የሾተል የሀገር ቤት ሚስጢር ....

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

የሾተል የሀገር ቤት ሚስጢር ....

Postby ቸካዩ » Sun Nov 18, 2012 11:50 am

ከፈረንሳይ ለጋሲዮን ጉራራ አካባቢ ተነስቶ ወደ መርካቶ በሚያመራው 12 ቁጥር አውቶቡስ የተሳፈረ ግለሰብ፣ በአንዲት ወጣት ላይ የመድፈር ተግባር በመፈጸሙ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት፡፡ ኅዳር 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት ነው ድርጊቱን መፈጸሙ በሰው ምስክሮችና በሰነድ በመረጋገጡ ግለሰቡ በአንድ ዓመት ከአሥር ወር ፅኑ እስራት ቅጣት ተጥሎበታል፡፡

ግለሰቡ ድርጊቱን ፈጸመ የተባለው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02 ክልል፣ ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ አውቶቡሱ ከፈረንሳይ ወደ ጊዮርጊስ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ፣ አምባቸው አባተ ደጀኔ የተባለው ተሳፋሪ የግል ተበዳይዋን ከኋላዋ በመተሻሸት ኃፍረተ ሥጋውን በማውጣት፣ የለበሰችውን ቀሚስ ወደ ላይ ከፍ አድርጎ የዘር ፈሳሽ በልብሷ ላይ ማፍሰሱን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ለመልካም ሥነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ ብልግናና አሳፋሪ ሥራን በአደባባይ በመፈጸም ወንጀል መከሰሱንም ገልጿል፡፡

ግለሰቡ ድርጊቱን ሲፈጽም የተመለከቱ አዛውንት ድርጊቱን በመኮነን ‹‹እንዴት እንደዚህ ያለ አፀያፊና ወራዳ ተግባር ትፈጽማለህ?›› ሲሉት፣ በያዘው የመስታወት መቁረጫ ስለት እጃቸውን ሁለት ቦታ እንደወጋቸውና እግራቸውንም እንደነከሳቸው ክሱ ያስረዳል፡፡

የዓቃቤ ሕግን ክስ የመረመረው ፍርድ ቤቱ ድርጊቱ በሰውና በሰነድ ማስረጃ መረጋገጡን ገልጾ፣ የወንጀሉ መጠን በከባድ የወንጀል ደረጃ መድቦታል፡፡ በመሆኑም የተጠቀሰበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ የሚያስቀምጠውን ከፍተኛውን የቅጣት መነሻ ይዞ በሁለቱም ድርጊት በድምሩ አንድ ዓመት ከአሥር ወር እንዲታሰር ወስኖበታል፡፡

ምንጭ http://www.ethiopianreporter.com/news/2 ... 31-52.html
ቸካዩ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 144
Joined: Fri Jul 30, 2010 8:26 am

Postby ክቡራን » Sun Nov 18, 2012 1:05 pm

Code: Select all
ግለሰቡ ድርጊቱን ፈጸመ የተባለው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02 ክልል፣ ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አምስተኛ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ አውቶቡሱ ከፈረንሳይ ወደ ጊዮርጊስ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ፣ አየለ መዓዛ ወልደ ዮሐንስ የተባለው ተሳፋሪ የግል ተበዳይዋን ከኋላዋ በመተሻሸት ኃፍረተ ሥጋውን በማውጣት፣ የለበሰችውን ቀሚስ ወደ ላይ ከፍ አድርጎ የዘር ፈሳሽ በልብሷ ላይ ማፍሰሱን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡ ለመልካም ሥነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ ብልግናና አሳፋሪ ሥራን በአደባባይ በመፈጸም ወንጀል መከሰሱንም ገልጿል፡፡


ሸቃዩ ወንድሜ ውሽት አትልመድ:: መልካም አይደለም:: አሁን ካላቆምንህ በኌላ ግመል አንክብክበህ ብትሄድ አንመልስህም:: አክባሪህ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7943
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 10 guests