ገላግሉኝ : ለዳኝነት ተቸገርኩ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ገላግሉኝ : ለዳኝነት ተቸገርኩ

Postby የዳንግላው » Wed Dec 05, 2012 8:45 am

ልጂቱን ቀድሜ ባውቃትም በእሷ ተዋውቄው ባልዬው ቤስት ጓደኛዬ ከሆነ ዐመታት ተቆጠሩ:: ከመቀረራረባችን የተነሳ እንዲያውም እኔን ብለው ካለሁበት ከተማ ድረስ ሙቭ አርገው ቤት ገዝተው ልጅ አፍርተው የተደላደለ ሕይወት ተያይዘዋል:: ግን ከጥቂት ጊዜ ወዲህ በመሐላቸው ትንሽ ንትርክ እየተጀመረ ነው::

ጉዳዩ እንዲህ ነው:: እነሱ ካሉበት ሰፈር ሀበሻ የለም ነጭ የሚበዛበት ነው:: ግን ከቤታቸው አጠገብ ቀጥሎ ያለው ቤት ሰውዬ ጥቁር ሚስትዬው ነጭ ነች:: የአንድ ትልቅ አሜሪካን ዩኒቨርስቲ ፉትቦል አሰልጣኝ ነው የሚኖረውም በሰራተኛ /ናኒ ነው እኔ ነኝ ያለ የዘነጠ ላይፍ ያለው ቤተሰብ ነው:: ሚስትዬው ሩቅ ድራይቭ እያረገች የምጸራና ያንድ ትልቅ መሥሪያ ቤት CEO ነገር ነች:: ባልዬዋ ግን ጊዜ የተረፈረው ገና ላይፍ ያልጠገበ ነገር ነው:: እናማ የጓደኞቼን ልጅ የሚያህል ጩጬ ሕጻን ስላለው ያን ሕጻን ምክንያት እያረገ ወደ ጓደኞቼ ቤት ነጋ ጠባ ጩጬውን እያስቀደመ በር እያንኳኳ ከቸች ይላል:: በዚያውም ወሬውን ይቀዳል ቶሎ አይወጣም::

ነገሩ በዚህ ቢያበቃ መልካም ነበር ግን:: እንደ ጓደኛዬ አባባል አጂሬው እግሩ ወደ ቤቱ ከማዘወተሩ የተነሳ አንዳንዴ መኪናውን ፓርክ የሚያደርገው ወደራሱ ጋራዥ ጋ እያመጣ እንደሆነ ነው:: የጓደኛዬ ሚስትም ፓርታይም ስለምትሰራ አብዛኛውን ጊዜ ቤት የምትሆንበት ጊዜ ይበዛል:: ጓደኛዬ ደግሞ ጥዋት ወጦ ማታ ይገባል:: እናማ ጓደኛዬ ይህን ዱድ ሆዱ ክፉኛ ጠርጥሮታል:: እንደ ቅርበቴ በመሐላቸው ገብቼ ትዳራቸውን ለማዳን ሀላፊነት ስላለብኝ እኔም ገባ ብዬ ሁኔታውን ስታዘበው በፍጹም አስፈርቶኛል:: ጓደኛዬ ጉዳዩን ለእኔ ካጫወተኝ በኋላ እኔም አንድ ቀን ድንገት ቤታቸው ብቅ ብል ልጅቱ ክቺን ኩክ ስታደርግ ስትሬንጀሩ ጎረቤት ባለጌ ወንበር ላይ ዱቅ ብሎ የምትሰራውን ወጥ እንደ አባወራ ያያል:: ባለቤቷ ቤት የለም:: ሰውየው ስያየኝ ጭራሽ ስሙን በመንገር ቀድሞ እየተዋወቀኝ ትከሻዬን መታ መታ እያረገ ዐይኑን በጨው አጥቦ በሰው ቤት ከሰው ሚስት አጠገብ ደረቱ እያሻሸ በልበ ሙሉነት < ዋሳፕ ማይሜን! > እያለ ወጥ መሥራት እየተማርኩ ነው ብሎ ወሬውን ሲቀድልኝ እሷ ግን ደንግጣ ተደነባበረች:: አያድረስ ነው:: :oops: በሀሳቤ በገንኩ ተቃጠልኩ ግን ምን ይደረግ ! እምምም አያድርስ ነው::

