምን መሆን አለባት?”“ማለት?” ልቡ ደም መርጨቷን ትታ ማፍሰሷን ተያያዘችው፡፡“ማለትማ ምን ማሟላት አለባት፡፡”“ክርስቲያን መሆን አለባት፡፡” የውሸት እየሳቀ፤ የጥያቄዋ አቅጣጫ እያስደነገጠው፡፡“ሌላስ?” ድፍኑ ሾላ ሰልችቷታል፡፡ጭንቅ እያለው “ሌላ ያው ልጃገረድ መሆን ይኖርባታል” አለ የሞት ሞቱን፡፡የማርታ ፊት ልውጥውጥ አለ፡፡ የተከፈለው አገጯ ፊቷን ሙሉ ለሙሉ የከፈለው ይመስል፡፡ ስቃዩዋንና የተሰማትን ስሜት ለመደበቅ ስትጥር ባለ ሁለት መልክ ሆነች፡፡ዮሴፍ ገባው፡፡ በነፍሱ ሰይፍ አለፈ፡፡ ወሬ ቀየሩ፡፡ ሾላው መልሶ ተደፈነ፡፡ ነብሱ ሙግት ውስጥ ገባች፡፡ ስለ እሷ ማሰብ ማቆም አልቻለም፡፡ ልክ እንደ ወፍ በፊቱ ብር….ብር ትላለች፡፡ ግን ክህነቱስ? ያን ሁሉ ሰንበት ተማሪ የመከረበት ብርታቱ የት ሄደ? መጽሐፍ ቅዱስ ሲገልጥ አንድ ቃል ብቻ ጎልቶ ይታየዋል፡፡ መፅሐፊ ኢዮብ ምዕራፍ ፬ “እነሆ አንተ ብዙዎችን ታስተምር ነበር፡፡ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፡፡ ባንተ ሲደርስ ግን ደከምክ…፡፡ ወፊቱ አሁንም ውስጡ ክንፏን እያርገበገበች ልቡን ታደማለች፡፡ ደሙን ብቻውን ያብሳል፡፡ ሰው አብረው አያያቸውም፡፡ ግን ከእሱ ተለይታ አታውቅም፡፡ እሷ የልቡን በር በክንፏ ያለማቋረጥ ትደበድባለች፡፡ ቁልፉ ግን በጭካኔ ባህር ላይ ተጥሏል፡፡
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ገልብጤ » Sat Oct 27, 2012 11:08 am

ፎቶግራፎቹ


ከአቢጃን ተነስቶ ካልካታ ከገባ 3ኛ ቀኑን ይዟል፡፡ ይህች በህዝብ የተጨናነቀች ታላቅ ከተማን እንደረገጠ የካልካታ ተወላጅ የሆኑት የ10ኛ ክፍል ህንዳዊ መምህሩ ስለዚህች ከተማ በአድናቆት የተናገሩትን አስታወሰና ቃላቱን በውስጡ አነበነበው ‘KALKATA IS A BIG CITY WHEN YOU THROW A STONE FROM THE SKY IT WILL NOT REACH TO THE GROUND’ (ካልካታ ታላቅ ከተማ ናት ከሰማይ ድንጋይ ብትወረውር ሰው ላይ ነው የሚያርፈው) ያሉት አባባል ትክክል እንደሆነ ተገነዘበ፡፡


አሁን የመጣበትን ጉዳይ ከውኖ ከተማዋን ለቆ ሊወጣ ነው፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ሆድን ጠርቀም አርጐ የሚይዝ ምግብ ተመገበና የሚወስደውን ነገር በጥንቃቄ ወስዶ፣ ወደ ካልካታ አውሮፕላን ጣቢያ አመራ፡፡ ሰፊውንና ረጅሙን የመስታወት በር አልፎ ገባ፡፡
የአዳራሹ መስክ በመንገደኞች ተሞልቷል፡፡ ሰልፍ ያዘና አነስተኛ ሻንጣውን አስፈትሾ ወደ መንገደኞች መቆያ ክፍል ከገባ በኋላ፣ ወንበር ላይ ተቀምጦ የበረራ ፕሮግራም የሚያሳየውን ሰሌዳ ተመለከተ፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ..በረራ ቁጥር..... በአዳራሹ ውስጥ ያለው የድም ማጉያ ጐልቶ ተሰማ ..ሲንጋፖር፣ ካራቼ፣ ኢስታንቡል፣ ካይሮ፣ አዲስ አበባ፣ አቢጃን፣ ሎሜ በሉፍታንዛ መስመር.... ተጓዦች... በረራ ቁጥር..... ተናጋሪዋ መልእክቱን በተለያዩ ቋንቋዎች አስተላለፈች፡፡
ዴቪድ ከሌሎች ተጓዥ መንገደኞች ጋር ቀለል ያለ የጉዞ ሻንጣውን እንደያዘ መተላለፊያውን ተሻግሮ ወደ አውሮፕላኑ ካመራ በኋላ ወንበሩን በዓይኑ አማተረና ቦታውን ያዘ፡፡
አውሮፕላኑ ጉዞውን እንደጀመረ በእፎይታ ተነፈሰ፡፡
እንዲህ አይነት ረጅም አሰልቺ፣ አደጋ የተሞላበት ጉዞ ሲያደርግ ለ3ኛ ጊዜ ነበረ፡፡ ሆኖም ይህኛው የጉዞ መስመር ትንሽ ረዘም ያለ መስሎ ተሰማው፡፡
ይህን መሰል አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ሊገባ የቻለው ለሚስቱ ባለፈው ከፍተኛ ፍቅር ነው፡፡
ከአራት ዓመት በፊት እርሱ ለአንድ ሳምንት የሰርከስ ትርዒት ለማቅረብ በመጣ ጊዜ ነበር ከባለቤቱ ከኢሌኒ ጋር የተዋወቀው፡፡ የኢሌኒ ማራኪ ቁመና፣ ቸኮላት መልክ፣ ረጅም ፀጉርዋና ዳሌዋ የዴቪድን ቀልብ ከሳቡት ክፍሎችዋ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በአንድ ሳምንት ቆይታው ሁለቴ የእራት ግብዣ አድርጐለት፣ ቤቷ ድረስ እያደረሰ በኮንትራት ታክሲ ሆቴሉ ያመራ ነበር፡፡ ወደ ሀገሩ በተመለሰ ጊዜ በየሳምንቱ እየደወለ ሲጠይቃት ከርሞ ወደ ሀገሩ እንድትመጣ ፈቃደኝነትዋን በገለፀችለት ጊዜ፣ አባቱን አግባብቶ አስፈላጊውን መሰናዶ አድርጐ በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ጠቅልላ ወደ አቢጃን እንድትመጣ አደረጋት፡፡
ዴቪድ ከባለፀጋ ቤተሰብ መሃል የተገኘ ለቤተሰቡ ብቸኛ ልጅ በመሆኑ ተሞላቆ ነበር ያደገው፤ በወጣትነት እድሜው ከበርካታ ሴቶች ጋር የነበረው ግንኙነትና ያለአግባብ ገንዘብ አባካኝ መሆኑ አባቱን በጣም ያስከፋው ስለነበር፣ አሁን በፍቅር መውደቁን አባቱ ሲሰማ ተደስቶ በጋብቻ እንዲታሰር አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ጋብቻ እንዲያደርጉ አስችለውታል፡፡
ሆኖም ዴቪድ ከሀገር ሀገር ኢሌኒን ለማስደሰት እየዞረ ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚያባክን፣ ለርሱ ሲል ጊዜና ገንዘባቸውን ማባከን እንደሌለባቸው የተረዱት ሚስተር ኦሊሴ፤ በካንሰር ህመም ተሰቃይተው ከመሞታቸው በፊት ከፍተኛ አክሲዮን ያላቸውንና በዋና ሥራ አስኪያጅነት ይመሩት የነበረውን ኢንሹራንስ ድርጅት ድርሻ ለታናሽ ወንድማቸው ሲሶውን ድርሻ እንዲያስተዳድሩና እንዲመሩ በፍርድ ቤት በመሰየም ሲያዞሩ፣ አንድ አራተኛውን ድርሻ ደግሞ ለዴቪድ በደሞዝ መልክ እንዲከፍለው ያደረጉ ሲሆን፤ ሙሉ ድርሻው በስሙ እንዲዞር አድርገው ነበር የሞቱት፡፡
ዴቪድ ከቀለም ትምህርት ይልቅ በአስደናቂ ትርዒቶችና በሰርከስ ትእይንቶች ይመሰጥ ስለነበር ገና በ15ኛ እድሜ ላይ ሳለ ከአንድ የሰርከስ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ገባ፡፡ ወደ ሃያዎቹ አካባቢ ሲጠጋ በጣም የተዋጣለት ኳስ አንቀላላቢ JUGGLER በመሆን ..ዴቭ THE JUGGLER” የሚል ቅል ስም ሲሰጠው፣ ከጓደኞቹ መሃል እጅግ ደፋር በመሆኑ ብዙዎቹ የማይደፍሩትን ጩቤ መሰል ረጅም ስለት በጉሮሮው በመላክ፣ እስከ ሆድ ዕቃው ድረስ በማዝለቅ አስደናቂ ትእይንቶችን ያቀርብ ነበር፡፡
ሆኖም አባቱ እንዲህ አይነቱን አደገኛ ትእይንት እንዲያቆም ቢመክሩትም አሻፈረኝ በማለቱ ለህይወቱና በማንኛውም ነገር ሊደርስበት ለሚችለው አደጋ ከፍተኛ የሆነ የኢንሹራንስ መድህን ለመግዛት ተገደዋል፡፡
ዴቪድ፤ እናቱ ገና የ11 ዓመት ልጅ እያለ ነው በመኪና አደጋ የሞቱት፡፡ አሁን እድሜው 28 ዓመት ሆኖታል፡፡ ልብ እየገዛ መምጣት እንደጀመረ አባቱ በካንሰር ህመም ተሰቃይተው ሞቱ፡፡
ይህ ከሆነ 10 ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡
አሁን የባለቤቱ ኢሌኒ እናት በጭንቅላት ዕጢ ህመም እየተሰቃዩ እንደሆነ ከሚወዳት ሚስቱ ተረድቷል፡፡ እርሳቸውን ለማሳከም ወደ 40ሺ ዶላር ገደማ እንደሚያስፈልግ ሚስቱ ነግራዋለች፡፡ እርሱ እናቱን ልጅ እያለ አጥቷል፤ የኢሌኒን እናት እንደ እናቱ ሊያያቸው ይገባል፡፡
አንድ ቀን አጐቱ ኦቻና ዘንድ ሄደና ከድርሻዬ ላይ የሚታሰብ 40ሺ ዶላር ስጠኝ ብሎ ያጋጠመውን በሙሉ አወያየው፡፡ አጐቱ ኦቻና ግን ሙሉ ለሙሉ እምቢ ባይለውም አንድ የማግባቢያ ሃሳብ አቀረበለት፡፡ ..አንተ በጉሮሮህ አሾልከህ ሆድ ዕቃህ ድረስ ረጅም ስለት ሰደህ ማስቀመጥ ትችላለህ ይህን ተሰጥኦህን ለምን በብር አትቀይረውም፡፡ የተወሰኑ ሀገሮች በመሄድ በሆድህ ውስጥ ዕቃ ቀብረህ ትመጣለህ፤ ከአራት ጊዜ በላይ ያልበለጠ ጉዞ አድርገህ ከ25ሺ ዶላር በላይ ታገኛለህ፡፡ የተቀረውን እኔ እሞላና የህክምናው ወጪ ይሸፈናል.. የሚል ድርድር አቅርቦለት ተስማማ፡፡
የአሁኑ በረራው ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው - ዴቪድ፡፡ አንድ ተጨማሪ በረራ ከዚህ ረጅም ጉዞ በኋላ ይጠበቅበታል፡፡ በረሃብ እየተሰቃየ፣ አደጋ እየተጋፈጠ ...ሦስተኛውን ጉዞ በድል ሊወጣ 10 የሚሆን ተጨማሪ ሰዓት ብቻ ይቀረዋል፡፡ ረሃብና ድካም ቢጠናበትም በፍቅር ሁሉ ነገር ይቻላል ሲል አሰበ፡፡ እስካሁን ለ34 ሰዓታት ያለ ምግብና መጠጥ ተጉዟል፡፡
እቤቱ እንደገባ በእቅፉ ስር አድርጓት፣ ለስላሳ ፀጉርዋን እያሻሸ በከንፈሩ እየዳበሰ ደረቱ ላይ ልጥፍ አድርጐ በስሜት ሰመመን አብሯት ሲዳክር፣ ለእርሷ ብቻ እንደሚኖር ተሰማው፡፡
የበረራ አስተናጋጆች በጋሪ የሚገፉ ምግብና መጠጥ ይዘው መለስ ቀለስ ሲሉ፣ በረሃብ የታጠፈ አንጀቱን እንደቆለፈ፣ ለመብላት እየጐመጀ አለፈው፡፡
አዲስ አበባ የሚወርዱ ተጓዦች ጥቂት ነበሩ፡፡
ከአውሮፕላኑ እንደወረደ ከአጐቱ የተነገረውን መልእክት አስታውሶ፣ ቦሌ ኤርፖርት ውስጥ ካለ ለንደን ካፌ ውስጥ ገባ፡፡
በዚህ ካፌ የምታስተናግድ ቅድስት የተባለች ወጣት አስጠራና፣ ካነጋገራት በኋላ የሞባይል ስልኳን ተውሶ አዲስ አበባ መድረሱን አቢጃን ላለው አጐቱ መልእክት አስተላለፈ፡፡ ከዚያም 50 ዶላር በጉርሻ መልክ ጭምር ሰጣትና ወደመንገደኞች መጠባበቂያ ክፍሉ አመራ፡፡ ለተወሰኑ ደቂቃዎች እንደተቀመጠ ቅድስት የመንገደኞች መጠባበቂያ አቋርጣ፣ ወደ አንድ ክፍል የሞባይል ስልክ እያወራች ስታመራ ተመለከተ፡፡
መልኳ፣ ፈገግታዋና አካሄዷ ሁሉ ቁርጥ ኢሌኒን መስላ ታየችው፡፡
ከ15 ደቂቃ በኋላ ሁለት የፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ሰዎች እርሱ ወዳለበት ቦታ ሲቀርቡ ተመለከተ፡፡
ሰላምታ ካቀረቡለት በኋላ ለጥያቄ እንደሚፈልጉት ፈቃደኝነቱን ጠይቀው እንደተስማማ አጅበውት ኤርፖርት ውስጥ ካለ አንድ ክፍል ውስጥ ወሰዱት፡፡
አራት በአራት ሜትር ከምትሆን መለስተኛ ክፍል ያለ መቶ አለቃ፤ ..በኢትዮጵያ የአደንዛዥ ዕ መከላከያ ግብረ ሃይል..... በማለት ራሱን አስተዋውቆ በቀጥታ ወደ ጉዳዩ ገባ፡፡
..በመጀመሪያ ስምህን ብትገልልን?..
..ዴቪድ ኦሊሴ.. ግራ በመጋባት መለሰ፡፡
..ከየት ነው የተሳፈርከው?..
..ለምንድን ነው የምትጠይቁኝ ምን የተፈፀመ ወንጀል አለ?..
በምን ሊያገኙኝ ይችላሉ ብሎ አሰበና ..ከጉዞ ማህደሬ ላይ ፈልጉ.. አለ፡፡
..ይገባሃል ሚስተር ዴቪድ፤ እዚህ የትራንዚት ቆይታህ እንደሚገባኝ ሁለት ሰዓት አይበልጥም... ስለሆነም ከኛ ጋር ቀና ትብብር ካደረግህ አውሮፕላኑ ሳያመልጥህ ጉዞህን ትቀጥላለህ.. አለ መቶ አለቃው፡፡
..እሺ... ከካልካታ ነው የተነሳሁት..
..ከዚህ ቀደም እዚህ አዲስ አበባ ትራንዚት አድርገህ ታውቃለህ?..
..አዲስ አበባ ውስጥ ትራንዚት ማድረግ ተከልክሏል እንዴ?..
..አይደለም ሚስተር ዴቪድ፤ አንተ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁለት ወር ውስጥ ትራንዚት ስታደርግ ለሦስተኛ ጊዜህ መሆኑ ጥቆማ ደርሶናል፡፡ ...በዚህ ላይ የምትመጣባቸው መስመሮች ተመሳሳይና በአደንዛዥ ዕ ዝውውር የወንጀለኛ መቅጫ ህጋቸው ቀላልና አደንዛዥ ዕ የሚተላለፍባቸው ሀገሮች ናቸው፡፡ ...በዚህ ላይ አንተን ስናጤንህ ታላቅ ድካም የርሃብ ስሜትና የመቅበጥበጥ ሁኔታ ስላየንብህ ነው ያስጠራንህ፡፡ ....በዚህ ላይ ጥቆማም አለብህ፡፡..
..ድካም ያለበትና የሚቅበጠበጥ ተጓዥ ወንጀለኛ ነው ማለት ነው?..
..የለም... የለም ምግብም ሆነ መጠጥ አልቀመስክም... ያ ደግሞ ትንሽ ሆድህ ውስጥ ምናምን ስላለ ሊሆን ይችላል፡፡ ...ስለዚህ ትኩስ ነገር ጠጣና ወደ መጣህበት ተመለስ፡፡.. መቶ አለቃው ትእዛዝ አዘል በሚመስል ቃና ተናገረ፡፡
..የለም... ምንም ነገር አልወስድም ፆመኛ ነኝ፡፡ አመሰግናለሁ..
ዴቪድ ፊት ላይ ድንጋጤ መታየት ጀምሯል፡፡
ትኩስ ነገር እንድትጠጣ ትገደዳለህ፡፡ ...ያለዚያ ግን ወስጥሀን በጨረር ለማየት እንገደዳለን፡፡ መቶ አለቃው ፍርጥም ብሎ ተናገረ፡፡
በዚህን ጊዜ ዴቪድ ብድግ ብሎ ተነሳና ..መብቴን እየጣሳችሁ ነው... እከሳችኋለሁ... አይሆንም፡፡ ወደ ኤምባሲዬ እደውላለሁ..... አለ ድምፁ መቆራረጥ ጀምሯል፡፡
..ኤምባሲዎችህ በፍተሻው ይስማሙበታል.. አለ መቶ አለቃው ኮራ ብሎ፡፡
ዴቪድ ለአፍታ ራሱን አረጋጋና ሁኔታውን ለማጤን ሞከረ፡፡
ፖሊሶቹ እንደማይለቁት ተረዳ፡፡ ምግብና ውሃ ከቀመሰ 35 ሰዓታት ሆነውታል፡፡ እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ለማደር ርሃብና ድካሙ አስገድደውታል፡፡ ሆድ እቃው ላይ ያለው ጥቅል የህመም ስሜት ፈጥረውበታል፡፡
ከአንድ ሰዓት በኋላ የጨረር ምርመራ ከአካሄደ በኋላ ቀዝቃዛ ዘይትማ ነገር በፌዴራል ፖሊስ ሪፈራል ህክምና ማዕከል ከጠጣ በኋላ በስስ ላስቲክ የተጠቀለለ 640 ግራም የሚመዝን ክኒን መሰል በሰገራ መልክ ከሆዱ ወጣ፡፡ የላብሯተር ውጤቱ ክኒኑ ኤሜታፊን የሚባል አደገኛ ዕ መሆኑን አስረዳ፡፡
በሳምንት ውስጥ ዴቪድ ኤሜታፊን የሚባል ዕ በሆድ ውስጥ ከቶ ለማዘዋወር ሲሞክር መያዙን አስመልክቶ ክስ ተመሰረተበት፡፡
ክሱ በሚሰማበት ወቅት ዴቪድ በጠበቃው አማካኝነት አባቱ ድንገት መሞቱን፣ ኢትዮጵያዊ ሚስት እንዳለውና የባለቤቱ እናት በጭንቅላት እጢ እንደሚሰቃዩ ጠቅሶ፣ ለህክምና ወጪ ማሟያ ሲል ወንጀሉን መፈፀሙን አምኖ ቅጣቱ እንዲቀልለት አመለከተ፡፡
አቃቤ ሕግ በበኩሉ የተያዘበትን ኪኒንና የሰው ማስረጃዎች እንዳለው ገልፆ፣ ተከሳሹ በተደጋጋሚ ጊዜ በአዲስ አበባ ትራንዚት ያደርግ እንደነበር፤ የጉዞ ማስረጃውን አያይዞ ከባለፀጋ ቤተሰብ የተገኘና የገንዘብ ችግር የሌለበት፤ በቂ ትምህርትና እውቀት እንዳለው ጠቅሶ፣ የባለቤቱ እናትም ምንም የጤና ችግር የሌለባቸው መሆኑን በማስረጃ አስደግፎ በማቅረብ፣ ተከሳሹ ሴሰኝነት የተጠናወተው በመሆኑ ብቻ ወንጀሉን ሊፈም እንዳነሳሳው በማስረዳት፣ ቅጣቱ እንዲከብድበት ሲል ፍርድ ቤቱን ጠየቀ፡፡
ዳኛው ግራና ቀኙን ለአንድ ዓመት ያህል ከሰሙ በኋላ ተከሳሹ የታሰረው ጊዜ ታሳቢ ሆኖ በአምስት ዓመት ኑ እስራት እንዲቀጣ ወስነው ፋይሉን ዘጉ፡፡ ዴቪድ እስር ቤት ሳለ አንድ ጊዜ ባለቤቱ ከአቢጃን መጥታ ስትጐበኘው፣ አልፎ አልፎ በተለያዩ ሰዎች እያስላከች ስንቅና ገንዘብ ታቀብለው ነበር፡፡
ዴቪድ በእስር ቆይታው የሚከነክኑት አንዳንድ ነገሮች ቢኖሩም፣ አቃቤ ሕጉ የባለቤቱ እናት ፍፁም ጤነኛ እንደሆኑ መግለፁ ሲያብከነክነው የቆየ ጉዳይ በመሆኑ፣ ከእስር ቤት እንደተፈታ በቀጥታ ያመራው ወደባለቤቱ እናት መኖርያ ቤት ነበር፡፡ የኢሌኒ እናት መኖሪያ ቤት ከ7 ዓመት በፊት አዲስ አበባ እያለ ከሚያውቀው በላይ እጅግ የተዋበ ሆኖ ሲያገኘው፣ የእናትየው ጤንነትም የተሟላና ከራስ ምታት ውጪ ምንም ነገር ሆነው እንደማያውቁ ከአካባቢው መረጃ ለመሰብሰብ ችሎ ነበር፡፡
ሆኖም በነገው እለት ወደ አቢጃን ከመብረሩ በፊት የኢሌኒ እናትን በአካል አግኝቶ ሊጠይቃቸው ወሰነ፡፡
የግቢያቸውን በር አንኳኩቶ ተከፍቶለት እንደገሃ የባለቤቱ እናት ከአቢጃን የመጣ እንግዳ በመሆኑ ብቻ ድንገት ለመጣው እንግዳ መስተንግዶ ለማድረግ ከቤት ውስጥ አስገብተው ሽር ጉድ ማለት ጀምረዋል፡፡
ዴቪድ ለርሳቸው ጤንነት ሲል ወህኒ ቤት 5 ዓመት እንደቆየ ቢረዱ ምን ሊያደርጉለት እንደሚችሉ ለመገመት አላስቸገረውም፡፡ በወህኒ ቤት ቆይታው አማርኛ አቀላጥፎ ለመናገር በመቻሉ ከኢሌኒ እናት ጋር ለመግባባት አልተቸገረም፡፡
ዴቪድ ጤንነታቸው መልካም እንደነበረ ከርሳቸው አንደበት ለመረዳት ችሏል፡፡ ግን ለምን ይህን አደረገች? እያለ ቤቱን ቃኘት ሲያደርግ፣ ሳሎን ውስጥ በፍሬም የተሰቀለ የኢሌኒንና የአንዲት ሴት ፎቶ ተመለከተ፡፡ ከጐንዋ ያለችውን ሴት የት እንደሚያውቃት አሰላሰለና በቀላሉ ለያት፡፡ ፍፁም ከኢሌኒ ጋር የምትመሳሰለው ለንደን ካፌ የምትሰራው ሞባይል ያዋሰችው ቅድስት!
አሁን ልቡ መደንገጥ ጀመረ፡፡ በአግራሞት ወደ ኋላው ማብሰልሰል ያዘ፡፡ አንዳንድ ትእይንቶች እየተቆራረጡ ይመጡበት ጀመር፡፡ እርሱ አዲስ አበባ ገብቶ ስልክ ለምን መደወል አስፈለገው? ይህች ሴት ደግሞ በቀጥታ ወደ ኤርፖርት ፖሊሶች ክፍል ለምን መጣች? ለዚህ መልስ ገና ሌላ ጥያቄና ፈተና ያሻዋል፡፡ በዚህ ጥያቄ ግራ እየተጋባ ሳለ ከጠረጴዛው መስታወት ስር ካለ የፎቶ አልበም ላይ አይኑን ተከለ፡፡ አልበሙን አንስቶ ገና ከመግለጡ በድንጋጤ ይበልጥ ፎቶውን አቅርቦ መመልከት ቀጠለ፡፡ አሁንም ሲገልጥ የበለጠ የሚያስደንቁ ትእይንቶችን ከፎቶው አልበም ውስጥ ተመለከተ፡፡ የገዛ ትንፋሹ ሲሞቀው ልቡ በሃይል ሲመታ፣ ሰውነቱ ሲርድ እልህ፣ ቁጭት፣ ንዴት፣ በቀል፣ ድንጋጤ፣ ብቸኝነት፣ ክህደት፣ ውርደት፣ ሀዘን ተሰማው፡፡ ያየውን ማመን አቅቶት ደጋግሞ እየገለጠ አስተዋለው፡፡
አጐቱ ኦቻናና ባለቤቱ ኢሌኒ ሲሳሳሙ ሲዝናኑና ሲሳሳቁ፤ ቀለበት ሲያደርጉ የሚያሳይ ፎቶግራፍ ነበር፡፡ ዋና አስረጅ ይሆኑኛል ያላቸውን የተወሰኑትን የኢሌኒ እናት ሳይመጡ ፈጠን ብሎ ከአልበሙ ላይ መዞ አወጣና ከጃኬት ኪሱ ውስጥ ከተታቸው፡፡
አሁን ያልተሟሉ ጥያቄዎቹ በራሳቸው ጊዜ መልሳቸውን ይዘው መጡ፡፡ እንደኔ አይነት ጅልና ሰው አማኝ በአለም ላይ ሊኖር አይችልም አለ፡፡ ለራሱ እየተቆራረጡ የመጡት ትእይንቶች በስርአት እየተደረደሩ መጡለት፡፡
ኢሌኒና አጐቱ በምስጢር እንደሚገናኙ ያውቅ ነበር፡፡ ነገር ግን በርሱ የወደፊት እጣና ብኩንነት ዙሪያ ሊወያዩ እንደሆነ የሰማውን አምኖ ተቀብሏል፡፡ ረጅም የጉዞ መስመር መጠቀሙ በፕላስቲክ የተጠቀለለው ኪኒን ሆዱ ውስጥ እንዲፈነዳና እንዲሞት ታስቦ እንደሆነ ገመተ፡፡
አባቱ ለህይወቱና ለጤንነቱ የገባለት ከፍተኛ ኢንሹራንስ እርሱን ለአደጋ በማጋለጥ እንዲሞት ሲደረግ፣ ባለቤቱ ኢሌኒ እንድትወርሰው፤ ከዚያም አጐቱና ባለቤቱ ሊጋቡ አስበው እንደሆነ ገመተ፡፡
የባለቤቱ እናት ታመዋል መባሉ ለዚህ አደጋ ለበዛበት ረዥም ጉዞ እርሱን አደጋ ውስጥ በመክተት ለሞት እንዲዳረግ ታስቦ መሆኑንም ተገነዘበ፡፡ ይህን ሁሉ አደገኛ ሁኔታ በድል ለመወጣት ዳር ላይ ሲደርስ በእህቷ ቅድስት አማካኝነት ተጠቁሞ የመያዙ ሴራ፣ የነርሱ ውጥን እንደሆነ አሰበ፡፡
እናትየው ዘና እንዲል ገባ ወጣ እያሉ አጫወቱትና ነገ እንደሚመለስ ነግሮአቸው ያቀረቡለትን ቡና ጠጣና አመስግኖ ከቤታቸው ወጣ፡፡
ነገ ጉዞ ወደ አቢጃን ያደርጋል፡፡ ይህን ፎቶግራፍ ያባዛል፡፡ ለኢሌኒና ለአጐቱ ይልካል፡፡ ከርሷ ጋር ፍቺ ይፈማል፡፡ አባቱ የጣሉበት የ5 ዓመት የውርስ ገደብ ይነሳል፡፡ ይህን ሁሉ በቤተሰቡ ጠበቃ አማካኝነት ይፈማል፡፡ እስር ቤቱና ፎቶግራፉ አጠንክረውታል፡፡ አሁን ያሻውን ማግባት ይችላል፡፡ የበርካታ መልካም ሴቶች ግፍ ነበረበት፡፡ አንዷን ይበልጡኑ ከአንጀቷ የምታፈቅረውን ሉቺያን ያገባል፡፡
ከእንግዲህ ያለ ምግብ አደጋ ያለበት ጉዞ አያደርግም፡፡
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ገልብጤ » Sat Oct 27, 2012 4:47 pm

ፍቅር እና ጉዞው


ለሁለተኛ ጊዜ ያፈቀርኩት ሀይገር ባስ ውስጥ ነው፡፡ ፍቅርና ጉዞ አንድ ናቸው፤ ሁለቱም ያስከፍላሉ፣ ሁለቱም ያደርሳሉ፡፡
ትላንትና ምሽት ሀይገር ባስ ውስጥ ሳለሁ የጀምስ ጆይስ መፅሀፍ ከሆነው “A portrait of an artist as a young man” ውስጥ በገፅ አርባ አምስት ላይ ያነበብኳትን አንቀፅ በአዕምሮዬ እያውጠነጠንኩ ነበር፡፡ በባሱ ውስጥ የተለያየ ሰው እየገባ ነው፡፡ የሹፌሩና የረዳቱ ምርጫ ቢሆን ካጠገቤ ላለው ወንበር ከፍዬ ብቻዬን ብቀመጥ እወድ ነበር፡፡ አልሆነም …፡፡ ካጠገቤ አንዲት ወጣት መጥታ ተቀመጠች፡፡ እንደተቀመጠች ይዛው የነበረውን መፅሀፍ ገልጣ ማንበብ ጀመረች፤ የአይኖቼ ብሌን ተቅበዘበዙ፡፡ ቃላቶች የጠገቡ ገፅ ሊመለከቱ ከመፅሀፉ ደፍ ስር ደጅ ጠኑ …
“… each man has his own particular paradise. For you, Paradise will be stocked full of books and big demijohns of ink. For someone else it will be full of casks of wine, of rum and brandy … for me paradise is this; a little perfumed room with gray colored dresses on the wall, scented soaps, a big bed with a good springs, and by my side the female of species…”

ከመፅሀፉ ጋር ግጥሚያ የፈጠርኩ መሰለኝ፡፡ የመጀመሪያዋን አንቀፅ አንብቤ እንደጨረስኩ ከመቀፅበት ቀና ብዬ ልጅቷን አየኋት፡፡ እጅግ በረዘሙ የአይን ሽፍሽፍቶች ብሌኖቿን ከአለም ደብቃ በዚህ ረቂቅ መፅሀፍ ውስጥ የተሰደደች ሴት ሆና አየኋት፤ የጉንጮቿ ግለት ከፀሀይ ንዳድ ሳይሆን፣ ከንባብ ጡዘት ያበራዩ የስሜት ቀለም እንደሆኑ አምኜ አየኋት፤ ተጠንቅቄ ቀልቤን ሳልለቅ፡፡ አይኔ ፈጠነብኝ … አምልጦኝ የተፈጥሮን ህግ ጣሰብኝ … አይኔ አፍ ሆነ … አወራ፡፡
“ላንቺ ገነት ምንድን ነው?”
መጠየቄን ያወቅሁት ቀና ብላ ከዚህ ቀደም ለሰው ልጅ ፍጥረተ አለም በሙሉ እንግዳ በሆነ አስተያየት ስታየኝ ነው፡፡ እንግዳ የሆነ አይን፤ ልቤ ድረስ ገብቶ ሸረከተኝ፡፡ እይታዋን አመለኩት፡፡
“ለምንድን ነው የጠየከኝ?”
“እኔጃ”
“ምን አልባት ገነት የምትለው የማስገጃ ቃል ባንተ መልስ ውስጥ ቢኖርስ?”
“ያልመለስኩልሽ፤ ቃላቶቼን ፈልጌ እስካገኝ ነው”
“ምን አልባት ቃላቶችህ እኔ ብሆንስ?”
“አንቺ ማነሽ?”
“ማንነቴ እንግዳ ከሆነው ስሜትህ አላቆህ ወደኔ ያመጣህ የራስህ መንፈስ ነው”
“ጥያቄዎቼን እየመለሽልኝ ነው…?”
“መልሶችህን በጥያቄህ እየነገርከኝ ነው”
መልሳ ወደ መፅሀፉ አቀረቀረች፡፡ ከኮተቤ ነበር ሀይገር ባሱ የተነሳው፣ አሁን ላምበረት ደርሷል፤ ልቤ ግን በጊዜ ቀመር ውስጥ ቀጥ ብሎ ከስርቻው ቆሟል፡፡ አሁንም ደግሜ አቀርቅራ ያለችውን ሴት አየኋት፤ ፀጉሯን አየሁባት (ጥቁር ፏፏቴ)፣ ገብቼ እንዳልሰምጥ አይኔን ከጥቁሩ ማዕበል ውስጥ አንቦጫርቄ አወጣሁት፡፡ በልቤ ላይ አይሆኑት መብረቅ ጣለችብኝ … ከየትም ያልተጀመረ ወሬ ትቀጥል ጀመር …
“አሁን ምን አልባት የማንበቢያ ጊዜዬን እየቀማህኝ ነው፣ እየቀማህኝ ያለውን ደግሞ ታውቃለህ፤ ፍቃድህ ከሆነ ሀሳብህን ከላዬ ላይ አንሳልኝ፤ ካልሆነ ዝም ብለህ አውራ፣ እኔም ላንብብ፤ በቃላቶችህ ተደብሬ ቢሆን ከቀደሙት ፌርማታዎች በአንዱ ወርጄ ሌላ መኪና በያዝኩ ነበር፡፡ ሆኖም የተመቸኝ እንግድነትህ ፍፁም በሆኘው ሀሳብህ ስለተመታ በራስህ መራቅህ እየሳበ ያመጣህቀ ከኔ ነው፤ ከኔ ላይ ውረድ፡፡”
“ቀና ብላ አየችኝ፡፡ ምዕራፎቿን በሙሉ ወደድኳቸው፣ ምዕራፎቿ ሁሉም ተሰባስበው የኔን መቅድም አጥፍተው መውጫዬ ላይ ሰቀሉኝ፡፡ የመውጫዬ ቃላት የተገመቱ እንደሆኑ የነገረችኝ እሷው ናት … ባይኖቿ ነው የነገረችኝ፡፡
“ደግሜ ላገኝሽ እፈልጋለሁ?”
“አሁንስ ደግመህ አግኝተህኝ እንዳልሆነ በምን አወቅህ?”
“ልከተልሽ እሻለሁ … የምትሄጂበትን እየረገጥኩ…”
“ታዲያ አንተ ለምን ትቀድመኛለህ”
“ስምሽ ማነው?”
“እመነኝ በዚህ ሰዓትና ቦታ ላይ ባንተ የተፈጠርኩ ሰው ነኝ … ስሜን ልታወጣልኝ የሚገባህ አንተ ነህ”
“ሚስጥረ አልኩሽ”
“እንዳልክ ይሁን”
እስራኤል ኤምባሲ ጋር ደረስን፤ ልቤ ላይ ቀልጣለች ሚስጥረ፣ ልቤን እያደሰችው ነው፡፡
“የት ነው ሰፈርሽ?”
“ወሰን ግሮሰሪ”
“ደግሜ ላገኝሽ እፈልጋለሁ?”
“የምታወራው ማንን እያዳመጥክ ነው?”
“ሁሉንም…”
“ችግሩ ሁሉም ውስጥ ያልሆንኩትን እኔን ማድመጥ ያቃተህ ጊዜ ነው”
ዝም ብላ አየችኝ፡፡ እንዳያት ብቻ የምታወራ እንዳይመስለኝ፣ አተኩሬ የፊቷን ብልቶች በሙሉ አደመጥኳቸው፡፡
“አሁንስ የምልህ ገባህ?”
“ገባኝ”
መገናኛ ስንደርስ ሁለታችንም ወረድን፡፡ ምንም ቃላት ሳንሰጣጥ እስከ ሀያ ሁለት ሰፈር ተጓዝን፡፡ ቃላት! ምንድናቸው ቃላት፣ ምንድናቸው እነዚህ የአንደበት ስዕሎች? ለመግባባት ነው የተፈጠሩት ወይስ ለመራራቅ? ታዲያ ለምን በፀጥታ ይሸነፋሉ፣ ማስረዳታቸው ለምን የዝምታ ዲቃ ድረስ መክተም አይቻለውም? ሄደው እስኪያመልጡን ዝምታዎቻችን ለህይወታችን ህይወቶች ናቸው፡፡
ሚስጥረን በዝምታ አፈቀርኳት፡፡
ሀያ ሁለት ስንደርስ፣ ለአፍታ ቆም ብላ እንደጉድ የሚተራመሰውን ሰው ተመለከተች፤ በስሱ ፈገግ አለች፡፡ ስለ ፈገግታዋ የፈጠራት ይናገር፣ እኔ ግን የፈጠራትን ፈገግታዋ ውስጥ አይቼዋለሁ፡፡ ዞር ብላ በላሙ አይኖቿ ውጥንቅጤን ካወጣችኝ በኋላ ፈጠን ፈጠን እያለች ታወራ ጀመር …
“ፀጥ ያለ ቦታ መሆን እፈልጋለሁ”
“እኔ ያንን ቦታ ልሆንልሽ እወዳለሁ”
“እንግዲያውስ ወደ ቦታህ ጥራኝ”
ሀሳቤን ፈተነችብኝ፡፡ ከፊቴ እንዳለች አንስቻት ወደ ህሊናዬ በመክተት የወደደችውን ብሰጣት ተመኘሁ፡፡ ሆኖም የተፈጥሮን ህግ እንዳትጥስ ተደርጋ የተፈጠረች እሷ ብቻ ነበረች፡፡ ቦታ አፈላለግሁኝ፡፡ አገኘሁ፡፡ የቦሌ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ጀርባ፡፡
“ተከተይኝ?”
“የቴሌ ብራስን ታክሲ ይዘን ወደ መድሃኒያለም ተጓዝን፡፡ በመሀል በመሀል ቀና እያለች ታየኛለች፡፡ ቀና ስትል ሁለመናዋ ይናገራል፤ ካይኖቿ ላለመሰወር፣ ለመኖር ጥረት ማድረግ ጀመርኩኝ፡፡ ለቅፅበት አለመሞትን መረጥኩ፡፡
ቤተክርስቲያኑ ጋ ስንደርስ ወርደን በዝምታ ተሳለምን፤ በዝምታ ግቢውን አቋረጥን፣ በዝምታ ከጀርባ ያለው አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀመጥን፡፡ መቀመጣችን መሳፈራችን ሆኗል ለካ፡፡ የተሳፈርነው ፍቅር ወደሚባለው የመለኮት መገለጥ ድረስ ነው፤ እስከከፈልነው ድረስ እንጓዛለን፡፡
“ባል አለሽ?”
“እንዳልገምትህ ሆነህ ለእዚህች ቅፅበት መኖር አትችልም?”
“የወሰድሽብኝን መልሽልኝ”
“የወሰድከውን እወቀው”
“ወስጄብሻለሁ እንዴ?”
“አይኖቻችን ናቸው ቃላቶቻችን፤ ወፍ ስትተነፍስ ማድመጥ አይጠበቅብህም፤ በባህሩ ወለል ላይ ያለው የፀሀይ ድርሰትን ለመረዳት ሄደህ የማየት ግዴታ የለብህም፤ የህይወትህን መጀመሪያና መጨረሻ ማየት ቢያሻህ አሁንነትህን ካልረሳህ መልሶ በእጅህ አይደርስም፡፡ መጨረሻ ላይ የሚታይህ ሁሉ መጀመሪያ ነው፣ መጀመሪያውንም ያልተፈጠረ ዘላለም ነው፡፡”
“በህይወት ሳለሁ ቀኖቼን ሁሉ ልሰጥሽ ቃል እገባልሻለሁ፡፡”
“በህይወት ሳለህ ኖሮህ የማያውቀውን ብትሰጠኝ ፍቃዴ ነው፡፡”
“ወዴት እየወሰድሽኝ ነው ያለሽው?”
“አንተ ወደፈቀድከውና እኔ ወደምጠብቅህ፡፡”
“ከዚህ በላይ መፈቀርን ለምን ትፈልጊያለሽ?”
“ፍቅር የሚያዳልጥ የስሜት ሂደት ነው፣ አዳልጦህ የምትከትመው ደግሞ ዘላለም ውስጥ ነው፣ ዘላለም ውስጥ ሆነህ ደግሞ የምትጠይቀው ጥያቄ ካለህ ገና ያልደረስክበት አንተነትህን እንጂ ሌላ ያመለጠህን አታገኘውም፡፡ ልብ ብለህ አስተውል፤ መነጠቃችን የእርቃን ነፍስ ባለቤት አያደርገንም፣ ስጋችን የሚሸነግለን ከመሰለንም በእውነትም ህያው ሆኖ መኖር አይቻለንም፡፡”
“አሁን በስጋዬ የተሸነገልኩ ሆኖ ነው የሚሰማኝ፡፡”
ምራቅ የሚያስውጥ ፈገግታ አሳይታኝ ልትናገር ቸኮለች፡፡
“የህሊናህ ጌታ ሁን፣ ፍርድን ከሌላ አትቀበል፣ የራስህ ሁን፣ ዝም ብለህ አትሰቃይ፤ በዚህ ሰዓት ያሻህን ብትዘላብድ የምትጠብቃቸውን ቃላቶች ላልሰጥህ እችላለሁ፣ ነፍስህን ጠለቅ ብለህ ተመልከታት፤ ስትሻው የነበረው ሙሉ ሆኖ ይታይሀል፡፡”
“እወድሻለሁ ሚስጥረ….”
ከት ብላ ሳቀችብኝ፡፡ በጣም የማሳዝን ፍጡር ሆኜ ራሴን ተመለከትኩ፡፡ ከሚስጥረ ጋር ሆነን በራሴ ላይ ሳቅንበት፡፡ ለረዥም ደቂቃ ሳቅን፡፡ በሳቃችን እንጠፍጣፊ መሀል ቀና ብዬ ሳያት መቼምም ልለያት የማልፈልጋት ሴት እንደሆነች አወቅሁ፡፡
በእጇ የያዘችውን በNikos Kazntakis የተፃፈው “Zorba the greek” የተባለ መጽሐፍ ወደኔ አቀረበችው፡፡
“ተቀበለኝ?”
ፈራ ተባ እያልኩ ተቀበልኳት፡፡
“መውረጃህ ደርሷል፡፡ ለእስካሁን ተሳፍረህ ስትሄድ የነበረው በኔ ውስጥ ነው፡፡ እስከከፈልክበት ድረስ ወስጄሀለሁ፡፡ አሁን ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ፡፡ ይሄው ነው….”
“መጽሐፉን ታዲያ ምን ላድርገው?”
“ዘወትር በዚህ ሰዓት ከዚህ ቦታ እገኛለሁ፡፡ ቦታውን ፍፁም ወድጄዋለሁ፡፡ ብዙ የምሄድባቸው የስሜት ርቀቶች አሉ፤ ልሳፈርህ ፍቃደኛ ብትሆን ከዚህ መጽሐፍ ጋር ተመልሰህ ና፤ ይህ በእጅህ የያዝከው መጽሐፍ መጠበቄን ይናገርልኝ፡፡”
በሀይል አተኩሬ አየኋት፡፡ ሚስጥረ እንደሌሎቹ የከተማውን ቡቲክ በላያቸው ላይ ከምረው እንደሚንጠራወዙት የጨርቅና የኩል ነፍስ ያላቸው ሴት አይደለችም፡፡ ፍትወት ቅርባቸው ሆኖ በቅጽበቶች ልዩነነት ከአንድ ወንድ ገላ ወደሌላው የሚዘሉትን አትመስልም፤ በመቀመጫቸው እና በጡታቸው ትልቅነት ልክ ህይወታቸው የምትጠብባቸው ዓይነት ሆና የምታውቅ አይመስለኝም፤ ሚስጥረ ያልኳት፤ ያልተገለጠች፣ ገና ያልተደረሰበትን የሴት ልጅን ህቡዕ ስብዕና ገላልጣ ለብቻዋ የምትዝናና የተደበቀች ሴት ናት፡፡
ለጉድ የተጐለጐሉት አይኖቼን ድል ነስታ፣ በቀዘዙ ቃላት በችኮላ ተሰናበተቻቸው፡፡
ታዘዝኳት…፡፡
መኖሪያ ቤቴ ጋ ስደርስ መሽቶ ነበር፡፡ ደክሞኛል፡፡
በውስጤ ያቺ ሚስጥረን ምነው በህልሜ በቀጠርኳት ነበር፤ እያልኩ መቆጨት ላይ ነኝ፡፡ በሩን እያንኳኳሁ በድንገት … “መጣሁ” የሚለውን የልጄን የዮሴፍን ድምጽ ሰማሁት፣ እጅግ ደነገጥኩኝ፡፡ እየሄድኩ ነው እየመጣሁ? በሩ ተከፍቶልኝ በዝግታ ወደ ውስጥ ስገባ፣ ባለቤቴ ሩት ከበረንዳ ላይ ተቀምጣ እሳት እያቀጣጠለች አየኋት፡፡ ለምንድን ነው ይህን ሁሉ ውበት እርግፍ አድርጌ የረሳሁት? ለምንድን ነው ይህ አሁን የማየው ቅድም ሆኖ ቅድም ትዝ ያለለኝ?
ምግብ ቀርቦ ልጄና ባለቤቴ በሀይል እየተሳሳቁ ሲፈነጩ፣ እኔ ልቤ ውስጥ ባለች ስርቻ ስር አነባ ነበር፡፡ ለአስር አመታት በፍቅር የኖርኳት ሴት በአስር ደቂቃ ልዩነት አጣኋት፡፡ አሁን በዚህ ሰዓት በዚህች ሴት ውስጥ ሰጥሜ ወደ ፍቅር የሚወስደውን ትራንስፖርት ልይዝ አይቻለኝም፡፡ ምክንያቱም የምከፍላት አንዳችም የለኝም፡፡ ተዘርፌ ነው የመጣሁት፤ እሷ ይህን ብታውቅልኝ ምን ያህል በቀለለኝ፡፡ በዛች ሚስጥረ በለቀቀችብኝ እዚም ፈዝዤ ለባለቤቴ የምሰጣትን ተቀምቻለሁ፡፡
ልጄንም ተመለከትኩት፤ ሁሉም ነገሩ፣ ንብረቱ፣ ፍቅሩ፣ መተሳሰቡ፣ እውቀቱ፣ እውነቱ፣ መጠጡ፣ ምግቡ…ሁሉም ነገሩ ያለው ከኔው ዘንድ እንደሆነ አወቅሁኝ፡፡ ነገር ግን እንዴት አድርጌ ልስጠው፣ ያጠራቀምኩበትን መጋዘን ሚስጥረ በመክፈቻው ላይ ክታቧን አኑራበት በምን ልከፍለው ተቻለኝ፡፡ ያለኝን በሙሉ ቀምታኛለች፡፡
ያፈቀርኳትን ያህል ጠላኋት፡፡ በጃኒኒሻር ድግምት የተሰወሩትን ትውልዶች ጠርቼ፣ እንደዛር ውስጤን እንዳወከችው ውስጧን ቢያውኩባት ምርጫዬ ነበር፡፡
በእፀ - መሰውር ከአይነ ስጋዋ ተለይቼ፣ የደረሰችበት እየደረስኩ ያላትን ብቀማት ብዬ መናፈቅ ጀመርኩ፡፡ ወይ ደግሞ በእጄ ልትገባ የማይቻላትን፣ የህይወቴና የቀናቶቼ እብደቶች ከሆነችብኝ፣ በድግምት ያሻኝ እና የምጠላው ወንድ ስር ትጋደም ዘንድ አደርጋታለሁ፡፡ አዎ…ሚስጥረን ልኬቱ በማይታወቅ ፍቅር ውስጥ ገብቼ ጠላኋት፡፡
በምሽት ላይ ባለቤቴ ከእቅፌ ገብታ ፍፁም በሰላም ስታንቀላፋ ምቾቷን እየፈራሁት ተደሰትኩላት፡፡ መውደዴን ግን መጠራጠሬ የሞት ሽታን እንዳሸት አስገደደኝ፡፡ ከደረቴ ላይ ተኝታ፣ ውበቷ ግን ከህሊናዬ ውስጥ ተሸርሽሮ ጠፋብኝ፡፡ በዚህ ሰዓት የምወድቅለት ውበት የሚስጥረ ብቻ ነው፡፡ ሚስጥረ ደግሞ ባለቤቴ አይደለችም፡፡
በበነጋታው የቦሌ መድሃኒያለም ጀርባ ካለው ስፍራ አገኘኋት፡፡ ተቀምጣ ሩቅ እየተመለከተች ለራሷ ፈገግ ትላለች፡፡ በሀይል እየተራመድኩ ሄጄ ቀረብኳት፡፡ መናደዴን እንድታውቅብኝ ፈልጌያለሁ፡፡ በእጄ የያዝኩትን መጽሐፍ የተቀመጠችበት አግዳሚ ላይ ወረወርኩት፡፡ እሷ ግን የተለየች ነች፤ እንደዚህ አይነት ኮሶ ፊት አይታም ቢሆን ተረጋግታ ነው የምታወራው…
“ባለ ትዳር ነህ?”
“አዎ”
“ልጅ አለህ?”
“አንድ ልጅ አለኝ…”
አይኖቿን ከፍ አድርጋ በተመስጦ ወደ ሰማዩ ተመለከተች፡፡
ከላይ በሰልፍ የሚሄዱ እርግቦች ይታያሉ፡፡ ለሷ ብለው፣ በሷ ጌትነት ስር በትዕዛዝ የሚከንፉ ይመስላሉ፡፡ ዝግ ብላ መናገር ጀመረች…
“ይታይሃል…ከዛ ያለው የእርግቦቹ ሰልፍ? ማንም ጂኦሜትሪ አላስተማራቸውም፣ ነገር ግን የፈጠሩት መስመር ለአይን ትክክል ነው፤ የሚመራው የፊተኛው ወፍ መሪነቱን አያውቅም፤ ነገር ግን ሌሎቹ በሁሉ ነገራቸው እንዳይስቱ አድርጐ ከክንፉ ደርዝ ስር ያበራቸዋል፤ ሰማዩም ሜዳቸው ነው፣ አየሩ መጓጓዣቸው፣ ሀሳባቸው ደግሞ የሚደርሱበት ቦታ ነው…”
እንደህፃን ልጅ ቃላቶቿን የምከተለውን፣ እኔን ትኩር አድርጋ አየችኝ፡፡
“እንግዲያውስ እኔና አንተ በትላንት እና በነገ ባልተገደበ የጊዜ ርቀት ውስጥ እነዚህን እርግቦች መስለን አብረን ኖረን ነበር፡፡”
ፈገግ ብላ ታየኝ ጀመር፡፡ ሌሊቱን ሙሉ የወጠንኩት ውሳኔ ነበረኝ፤ ያንን ልታውቅ ይገባታል፡፡
“አንቺን መግደል አለብኝ፤ ከዛ በኋላ ተመልሼ ወደ ቤተሰቦቼ እቀላቀላለሁ፣ የቀማሁትን የባለቤቴን ውበት አስመልሳለሁ፤ የልጄን ፍቅር የሚስተካከለውንና ሊያሸንፈው የሚታገኝን ከውስጤ እሰርዘዋለሁ፡፡ ይህ ሁሉ ደግሞ የሚሆነው አንቺ ስትሞቺ ነው፡፡”
እሷ ግን ልክ ስወለድ ወደነበረኝ ንፅህናዬ በአይኖቿ ትመልሰኛለች፡፡ እጅግ ሃያል የሆነ ሃጥያትን ተሸክሜ ሳለሁ በአንድ እይታ ብቻ ታነፃልኛለች፡፡
“ባትገለኝ ነው የሚሻልህ፡፡ ብትገለኝ እስከዘላለም ድረስ ይዘኸኝ ትኖራለህ፡፡ የምትነካው በሙሉ እኔ እሆናለሁ፤ የምትሻው በሙሉ ከኔ መዓዛ የራቀ አይሆንም፤ ምንም ላልከፈለ ምንም አትስጠው፣ በግድ ከፍለህም በግድ አትንጠቅ፣ አሁን ሂድ ወደቤተሰቦችህ፡፡ ወደ ፍቅር የምታደርገው ጉዞ ክፍያው ብዙ ነው…ከስሜትም ይልጥ የሚያስከፍል፡፡ መስጠት ይኖርብሃል፣ የምትሰጠው ደግሞ ምን እንደሆነ እኔ ልነግርህ አይቻለኝም፡፡ ካንተ ጋር በመተዋወቄ ደስተኛ ነኝ፡፡”
እተቀመጠችበት እንዳዘነች አቀረቀረች፤ እኔም እጅግ ልቆጣጠረው ያቃተኝን እንባዬን ከታፋዋ ስር ተንበርክኬ አዘነብኩት፡፡ እጅግ በጣም እንደማፈቅራት ገባኝ፡፡ እዛው እያለቀስኩ በሀይለኛ ድካም ተጠምጄ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
ስነቃ ፀጉሬን እያሻሸች፣ አይን አይኔን እያየችኝ አገኘኋት፡፡
“እንዳልቀሰቅስህ ብዬ ነው፡፡”
ሰዓቱ ነጉዷል፡፡ በድንጋጤ ተነሳሁ፣ በቦታው የሚያልፈው ሰው በሞላ እየገላመጠን ነው ሚስጥረ ግን የአይናቸውን ንቀት የሚያጠፋ ስብዕና በውስጧ ስለያዘች ለኔም አበድራኝ፣ በቦታው ምንም የማንፈራ ሁለት የህይወት ልጆች ሆነን ነበር፡፡ ከተቀመጥንበት ተነስተንም ብዙ ተጓዝን፡፡ በስተመጨረሻ አንድ ማሳለጫ ጋር ቆማ ወደኔ በትኩረት ስትመለከት ከቆየች በኋላ ቆጣ ባለ አንደበት ተናገረችኝ… “ካሁን በኋላ መገናኘት ይኖርብናል ብለህ የምታስብ ከሆነ፣ ከህይወት በምታገኘው አሰስ ገሰስ መጠርቃት ያቃተህ ነህና እራስህን ታዘበው፤ ፍፁም ልትሸሸኝ ብትሞክር፣ የፍርሃትህን ጽኑነት ያልተረዳውን ህሊናህን ያልተረዳህ ግራ ገብ የሆንክ እንግዳ ሰው መሆንህን ተረዳ፤ ቤተሰቦቼን ጥዬ ካንቺ ጋር ረዥም መንገድ እጓዛለሁ የምትል ከሆነ፣ የምትለውን የማታየው መደንገጥ ቢሰለችህና ቢቀፍህ ነው ብዬ የምተረጉምብህ አይምሰልህ፡፡” ተንጠራርታ ጉንጬን ሳመችኝ፡፡ ቀልቤን ማዕበል ሆኖ ያናወጠው ፈገግታዋን ከዓይኔ ላይ አትማብኝ ከጨለማው ሰመጠች፡፡ ከመቅጽበት ቦታ መፈለግ ጀመርኩ፤ ይህችን ሴትና ቤተሰቦቼን የማላገኝበት፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህን አሁን የተሸከምኩትን ማንነት የሚነጣጥለኝ ቦታ፣ ቢቻል “እዚህ ጥግ ስር” የማልለው ቦታ፡፡ ያልተፈጠረ ቦታ ፈለግሁ፡፡
በፍጥነት መሳፈር እንዳለብኝ ገባኝ፡፡ ርቄ መጥፋት አለብኝ፤ ስጋለብ ኖሬያለሁ፤ አሁን ጋላቢው እኔ ነኝ፡፡ ዝም ብዬ ረዥም ረዥም፣ ርቆ የሚወስድ፣ በዘላለማዊነት ተምሳሎት በነፃ የተለቀቀ መንገድ ፍለጋ ባይኔ ማሰንኩ፡፡ አንድ ረዥም መንገድ አገኘሁ፡፡ ሮጥኩ፤ ሮጥኩ…የጣልኩትን ላላይ…ፍርሃቴን ልጥስ…ከእስር ቤቱ ላመልጥ…ከስሜት የራቀውንቅርሴን ሸጬ ወደ ፍቅር ልሳፈር…የጣልኩትን ላላይ…ሮጥኩ…ሮጥኩ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ገልብጤ » Sun Nov 04, 2012 6:22 pm

Qጦር


ይሔ አካሄድ አፎቱ ሁለት ነው፡፡
አንድም በራሱ… አንድም በእኔ፡፡
***
የሁለቱም አይደለችም፡፡
መሬት ላይ እንደሚውድቁት ካርታዎች ዋጋ የላትም፡፡
ቀድማ ራሷን ዲካርድ ስታለች፡፡
***
ዙሩ ከሯል፡፡
አይኖች የሚጣሉት የሚነሱት ላይ ጦራቸውን ወድረዋል፡፡
እጆች ድል ለመምዘዝ አሠፍስፈዋል፤… አሁን አብይ ከዘጋ ሶስተኛው ስለሆነ… ይቦንሳቸዋል፡፡ አኪር እያፏጨች እየዘፈነችለት ነው፡፡ …/አንዳንዴ ይሔ ልጅ ካርታው ላይ ምልክት አድርጐበታል እንዴ/ ይላሉ… እኔ ደግም በተከታታይ አንዴም ሳልዘጋ ተበልቻለሁ፡፡ …በተከታታይ ቸክዬ ካልዘጋሁ… ከከተማ ውጭ አብሬአቸው አልሔድም፡፡ በዚህ ሁኔታ ከቀጠልኩ ቁጭ ብዬ መውደቄ ነው፡፡
***


ከአለም ብርሃን ጀርባ ነፋሱ ከፈጣሪው ጋር ትግል የገጠመ ይመስል… አስቀያሚ ሽታና አቧራ እየቀላቀለ ይገማሸራል፡፡ በግ አራጆች አርደው የሚደፉት ፈርስና አንጀት ሽታው አፍንጫ ይሰነጥቃል፡፡
የግራዋው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ… አብነትና ካሱ ወደል ድንጋይ ተንተርሰው… በጀርባቸው ፈልሰስ ብለው… ከእግዜር ለመከለል…
በአብነት ጠይም ሻርብ ፊታቸውን ከገዛ ሀፍረት ቡዳነት ጋርደው… በከንፈራቸው ዳንቴል ይሰራሉ… የካሱ ግራ እጅ በአንገቷ አልፎ ሁለት ሥራ እያከናወነ ይገኛል… እቅፍ አድርጐ በደረቷ ገብቶ ብሎን እንደሚፈታ መካኒክ የጡቶቿን ዳዶ (Nipple) በስሜት ያጠብቃል…
አብነት ቀስ እያለች መንሳፈፍ፣ ግራ እግሯን ከካሱ ጭኖች ስር ጥብቅ አርጋ ወተፈች… ፍንክንክ… ቅ.ብ.ጥ.ብ.ጥ… አለች፤ ከስር ልምላሜ የራቀው አፈር መልካም ነገር ድርቅ የሆነበት… ከላይ በመጠኑ ፈገግታ የተኳለች ፀሐይ ብቻ ናቸው የሚያዩዋቸው፡፡ ግራዋዎቹ በድን ናቸው፡፡ ጣዕማቸውም ሽታቸውም መራራ ነው… /ቅንነት እንደጐደለው ሰው/ የአብነት ግራ እጅ የካሱን የሱሪ አዝራሮች መነካካት ጀመረ… ከመሬት ከፍ… ከግራዋው… ዝቅ ማለት ጀመሩ፡፡
***
አፈሩ… ቦነነ፡፡
***
አካሉ በጣም ጨንቆታል… ፊቱ በሳማ የተለበለበ ሥሥ ገላ መስሏል፡፡ በተመስጦ ስለሚከታተል… አፉን ገርበብ አድርጐ ከፍቶታል፡፡
ሁለቱ የተነቀሉት የፊት ጥርሶቹ የራበው የህፃን ልጅ ሆድ ይመስላሉ… ጭንቅላቱ ትልቅ ስለሆነ… Kwasharkor የያዘው ነው የሚመስለው፡፡ (በጭቃ የተጠፈጠፈ አሻንጉሊት… ለዛውም ህፃናት የጠፈጠፉት)
***
ሁሉም የአብይን እጅ ይከታተላሉ… /እንኳን ካርታ ቀርቶ ከአፍ ውስጥ ምራቅ ይሠርቃል/ ግን ምኑ ውስጥ እንደሚከተው ማንም አያውቅም፡፡ ለእኔ ግን ሌሎች ከሚዘጉ እሱ ቢዘጋ ይሻለኛል… ምንም ይሁን ምን ይበጥስልኛል፡፡
***
አካሉ ከጭንቀቱ የተነሳ አቧራ ላይ የተርከፈከፈ ውኃ የፈጠረው ቅርፅ ፊቱ ላይ ይታይበታል… እየቆየ እየቆየ… የተጨመቀ የዳማከሴ ቅጠል ይመስል… ደሙ እየቀዘቀዘ መጣ… በየደቂቃዎች ይለያያል…
አብይ ቀና ብሎ ሲያየኝ ጠቀስኩት… Q ጦርን ትቶ ሳበ… ስምንት ልብ ነበረች… ጆከር ለመሬት ጥሎ ቦነስ ቦነሳቸው፡፡
አካሉ ካርታው እጁ ላይ እንዳለ… በጀርባው ወደቀ… ሰውነቱ በቸንካር ተገድግዶ ፀሐይ እንደጐበኘው የለፋ ቆዳ ተወጣጠረ… አፉ ደረቀ ደፈቀ… ልክ እንደተገነደሠ ግንዲላ በተቀመጠበት ግምስ ሲል… አቤላ ቀድማ አይታው ስለነበር… ግራ እጇን የሞት ሞቷን ሰደደችለት… እጇ ባይታደገው ኖሮ… የእነ ነፃነት የበሠበሠ የማድቤት ቆርቆሮ አንገቱን ይሸረክተው ነበር…፡፡ እየተንፈራገጠ አረፋ እየደፈቀ ሁሉም “ክብሪት… ክብሪት” እያለ ሲሯሯጥ… አብይ ዘጠና ሶስት ብር ቆጥሮ ኪሱ ከተተ…
አካሉ ሲጨናነቅ… ሁሌም ፈንግል እንደ በረታበት አውራ ዶሮ መፈንገሉ የተለመደ ነው፡፡ ብዙ ክብሪቶች ተተርኩሠው ጭሱን ምጐ… ረጅም ሠዓት እንደተኛ ሰው ብንን ብሎ ነቃ…! (ሁሌም የማይገባኝ አንድ ነገር አለ… እንዲህ ወድቆ ለሚንፈራገጥ ሰው ክብሪት ሲለኮስ ነው፤… እርቦትስ ቢሆን…? ወይ ሌላ ነገር… ላይክ… አጋንንት… ወይም ሌላ ሌላ ነገር… ብቻ ሌላም ሌላም እኛ የማናውቀው እግዜር የሚያውቀው … ልክ ተመራማሪዎች የሽበትን አሸባበት መንገዱን እንዳልደረሱበት… ወይም ደግሞ… የእናትን የጡት ወተት እነሱ እንዳልፈጠሩት… አይነት…) አብይ እቅፍ አደረገውና … ስድስት ብር በግራ እጁ አስጨብጦ ወደ ታች… ወደ አለም ብርሃን ሸኘው፡፡
ሁልጊዜ ከእኛ ጋር ለመጫወት ሲሠየም... ይጨንቀናል… ሲበላ /ይጠብቃል/ ስለሚወድቅ… ሙዳችንን አብሮ ያንፈራፍረዋል፡፡
“እወድሃለሁ”
“አውቃለሁ”
“እንዴት ልታውቅ ቻልክ?”
አይኖቿን እያየ ሳያንኳኳ ወደ ውስጥ ያለ ከልካይ ጠለቀ… በረበራት… ባለ አራት ክፍል ልቧ ሁለት መደብ እንዳለው አየ… አንዱም ግን እሱን አላስቀመጠም…
“መልስልኝ እንጂ…?” አለችው በአይኗና በከንፈሯ ለማሽኮርመም እየጣረች…
“እ…” ባነነ፤ ቆሞ መተኛት… አቅፎ መናፈቅ… ልክ ሽሮ እየተመገቡ የመራብ ያህል ደነዘዘ… ተስገበገበ!፡፡
“ስለ… ስለምወድሽ እንደምትወጂኝ አውቃለሁ…” አላት… ሞኝ… ወንዝ ዳር ተተክሎ የደረቀ ቄጤማ…! ጨለማ ውስጥ ያቀመሠችውን ትርፍ ከንፈሯን እያሰበ ልቡን የሸና ጅል! ብልጠት ያልተሞላበት ስስ… ቀዳዳ… ሥልቻ…! እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ብልጥ መሆን ያልሞከረው ቀረፎ… አይጥ አድና ወደ ግልገሎቿ እንደምትበር ቀበሮ፣ ሳንቲም ሲያገኝ ይፈልጋታል… እሷ ነፋስ… እሱ ገለባ… እሱ ለሷ ምኑን እንደመረጠችለት አታውቅም… ደረቱ በፑሻፕና… ብረት በመግፋት ዳብሮ ጥሩ ቅርፅ አለው፣ መጀመሪያ አግኝታው ውራ ያደረገችው ብልጥ መሣይ ሞኝ ናት… አብነት፡፡ ጠዋት አግኝቶ አይን አይኗን እያየ ያላንዳች ወሬ በመዳበስ ብቻ ይመሽበታል፡፡
***
ከጥቂት መደናዘዝ በኋላ ካርታው ተፐውዞ ታደለ… የነጺ እናት “ስልክ” ብላ ጠራችኝ… ሠምቻለሁ ግን ለመጫወት ስለጓጓሁ… ዝም አልኳት… /ላሽ/ “አንተ ደማ… እየጠራሁህ አይደለም…!” ተቆጣች /ደማ ቅፅል ስሜ ነው… ማን እንዳወጣልኝ አላውቅም… እትዬ መስቀሌ ማር ማለት ነው ብለውኛል… ድንቄም! እኔን የመሰለ ያልታጠበ ቡሃቃ ፊት ማር ሲባል “ማነው” አልኳት ያልሠማሁ በመምሰል…
“እኔ… ምን አውቅልሃለሁ ማን እንደሆነች… ብለህ ብለህ… ለህፃን ልጅ ደውሉልኝ ማለት ጀመርክ?!” ሁሉም ሳቁብኝ… አብይ ጠቀሰኝ…
…ጥቅሻው ማፅናኛ ጠብደል ጉርሻ መሆኑ ነው፤ አብዬ የአብነትን ድምፅ ያውቀዋል… አምልጦት ከት ብሎ ሳቀ… “እመለሳለሁ” ብዬ ካርታዬን አስቀምጬ ተነሳሁ… ሁሉም እኩል በሉ የተባሉ ይመስል…
“አጠሪራ አድርገው እሺ…” ብለው አልጐመጐሙብኝ… ሸዋለም ቶሎ በል በሚል ግልምጫ አይሉት ቁጣ ገሸለጠችኝ… ቁጣዋ አይሰማም እንጂ ጠንካራ ወረቀት ሲቀደድ አይነት የሚያሰማውን ስሜት ይመስላል፤
ያን ጐርፍ የሰረሰረው የመሠለውን ምድር ቤት በሁለት እርምጃ ፉት ብዬ ቤቷ ግራ ክንፍ እጥፍ አልኩ…
“ሔሎ…”
“ምን መሆንህ ነው… የዚህን ያህል የምትጀነነው…! …ከጐንደር ነው እንዴ የምትመጣው?!…” ተቆጣች አይገልፀውም…
“አብሽዬ… ይቅርታ… ፀጉሬን እየታጠብኩ…”
“ሲበቅልም የዚህን ያህል አልቆየ እንኳን መታጠብ…!” ድጋሚ አምባረቀች… ላስተባብል ስል…
“ተወው ተወው ጀብ መሠልኩህ… በዚህ ሰዓት እደውላለሁ… እዛው ቦታ አንዣብ አላልኩህም!”
“እዛው ነበርኩ እኮ…” ውይ ቅሌት… ማለቴ እዛው ነበር ስታጠብ የነበረው…” ከት ብላ ሳቀች፤ ውሸት እንደማልወድና እንደማልችልበት ታውቃለች፡፡
“ለማንኛውም… ----!…”
“ማን?” ድምጼ ከውኃም ቀጠነ… የሆነ ቦጭረቅ ያለ ድምጽ አሰማሁ…
“----!… እንዴት አይገባህም…? ያ… ---- ወንድሜ ነዋ!”
“እ…” ትንፋሼ የተመለሠውን ያህል ተበጣጠሠ… አብዬ ሥትስቅ ጠይም አደይ አበባ ትመስላለች /የእናቴን አይነት/ ስትቆጣ ግን ለዛዋ ይሟጠጣል… ሙሉ ፊቷ የኮሽም እሾህ ይመስላል … ምንም የሚስብ ነገር የላትም!
“ፍቃድ ሥለከለከለኝ … የተባባልንበት ቦታ አልሔድም!… ያቺ ተልባ አፍ ነግሬአት… ስትነግረው ቀረች… ለዛ ነው… በጣም ስለተበሳጨሁ ራስ ምታቴ ተነስቶብኛል እና ቅቤ ስለምቀባ ከቤት አልወጣም፤ እስቲ እኔን እያየ ኪሎ እንደሚጨምር አየዋለሁ…” ድጋሚ ክው አልኩ…፡፡ ቀጠሯችንን ከነገርኳት ቀን ጀምሮ ሁለት ቀን እንቅልፍ እምቢ ብሎኝ ነበር፤ እንትኗን ለመውሰድ መጽሐፍ አገላብጬ ያላገኘሁትን ምክር እናብዬ ነገሩን… በሶስተኛው ቀን የምደግምበትን ወጪ አብዬ እንደሚሠጠኝ ቃል ገብቶልኝ ነበር… ያ ሁሉ እቅድ… ያ ሁሉ ፕሮጀክት መና ቀረ…
የማንም አለመሆን ከባድ ነው!...
በተለይ ከራስ መራቅ…!
አርፎ አለማረፍ… ከህሊና መጋጨት… ከፈጣሪ መጣላት… በመንፈስ መታመም… ርቀው ላይርቁ መብረር… ሳይተኙ መባነን፣ መበርገግ… መንገድ ላይ ያገኙትን እየቀመሱ /ላይጥም/ መሔድ፤ በመኖር ውስጥ መጉደል… በመጉደል ውስጥ ማነስ… በማነስ ውስጥ አለመኖር… አለማለም… ብርሃንን ተስፋ አለማድረግ… መነሻን መርሳት… እሚደርሱበትን አለማወቅ… የሆነ ሰው ነኝ ብለው እያሉ… የማንም አለመሆን… የራስም!… ይሔ… ላመነ… ፈጣሪን በመፍራት ለሚኖር ሰው ከመክበድም በላይ ከባድ ነው፡፡
***
ስንት ህልም ቋጥሮ፣ ፈትቶ… የወንድነት ልኩን የሚያይበትን ቀጠሮ ወፏ ቀረችበት (ሴቷ)… ዛፉ ቅርንጫፉ ደረቀ… ውኃ የሌለው መሬት ፍሬ ያለው ዛፍ አይኖረውም… ወንዱ ወፍ አኮረፈ፡፡ ስልኩን ዘጋና ለምቦጩን ዠልጦ… ካርታው ጋር መጣ፡፡
***
ቆቅ፡፡ አብይ ቀና ብሎ አየኝ… ፊቱ የዘንጋዳ ሊጥ መስሏል፡፡ እኔ ደግሞ አመዳምነቴ ላይ ሌላ አመድ ተነስንሷል… ውስጤ የጠፋ እሳት ይመስል ጨሠ…፤ በልቤ ወንድሟን በምርጥ ብልግና ሰደብኩት… (እናቴ መሳደቤን ብታውቅ ታዝንብኝ ነበር) ሲያንሠው ነው፡፡ ሸዋለም… እዛው ዋሻ ውስጥ ሆና (ቁጣዋ ስለት ነበረው) “አንተ… ቆረቆራም… እኔ ያንተ ኦፕሬተር ልሁን… ና!… አናግራት… ቆይ…” እጇን ወደ ላይ ቀስራ… “ልጅህ ናት… ምንህ ናት?” የሷ መጮህ ሳያንሠኝ… ሁሉም ሳቁብኝ ድጋሚ፤ ከወንድሟ መከልከል በላይ ሳቃቸው አመመኝ፡፡ የሸዋለም ቁጣ… ጣት ውስጥ እንደ ተሠነቀረ ስንጥር ቆጠቆጠኝ… “ኧረ… ተጐረመሠልኛ…” አለች…
እግሬ የምድር ቤቱን ደረጃ ሳይረግጥ ካርታውን ፐወዙት… ይበልጥ ተበሳጨሁ… “አቤት” ትዕቢት ልቤን ነፋው!… ለመለሳለስ አልሞከርኩም… ይብስ ሽልጦውን እንደ ነጠቁት ህፃን ተጉረጠረጥኩ… ከሥልኩ ውስጥ ሥሜቷ ታወቀኝ… አብቲ ቱግ ሥትል… “አንተ ነህ… ሳታስጨርሠኝ ጆሮዬ ላይ የምትዘጋው?” ድምጿ እንደ ጅራፍ ጮኸ… ሁለት ነገር ተሠማኝ… እቺ ልጅ… እየወደደችኝ ነው?… ወይስ ስትፎግረኝ?…
“ምን ፅናት ኖሮኝ እንድሰማሽ ትፈልጊ ነበር…?” ፎቶ የተነሣን ቀን የሳመችኝ ትዝ አለኝ…” ልቤ ሞላ… ወጠር አለ፡፡
“እስቲ አስቢ… እማዬን ስንትና ስንት ነገር ፎግሬ … ያ … ጣውላ ራስ ወንድሜን … እግሩን ልሼ… ያስፈቀድኩትን ምርጥ አጋጣሚ ዝም ብለሽ… ‘ወንድሜን እምቢ አለኝ’ ትይኛለሽ…!?”
“እና ምን ማድረግ ነበረብኝ…! እስቲ ንገረኝ … ምን ማድረግ ነበረብኝ? ቁጣ … ንዴት … መብገን … መንተክተክ… ‘እውነት ምን ማድረግ ነበረባት … አበሻን ለመሠለች ለጋ ቅቤ … ፍቅር የሚበረታው ብልግናው ሲበዛ ነው የሚመስላት … በዚህ በዚህ ደግሞ … ካሱ ላባዋ እስኪርገፈገፍ … ያስደስታታል … አጥንቷ እስኪልም … ቀሚሷን ሳይሆን ገላዋን ቀዳለታለች፡፡
“አንቺ እውነት መሔድ ብትፈልጊ ኖሮ … ተወዉ በኔ መብት መወሠን አትችልም ብለሽ አትነግረውም?!”
“ተመልሼ የት ልገባ…?” አሮጊት ይመስል ተንጣጣችብኝ … “ስማ እዛ ቤት ልታሠራልኝ መሠለህ የምንሔደው…? … ወይስ ስንመለስ እናንተ ቤት ልኖር…?” አሸሞረች … ገባኝ … የእና ሶስት ክፍል ቤት ለእኛም እንዳማይበቃን ታውቃለች፡፡ ከርግብ ቤት ትንሽ ነው ከፍ የሚለው … ቀለም ስለተቀባ … ድምጿ ውስጥ የፉጉ ቃና ነበረው፡፡
“እና በቃ አትሔጂም…?” የእውነቱን አዝኖ ጠየቃት … ፊቱን ላየው አጭር የሀዘን ደብዳቤ ነው የሚመስለው፤
“አልተግባባን እንዴ…? አማርኛ እያወራን … ሌላ ጊዜ አመቻችተን እንሔዳለን … እ… እ… ናንተስ ምን ላይ ደረሳችሁ…?” መሔድ አለመሔዳቸውን ለማረጋገጥ የፈጠነችው ፍጥነት … ይሔን ሁሉ ተከትሎ ሀሳቡን ለመስማት የመቸኮሏን ጉጉት እንደቀዘቀዘ አጥሚት ጣዕም አልባ አደረጋት፡ …
“በቃ አብይም እኔም መሔዱን ትተነዋል … ማንም የሚሔድ አይመስለኝም” አፌን መረረኝ … የሁሉን ድምዳሜ ተናገርኩ… የተበላሸ ለውዝ የበላሁ መሠለኝ… እሷ ድምፅ ውስጥ ግን እ.እ.እ… የሚል ጉጉት የሚወልድ ፅንስ ያለ ይመስላል…
“ቻው እሺ …” ትንፋሿ እርካታ ነበረው … “እወድ…” ሳትጨርሰው ዘጋሁት … እሷም መልሴን ሳትሠማ ቀረች … ‘ምን ሆኜ ነው ግን ከዚች ልጅ ጋር ፍቅር የያዘኝ …’ ድምጿ ይጣፍጣል … ዐይኖቿ ከወንዝ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሠሩ ነው የሚመስሉት … መቀመጫዋ አርክቴክቶች ተሠብሥበው፣ ተጨንቀው፣ ተጠበው የሠሩት የማዕዘን ድንጋይ ይመስላል … “በምን ፍርጃ ነው እንዲህ እፍ ያለ ፍቅር ውስጥ የገባሁት …?” መልስ የሌለው መደመር … መቀነስ የሌለው የሒሳብ ሥሌት … ማባዛትስ …? ማካፈል ግን ትትላለች … እሷ … እ…፡፡
እንደቀልድ አሁን ጳጉሜ ሁለት አመት ይሞላናል…እኔ ለሷ በበረዶ ምጣድ ላይ የተጋገርኩ ቂጣ ነኝ…እሷ ለኔ ቃተኛ…ጣት ምታስልስ፡፡ ላጠና ደብተሬን ስዘረጋ ፊደሎቹ “ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ መሆኗን…ፊደል እየፃፉ ይነግሩኛል…ለድመት ማስቸገሯን ጭምር፡፡
የስልኩን እጀታ ዘግቼውም እጄ ላይ ነው…ሙዴ ዘጭ ብሎ የበጋ ጭቃ ላይ ተነከረ፡፡
***
አብነት…ክንፏ እንደገጠመላት የቤት ርግብ…ተር ተር ብላ ሳቀች…ቤቱ ውስጥ ማንም አለመኖሩ እሱ አንሄድም ካላት በላይ አዘለላት፤ ራቁትነት ተሠማት…ሰው ቢኖርማ ለመደወልም ባልሞከረች፣ መልሳ የስልኩን እጀታ አንስታ ከሱ ጋር ቁጥሮቹን መታች…ኩይሳ ስሜቷን ለመናድ…፡፡
***
እቺ…ጡት እንኳ በቅጡ ሳታበቅል እንዲህ ልቧ የስምንት ሴሰኛ ሴቶች ያህል አቅል ያሳጣት ልጅ…እየበረረች ካሱ ጉያ ትወተፋለች…ካሱ ደግሞ እንኳን ጉርሻ ጉረስ ተብሎ ቀምቶም ለመብላት የሚመለስ አይደለም…ስትበር ስትበር ትመጣና ዛፍ ሆኖ ይጠብቃታል…ለዛውም ጐጆ ያለው ዛፍ…ከብዙ ነገር ያሳርፋታል፡፡ ስክን ያደርጋታል…እንዳትታፈስ አድርጐ ያፈሳታል፡፡
***
ደረጃው ላይ በተሠነጠቀ የላስቲክ መዘፍዘፊያ ፓንትና ካልሲ የምታለቀልቀዋ ሸዋለም ቀና ብላ “ምን ሆንክ ደግሞ…?” አለችኝ፤ ለካ የታችኛው ለንጨጩ ደረቴ ላይ ተለጥፏል…“ምንም፡፡”
አልኳት ሳላያት…ድምጼ ራሱ እምክ እምክ ሸተተኝ… “ተዋት…ወሔነት የገጉ” ሳቀች ወይም ሳቀችብኝ…የዋህ ስለሆነች ሳቋ እንደ ጨጨብሳ ይጣፍጣል…ሁሌም ሸዋለም…ትተርታለች…”ደግነት ለራስ ነው…ነው…ወሔነት የገጉ” እውነት ነው…ደግ መሆንና ታማኝ መሆን ለራስ ነው…የሰው ልጅ ሌላኛውን ሰው ከመዋሸቱ በፊት የገዛ ህሊናውን ቀድሞ መግደል አለበት…
ተመልሼ ጨዋታው ጋር መጣሁ…ተሰየምኩ (ቆሞ ማየት እስኪያልቅ) ቅድም የአካሉ ጠረን የሸተተኝ መስሎኝ ነበር…ለካስ የራሴ ስራ ነው እንዲህ እንደሞተ የውሻ ቡችላ የሸተተኝ…ስለ ተበሳጨሁ…ሰውነቴ ግሏል…ካርታውን እያየሁ ባቦ ጋያ ከአብሻ ጋር ውሃ ውስጥ ተከለመኝ…እየተሯሯጥን…በነዛ በሚያማምሩ ሳሮች ላይ/ሳልከልማቸው በሀሳብ/ እያንከባለልኩ ሳንከባልላት…እየሳምኩ ስመጨምጫት..እጆቼን ያለ ከልካይ…አካላቷ ላይ ሳነግሳቸው…ከንፈሯ ላይ ዋሽንት ስነፋ…
እሷ እስክስታ ስትመታ…መታ…መታ…አለው ደስታ አይነት ነገር…
በተለይ እጆቼ ሁለቱ ጡቶቿ ላይ ያላንዳች ተቀናቃኝ፣ ታይቶ የማይተነተን ስእል ስስል…ታየኝና ታየኝ…ምን ዋጋ አለው…የፈሠሠ ቀጠሮ!፡፡
አንድ ቀን እማዬን…እንጀራ ሸጣ ስትመለስ…አድርጌ የማላውቀውን በድፍረት አስር ብር ጠየኳት…”ለምንህ?” ሳትለኝ አሮጌ ቦርሳዋን ከብብቷ አውጥታ ሁለት አምስት ብር አሻረችኝ (እማ ጠረኗ ይጣፍጣል…ልቅ እንደ ቤተመቅደስ እጣን) በስመአብ እፊቷ ዘፈንኩ…እማ ተገረመች…የጤና አልመስል እስኪላት…ሳቀች…ጥይምናዋ ላይ በአንድ አፍታ የጠዋት ፀሐይ ወጣች…አፋራም ፀሐይ…እማን እወዳታለሁ፤ ባየኋት ቁጥር በስስ ሥጋ የተበጀችው ልቤ ቅልጥ ትልብኛለች፤ እሳት ዳር እንደተጠጋ ቅቤ…ፊቷን በሙሉ ስሜ የቀረኝ የለም…ልብሴን ቀይሬ…ወጣሁ ያለወትሮዋ…”ቶሎ ተመለስ” አላለችም (ቅዳሜ ከሰዓት ነዋ) መጐርመሴ የገባት ስለመሰለኝ ገባኝና ገባኝ…እንደ ፌንጣ እየዘለልኩ ከጊቢ ወጥቼ አብሻ ጋር ደረስኩ…”ከንፈሯን ካቀመሰችኝ በኋላ በትኩስ ትንፋሽ…”ቲያትር እንግባ” አልኳት…ጥርስ በጥርስ ሆኜ፡፡ “አቦ ቲያትር አይመቸኝም” አለችኝ…እጇን እያወናጨፈች…(የእጇ አወነጫጨፍ ገደል ግባ አይነት ይመስላል) አልገባትም…ምርጥ ከሚባል ፊልም ቀሽም ቲያትር እንደሚበልጥ…ለሷ መዝናናት…ሲኒማ ኢትዮጵያ የቅንጣቢ ሥጋ ሳንድዊች በለስላሳ እየበሉ የህንድ ፊልም ማየት ነው…ቲያትር እንዳማረኝ ቀርቶ ሲኒማ ገባን…፡፡
ቆሜ እንደፈዘዝኩ አብይ አየኝ…
“ነቃ በላ” አለኝ…በእግሩ እግሬን እየመታ…ባነንኩ (ከገነት የተባረርኩ ነው የመሰለኝ…) “አብዬ can you lend me fifty birr?” የሆነ ቦታ ለመሄድ ፈለኩ…
“Anything special?” እያፌዘ መሰለኝ፤ መልስ አልሰጠሁትም…
“ጣጣ የለውም… ተረጋጋ… አትበሳጭ…” ሲያረጋጋኝ እርጋታው ድምፁ ውስጥ ነበር… “እንዲያውም ቅዳሜና እሁድን ሶደሬ ነው የምንሄደው!” ደንግጬ ተጠጋሁት…”የምርህን ነው?”
“ሙት…ከዚህ መጠጣችንን ፓንች አድርገን አምስታችንም እንሄዳለን” አለኝ…ትልቁን ጉዳይ እንደቀልድ…አምነዋለሁ…አብዬ ካለ አለ ነው…አርብ ላይ ቆሞ የቅዳሜና የእሁድን ውሎ መስማት የሆነ ያህል ይሆናል፡፡
አጠገቡ ቆሜ እንደህፃን ራሱን አሻሸሁት (ብስመው ራሱ ደስ ይለኝ ነበር)
አቤላ Q ጦርን ጣለች…ቅድምም ማነው ሲጥላት አታንሣ ብዬ ጠቅሴው ነበር…አሁንም ጭንቅላቱን በጣቴ ሳላስጠጣ ነካ አደረኩት…ቀጥሎ የሚጥለው ያስዘጋዋል…Q ጦርን ትቶ ሳበ…አራት ዳይመንድ ስቦ ኤኒ ገቢ ሆነ…ዞሮ ሲመጣ ዘጋ፡፡
***
እውነትን ይዤ ስደክም …ያን ጊዜ ሐይለኛ እሆናለሁ፡፡
ለዝሙት አልወድቅም፡፡ ለኔ ላልሆነ ነገርም አልንበረከክም፤
የኔ የሚሆነው እስኪሆን የሌላ ለመሆን አልሆንም፡፡
***
ጠዋት ነው፡፡
ፀሐይዋ እንደ ጐረምሳ ሙቀት እያፏጨች…ደረቷን ሳትሸፍን…ትስቃለች፡፡ ከ15 ቀበሌ ጠላ ገዝተን…ብርቱካንና ሙዝ፣ አናናስ፣ ተፈጭቶ ተጨምሮበታል፡፡ ካሜራችን ዝግጁ ሆኗል፤ እኔ፣ አብይ…አቤላ…ሲሳይ…ፍሬው…ሥራ ተከፋፍለን ተዘገጃጅተናል…መሄድ ብቻ…ልቤ አንድ ነገር አዘዘችኝ…እነ እትዬ ሱቅ ገባሁና አብነት ጋር ደወልኩ…ታላቅ እህቷ ስታነሳ እማወራው ጠፋኝ…”አ.ብ.ሻ.ን. ነበር” ስል ከወዲያ “የለችም በይ የለችም በይ” የሚል የራቀ የሚመስል የቀረበ የጥድፊያ ድምጽ ተሰማኝ…(የሆነ ነገር ወረረኝ) እህቷ በትህትና “መልዕክት ካለ… ወጥታለች” አለችኝ፤ ጨዋነቷን የአንደበቷ ለዛ ሹክ አለኝ…ምናለበት ከልቤ በወጣች ብዬ ተመኘሁ…ስልኩን ዘግቼ እዛው ቆምኩ…ጅል እኮ ነኝ…”እወድኋለሁ” ስትለኝ “አውቃለሁ” ያልኳት ቀን…”እንዴት ልታውቅ ቻልክ?” ያለችኝ ጊዜ…ነቄ መሆን ነበረብኝ…ሠራተኛ ሰፈር ጅል ማነው ቢባል እኔና እኔ ብቻ ነን…ቀድማ እየነገረችኝ…ያልሠማሁ…ሒድ ብላ ቅኔ እየተቀኘችልኝ ነቄ ያላልኩ…ገገማ ችኮ…ደግሞ አንጀቴን ስትበላ…እንደ እማዬ ጣቶቿን የራስ ቅሌ ፀጉር ውስጥ ወትፋ ትዳብሠኛለች…ያኔ ይሆን ልቤን ወስዳ የጣለችብኝ…?
ከአሁን በኋላ ሰው እወድሃለሁ ሲለኝ…”አውቃለሁ” አልልም…ከእማ በስተቀር፡፡ ግድ አለኝ እንዴ ባይወዱኝ! ለመሸወደ ለመሸወድ መወደድ ምን ፋይዳ አለው…በአንድ እጅ መዳፍ ሁለት ነገር መጨበጥ፡፡
ትዝታዋን ከህሊናዬ ለማስወጣት እፈልጋለሁ፡፡
ፍቅር ዘይትና ውሃ ሆኖበታል፡፡ ያልተዋሃደ…ግን ያልተለያዩ…ዘይቱ ውኃው ላይ ራቁቱን በደረቱ ተኝቷል፤ ውሃዋም …ራቁቷን ለዘይቱ ደረቷን ሰጥታዋለች፡፡…
እሱም እንደዛው ነው፡፡ ያልተደባለቀ…ግን ያልተለያየ…የስልክ ሃምሣ ሳንቲም ከፍሎ ከፍሬው ጐን ቆመ…መፍዘዙን ሲሳይ አይቶት ምን ሆነህ ነው ማለቱ ይብስ ማስቆዙም ስለመሰለው ዝም አለው፡፡
ልቡ እየዋለለበት ተቸገረ…ያለችውን እያመላለሰ ማመንዠግ ጀመረ…ካፌ ቁጭ ብለው…ከቦርሳዋ የኪስ ካላንደር አውጥታ እየቆጠረች ስታስብ…መላልሶ ታየው…”ለእኔ ገላዋን ከልክላ…ለሌላ…ይብላኝ ለራሷ…እኔስ የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም ነው…አሁን ብትሰጠኝ ምን ነበር? አያልቅባት” ያሰበውን አሰበ፤ መልሶ በልቡ…ልርሳው ካሉ ምን የማይረሱት ነገር አለ…ይሄን ሁሉ ፍሬው አጠገብ ቆሞ አምሠለሰለው…ፍሬውን ሲያየው ካለውም እጥረቱ ላይ ያጠረበት መሠለው…”እንጐ እንጐ…”የሚለው ድምጽ አነቃው…አቤላ ያመጣችውን አገልግል ሰጡትና ዳገቱን ተያያዙት፡
***
ሞቱ ለኃጥአ ጽዋግ፡፡
***
ሒደቱ ፈጣን ነው፡፡
ሃሳቡን እያላመጠ…ተሳፋሪውን በሳቃቸው እያሳቁም…እየበጠበጡም መድረሻቸው ደረሱ…የመጨረሻው ርካሽ አልጋ መንደር ወስጥ ተፈልጐ ተያዙ…ለሁለት ቀን ደስታ…ገላ የትስ ቢወድቅ..ምን ችግር አለው፡፡
***
ካሡ ልቡም ኪሱም ሞላ ሞላ ብሎ በሙሉነት የአብነትን ሞንዳላ ሰውነት አቅፎ እንደወጌሻ እያሻሸ ነፍሱን እስክስታ ያለማምዳል፤ ፊትለፊታቸው ያሉትን ሰዎች ከመጤፍም አልቆጠሯቸውም! ስብሃትን እቅፍ፣ እንቅ አድርጐ በከንፈሩ ከንፈሯ ላይ እሽክምክም እያለ ነው…አንድ ሁለቴ…የተጐነጨውን ቢራ በአፉ አፏ ውስጥ በአደራ ያስቀምጣል…
***
አገልግሉን ግማሹን አጣጥመው ተነሱ…ጠላው ባህሪውን ቀይሯል…ደማ አንድም ሳይጐነጭ …ሲሳይና ፍሬው ደገምገም አርገው በደንብ አጣጣሟት..የተከራዩት ጊቢ…የዝንቡ አበዛዝ…የንብ ማነብያ ጊቢ እንጂ…መደዳ የተደረደሩት ክፍሎች ማስቀየማቸው…ፅዳት የናፈቀው ወለል…ብቻ ሁሉም ለአይን ደስ አይልም፡፡ ዘጭ ካሉ ምን ክብር አለ፡፡
***
የነፍሷን መድኃኒት መልካም ግብር መሥራት ለምን ረሳች?
ኩነኔ መኖሩን አላውቅም ነበር ልትል እኮ ነው…!
ካህናትና መጻሕፍት…አልነበሩምን? ይላል እንዳንወድቅ የሚታገል ቅዱስ መንፈስ፡፡ የሀጥህ ሞቱ የከፋ ነው የመረረ…
***
“እኔ ቡና አምሮኛል…”
“እኮ አብረን መዝናኛ እንገባና ቢራም ቀመስመስ አድርገን…” ሁሉም ተስማሙ…ያ ድንክ ፍሬው ብብቱን እንደተኮረኮረ ህፃን…ሳይነኩት ይፈግጋል…እየሳቁ እየተተራረቡ ገቡ…
***
አብነት ሁለተኛ ቢራዋ ነው…ካሡ ቢራው ውስጥ ጐርደን ጅን አስጨምሮ ነው የሚጠጣው…ትንፋሿ ቀየር ሳቋ ሞቅ ማለት ጀመረ…እሱ የመጨረሻ ልጁን ጭኑ ላይ አድርጐ እንደሚያጫውት አባት ጭኖቹ ላይ አጋድሞ የዝቅዝቅ እያየ ያዋራታል…ከንፈሯን እየመጠጠ የታፕስ እንጆሪ አለ መስሎታል…
***

ሃፍራታም ናት (ሀጢያት ነው የሰራችው፡፡)

ለማንም ቀርቶ…ለራሷም አትሆን፡፡

ሐሳቤን ለውጫለሁ (ሐሳቡን)

መታመም አልፈልግም…መውደዴ ተለውጦ ፍቅር ወልዶ ነበር…

ሠርዧታለሁ ከልቤ (ከልቡ)
***
ወደውስጥ ሲገቡ የፊልም አክተር ይመስላሉ…ሁሉም ሰው የገዛ ራሱን ጨዋታ ነው የሚከታተለው…ከጥቂት ሰዎች በስተቀር የማንንም ትኩረት መሳብ አልቻሉም…ቆመው ስለላ አካሄዱ…ጥግ ብቸኛ የሆነ የአራት ሰው መቀመጫ አዩ…ወደዛው እየሄዱ ሳለ…አስተናጋጁ አንድ ወንበር እንዳልተጠበሠ አሳ አንጠልጥሎ ከኋላ ተከተላቸው…ልጅነት ጐጆውን የሠራበትን ፊታቸውን እየተመለከተ አጠናቸው…
ትከሻቸው ሰፋ…ከደማ በስተቀር ሁሉም ትንፋሻቸው መረር ብሏል፡፡ ጨዋነታቸው ጥቂትም ብትሆን አልተሸረፈችም፡፡ ደማ ተሽቀዳድሞ የወረደ ቡና ያለስኳር አዘዘ…አራቱ ተያዩ…አቤላ “ጣጣ የለውም” በሚል ቢራ ያላበው ለአራታቸውም አዘዘች…ጨዋታውን አጨሠችው፤ ደማ ታጥቦ ታጥኖ ስለመጣ፣ ማሠሪያ የሌለውን ጫማውን አወለቀ፤ ቀበቶውን አላላ…የፍሬው አይኖች እሚያርፉበት አጡ…
***
አብነት ቆማ ለካሱ አለመስከሯን ታሳየዋለች…መሀል ላይ ናት “መጣሁ የኔ ጌታ ሬስት ሩም ደርሼ” ከንፈሩን ስማው ሄደች፡፡
***
ቆመ…ልቡን ማመን አቃተው፣ አይኑን ሳይሆን፡፡ ሱሪው እንደወረደ ያወቀው አብይ ከፍ ሲያደርግለት ነው…ሁሉም አይዋት…ራሷ ናት አብነት! ፍሬው ካሱን ያውቀዋል ግን ከአብነት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ፈጽሞም አያውቅም…መሄድ ጀመረ …ለባዶ እግሩ ግድም አልነበረውም…ነጩ ካልሲ የመሬቱን ቅዝቃዜ አልነገረውም፡፡ ቀጥ ብሎ ካሱ ፊት ቆመ…
“አቤት…” ካሱ ለጠጥ ብሎ ተቀመጠ…ፊትለፊቱ የቆመው ማን እንደሆነ ፈጽሞ አላወቁም…እነአብይ በተመስጦ የሚሆነውን እያዩ ነው…አብይ እንደማይጣላ ያውቃል…ለዚህ ነው ያልተከተለው….
“አብነት ምንህ ናት?” ድምጹ ውስጥ መንበርከክ አለ…ትህትና፣ ፍቅር…ርህራሄ፡፡ ከጀርባ ሲሳሳሙ አይቷቸዋል…ግን አብነት ትሆናለች ብሎ መች ጠረጠረ…እሷማ እቤት ቅቤ ተቀብታ ተቀምጣለች፡፡
“ጓደኛዬ…ማለት ፍቅረኛዬ ናት…” ካሱ ርህራሄ የተሞላበትን ፊት እያየ ያልፈጠረበትን ትህትና አሳየ…
“አየህ…” ብሎ ከኋላ ኪሱ ቦርሳውን አወጣና ከአብነት ጋር ተቃቅፈው የተነሱትን ፎቶ አሳየው፡፡ “አየህ የሁለት አመት ውዴ ናት” እንባው መጣ፡፡ ካሱም ከኋላ ኪሱ ዋሌቱን አወጣና በቄንጥ ተቃቅፈው፣ ደረቱ ላይ ፈልሰስ ብላ ከጀርባው አዝሏት ብዙ ፎቶ አሳየው “ለእኔ ደግሞ የአምስት አመት ፍቅረኛዬ ናት…” ከዚህ ሌላ ምንም ሊለው አልቻለም…ከቀኝ አይኑስር ተነጥላ እየተንከባለለች የወረደችውን እንባውን ሲያይ አዘነ…
ካሱ አላለቅስም አይነት ጥርሱን ነከሠ፡፡
እነ አብይ የሚሆነውን በስስት እና በስጋት እያዩ ነው፡፡
“እና”
“ምን እና አለው ወንድሜ” ካሱ አንገቱን ቀበረ፡፡
አብነት እየፈነጠዘች ስትመጣ ካሱ አቀርቅሮ፣ ደማ ቆሞ…አፈራርቃ ተመለከተቻቸው፡፡
አያት፡፡
ፊቷን ከፊቱ መለሠች፡፡
ካሱም አያት፡፡
አላየችውም፡፡
ካሱ እጁ እየተንቀጠቀጠ ፎቶዎቹን ዘረገፋቸው…አብነት ሁለት እርምጃ ወደ ኋላ ሸሸት አለች፡፡ እነ አብዬ ከተቀመጠበት ተነሱ…
***
የኃጥዕ ሞቱ የከፋ ነው፡፡
***
የሁለቱም አይደለችም፡፡ መሬት ላይ እንደሚወድቁት ካርታዎች ቀድማ ራሷን ደክርታለች፡፡ ማንም አያነሳትም፡፡
ሶስቱም ተያዩ፡፡
ዙሩ ከሯል፡፡

ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ገልብጤ » Tue Nov 06, 2012 12:25 pm

ፍጽምና


የሞፓሳ ምርጥ አጭር ልብ-ወለድ ናት፡፡
የፅሁፉ ዋና ገፀ-ባህሪ ውብ እና የሚወዳት ሚስት አለችው፡፡ ኑሮዋቸውን የሚደጉመው እየዞረ በሚያሳየው ሠርከሥ ነው፡፡ ችሎታው አንድን ጩቤ ከረዥም ርቀት (5 ሜትር፣ 10ሜትር፣ 15ሜትር …) የተባለው ቦታ ላይ ወርውሮ መሠካት ነው፡፡ ሥቶ አያውቅም፡፡ በፍፁም ስቶ አያውቅም፡፡ ብርቱካኖችን፣ የፖም ፍሬዎችን ከተለመደው ርቀት ጩቤ ወርውሮ ይገምሳቸዋል፡፡ ከብዙ ልምምድ በኋላ የተቀዳጀው ችሎታ ነው፡፡በትርኢቱ ፍፅምናን ተቀዳጀ፡፡ እናም ትዕይንቱን ወደ አስደሳች ግን እጅግ አደገኛ ወደ ሆነ ደረጃ አሳደገው፡፡ እንደ ቀድሞው ኢላማዎቹ የዛፍ ግንዶች፣ ፍራፍሬዎች ወይም ሠሌዳ ላይ የተሣሉ ነጥቦች አይደሉም፡፡ ሠው ነው ኢላማው፡፡ ጩቤውን ወርውሮ ሠው መምታት ግን አይደለም፤ መሣት ነው፡፡

ለትርኢቱ ፈቃደኛ የሆነ ደፋር ሠው (መጀመሪያ ፈቃደኛ በሆነችው ውብ እና ውድ ባለቤቱ ነበረች) ሊዮናርዶ ዳቪንቺ እንደሳለው “The Petruvian Man” ንድፍ ሆኖ ይቆማል፡፡ ከዛ ባለ ጩቤው ሠውዬ ጩቤውን እየወረወረ ለኢላማ የቆመው ሠው ዙሪያ ይሠካል፡፡
ለኢላማ በቆመው ሠው ዙሪያ ከቆዳው የቆዳን ታህል ክፍተት ባለው ሁኔታ ጩቤውን ከተወሠነ ርቀት እየወረወረ መሠካት ነው፡፡ የቆዳን ወይም የሌላን ነገር ውፍረት እምታህል ስህተት ቢፈፀም ጩቤው የሚያርፈው ሠውየው ወይም ሴትየዋ ላይ ነው፡፡ አካል ይጐድላል ወይ ህይወት ይጠፋል፡፡ ሠውየው ግን በቃ ተሳስቶ አያውቅም፡፡ እና ለኢላማ የቆመው ሠውዬ/ሴትዮ ቦታውን ሲለቅ በጩቤ የተሳለ ሠው ግድግዳው ወይ ሰሌዳው ላይ ይቀራል፡፡
ከዚህ በላይ አደገኛ፣ አስደሳች እና ፍፅምናን የሚጠይቅ የሠርከስ ትርዒት አለ? ፍፅምና ከዚህ በላይ ከየት ይመጣል?!
አንድ ቀን ይህ ፍፅምናን የተቀዳጀ ሠርከሠኛ፣ በፍፁም ደስታ ተሞልቶ ቤቱ ሲመለስ ውድ ሚስቱ እና ውድ ጓደኛው አልጋው ላይ ትኩስ ወሲብ ሲፈፅሙ አገኛቸው፡፡
ምንም አላለም፡፡
ተጠቅልሎ ተኛ፡፡
አሪፍ እንቅልፍ ወሠደው፡፡
ጠዋት ሲነሳ ሚስቱ እንደ ወትሮው የሚወደውን ቁርስ ሠርታ፣ የሚወደውን ሻይ አፍልታ ጠበቀችው፡፡ እንደ ሁሌው አብረው በሉ፡፡ ምንም ከበፊቱ የተለወጠ ነገር አልታየባቸውም፡፡
ጩቤዎቹን እና ሌሎች ትጥቆቹን ይዞ ሊወጣ ሲል ሚስቱ እንደ ሁልጊዜው እበሩ ድረስ ሸኘችው፡፡ በሩን ዘግቶ ሊወጣ ሲል እጁን ያዘችው፡፡
“ወደ ስራ ነው የምትሄደው?”
“አዎ፡፡”
“አብሬህ ልሂድ?”
“ለምን?”
“ዛሬ ኢላማህ እኔ ልሁን”
ልትክሠው አስባለች፡፡ እንዲገላት ፈልጋለች፡፡ አይኖቿን አየ፡፡ እውነቷን ነው፡፡ መሞት ፈልጋለች፡፡
“እሺ” አላት ቁና ቁና እየተነፈሰ፡፡
“እሺ” አላት ደግሞ በደስታ እራሱን እየነቀነቀ፡፡
አንዲት ሴንቲ ሜትር አንገቷ ጋ ይሳሳታል፡፡ በቃ ፀጥ ትላለች፡፡ አሪፍ፡፡ ለኢላማ የሚቆሙ ሠዎች ሥህተት ቢፈጠር ለመቀበል ሙሉ ፈቃደኛ ሆነው ነው፡፡ በህይወታቸው ፈርደው ነው፡፡ እንደው ድንገት ስህተት ቢፈጠር ጩቤ ወርዋሪው ሠውዬ አይጠየቅም፡፡ ባጭሩ ፈቃደኛ የሆነ ብቻ ነው ለኢላማ የሚቆመው፡፡ አደገኛ ግን ደስ የሚል ትርዒት ነው፡፡ ፍቃደኛ በሽ ነው፡፡ ክፍያም አለው፡፡ ከሚያገኘው ገቢ ያካፍላቸዋል፡፡ ተመልካችም በሽ ነው፡፡
አብረው ሄዱ፡፡ … ሚስቱ ኢላማው ሆና ቆመች፡፡ ሥህተቱን የሚፈፅመው እሷ አስባለች ብሎ እንደገመተው አንገቷ ጋ አይደለም፡፡
እንድትሞት አይፈልግም፡፡ ጩቤውን ኢላማ ሊያስት የፈለገው ሀፍረቷ ጋ ነው፡፡ እሱ ነው ጠላቱ፡፡ ጩቤውን ወርውሮ እሱ ላይ መሠካት፡፡ አሪፍ ሲቃ፡፡ በቃ፡፡
ወረወረ 1፣ ወረወረ 2፣ ወረወረ፣ ወረወረ … ወረወረ… ደረሠ፡፡
ሁለቱም ትንፋሻቸውን ዋጡ፡፡ አለመ፡፡ ወረወረ፡፡ ልክ እንደሌሎቹ ጩቤዎች የተለመደው ቦታ ተሠካ፡፡ ሀፍረቷን ሳተ፡፡ የልምዱን ቦታ ግን አልሳተም … (በነገራችሁ ላይ ለኢላማ የምትቆመው ሴት ከሆነች በሙታንቲ እና በጡት መያዣ፣ ወንድ ከሆነ ደግሞ በሙታንቲ ብቻ ነው፡፡) … ቀጠለ … ወረወረ፣ ወረወረ፣ ወረወረ … አለቀ፡፡ በተለመደው ሁኔታ አለቀ፡፡
ሚስቱ የኢላማውን ቦታ ለቃ እየሳቀች እሱ ፈዞ ወደቆመበት ሄደች፡፡ ከኋላዋ ሠሌዳው ላይ በጩቤ የተሣለ የሠውነቷ ቅርፅ ቀረ፡፡ ፈዞ እያያት አጠገቡ ደረሰች፡፡
“ያልተሳሳትኩት፣ ያልገደልኩሽ ስላዘንኩልሽ ማለት ስለምወድሽ ነው” አላት እየተንተባተበ፡፡
“አይደለም” አለችው ሳቋን ሳታቋርጥ፡፡
“እና ታዲያ?!” አለ ደንግጦ፡፡
“እንደምትወደኝ አምናለሁ ግን …”
“ግን ምን?!”
“መሳሳት አትችልም፡፡ የአንዲት ሴንቲ ሜ. ስህተት መፈፀም አትችልም፡፡ ሮቦት ሆነሃል” ብላ ሳመችው፡፡
“አዎ” አለ በትንፋሽ አይነት ድምፅ፡፡ “ያንን ታውቂ ነበር?”
“አዎ” አለችው በእርግጠኝነት፡፡ እቆመበት ሆኖ አለቀሠ፡፡
እነማን ነበሩ ሠው የእግዚአብሔር ነው ወይስ የመንግስት ሮቦት እያሉ ሲከራከሩ የነበሩት?!
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby Gosa » Tue Nov 06, 2012 2:43 pm

ገልብጤ!!!!
አሁን ገና የዴቪድን ታሪክ አንብቤ ጨርስኩ:: ከሱ በላይ በጣም ቅጥል ብያለሁ በንዴት:: ሳላመሰግንህ ወደሌላው ማለፍ ስላልፈለኩ ነው:: ተባረክ ወንድሜ!!
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby recho » Tue Nov 06, 2012 2:50 pm

Gosa wrote:ገልብጤ!!!!
አሁን ገና የዴቪድን ታሪክ አንብቤ ጨርስኩ:: ከሱ በላይ በጣም ቅጥል ብያለሁ በንዴት:: ሳላመሰግንህ ወደሌላው ማለፍ ስላልፈለኩ ነው:: ተባረክ ወንድሜ!!
አንተ ቅቅቅ ማሪያምን ውሸቴን እንዳይመስልህ እሺ .. አሁን የሆነ ቅዥብሪያም ቡና ጠጣሁና ኤጭ ያ ጎሳ የታለ ስለቡና ኮምፕሌን አብሬው እንዳላደርግ ብዬ እየፈለኩህ እኮ ቅቅቅቅ ሰላም ነው ? በናትህ ቡና አለህ ? ቡናዬን ጨርሼ ይሄው እዚህ የሚያፈሉትን ቡና ብቀምሰው ቀለሙን ወደቡና አይነት ከለር የቀየረ ውሀ ነው .. ትኩስ ውሀ እና ያተረፍኩት ነገር ሽንትቤት መመላለስ ነው .. አበድረኝ አንድ ሲኒ .. ነገ መግዛቴ አይቀርም በእጥፍ ከፍልሀለሁ ..

ጎሽ ጎስዬ :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby Gosa » Tue Nov 06, 2012 3:50 pm

recho wrote:
Gosa wrote:ገልብጤ!!!!
አሁን ገና የዴቪድን ታሪክ አንብቤ ጨርስኩ:: ከሱ በላይ በጣም ቅጥል ብያለሁ በንዴት:: ሳላመሰግንህ ወደሌላው ማለፍ ስላልፈለኩ ነው:: ተባረክ ወንድሜ!!
አንተ ቅቅቅ ማሪያምን ውሸቴን እንዳይመስልህ እሺ .. አሁን የሆነ ቅዥብሪያም ቡና ጠጣሁና ኤጭ ያ ጎሳ የታለ ስለቡና ኮምፕሌን አብሬው እንዳላደርግ ብዬ እየፈለኩህ እኮ ቅቅቅቅ ሰላም ነው ? በናትህ ቡና አለህ ? ቡናዬን ጨርሼ ይሄው እዚህ የሚያፈሉትን ቡና ብቀምሰው ቀለሙን ወደቡና አይነት ከለር የቀየረ ውሀ ነው .. ትኩስ ውሀ እና ያተረፍኩት ነገር ሽንትቤት መመላለስ ነው .. አበድረኝ አንድ ሲኒ .. ነገ መግዛቴ አይቀርም በእጥፍ ከፍልሀለሁ ..

ጎሽ ጎስዬ :lol:

ሪቾ!!!
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ:: አለሽልን ወይ? ያኔ የጠቆምሽኝን የኮሎምቢያ ቡና እንደምንም አፈላልጌ አስመጥቼ አንድ ሲኒ ብጠጣ መኪናዬን መለየት አቅቶኝ ድራግ ኦቨርዶዝ ተብዬ ለስንት ጊዜ የዶክተር ኪሊራንስ ሴርቲፊኬት ተከልክዬ ያለ ስራ ስንት ጊዜ ተኝቼ ትላንት ብመለስ ዛሬ አንችኑ እዚሁ ላግኝሽ? ያውም የቡናን ስም እየጠራሽብኝ:: ተልከሽብኝ እንደሆን ለምን ቁርጡን አትነግሪኝምና ተስፋ አታስቆርጪኝም? ወይ ሪቾ:: ሻይ እንኳን መጠጣት አቁሜያለሁ:: ቅቅቅቅ
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby recho » Tue Nov 06, 2012 3:57 pm

ይጭ ምን ያለህው ነህ አንተ ደግሞ ጎሳ :twisted: :evil: አሪፍ ነው እንጂ .. ሀይፐር ሆነህ መዋል እያለ ቅቅቅ ኮኬን አንሞከር እንግዲህ በቡና ማዝገም እያለ ... ይብላኝ ላንተ እንጂ እኔስ ቡናዬን አጊንቻለሁ ቅቅቅቅቅቅ ኦላላላላላላላላላላ .... አማን ነው ለሁሉም ? ጠፋህ እኮ .. በሰላም ነው ?

ገልቡ ሰላም ብያለሁ ወዳጄ .. እዛ ቤት ለማ + ገልብጤ = ለገልብጤማ ብለው ያሙሀል .. ምንድነው ጉዱ ? :lol: :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests