እናንተስ: ብትሆኑ?

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

(-:

Postby ደጉ » Wed Oct 31, 2012 9:55 am

ቂቅ wrote:.....ሪቾ :lol: :lol: ሁለት አመት ሙሉ አንዴ ወደ ፊት አንዴ ወደኍላ አንዴ ራቁቱን እያስደረገች በዌብ ካም ወላይትኛ ስታስጨፍረው ኑራ ዛሬ ፓስወርድክን ስትለው ግራ ይገባዋል እንዴ እንዴ .....

:D ቂቅ በዚህች የፓል ህይወት ውስጥ ትንሽ ተቀጥተህ ያለፍክ ለመሆኑ አጻጻፍህ ይመስክራል....;) አንተም መቼም ዋርካ የቆየህ ለመሆኑ ባያጠያይቅም ...የዋርካውን እንተውና እስኪ ስለ ፓል ጥሩም ሆነ መጥፎ ልምድ ያካበትከውን ንገረን..መቼም የፍቅር ትሬድ ላይ ስለ ፍቅር እናውራ...ግድቡን ደግሞ ግድብ እሚወራበት ቦታ እናወራዋለን ...ፎረም ላይ በአፍ ገንብተን ምናልባት ቶሎ ብንጨርሰው... :D
....ግን አንድ ነገር የዋርካ የቆየ ባህል ሆኖ ሰው ምክር ሲጠይቅ በቅን ከመምከር ይልቅ በስድብ እምንጀምረው...በቅን የመለሳችሁትን አይመለከትም.....ስለ ጉዳዩ ለመናገር እማንችል ከሆነ እና ህሳቡም እውቀቱም ከሌለን ሰው እሚለውን ማንበብ... የሳይበር ላይ ፍቅር በአሁን ሰአት በየትኛውም የአለም ህብረተሰብ ውስጥ ይተቀሙበታል....እንደ ፓል ቶክ ሁሉ ፌስ ቡክ ቲዊተር ...እዚህም ብዙ ሳንርቅ ሳይበር ኢትዮጵያ...Ethio love አሁን ይኑር አይኑር አላውቅም...እነዚህ ሁሉ ብዙ እማይተዋወቁ ሰዎችን እሚያገናኙ ናቸው....ፓል ቶክ እርግጥ የከፋ ጎን እንዳለሁ ሁሉ የትወሰነ ጥሩ ጎንም አለው...ሳያ ቁዋርጥ 24 ሰአት እሚገባ ሰው ወይም በማንኛውም ጊዜ ስትገቡ እምታገኙት ሰው ካለ....የ አእምሮ ጤነኛ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችሁዋል...የዛኑ ያክል በተለያየ ምክንያት እዛ ላይ እማይጠፉ ሴቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ጤነኛ ሆነው እሚያጠቡ ወይ ከልጅ ጋ እሚውሉ እናቶች የሆኑም አሉ....ከዛ ወጣ ብሎ ደግሞ በጣም ጥቂት ባይሆኑም በስራ ላይ ያሉ...የራሳቸውን ስራ እሚሰሩ ጊዜ ሲያገኙ ለጨዋታ እና ቀኑን ሙሉ ሲያወሩ እሚውሉ ሩሞችን እንደ ሬድዮ እሚያዳምጡም አሉ....የሰዎቹም ክላስ እንደ ሩሞቹ ይለያያል....እንደ SINGLE ROOM. Etio Love ROOM, Free YOUR MIND, Sex Extra Vag, etc አይነት ሩሞች አዘውታሪ ከሆንክ ክልልህን (ምድብህን) እራስህ ታውቀዋለህ.. :D እነዚህ ሩሞች ደንበኛ ከሆንክ ከላይ የጠቀስከው አይነት ካም አስከፍተውህ ያንጎራድዱህና ...ከዛ ኒክህን ከ እነ ካም ኤግዚቢት ድምጽህን ጨምረው ሩም ውስጥ ያሰሙልህል..ከዛ በቃ ተማረህ ኒክህን ትቀይርና እዛው ትሆናለህ ወይ ወደ ዋርካ ትመጣና ብሶትህን በተለያየ መልኩ ታወጣዋለህ.. :D
...ፖለቲካ ሩም ደግሞ ስትገባ ምንም የፖለቲካ እውቀት ከሌለው አንስቶ በማርክስና ኤንግልስ በቀበሌ እስካጠናው ድረስ እውቀት ያለው ይኖራል....ከዛም አልፎ ምናልባት ሩስያ ውስጥ ፖለቲካ የተማረም ላይጠፋ ይችላል...ሌላው ግን በገዛ ፈቃዱ ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ እሚዳክር ነው.. :lol: እዛ ላይ እነ ማን ይውላሉ....? ከ እኔ ይልቅ ወያኔ አለቆችህን እና ጉዋደኞችህን ብትጠይቅ መልስ ታገኛለህ... :D
.....ወደ ምእራፍ ችግር ስንመጣ ...መተማመን ካለ ይላል ቅዱስ መጽህፉ ሁለት ሆናችሁ ተራራ መግፋት ትችላላችሁ...ሁለት አመት ሊያቆያችሁ የቻለ የራሳችሁ ምክንያት ሊኖር ይችላል....የስራ ጉዳይ ወይ የአገር መራራቅ ወዘተ...እንደ እኔ እንደ እኔ ግን እስክትገናኙ ግንኙነታችሁ ጥሩ ባላንስ የጠበቀ ይሁን ...ከተገናኛችሁ በሁዋላና የሁለታችሁ ኬምስትሪ ፊት ካደረገ ..አይደለም ፓስ ወርድህን ነፍስህን ዋርካ ላይ ነፍሴን ልስጥ ወይ ብለህ ሳትመጣ እዛው መስጠት ትችላለህ.. :D
....በልብ መታመን ከሁሉም ይበልጣል ...ልጅትዋ እምነት አታብህ ከሆነ ለመታመን ሞክር እንደ አገላለጽህ ልጅትዋ በጣም እምውትወድህ ትመስላለች ለዛም ነው ልቡዋ እምነት እንዲኖረው እና ሰላም እንድታገኝ ወጪ ገቢህን መቆጣጠር የፈለገችው...ያ ትክክል እንዳልሆነ ታውቀዋለች ...ምናልባትም ምን ያህል ለ እሱዋ ኦፕን መሆንህን ለማወቅም ይሆናል....እሺ ብትላት ላትቀበልህም ትችላለች ...ሴቶች ወንድን ብዙ ጊዜ መፈተን ይወዳሉ....;) እኛ ደገሞ ሁሌ ፈተናቸውን አናልፍም እንወድቃለን....ወይ እኛም ፈተና እናውጣ መሰለኝ...;)

ሰላም እንሁን :)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4466
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ለማ12 » Wed Oct 31, 2012 4:34 pm

እረ ተው አንተ ልቤን አፍርሰህ አትጨርሰው
:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ታዲያ ይህን ሁሉ ከአደረገ እኮ ብዙ ፈተናዎችን አልፏል ማለት ነውቂቅ wrote:ሪቾ :lol: :lol: ሁለት አመት ሙሉ አንዴ ወደ ፊት አንዴ ወደኍላ አንዴ ራቁቱን እያስደረገች በዌብ ካም ወላይትኛ ስታስጨፍረው ኑራ ዛሬ ፓስወርድክን ስትለው ግራ ይገባዋል እንዴ እንዴ :roll: :lol: :lol:

ወ/ሮ ሉሊት አንች ከሆንሽ ይህን ሸክላ ራስ ፓስወርዱን ብትቀበይም ምንም የሚረባ ነገር አታገኝበትም እዚህ ዋርካ ውስጥ የሾተል የፍንድድ ወላይትኛ ዳንስ አለ እሱን አሳይውና ይህንን ተለማምደህ ራቁትህን ሆነህ ጨፍርልኝ በይው ይልቅስ :lol: :lol: :lol: አንች ምእራፍ ምእራፍ እያልሽ እያጨበጨብሽለት እሱ አፈንድዶ ይጨፍር ጕደኞችሽን ይዘሽ ተዝናኝበት እኔም ዛሬ እላዩ ላይ የሾተልን ዳንስ ነው የደነስኩበት :lol: :lol: :lol: :lol:

ጆሮህን ይዤ ልምከርክ አለኝ እኮ ይህ የ 10 አመት የፓልቶክ ጉልት :roll: :lol: :lol:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ወ/ሮ ሉሊት » Wed Oct 31, 2012 5:57 pm

recho wrote:እዋይ እዋይ እዋይ ቂቅ ቅቅቅቅቅቅ የታባህ ነህ ያለህው በሳቅ ልሞት ነው ዛሬ ቅቅቅቅቅ ያው ፓስዎርድ ጠያቂዋም ወይዘሮ ተጉዋተው መጥተውልሀል ..የዘመናት ጭቅጭቅ የወለደው ጀንግናው የፖልቶክ ሰራዊት ምእራፍ ይጠቀምበትን ዋርካን ተቆጣጥሮታል .. ጉንበት ሀያ ሺ ዘጠን መቶ ሶማኒያሶስት አመተምረት :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ..... ሉሊትዬ እንዳታጦዢኝ በናትሽ ዛሬ ጥሩ ሙድ ላይ ነኝ ለቀልድ ነው ቅቅቅቅ

[quote=
ሪቾ :- በመጀመሪያ ሰላም ላንቺ ይሁን ከይቅርታ ጋር እኔ አንባቢ ነበርኩ አሁን እናንተን ለመምስል ገባሁ እንጂ ጉዳዩ አይመለከተኝም እኔ ባለትዳርና የ 3ልጆች እናት ነኝ :: ግን ነገሩ ገርሞኝ ነው ለመፃፍ የተገደድኩት ሰለዚህ ሀሳብ አይግባሽ ግን ለማማር ከሆነ ወገንተኛ ባንሆን ጥሩ ነው
ወ/ሮ ሉሊት
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Mon Oct 29, 2012 10:09 am
Location: Japan

Postby recho » Wed Oct 31, 2012 6:46 pm

ወ/ሮ ሉሊት wrote:ሪቾ :- በመጀመሪያ ሰላም ላንቺ ይሁን ከይቅርታ ጋር እኔ አንባቢ ነበርኩ አሁን እናንተን ለመምስል ገባሁ እንጂ ጉዳዩ አይመለከተኝም እኔ ባለትዳርና የ 3ልጆች እናት ነኝ :: ግን ነገሩ ገርሞኝ ነው ለመፃፍ የተገደድኩት ሰለዚህ ሀሳብ አይግባሽ ግን ለማማር ከሆነ ወገንተኛ ባንሆን ጥሩ ነው

እትዬ ሉሉትዬ .. አማርኛዎ ቀልጠፍ ሲል ነው የተጠረጠሩት .. እንዲያ ከሆነስ ይሁን .. :lol: ዶንት ማይንድ ይቺን ሪቾን .. እንደው ደርሳ ሰው ትዳፈራለች .. ማጋጨት ነበር .. ለመማማር ላሉት ግን .. እሱን ይተውት .. ወገንተኛ ላሉት .. እንግዲክ እንሞክራለን .. ቀለል ያርጉት ለሁሉም .. ከፈኑ በስተጀርባ እኮ ቁምነገርም ጽፌ ነበር .. ዘለሉዋት እንጂ ...