አንድ ነገር መጣልኝና ይሄን እንዲያደርግ መከርኩት:: ድምጽ የሚቀዳ ቮይስ ሪኮርደር ቤት ውስጥ እንዲያስቀምጥ መከርኩት:: አደረገ:: ሰውዬው በየቀኑ ሁሌ ከች ይልና እንደሚያወራት ነገረኝ:: ከወሬው ውስጥ ግን እሷን ፊዚካሊ የሚነካካበት ሁኔታ ባይኖርም ወደ ሌላ ነገር የሚያስገባ መስመር የለቀቀ ሴክሿል ጨዋታ እያመጣ በተደጋጋሚ ሲሞክር ይሰማል ብሎኛል:: ለእኔ ይሄ በቂ ማስረጃ ነው:: ፊት ለፊት እንደ ወንድ ንገረው እኔ በለለሁበት ቤቴ እንድትመጣ አልፈልግም ጉዳይህ ከባለቤቴ ጋር ሳይሆን እንደጉርብትናችን ከእኔ ጋር መሆን አለበት ብለህ አስጠንቅቀው እምቢ ካለ የቀዳሄውን ሚስቱ አሰማ አልኩት:: ጓደኛዬ ግን ዘሎ በሚስቱ ላይ እየፈረደ ነው እሷው ናት ያስደፈረችኝ እያለ ነው እሱ የነገረኝ ታሪክ ከዚህ የባሰም ነው:: ሰውዬው በገዛቅ አፉ እንደነገረው ሞተር ባይስክል እያላመድኩልህ ነው ሁላ ብሎታል::

ልጁ(ባልዬው) ለገዛበት ቤቱ ትዳሩና ሕይወቱ በጣም ኢንቨስት አርጎበታል በቀላሉ ለማፍረስም ይከብዳል አሁን የናንተን ምክር የምፈልገው ሁለቱንም በምን ዐይነት ቀርቤ ነው ትዳራቸውን ማዳን የምችለው ወይም ከሕሊና የጸዳ ፍርድ መስጠት እንድችል ምከሩኝ እባካችሁ !!!
የዳንግላው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 69
Joined: Sat Dec 18, 2004 9:11 am
Location: Blackburn - Uk

(-:

Postby ደጉ » Wed Dec 05, 2012 11:49 am

...የዳንግላው :D "በጊዜ ያልታሸ ለምርኩዝ ያበቃል" ይባላል....ይሄን ሁሉ ትያትር አንተም ሆነ ባልየው ከምትሰሩ....ሰውየው እሱ በሌለበት ወይም ከነ ጭራሹ እንዳይመጣ ማድረግ አይቀልም....?? ምን እስኪሆን እየጠበቃችሁ እንደ ሆነ ካጻጻፍህ አይገባኝም... አንድ ቀን ሬፕ ቢያደርጋትስ..? ለ እናንተ እምታማክራችሁ ይመስላችሁዋል...? ;)
....አንተ ነገር ዛሬ ሳትል ሁለቱንም ይዘህ ቁጭ አድረገህ ንገራቸው ....ወይ መጀምሪያ ሚስትየውን ባልዋም ሆነ አንተ በሁኔታው ደስተኛ እንዳልሆናችሁ ሰውየውም ለማነሳሳት እየሞከረ መሆኑንም የቀዳችሁትንም አሰሙዋት ...:) እሱም እሱዋን ብሌም አድርጎ ወደ ሌላ ነገር (መግባት ወዳልፈለገችበት) እንትገባ አያድርጋት...ቁጭ ብሎ እንደ ጅል እሚሆነውን እየጠበቀ... 1 ሰው እሺ እንዴት ሁለት ህናችሁ ጅል ትሆናላችሁ...? :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4424
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ለማ12 » Wed Dec 05, 2012 1:50 pm

እዳሪ አድራ ፈርስ ልትሆነኝ ነው ወይ አለ አያ ጋሹ:


ፈረሱ ጠፋችና እህቴ አይዞህ አድራ ትገኛለች ኣለችው
ደግሞ ይቺ ቴቴ ዋጋ ሞኝ ናት
እዳሪ አድራ ፈረስ ልትሆነኝ ነው አለው:

አሁን የኛ ምክር ይረዳህ ይመስልሀል ያልቀውን ነገር ለምን እኛንስ ታስቸግራለህ ?

አደራችሁ እንዳትስድቡኝ:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1115
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby የተሞናሞነው » Wed Dec 05, 2012 5:49 pm

ስንት አይነት ሰው አለ ባካችሁ :lol: እንዴት የምወዳት ሚስቴን ከቤቴ አንድ ጠረንገሎ እየመጣ ሲያጫውታት ሰውን ለምክር እጠይቃለሁ...እስኪጠረጥር ድረስ ዝም የሚል እንዝህላል ሀበሻ...ለሷም ባል አይሆናት....ለጥቁሩ ይስጠው...ነፈዝ ሁላ :lol:
የተሞናሞነው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1129
Joined: Wed May 11, 2011 5:39 pm

Postby ጌታ » Wed Dec 05, 2012 7:16 pm

የዲያንግላው:

አይ የዛሬ ጓደኛ!!! ሰውየው ሚስጥረኛዬ ብሎ ያካፈለህን የጓዳ ታሪክ እዚህ መጥተህ ዘረገፍክለት!!! ሕዝብ እንዲያውቅለት ከፈለገ እኮ አንተን ከማማከር እሱው ሬድዮ ፋና ደውሎ አማክሩኝ ይል ነበር:: እንኳን አወቅሁህ እንጂ ፀሀይ በምዕራብ እንደምትወጣ በሚስጥር ልነግር አስቤ ነበር :lol: :lol: :lol: :lol:

በል ሌላም የነገረህ ነገር ካለ ናና ሹክ በለን :lol: :lol:

ከዳንግላ ባሻገር የብቸናው ነኝ
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ሾተል » Wed Dec 05, 2012 7:18 pm

የጨዋው ልጅ ጨዋው ጌታ ወንድማችን እንደምን አለኽልን?ከዋርካ ጠፋ ማለትኽን አውቀን ሁሌም ስናስብህ ነበር::ግን በሰላም ስላየንኽ ደስ ብሎናል::

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9647
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ጌታ » Wed Dec 05, 2012 7:32 pm

ሾተል ወንድማችን አለሁልህ:: ኑሮና ብልሃቱ ወጥሮን ከዋርካ 40 ክንድ ብንርቅም በሩቁ ማየታችን አልቀረም:: ባለፈው ይሄን ዩሮ ክርስማስ ዴኮሬሽን አስመስለኸው 'ጊዜ እንድገዛበት ላክልኝ' ልበልህ አልበልህ እያልኩ ስሟገት አይፎን5 ገዛህበት አሉኝ :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Re: (-:

Postby እህምም » Wed Dec 05, 2012 9:17 pm

ደጉ wrote:...የዳንግላው :D "በጊዜ ያልታሸ ለምርኩዝ ያበቃል" ይባላል....ይሄን ሁሉ ትያትር አንተም ሆነ ባልየው ከምትሰሩ....ሰውየው እሱ በሌለበት ወይም ከነ ጭራሹ እንዳይመጣ ማድረግ አይቀልም....?? ምን እስኪሆን እየጠበቃችሁ እንደ ሆነ ካጻጻፍህ አይገባኝም... አንድ ቀን ሬፕ ቢያደርጋትስ..? ለ እናንተ እምታማክራችሁ ይመስላችሁዋል...? ;)
....አንተ ነገር ዛሬ ሳትል ሁለቱንም ይዘህ ቁጭ አድረገህ ንገራቸው ....ወይ መጀምሪያ ሚስትየውን ባልዋም ሆነ አንተ በሁኔታው ደስተኛ እንዳልሆናችሁ ሰውየውም ለማነሳሳት እየሞከረ መሆኑንም የቀዳችሁትንም አሰሙዋት ...:) እሱም እሱዋን ብሌም አድርጎ ወደ ሌላ ነገር (መግባት ወዳልፈለገችበት) እንትገባ አያድርጋት...ቁጭ ብሎ እንደ ጅል እሚሆነውን እየጠበቀ... 1 ሰው እሺ እንዴት ሁለት ህናችሁ ጅል ትሆናላችሁ...? :D


:lol: እኔም ይሄንን እያሰብኩ ነበር:: እማላውቀው ሰው ቤቴ እየመጣ እሚጣድበት ምንም ጉዳይ የለውም :: ስነስረአት አይደለም:: plain and simple!
Homage to darkness : http://yekolotemari.blog.com/2010/02/09 ... -darkness/


"Is it stealing
if I take
the pains of others

and make it my healing?"
http://elicitbeauty.blogspot.com/
እህምም
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2509
Joined: Mon Dec 19, 2005 10:36 pm
Location: on a small rock; between an ocean and a sea.

Re: (-:

Postby የዳንግላው » Thu Dec 06, 2012 8:44 am

ደጉ wrote:...የዳንግላው :D "በጊዜ ያልታሸ ለምርኩዝ ያበቃል" ይባላል....ይሄን ሁሉ ትያትር አንተም ሆነ ባልየው ከምትሰሩ....ሰውየው እሱ በሌለበት ወይም ከነ ጭራሹ እንዳይመጣ ማድረግ አይቀልም....?? ምን እስኪሆን እየጠበቃችሁ እንደ ሆነ ካጻጻፍህ አይገባኝም... አንድ ቀን ሬፕ ቢያደርጋትስ..? ለ እናንተ እምታማክራችሁ ይመስላችሁዋል...? ;)
....አንተ ነገር ዛሬ ሳትል ሁለቱንም ይዘህ ቁጭ አድረገህ ንገራቸው ....ወይ መጀምሪያ ሚስትየውን ባልዋም ሆነ አንተ በሁኔታው ደስተኛ እንዳልሆናችሁ ሰውየውም ለማነሳሳት እየሞከረ መሆኑንም የቀዳችሁትንም አሰሙዋት ...:) እሱም እሱዋን ብሌም አድርጎ ወደ ሌላ ነገር (መግባት ወዳልፈለገችበት) እንትገባ አያድርጋት... ቁጭ ብሎ እንደ ጅል እሚሆነውን እየጠበቀ... 1 ሰው እሺ እንዴት ሁለት ህናችሁ ጅል ትሆናላችሁ...? :D


ደጉ በጣም አመሰግናለሁ:: በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው:: በትክክል አንተ እንዳልከው እኔም አደርጋለሁ ግን ልጅቱ በሚስጢር ድምጽ የተቀዳውን ብናሰማት ተናዳ እልህ ውስጥ ገብታ ነገር እንዳታበላሽም ፈራሁ:: በመሀላቸው ስገባ እኔንም የችግራቸው መንስኤ እንዳያረጉኝ በጣም እጠነቀቃለሁ:: ምክንያቱም ልጅቱ ከየዋህነት ይሁን አላውቅም ሰውዬውን በጣም ታከብረዋለች:: ጥሩ ሰው ነው ትላለች:: ለነገሩ ይህ የሁሉም ሀበሾች ችግር ነው::

ጌታው : የሰዎችን ስም አልጠራሁ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን አደባባይ አላወጣሁ ወዴት ወዴት ሄድክ ያገር ልጅ ? እረ እየተስተዋለ :roll:
የዳንግላው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 69
Joined: Sat Dec 18, 2004 9:11 am
Location: Blackburn - Uk

Postby የቦግዪ » Thu Dec 06, 2012 12:21 pm

አንድ ነገር ግልጽ አልሆነልኝም:: ቤቱ ስንት ክፍል ነው? ድምጽ መቅጃውን የት ክፍል ነው ያደረገው? ወይም ስንት የድምጽ መቅጃ ነው የተጠቀመው? ቪዲዎ አይሻለውም ነበር?

ግን እንደተባለው መቅዳት እና እሱን እንደ ማስረጃ መጠቀም በሱ ምክንያት ለመለያየት ካልሆነ በቀር መፍትሄ አያመጣም:: ቺት ማድረጉዋን ቢያውቅ ምን ሊያደርግ ነው? መለያየት ወይስ ብላክሜል? ስለዚህ በመቅዳት ምናምን ጊዜውን ከሚያጠፋ ሌላ ነገር እስኪፈጠር ከሚጠብቅ tell him to be the man of his house.
Gotta live my life like there's one more move to make.
የቦግዪ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Sun Oct 28, 2012 6:56 pm

Postby ኣሸወይና » Thu Dec 06, 2012 4:12 pm

ዉድ ወንድማችን የዳንግላዉ! መቼም ምከሩኝ ስላልክ የምችለዉን አንድ ሙሉ ባሊ የህይወት ተሞክሮ ምክራ ምክሮችን ልለግስህ እፈላጋለሁኝ ለአንተ ዕና ለጓደኛህ::
በመጀምሪያ ኒግሮ ወንድማችን የቀረበች የሀበሻ ቺክ ምንም ተስፋ የላትም!
like they said""once u go to Black U never come Back""እናም ሰዉየዉ ከወጥቤት ግድግዳ ጋራ እያጋጨ ሀይለኛ ብድ በድቱኣታል!!ይህንን የጥቁር ብድ አጋንንትየተባለዉን ብድ; ዕንኳን ሁለት ስራ የሚሰራዉ ወንድማችን ሀበሻዉ ይቅርና ነጮች እንኳን ቪያግራ ቢጠቀሙ እንደዚህ ሚስቶቻቸዉን ሊበዱ እንደማይችል ስይንሳዊ ሐቅ ነዉ::ስለዚህ ጛደኛህ ዕና አንተ ሁለት አማራጭ አላችሁ:: አንደኛዉ ፍቅር ከሚስቱ ካለዉ ጥቁሩ ያስተረፈለትን ፑሲ ባለችዉ እቃ እንደምንም ነካ ነካ አድርጎ መተኛት ልጅም ከወለደች ከጥቁሩ ብራዘር እንደራሱ ልጅ ማሳደግ እናም ጥቁሩ ለዋለለት ዉለታ ሚስቱን አንዳንዴ ከጥቁሩ ጋር ለVአኬሽን የሚሆናቸዉን ዶላር መስጠት እንዲሁም ጥቁሩ ጓደኛህ ቤት ማደር ከፈለገ ጓደኛህ አልጋዉን ለቅቆ ለጥቁሩ ብራዘር ወጥ እና ወጣወጦችን እንዲሁም ፒሳ በማምጣት ሚስቱን እና ጥቁሩን ሰዉዬ ማገልገል!! ሁለተኛዉ አማራጭ ወንድ መሆን የጥቁሩን እግር በሻት ጋን መቁረጥ!!ሶስተኛዉ አማራጭ ደግሞ አንቺ ቢች ሸርሙጣ ዕኔ አንበሳ ነኝ!!አንበሳ ደግሞ ሚስቱ ከሌላ ጋር ፍለርት ካደረገች ዕንኳን ለራሱ ትልቅ Value ስለሚሰጥ ያቺን ሴት መልሶ አያይትም ይንቃታል!!ዕናም ይቺን ሤት አይኑኣ እያየ ሌላ ሴት ይዞ ዕቤቱ መጥቶ ማሳየት ከተቻለም እዛዉ ሌላ ሴት መንጨት!!ከዛም የአለምንም ማገራገር ከዚች ከሸርሙጣ መለያየት ከግዻእኛህ ይጠበቅበታል!!አለበለዚያ ትዳሩን እናድን ብለህ እዚህ ላይ የምታለቅሰዉ ነገር አይገባኝም!!ምክኒያቱም! Cheater's no matter what they will be forever cheater's!!don't fool yourself she will be Act normal!!
ኣሸወይና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Sat Sep 12, 2009 1:31 am

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Thu Dec 06, 2012 6:22 pm

ኣሸወይና wrote:ዉድ ወንድማችን የዳንግላዉ! መቼም ምከሩኝ ስላልክ የምችለዉን አንድ ሙሉ ባሊ የህይወት ተሞክሮ ምክራ ምክሮችን ልለግስህ እፈላጋለሁኝ ለአንተ ዕና ለጓደኛህ::
በመጀምሪያ ኒግሮ ወንድማችን የቀረበች የሀበሻ ቺክ ምንም ተስፋ የላትም!
like they said""once u go to Black U never come Back""እናም ሰዉየዉ ከወጥቤት ግድግዳ ጋራ እያጋጨ ሀይለኛ ብድ በድቱኣታል!!ይህንን የጥቁር ብድ አጋንንትየተባለዉን ብድ; ዕንኳን ሁለት ስራ የሚሰራዉ ወንድማችን ሀበሻዉ ይቅርና ነጮች እንኳን ቪያግራ ቢጠቀሙ እንደዚህ ሚስቶቻቸዉን ሊበዱ እንደማይችል ስይንሳዊ ሐቅ ነዉ::ስለዚህ ጛደኛህ ዕና አንተ ሁለት አማራጭ አላችሁ:: አንደኛዉ ፍቅር ከሚስቱ ካለዉ ጥቁሩ ያስተረፈለትን ፑሲ ባለችዉ እቃ እንደምንም ነካ ነካ አድርጎ መተኛት ልጅም ከወለደች ከጥቁሩ ብራዘር እንደራሱ ልጅ ማሳደግ እናም ጥቁሩ ለዋለለት ዉለታ ሚስቱን አንዳንዴ ከጥቁሩ ጋር ለVአኬሽን የሚሆናቸዉን ዶላር መስጠት እንዲሁም ጥቁሩ ጓደኛህ ቤት ማደር ከፈለገ ጓደኛህ አልጋዉን ለቅቆ ለጥቁሩ ብራዘር ወጥ እና ወጣወጦችን እንዲሁም ፒሳ በማምጣት ሚስቱን እና ጥቁሩን ሰዉዬ ማገልገል!! ሁለተኛዉ አማራጭ ወንድ መሆን የጥቁሩን እግር በሻት ጋን መቁረጥ!!ሶስተኛዉ አማራጭ ደግሞ አንቺ ቢች ሸርሙጣ ዕኔ አንበሳ ነኝ!!አንበሳ ደግሞ ሚስቱ ከሌላ ጋር ፍለርት ካደረገች ዕንኳን ለራሱ ትልቅ Value ስለሚሰጥ ያቺን ሴት መልሶ አያይትም ይንቃታል!!ዕናም ይቺን ሤት አይኑኣ እያየ ሌላ ሴት ይዞ ዕቤቱ መጥቶ ማሳየት ከተቻለም እዛዉ ሌላ ሴት መንጨት!!ከዛም የአለምንም ማገራገር ከዚች ከሸርሙጣ መለያየት ከግዻእኛህ ይጠበቅበታል!!አለበለዚያ ትዳሩን እናድን ብለህ እዚህ ላይ የምታለቅሰዉ ነገር አይገባኝም!!ምክኒያቱም! Cheater's no matter what they will be forever cheater's!!don't fool yourself she will be Act normal!!


:lol: ፕራይስለስ!!
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Re: ገላግሉኝ : ለዳኝነት ተቸገርኩ

Postby brookk » Thu Dec 06, 2012 7:12 pm

የዳንግላው wrote:ልጂቱን ቀድሜ ባውቃትም በእሷ ተዋውቄው ባልዬው ቤስት ጓደኛዬ ከሆነ ዐመታት ተቆጠሩ:: ከመቀረራረባችን የተነሳ እንዲያውም እኔን ብለው ካለሁበት ከተማ ድረስ ሙቭ አርገው ቤት ገዝተው ልጅ አፍርተው የተደላደለ ሕይወት ተያይዘዋል:: ግን ከጥቂት ጊዜ ወዲህ በመሐላቸው ትንሽ ንትርክ እየተጀመረ ነው::

------ልጁ(ባልዬው) ለገዛበት ቤቱ ትዳሩና ሕይወቱ በጣም ኢንቨስት አርጎበታል በቀላሉ ለማፍረስም ይከብዳል አሁን የናንተን ምክር የምፈልገው ሁለቱንም በምን ዐይነት ቀርቤ ነው ትዳራቸውን ማዳን የምችለው ወይም ከሕሊና የጸዳ ፍርድ መስጠት እንድችል ምከሩኝ እባካችሁ !!!


የዳንግላው ከዚህ ጽሁፍህ እንደተረዳሁት -- "እነዚህ ጓደኞችህ" ልታድነው የምትችለው "ትዳር" የላቸውም ::
የሚያሳስበው የልጆቻቸው ጉዳይ ነው :: "ይህ ትዳር" መዳን የለበትም -- ማብቃት እንጂ ::
1- ከእንግዲህ ከሚስት ተብየዋ ጋር ጭቅጭቁ አስፈላጊ አይደለም --- በቀጥታ "ጥቁሩን" ሰውየ ቤት እንዳይመጣ ትንገረው -- ይሉኝታ እዚህ ላይ አይሰራም :
ካልቻለች -- ሲያንኳኳ በር እንዳትከፍት "ባል ተብየው" ይንገራት

2- እሷ እምቢ ካለች ልጁ እራሱ ይንገረው

3- ቢቻል ሞርጌጁን በሷ ስም አዙሩት --- እናም ለልጆቹ ሲል ብቻ ቤቷ ይምጣ -- ፊዚካሊ እራሱን መቆጣጠር ካልቻለ - በኮንዶም ከሷ ጋር ሴክስ አልፎ አልፎ ማድረጉ ባይከፋም --ኢሞሺናሊ አታችድ በፍጹም አይሁን

(ለልጆቹ ሲል አብሮ እየኖረ -- ማንም የሚጫወትበትን -- እሱስ ቢደርሰው?)

4- ሞርጌጅ አልችልም ወይም እምቢ አልከፍልም ካለች ቤቱን ይሽጡት
ይህንንም እምቢ ካለች መክፈል ያቁም -- ባንኩ ይውሰደው -- ሸጠው ትርፍ ካለው ይደርሰዋል

በተራ ቁጥር 1 ላይ የተቀመጠውን "ሚስት" ማድረግ ካልቻለች -- ጥርጣሬ ብቻ ሳይሆን ጉዳያቸው እውነትም ነውና 2, 3 ወይም 4ን ማድረግ ጭካኔ አይደለም -- ጊዜያዊ "ጉዳት" ነው
ሙቭ ኦን
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby የዳንግላው » Thu Dec 06, 2012 7:46 pm

ለተሳትፏችሁና ለሀሳባችሁ አመሰግናለሁ:: የአንዳንዶቻችሁ ኢሞሺናል ቢሆንም ይገባኛል:: ግን ጥቁር++ ሲባል ሁሉንም ጥቁሮች በስቴሪዮ ታይፕ አንድ ዐይነት ስም መለጠፍም የከብዳል::

ቺት ለማድረጓ ምንም ዐይነት የተጨበጠ ማስረጃ ባይገኝም ሚስትዬዋን ግልቲ የሚያሰኛት ነገሮች ወይም የሚያስጠረርጥሩ ነገሮች ለምሳሌ ሰውየው ሞተርሳይክል ብቻዋን ይዟት ሄዶ እንዳ ለማመዳት (ምንም ቢቀራረቡ ይህን ማድረግ በጣም የማይወጥ ቢሆንም) አስቀድማ ባልዋን ባለማስፈቀዷ ወይም ኢንፎርም አለማድረጓ ትልቅ ስህተት ነው:: :oops: ሁኔዎቹን ስጠይቃት በእሷ በኩል ያለው ታሪክ ደግሞ አሳማኝ ይመስላል:: የትም ርቀን ሳንሄድ እዚሁ በራፋችን ነው ባይኩ ላይ እንድወጣና እንዴት እንደሚነዳ በቆምኩበት ነው ያሳየኝ የትም አልሄድኩም ብላ በእንባ ነው ያስረዳችኝ:: ግን .... :?: ይህ እውነት ከሆነ ሰውዬውም ባለትዳር ሆኖ የሰው ሚስት ጎረቤት አገር እያየ ምን ማድረጉ ነው ??

ይህ ሁሉ ይሁንና በቅርብ ስለማውቃቸው ለፍርድ ከብዶኛል:: ልጆቹ በጣም ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፈው አብረው ተምረው በከፍተኛ ትምህርት እስኪመረቁ ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉበትና ልጅ አፍርተው እዚህ ደረጃ እስኪደርሱ ሳክሰሳቸውን ስለማውቅ በዛ ላይ ልጂቷ ፕሮፌሺናል ሥራዋን ያቆመችው ልጆቿን ለማሳደግ ብላ ስለሆነ በሁለቱ መካከል ሰይጣን ባይገባና ባይራበሹ ደስተኛ ነኝ:: እኔ እስከማውቃት ፈርሐ እግዚአብሄር ሜክአፕና ጌጣጌጥ እንኳን የማታደርግ ዝቅ ብላ የምትኖር ትሑት ጴንጤም ነች:: ባሏ ጴንጤ ስላልሆነ ቤተሰቦቿ እየተቃወሙ እንኳን አፍቅራው ያገባችው እሷው ነች:: በእሱ ምክንያት ከፋሚሊዋ ተራርቀዋል:: አይ ናው ጴንጤኔቷ ቺት ከማድረግ ያግዳታል ማለቴ ሳይሆን መልካም የትዳር ሴት ኢንተለጀንት ስለምትመስለኝ ነው::

ውይይቱን እዚህ ያመጣሁት በቤታቸው ያለ የሻከረ ኮሙኒኬሺን በእውነት በሁለቱም በኩል ያለውን ለመፍታት ከአእምሮዬ በላይ ስለሆነ ነው: የሁለቱም ስልክ ጥሪ አሰቃየኝ:: ለትንሹ ለትልቁም ሲጠሩኝ ካለሁበት ከተማ እነሱ ወዳሉበት አንድ 1 ሰዐት ከ20 ደቂቃ በእኩለ ለሊት እንኳን የነዳሁበት ቀን አለ:: እንደ ጓደኝነቴ ይህን መስዋዕትነት መክፈል ባይከፋኝም የሁላችንም ሕይወት ተመሰቃቀለ::

እባካችሁ ይህን ትዳር ለማዳን መላ መፈለጉ ላይ ብናተኩር ምን ይመስላችኋል ?? ልጂቱ እንደምትውደው ግንም ምንም ጥርጥሬ የለኝም ልቧ እስኪጠፋ ነው የምታፈቅረው:: እሱም እንደዚሁ ... ሁለቱም ይመጣጠናሉ በእድሜያቸውም ይቀራረባሉ::
Last edited by የዳንግላው on Thu Dec 06, 2012 8:09 pm, edited 1 time in total.
የዳንግላው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 69
Joined: Sat Dec 18, 2004 9:11 am
Location: Blackburn - Uk

Postby የቦግዪ » Thu Dec 06, 2012 8:06 pm

የዳንግላው wrote:እባካችሁ ይህን ትዳር ለማፍረስ መላ መፈለጉ ላይ ብናተኩር ምን ይመስላችኋል ??


I presume it's typo.
Gotta live my life like there's one more move to make.
የቦግዪ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Sun Oct 28, 2012 6:56 pm

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests