የዝምታ ጩኸት (በትዕግስት አለምነህ)

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

የዝምታ ጩኸት (በትዕግስት አለምነህ)

Postby ሙዝ1 » Tue Nov 20, 2012 7:08 pm

በቅርቡ በመጽሀፏ ምረቃ በአል ላይ ተገኝቼ ... የድርሻዬን ገዝቼ ወደ ቤቴ ብገባም እስካሁን አላነበብኳትም ነበር:: ቲጂ አሪፍ ጓደኛዬ ነች ... ... ገጣሚ መሆኗን አልዉቅም ነበርና አሪፍ ጕደኛዬ ከምል ብሮ አደጌ ብል ይሻላል ...

የመጽሀፏ አርዕስት ስቦኛል ... የዝምታ ጩኸት ... ሀሀሀሀ

ዛሬ ትንሽ ደብሮኝ ስለነበር ድብርቴን ለማባረር መጽሀፍቶቼን ጎብኘት ሳደርግ አየሗትና ገለጥ ገለጥ ከማድረጌ በፊት ... ከመጽሀፏ ጀርባ የተለጠፈችዉን ግጥም አነበብኩ ... እንዲህ ትላለች ....

ሌላዉ እኔን እኔን
እኔም አንተን አንተን
አንተ ደግሞ ሌላ
አብት የኛ ገላ
ሲከተል ይኖራል ሀሳቡ ላይሞላ::

ሸላይ ነች ይላል ዋናዉ ... ... ግጥሟ የሁላችንም ህይወት ብትሆንም የቋንቋ ዉበቷን ወድጃታለሁ .....

ለዛሬዉ ስሜቴ የምትሆን ደግሞ ገጽ 46 ላይ አገኘሁ

እኔ ለኔ በሆንኩ

መቸ ነዉ ምትኖረዉ ተደስታ ነፍሴ
ዉስጤ ያሰበዉን ምንም ሳልሳቀቅ የማድረግ ለራሴ?
ይሉኝታ ተብትቦኝ ሰዉ ምን ይለኝ እያልኩ
መኖሬ ቢበቃኝ እኔ ለኔ በሆንኩ::


ልቦናዬ ጽና

ገጽ 37

ባላሰብከዉ ቢሄድ የህይወት መንገድህ
ዞሮ ተሽከርክሮ ተቃርኖ ቢገጥምህ
መደሰት እንዳለ ምከፋት አለና
መወለድ እስካለ ሞት አይቀርምና
ተዘጋጅተህ ጠብቅ ልቦናዬ ጽና ....

ግጥም እወዳለሁ እንጂ አላዉቅም ... ... ከላይ ያሉት የቲጂ ግጥሞች ቀላል ቢሆኑም ለዚህች ቅጽበት ገልጠዉኛልና ወድጃቸዋለሁ .....

ሽኝት

ሸኚኝ ትለኛለህ ባህር ስትሻገር
እንዳለህ አላወክ ከልቤ ማህደር
ስርህ ከደሜ ነዉ በልቤ በቅልሀል
አልገባህም አንተ የራከን መስሎሀል
ለመምሰል ሸኘሁህ አካልህ ሲሸሸኝ
መንፈስህ ከኔ ነዉ መቸም አይለየኝ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Tue Nov 20, 2012 7:15 pm

ሰላም ነው ሙዝ?

ምን የማይገጥም ፍጡር የለም
ባለፈው ወቅትም ውዳላት ገዳሙ የግጥም መጻፍ መርቁ ብላ
አያልነህ ሙላት በግድ ይዞኝ ሄዶ 10 መጻፍ አስገዝቶኝ ነበር አንተ እንዳልከው ግን አላነበኩትም:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Tue Nov 20, 2012 7:38 pm

ሀይ ለማ1 እንዴት ነህ?
ሀሀሀ እንዴ እትየ ዉዳላት እድሜ ላይ ማንበብ ተጨምሮ ያበሰላት ነች ..... ጋሽ አያልነህም እንዲሁ ... ቲጂ ግን ገና ጀማሪ ነች ... ትምህርቷም ...የህይወት ልምዷም አናሳ ነዉ ... ቢሆንም ግን ፍቅር ነክ ጨዋታዎቿ ደስ ይላሉ ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Re: የዝምታ ጩኸት (በትዕግስት አለምነህ)

Postby recho » Tue Nov 20, 2012 7:45 pm

ሙዝ1 wrote:ልቦናዬ ጽና

ገጽ 37

ባላሰብከዉ ቢሄድ የህይወት መንገድህ
ዞሮ ተሽከርክሮ ተቃርኖ ቢገጥምህ
መደሰት እንዳለ ምከፋት አለና
መወለድ እስካለ ሞት አይቀርምና
ተዘጋጅተህ ጠብቅ ልቦናዬ ጽና ....


እህምምምምም! ይሁና! :cry:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Tue Nov 20, 2012 7:55 pm

ሰላም ነው ሰላም ነው ሙዝ


ያው በየጎደለበት መሙያ ስለሚያድረጉኝ ያው ይጎትቱኛል
ባሻ ከድርን ታውቃቸዋለህ ሙዝ ?