እንኩዋን ወደዋርካ ጸሀፊነት በሰላም መጡ .. :)
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Wed Oct 31, 2012 6:52 pm

እናንተ ሰዎች አትተውም
ደግሞ ልጅ አሳዳጊዎች አርፈን አንተኛበትrecho wrote:
ወ/ሮ ሉሊት wrote:ሪቾ :- በመጀመሪያ ሰላም ላንቺ ይሁን ከይቅርታ ጋር እኔ አንባቢ ነበርኩ አሁን እናንተን ለመምስል ገባሁ እንጂ ጉዳዩ አይመለከተኝም እኔ ባለትዳርና የ 3ልጆች እናት ነኝ :: ግን ነገሩ ገርሞኝ ነው ለመፃፍ የተገደድኩት ሰለዚህ ሀሳብ አይግባሽ ግን ለማማር ከሆነ ወገንተኛ ባንሆን ጥሩ ነው

እትዬ ሉሉትዬ .. አማርኛዎ ቀልጠፍ ሲል ነው የተጠረጠሩት .. እንዲያ ከሆነስ ይሁን .. :lol: ዶንት ማይንድ ይቺን ሪቾን .. እንደው ደርሳ ሰው ትዳፈራለች .. ማጋጨት ነበር .. ለመማማር ላሉት ግን .. እሱን ይተውት .. ወገንተኛ ላሉት .. እንግዲክ እንሞክራለን .. ቀለል ያርጉት ለሁሉም .. ከፈኑ በስተጀርባ እኮ ቁምነገርም ጽፌ ነበር .. ዘለሉዋት እንጂ ...

እንኩዋን ወደዋርካ ጸሀፊነት በሰላም መጡ .. :)
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Wed Oct 31, 2012 6:56 pm

ቅቅቅ ጋሽ ለምዬ ሀፍ ፈን .. የታባቱ .. ትንሽ ፈን እኮ እድሜ ትቀጥላለች :lol: :lol: :lol: አሁን ደግሞ ሪቾ ይሄንን አለች ብለው ዌብካም እንዳይገዙ .. ነገርኩ ሁዋላ ..
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Wed Oct 31, 2012 7:09 pm

እቤት አልገባም እንዳይሉ ልጆችን ሜዳ ታስበያቸዋለሽ
እድሜአችን ብዙ አሳይቶናል:
recho wrote:ቅቅቅ ጋሽ ለምዬ ሀፍ ፈን .. የታባቱ .. ትንሽ ፈን እኮ እድሜ ትቀጥላለች :lol: :lol: :lol: አሁን ደግሞ ሪቾ ይሄንን አለች ብለው ዌብካም እንዳይገዙ .. ነገርኩ ሁዋላ ..
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Wed Oct 31, 2012 7:14 pm

ለማ12 wrote:እቤት አልገባም እንዳይሉ ልጆችን ሜዳ ታስበያቸዋለሽ
አልገቢቶም :roll: :roll: :roll:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ገልብጤ » Wed Oct 31, 2012 7:20 pm

recho wrote:
ለማ12 wrote:እቤት አልገባም እንዳይሉ ልጆችን ሜዳ ታስበያቸዋለሽ
አልገቢቶም :roll: :roll: :roll:

ኤጭ አንቺ መቼ ይገባሽ እና ነው ..እንዲገባሽ አቅልሜ ልንገርሽ..ባራዳ ቋንቋ
እቤት አልገባም እንዳይሉ ልጆችን ሜዳ ታስነቅያቸዋለሽ

ነው የሚለው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ለማ12 » Wed Oct 31, 2012 7:24 pm

መምህር አይጥፋ እንደሱ አድርገህ አስረዳልኝ

የእኔ እናት እንድዋርካ ያሉ ነገሮች ሊአንቡ ቀርቶ 2ኛውን ካረገዙ ጀምረው መስታውት አያይዩም ነበር
ገልብጤ wrote:
recho wrote:
ለማ12 wrote:እቤት አልገባም እንዳይሉ ልጆችን ሜዳ ታስበያቸዋለሽ
አልገቢቶም :roll: :roll: :roll:

ኤጭ አንቺ መቼ ይገባሽ እና ነው ..እንዲገባሽ አቅልሜ ልንገርሽ..ባራዳ ቋንቋ
እቤት አልገባም እንዳይሉ ልጆችን ሜዳ ታስነቅያቸዋለሽ

ነው የሚለው
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Wed Oct 31, 2012 7:26 pm

ጀነራል ገልብጤ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: እንዲያ ነው ነገሩ .. ሪቾ ብለሺንግ ብለሺንግ ብለሺንግ .. :oops: እውይ ጋሽ ለምዬ ምን ሆኑብኝ .. :oops:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Wed Oct 31, 2012 7:52 pm

ትዲያ ምናባቴ ላድርግ
ገርድፌ ሳቀርብልሽ አኝኮ መዋጥ ያንቺ ፈንታ ነው.
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Wed Oct 31, 2012 8:04 pm

ለማ12 wrote:ትዲያ ምናባቴ ላድርግ
ገርድፌ ሳቀርብልሽ አኝኮ መዋጥ ያንቺ ፈንታ ነው.

ያንተ ነገር እንደው :lol: :lol: ( የድሮ ሰዎች አሉ ባላቸውን ሰው ፊት አንቱ ይሉና ለብቻቸው አንተ ይላሉ አሉ .. እውነት ነው ለምዬ ንገረኝማ ) :lol: :lol: :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Wed Oct 31, 2012 8:14 pm

:roll: :roll: :roll: :roll: :roll: :roll:
አሁን አሳቅሽኝ ታላቅ ወንድሜ ያገባቸው ሁሉም አንቱ ነው የሚሉት ነገር ግን አንዳ አንተ ስትለው እምቢ ብሎ ፈታት ለምን ነው ብለው ደግሞ እሳ ናት አንተ የምትለኝ ብሎ አሳቀኝ:

እኔ በተወለድኩበት አካባቢ ሴቶች ባላቸውን በስማቸው አይተሩም እሱ ነው የሚሉት ምክንያቱን አላውቅም የእኔ እናት ግን አይከሌ ነበር የምትለው
በጣም የሚገርም ነው:recho wrote:
ለማ12 wrote:ትዲያ ምናባቴ ላድርግ
ገርድፌ ሳቀርብልሽ አኝኮ መዋጥ ያንቺ ፈንታ ነው.

ያንተ ነገር እንደው :lol: :lol: ( የድሮ ሰዎች አሉ ባላቸውን ሰው ፊት አንቱ ይሉና ለብቻቸው አንተ ይላሉ አሉ .. እውነት ነው ለምዬ ንገረኝማ ) :lol: :lol: :lol: :lol:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1145
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Wed Oct 31, 2012 8:43 pm

ለማ12 wrote:
እኔ በተወለድኩበት አካባቢ ሴቶች ባላቸውን በስማቸው አይተሩም እሱ ነው የሚሉት ምክንያቱን አላውቅም የእኔ እናት ግን አይከሌ ነበር የምትለው
በጣም የሚገርም ነው:

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ከምሬ ነው ያሳቅከኝ ለምዬ ... እሱ ቅቅቅቅቅ የሚገርምህ አንድ እኔ እዚህው አገር የማውቀው ልጅ ሚስትን እስዋ ነው የሚላት እና ሪቾዬ ሆዬ አንድቀን በወሬ መሀል ቆይማ ለምንድነው ግን እሱዋ የምትላት ስምዋን ስትጠራ ሰምቼህ አላቅውም ምንድነው ብዬልኅኅኅህ ባልናሚስት አጣልቼ በሌሎቹ ጉዋደኞቼ ከፍተኛ ሳቅና የጭንቅላት ንቅነቃ ተለግሶኝ ወጣሁ እልሀለሁ .. ስለዚህ ከንግዲህ ለምዬ ምናምን የለም ... እሱ ነው የምልህ :lol: :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 10 guests