ሙዝ1 wrote:ሀይ ለማ1 እንዴት ነህ?
ሀሀሀ እንዴ እትየ ዉዳላት እድሜ ላይ ማንበብ ተጨምሮ ያበሰላት ነች ..... ጋሽ አያልነህም እንዲሁ ... ቲጂ ግን ገና ጀማሪ ነች ... ትምህርቷም ...የህይወት ልምዷም አናሳ ነዉ ... ቢሆንም ግን ፍቅር ነክ ጨዋታዎቿ ደስ ይላሉ ...
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: የዝምታ ጩኸት (በትዕግስት አለምነህ)

Postby ለማ12 » Tue Nov 20, 2012 8:03 pm

እኔስ ጅብ ጠላሁ አለ ያደካማ
ምነው ሪቺ ሞት ?
recho wrote:
ሙዝ1 wrote:ልቦናዬ ጽና

ገጽ 37

ባላሰብከዉ ቢሄድ የህይወት መንገድህ
ዞሮ ተሽከርክሮ ተቃርኖ ቢገጥምህ
መደሰት እንዳለ ምከፋት አለና
መወለድ እስካለ ሞት አይቀርምና
ተዘጋጅተህ ጠብቅ ልቦናዬ ጽና ....


እህምምምምም! ይሁና! :cry:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: የዝምታ ጩኸት (በትዕግስት አለምነህ)

Postby recho » Tue Nov 20, 2012 8:17 pm

ለምዬ
አንድ ሁለቴ ጎብኝቶኛል .. የሱ ሰውዬ ክፋት የሰው ነገር መንጠቅ ይወዳል .. የወሰዳቸው ብርቅዬዎቼን ነው .. እና ስሙ ሲነሳ ዋ .. ብዬ በሩቅ አያለሁ .. ምናልባት አዝኖ ቢመልስልኝ ብዬ .. እናልህ በዝግጅት የምትቀበለው .. በቃ ይመጣል ጽና ልቤ ብለህ የምትዘጋጅለት ነገር አለመሆኑን ገጣሚዋ አለማወቅዋ አሳዝኖች እህምምም አልኩኛ ወዳጄ ...

ለማ12 wrote:እኔስ ጅብ ጠላሁ አለ ያደካማ
ምነው ሪቺ ሞት ?
recho wrote:
ሙዝ1 wrote:ልቦናዬ ጽና

ገጽ 37

ባላሰብከዉ ቢሄድ የህይወት መንገድህ
ዞሮ ተሽከርክሮ ተቃርኖ ቢገጥምህ
መደሰት እንዳለ ምከፋት አለና
መወለድ እስካለ ሞት አይቀርምና
ተዘጋጅተህ ጠብቅ ልቦናዬ ጽና ....


እህምምምምም! ይሁና! :cry:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Tue Nov 20, 2012 8:24 pm

ሪቺ አዝናለሁ
ሁላችንም ተነክተናል ግን ምን ማድረግ ይቻላል?

ሰው እኮ የተፈጠረው ለዚሁ ነው አይዞን
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Tue Nov 20, 2012 8:30 pm

ለማ12 wrote:ሪቺ አዝናለሁ
ሁላችንም ተነክተናል ግን ምን ማድረግ ይቻላል?

ሰው እኮ የተፈጠረው ለዚሁ ነው አይዞን
አይ አይ .. እኔ የማልወደው ሰው የተፈጠረው ለሞት ነው የሚለውን እሳቤ ራሱ ነው .. ሰውማ የተፈጠርው ሊኖር ነው .. ሊኖርም ነበር .. በቴክኒክ ስተት ነው ሞት ጣልቃ የገባው .. ስለዚህ ሪቾ መቼም ቢሆን የምትወዳቸውንም ሆነ የራስዋን ሞት አሜን ብላ አትቀበልም ! በፍጹም! አጅሬ ሞት ላንተ ያለኝን ጥላቻ በታላቅ ፍቅርና አክብሮት እገልጽልሀለሁ ... መቼም ቢሆን አልወድህም .. ታስፈራራኛለህ ... አውቃለሁ እፈራሀለሁ .. ግን የምፈራህ ከምወዳቸው መለየትን ስለማልወድ እንጂ ያንን የገጠጠ አሽሙረኛ ፈገግታህን ወይንም ያንን ጥላሸት የመሰለ ፊትህን አይደለም ... ፈጽሞ ! ያንን ትፈራለች ብለህ ፊትለፊቴ ስትደንስ አትዋል .. ጊዜህን አታቃጥል ወደሚፈሩህ ሂድ .. ቀፋፊ! :twisted:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Tue Nov 20, 2012 8:37 pm

ለፈግታ አንድ ተረት ግን እውነት ልንገርሽ

አንዱ ትናንቱን አህያው ጠፍቶ ማታ ጅብ በላበት
በነጋው ማታ ደግሞ ጅብ ሲጭህ ሰማው ምን አላት መሰለሽ ሚስቱን አንቺ እኔስ
ጅብ ጠላሁ አለ ያነን ነው የጠቀስኩልሽ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Tue Nov 20, 2012 8:42 pm

ለምዬ :lol: :lol: :lol: :lol: እንደው በቃ በኩርኮራም ቢሆን ታስቀኛለህ እኮ ... ያንተ ነገር ... እኔ ደግሞ አጅሬውን ሙልጭ አርገህ ትሰድብልኛለህ ብዬ እኮ :lol: :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Tue Nov 20, 2012 8:47 pm

አላደርገውም:
ግን ይህን ቤት የከፈተው ጎረምሳ

ባላሳድገውም እንደአሳዳኩት ቁጠሪውና አሁን አጋባኝ እያለ እያስቸገርኝ ነው :
እግሬ ወደ ጉርጉአድ ሲሄድ ሚስት ፍለጋ ሂድ ተብዬ እየትንደባረኩልሽ ነው ::recho wrote:ለምዬ :lol: :lol: :lol: :lol: እንደው በቃ በኩርኮራም ቢሆን ታስቀኛለህ እኮ ... ያንተ ነገር ... እኔ ደግሞ አጅሬውን ሙልጭ አርገህ ትሰድብልኛለህ ብዬ እኮ :lol: :lol: :lol:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Tue Nov 20, 2012 8:57 pm

ውይ ሙዝራስ? ቅቅቅ ሙዝራስ እኮ የትምርትቤት ጉዋደኛዬ ነው ( በነገርህ ላይ አብረን አንድ ኮሌጅ ነው የተማርነው እና ብዙ ሂስትሪ አለን :lol: ) ለማግባቱማ ቅድሚያ የተሰጠው ለሱ ነው .. ተው ለምዬ አታስለፍልፈኝ .. :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ሓየት11 » Tue Nov 20, 2012 9:05 pm

አንቱ ሰውዬ ... ጤናም የሎት ልበል? :lol: :lol:

ምንድነው ነገሩ ... ተግር ተግር እየተከተሉ ተይች ኮረዳ አልላቀቅ አሉሳ ... ዋ ... ዝም ብዬ ባዮት ባዮት ... ከዛሬ ነገ ይሻሉ ይሆናል ... ብዬ ... ጊዜ ብሰጦት ... ተጣብቀው ሊቀሩ ነው እንዴ? ... እረገኝ :lol: :lol: ... በሉ ፈቅ ይበሉ ንዴ ... ምነው ጣሊያን :D

አንቺ ዶኬ ፊት ደግሞ ... ለምዬ ነው ጥላዬ ... ከምትይው ሰው ዳግም እንዳላይሽ ... እግርሽን ስብርብር አርጌ ... የመደብ ቁራኛ እንዳላረግሽ ... :lol: :lol:

ለማ12 wrote:አላደርገውም:
ግን ይህን ቤት የከፈተው ጎረምሳ

ባላሳድገውም እንደአሳዳኩት ቁጠሪውና አሁን አጋባኝ እያለ እያስቸገርኝ ነው :
እግሬ ወደ ጉርጉአድ ሲሄድ ሚስት ፍለጋ ሂድ ተብዬ እየትንደባረኩልሽ ነው ::recho wrote:ለምዬ :lol: :lol: :lol: :lol: እንደው በቃ በኩርኮራም ቢሆን ታስቀኛለህ እኮ ... ያንተ ነገር ... እኔ ደግሞ አጅሬውን ሙልጭ አርገህ ትሰድብልኛለህ ብዬ እኮ :lol: :lol: :lol:
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ለማ12 » Tue Nov 20, 2012 9:09 pm

አውቃው አረፈች ነው ያለው ያደሀ ጎብዝ እህቱን:

ምን ሆነ መሰልሽ

ያንዲቱ ሴትዮ አባት ይሞቱና 2 ወንድሞቸአ ንገሩ ተብለው ይላካሉ

ታዲያ እቤት ሲደርሱ አንገታቸውን ደፍተው ምን ሆናች ሁ ነው ደህና አይደላችሁም ? ሰው ሞተ ብላ ስትጠይቃቸው ?

አየ ልታውቀው ነው መሰል ይላሉ
እሱአም አንተ እናቴ ሞተች ስትል ስትጠቅ እሱአስ አይደለችም ይላል:
ታዲያ ማን ሞተ አባቴ ሞተ ብላ ስትጠይቅ

አይ አውቃው አረፈች አለ አሉ


አሁንም የዘበኑ ልጆች ሳናስበው ሁለመናውን እየቀደማችሁ እየጨረሳችሁ አስቸግራችሁን?

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

recho wrote:ውይ ሙዝራስ? ቅቅቅ ሙዝራስ እኮ የትምርትቤት ጉዋደኛዬ ነው ( በነገርህ ላይ አብረን አንድ ኮሌጅ ነው የተማርነው እና ብዙ ሂስትሪ አለን :lol: ) ለማግባቱማ ቅድሚያ የተሰጠው ለሱ ነው .. ተው ለምዬ አታስለፍልፈኝ .. :lol:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests