ገላግሉኝ : ለዳኝነት ተቸገርኩ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ሓየት11 » Thu Dec 06, 2012 8:12 pm

ወንድም በቁምነገር ነው የምታወራው :?:

እንደው የምር ግን ካንተ መፍትሄ ፈልገው ይሆን "ያስቸገሩህ"? ... አንተ ኮ ትዳሩን እያዳንክ ሳይሆን እያፈረስክ እኮ ነው ያለኸው አሁን? ... ከአቅምህ በላይ ሆኖብህ ከሆነም ... በቅርብ የምታውቃቸውን ሰዎች ባማከርክ:: ... ከሰው ተነጥለህ የምትኖር ከሆነም ... በስልክ በኢሜል በምናምን የምታውቃቸው ሰዎች ጋር መምከር ነበር ... የአዋቂዎች ስራ ... አደባባይ ላይ አውጥተህ ... የሰዎችን ገመና ከምትዘበዝብ ... :: ... በራስህ እፈር:: ...ምክንያቱም የምትሰራውን የማታውቅ ... ደነዝ ነህና:: ... ስማቸውን ባትጠቅስ ... የምትጽፈውን አያነቡም? ... ሊያነቡት አይችሉም? ... ሴትዮዋ ንጹህ ሆና ቢሆን ... ካሜራ ምናምን ማደረጋችሁን እዚህ አንብባ ብታውቅ ምን የሚፈጠር ይመስልሃል? ... ከብት ነህ:: ... እንደምትጠረጥሩት ሆኖ ቢሆንም ... ይህን ስታነብ ... ተሸናፊነትን አትቀበለም:: ... በሁለቱም በኩል ... ትዳሩን አዳንኩ ብለህ ... አፈር ድሜ አስጋጥከው ማለት ነው:: ... ድጋሚ በራስህ እፈር ... ድንጋይ ነህ::

ለነገሩ ባልዬውም ያንተ ቢጤ ጀዝባ ቢሆን ነው ... ሚስቱን ፊትለፊት እንደማናገር ... ካንተ ጋር ሆኖ ... ለመቅረጽ የወሰነው:: ... እየተናፉ ... ስታቃስት ብትሰሟትስ ምን ለመፍጠር ነው? ... እንደዚህ አይነት ተልካሻ ስራ የሚሰራ ሰው... ትዳሩን የማይፈልግ ... ሰው ነው:: ... አለ አይደል ... ሰበብ ሲፈልግ ቆይቶ ... አሁን አገኘሁሽ የሚል አይነት ሰው ... ቅቅቅ... ከዛ የጥቅም የምናምን ቅርምት ሲነሳ ... ያቺን ጠባሳ እያነሳ ... ጌም የሚጫወት ... ጭባ የዳንግላ ሰው መሆን አለበት ይላል ... ሊቁ ሓየት::
የዳንግላው wrote:ሁላችሁንም ለተሳትፏችሁና ለሀሳባችሁ አመሰግናለሁ:: የአንዳንዶቻችሁ ኢሞሺናል ቢሆንም ይገባኛል:: ጥቁር++ ሲባል በስቴሪዮ ታይፕ አንድ ዐይነት ስም መለጠፍም የከብዳል::

ለመማገጧ ምንም ዐይነት የተጨበጠ ማስረጃ ባይገኝም ሚስትዬዋን ግልቲ የሚያሰኛት ነገሮች ወይም የሚያስጠረርጥሩ ነገሮች ደርሼበታለሁ:: ለምሳሌ ሰውየው ሞተርሳይክል ብቻዋን ይዟት ሄዶ እንዳለማመዳት ምንም ቢቀራረቡ ይህን ማድረግ በጣም የማይወጥ ቢሆንም አስቀድማ ባልዋን ባለማስፈቀዷ ወይም ኢንፎርም አለማድረጓ ትልቅ ችግር ነው:: :oops: እሷን ቀርቤ ሁኔዎቹን ስጠይቃት በእሷ በኩል ያለው ታሪክ ደግሞ አሳማኝ ይመስላል:: እኔን እመኑኝ ባይ ነገር ነች:: ግን .... :?:

ይህ ሁሉ ይሁንና በቅርብ ለሚያውቃቸው በተለይ እንደ እኔ ላለ ሰው ለፍርድ በጣም ይከብዳል:: ልጆቹ በጣም ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፈው አብረው ተምረው በከፍተኛ ትምህርት እስኪመረቁ ብዙ መስዋዕትነት የከፈሉበትና ልጅ አፍርተው እዚህ ደረጃ እስኪደርሱ ሳክሰሳቸውን ስለማውቅ በዛ ላይ ልጂቷ ፕሮፌሺናል ሥራዋን ያቆመችው ልጆቿን ለማሳደግ ብላ ስለሆነ በሁለቱ መካከል ሰይጣን ባይገባና ባይራበሹ ደስተኛ ነኝ:: ውይይቱን እዚህ ያመጣሁት በቤታቸው ያለ የሻከረ ኮሙኒኬሺን በእውነት በሁለቱም በኩል ያለውን ለመፍታት ከአእምሮዬ በላይ ስለሆነ ነው: የሁለቱም ስልክ ጥሪ አሰቃየኝ:: ለትንሹ ለትልቁም ሲተሩኝ ካለሁበት ከተማ እነሱ ወዳሉበት አንድ 1 ሰዐት ከ20 ደቂቃ በእኩለ ለሊት እንኳን የነዳሁበት ቀን አለ:: እንደ ጓደኝነቴ ይህን መስዋዕትነት መክፈል ባይከፋኝም የሁላችንም ሕይወት ተመሰቃቀለ::

እባካችሁ ይህን ትዳር ለማፍረስ መላ መፈለጉ ላይ ብናተኩር ምን ይመስላችኋል ?? ልጂቱ እንደምትውደው ግንም ምንም ጥርጥሬ የለኝም ልቧ እስኪጠፋ ነው የምታፈቅረው:: እሱም እንደዚሁ ... ሁለቱም ይመጣጠናሉ በእድሜያቸውም ይቀራረባሉ::
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby የዳንግላው » Thu Dec 06, 2012 8:20 pm

ሐየት > አያት ምናምን ተብዬው ስድብህን ተቀብያለሁ :: ሌላም ካለ እየተመላለስክ ስደበኝ:: ግን አርእስቱን አታዛባ ብትችል እዚያው ፖለቲካ ቤት ውሰድና ይውጣልህ :P ፖለቲከኛ ስለሆንክ በደምህ ውስጥ ሁሉ ያለ ያ ስድብ የማያልቅበት ከንቱ የነገር ስቶሬጅ ስላለህ ልትኮራ ይገባሀል:: ላንተ መልስ እየሰጠሁ ጊዜዬን አላቃጥልም በተረፈ ሌላ አትንገረኝ ይበቃሀል:: :idea: ባጭሩ ግን ሰዎቹ ዋርካን አያውቁም ይህን ደግሞ ስለማውቅ ነው የማደርገውንም ስለማውቅ አትጨነቅ:: እሺ?
የዳንግላው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 69
Joined: Sat Dec 18, 2004 9:11 am
Location: Blackburn - Uk

Postby ገላጋይ-1 » Thu Dec 06, 2012 8:28 pm

የዳንግላው

... ሴትዮዋ ከጥቁሩ ጋር እንደጀመረች ምንም ጥርጥር የለውም ... ብዙ ታሪኮችን አይተናል እዚህ አገር.... ደግሞም ለባልዋ አላደረግኩም ብላ ትክዳለች እንጅ ከሌላ ወንድ ጋር ተኛሁ ብላ አትነግረውም ...

... ባልየው ግን የማይረባ ነው .... ለምን ለጥቁሩ ቤቱ እንዳይመጣ አይነግረውም? ምን አስፈራው? ለምን ሚስቱንስ አያስጠነቅቃትም? ...

ሚስትየዋ ባልዋን በሆነ ነገር የናቀችው ይመስለኛል .......
ገላጋይ-1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Fri Aug 25, 2006 5:43 pm

Postby brookk » Thu Dec 06, 2012 8:29 pm

"የሁለቱም ስልክ ጥሪ አሰቃየኝ" ??????

የችግራቸው አንዱ መንስሄ የ"ጥቁሩ" ቤታቸው መገኘት ነው አይደል ?

ሰውየውን አትምጣ ማለቱ ምነው ከባድ ሆነባት ?
ባልተብዬውስ አትምጣ ቢለው ችግሩ ምንድነው ?

በትንሹ ይቺን ያድርጉ እስቲ --- "አፌር" ካለ ግን ይህም መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል አላጣሁትም ::

ይህ ትዳር አይጠገንም --- የልጆቻቸውን ስቃይ ግን መቀነስ ይቻላል --- ተስማምተው ቢለያዩ ::
brookk
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 322
Joined: Tue Nov 11, 2003 3:46 pm
Location: ethiopia

Postby ሓየት11 » Thu Dec 06, 2012 10:30 pm

... እረ እኔ አልሰደብኩህም ወገኔ ... እንቅጭ እንቅጯን ነው የነገርኩህ ... የምትሰራውን የማታውቅ ደነዝ ነህ:: አራት ነጥብ::

... ዋርካን እንደማያውቁም ታውቃለህ ... ቅቅቅ ... ቆይ ሌላስ ምን የምታውቀው አለ? ... :lol: :lol:

እውነቴን ነው የምልህ ... አሁን ባይገባህ ቀስ ብሎ ይገብሃል ... የሰው ትዳር እያፈረስክ ነው:: ... አፍህን ዝጋና አርፈህ ተቀመጥ:: ... እስካሁን የተሰጠህን አስተያየት አይተህም ይህን መገንዘብ ትችል ነበር ... ግን ሰውዬው ድንጋይ ነሃ ... ቅቅቅ ... ኦልሞስት ተሳታፊው ሁሉ "ትዳርዬው" እንዲፈርስ አስተያየቱን የሰጠህ መሰለኝ ... እንኳን ልታቃና ... አንተም ዞሮብህ ... "ይህን ትዳር ለማፍረስ መላ መፈለጉ ላይ ብናተኩር ምን ይመስላችኋል" ስትል ጽፍሃል ... ቅቅቅ ... ፍልጥ መሃይም ... :lol: :lol: :lol:የዳንግላው wrote:ሐየት > አያት ምናምን ተብዬው ስድብህን ተቀብያለሁ :: ሌላም ካለ እየተመላለስክ ስደበኝ:: ግን አርእስቱን አታዛባ ብትችል እዚያው ፖለቲካ ቤት ውሰድና ይውጣልህ :P ፖለቲከኛ ስለሆንክ በደምህ ውስጥ ሁሉ ያለ ያ ስድብ የማያልቅበት ከንቱ የነገር ስቶሬጅ ስላለህ ልትኮራ ይገባሀል:: ላንተ መልስ እየሰጠሁ ጊዜዬን አላቃጥልም በተረፈ ሌላ አትንገረኝ ይበቃሀል:: :idea: ባጭሩ ግን ሰዎቹ ዋርካን አያውቁም ይህን ደግሞ ስለማውቅ ነው የማደርገውንም ስለማውቅ አትጨነቅ:: እሺ?
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ሀሪከን2 » Fri Dec 07, 2012 1:54 am

የዳንግላው
እባካችሁ ይህን ትዳር ለማዳን መላ መፈለጉ ላይ ብናተኩር ምን ይመስላችኋል ??

ወዳጄ አንተም ባልየውም የምትገርሙ ሰወች የድምጽ መቅረጫ ከመግዛት እሱን ኢንስቶል ከማድረግ ከዛም ሚስትየዋን ከመሰለል እንዴት አጭሩ መፍትሄ ተሰወረባችሁ እቤታችን እንድትመጣ አልፈልግም ማለት እንዴት ጔደኛህ ተሳናው አንተስ ይህን ብሎ መምከር እንዴት ተሳነህ ??? :roll:

ሀያትን ተወው እሱ በረሀ እያለ የሰፈረበት የስድብ ሰይጣን ነው እንዲህ በየደረሰበት የሚያሳድበው :roll:

ጌታ ዝትብሀል ሽማግሌ ከሜልሀ ብየሀለው በገዥወቻችን ቌንቌ :lol: :lol:
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby የዳንግላው » Fri Dec 07, 2012 8:48 am

እባካችሁ ይህን ትዳር ለማፍረስ ተብሎ የተጻፈው የታይፕ ስሕተት ስለሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ:: ትዳርን ለማፍረስ ከተፈለገ ምንም እርዳታና ጥያቄ አያስፈልገውም እንዲህም አይባልምም ደግሞ ኮመን ሰንስ ነው:: በዚህ ጊዜ አናቃጥል:: ከላይ ስሕተቱን አርሜ እንደገና ፖስት አርጌዋለሁ:: ፕሊስ :!: :!:

ይሁንና ከልብ ለመርዳት ላሰባችሁት ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ:: እንዴት ሴትዬዋ ወይም ባልዬው ሰውዬው ወደ ቤታቸው እንዳይመጣ አይነግሩትም ለተባለው :- መልስ ልስጥ

ባልዬው በድብቅ የተቀረጸው ድምጽ የሰውዬውን መሥመር የለቀቅ አነጋገር እስኪሰማ ድረስ ከሰውዬው ጋር በጥሩ ጉርብትና የተመሰረተ ወዳጅነት ነበራቸው:: ባከባቢው ጥቁሮች እነሱ ብቻ ስለሆኑም በቆዳ ቀለምነት ጓደኝነት የፈለገ መስሎታልም::

ግን ብዙዎቻችሁ እንዳላችሁት ባልዬው ቸኩሎ ከሰውዬው ጋር አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ ገብቶ ጠላትነት ከሚያተርፍ ሚስቱ ስላስደፈረችው ያለውን ነገር ሁሉ ሊቆርጥ በጣም የመረረ ውሳኔ ላይ መድረስ ስለፈለገ እኔ ግን ስለ ልጆቻቸው ስለትዳራቸው በማሰብ ያንድ ሰሞን የሰይጣን ሥራ የዘላለም ጸጸት እንዳይሆን እያልኩ እንጂ እሱ ግን የቆረጠለት ይመስላል:
የዳንግላው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 69
Joined: Sat Dec 18, 2004 9:11 am
Location: Blackburn - Uk

Postby ዎቻኖ » Fri Dec 07, 2012 9:26 am

የዳንግላው :- እንደ ጓደኝነትህ የሰዎቹን ትዳር ለማዳን ያሳየሄው ጥረትና ጭንቀትህ ቢደነቅልህም ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው ይባላልና ባልየው ራሱ እንደቆረጠለት አንተው ተናግረሀል እነሱው ብዙ ያሳለፉ ብዙ ተፋቅረው እዚህ ደረጃ ደርስዋል ብለሀል ነገር ግን በትዳር ሂደት አንዱ ወገን ቃለ አባይ መሆን ሌላኛው ደግሞ ታማኝ መሆን ያለና የሚኖር ነው:: ዌል ይህ ክስተት በጓደኞችህ ቢደርስ የዐለም መጨረሻ አይሆንም:: ጴንጤና ትሑት በመሆንዋና ሀጢአት አትሰራም ማለትም አይቻልም:: ቺቲንግ ብዙ ጊዜ በ2 መንገዶች ወደ ትዳር ይገባል 1ኛው ጤናማ ወዳልሆነው ትዳር በቀላሉ ሲገባ 2ኛው ግን ከመላመድ የሚመታ ነው የግዋደኞችህ ታሪክ ዐይነት መሆኑ ነው:: ወዳጄ:- ዋናው ነገር ግን ምርጫውን አሁንም ለሁለቱ ሰዎች ብትተው ይሻላል:: ያንተ ድርሻ መሆን ያለበት ኃላፊነት ያለበት ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ መዳቱ ላይ ነው:: አስተውስ ሰዎቹን ብታስታርቅ እንኳን ያ ጎረቤታቸው ካባለቤትዬው ጋር ያለውን ግኑኝነት በግልጽ ቢቀጥልና ከዚህም የከፋ ደረጃ ቢደርስ ምን ይውጣሀል ??? ያገር ልጅ ምክሬን አትናቃት >
ዎቻኖ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 29
Joined: Mon Dec 06, 2004 3:41 am
Location: kenya

(-:

Postby ደጉ » Fri Dec 07, 2012 1:56 pm

brookk wrote:...የችግራቸው አንዱ መንስሄ የ"ጥቁሩ" ቤታቸው መገኘት ነው አይደል ?

ሰውየውን አትምጣ ማለቱ ምነው ከባድ ሆነባት ?
ባልተብዬውስ አትምጣ ቢለው ችግሩ ምንድነው ?

በትንሹ ይቺን ያድርጉ እስቲ --- "

...ብሩክ ወንድማችን ነጥቡ ያለው እዚህ ላይ ነው..ለዛም ነው ያን ሁሉ ትያትር መስራታቸው ያልታየኝ...በቀላሉ ባልየው ማለት ለሚስቱም ለሰውየውም የአይኑ ቀለም አላማረኝም ቤቴ በማንኛውም ጊዜ እንዲመጣ አልፈልግም ማለት መብቱ....እሱዋም ትዳርዋን ካለች ያን አክብራ መቀበል አለባት ....ብትፈልግ እሱዋ እሱ ቤት ትሂድ ...የዛን ግዜ ግልጽ ይሆናል ...እቤት ሲመጣ እሚናገረውን መስማት እሚያደርገውን መከታተል ግን እራሳቸው ወደ ልጅትዋ ለፈተና የላኩት አስመሰሉት...አይታይህም ይሄ ሁሉ የ ፕራይቬት ዲክቴክቲቭ ስራ ... :D
...የችግራቸው ቁልፉ ያለው እየመጣ ያስቸግረው ሰው ሲሆን እሱን ትተው በራሳቸው ኦርቢት መሽከርከራቸው የት እንድሚያደርሳቸው ባየን ብቻ.. :D
...ወይ ሰውየው ትልቅነቱ ምናልባት 2 ገበሬ ከ 1 እረኛ ይወጣው ይሆናል ማን ያውቃል ....እሱን ፈርቶ ከሆነ በጽሁፍ በሩ ላይ ማሳወቅ ነው...;)
...እህምም ቀደምኩሽ አይደል ... :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4426
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ለማ12 » Fri Dec 07, 2012 2:21 pm

...ወይ ሰውየው ትልቅነቱ ምናልባት 2 ገበሬ ከ 1 እረኛ ይወጣው ይሆናል ማን ያውቃል ....እሱን ፈርቶ ከሆነ በጽሁፍ በሩ ላይ ማሳወቅ ነው ...


እግዜር ይይላችሁ:


:roll: :roll: :roll: :roll: :roll: :roll: :roll:
አሁን ይህ ምክር ነው ??
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1128
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ክቡራን » Fri Dec 07, 2012 2:29 pm

የዳንግላው :- "" ቡዙ ምክር ሲበዛ ያሰክራል " ይላሉ አባቶች ሲተርቱ:: ከላይ እስከ ታች የተጻፈውን ሳነብ ከጥቂቱ በስተቀር ባብዛኛ ው ጠቃሚ ምክሮችን አግኝተሀል...እረ እንደውም ይሄን ጉዳይ በተመለከተ ከበቂ በላይ አግኝተሀል ማለት ይቻላል.. :D እኔ ምክር ሳይሆን ጥያቄ ብጤ ነው ያለኝ.."" ልብህ ከጔደኛህና ከሚስቱ ወደ ማናቸው ያደላል..? ከቻልክ መልስልኝ ካልቻልክ ተወው...
ሰላም ያውላቹ ሁላችሁንም :: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8111
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሓየት11 » Fri Dec 07, 2012 6:18 pm

የዳንግላው wrote:ይሁንና ከልብ ለመርዳት ላሰባችሁት ሁሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ::

አይይይ የነፈዝ ሰው ነገር ... እስኪ ማነው ከልቡ ለመርዳት አስተያየቱን የሰጠኽ? ... እንዴ መፍረስ አለበት እኮ እያሉህ ነህ ... አይገባህም እንዴ ድንጋዮ?! ... ዩ ሲ ካንተም አልፎ ... በሰው ትዳር ላይ የመፍረስና የመቀጠል ውሳኔ የሚሰጠው ... የዋርካ ከብት ሆነ ... ቅቅቅ ... እረ እናንተንስ ... ዘላለም አደድቦ ባኖረልኝ ... ቅቅቅ

ግን ብዙዎቻችሁ እንዳላችሁት ባልዬው ቸኩሎ ከሰውዬው ጋር አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ ገብቶ ጠላትነት ከሚያተርፍ ሚስቱ ስላስደፈረችው ያለውን ነገር ሁሉ ሊቆርጥ በጣም የመረረ ውሳኔ ላይ መድረስ ስለፈለገ እኔ ግን ስለ ልጆቻቸው ስለትዳራቸው በማሰብ ያንድ ሰሞን የሰይጣን ሥራ የዘላለም ጸጸት እንዳይሆን እያልኩ እንጂ እሱ ግን የቆረጠለት ይመስላል:


ያንተ ቢጤ ጅላንፎ ነው ብዬህ ነበር ... በራሱ የማይተማመን ድኩማን:: ... በዛ ላይም ሰበብ ፈላጊ ... ደነዝ ነው ብዬህም ነበር:: ... ሊቅነታችን መሬት እንደማትልስ ስላረጋገጥክልኝ ... እግዜር ተመስገን:: ... ይታይህ እንግዲህ ... አንድ ጤነኛ ... ትዳሩን አክባሪ ሰው ... ከአንድ አራሙቻ ... ጠረንገሎ ባርያ ጋር ... ጸብ ከሚያተርፍ ... ሚስቱንና ትዳሩን ቢበትን ይመርጣል ... ቅቅቅ ... እኔ ምለው ... ባርያ ተብዬው ... ባልዬውንም ነው ንዴ ... በቁሙ የሚከካለት ... ቅቅቅ ... አሃ እንደዛ ቢሆን እኮ ነው ... እሱን ከሚያጣ ... ሚስቱን ቢያጣ መምረጡ ... ቅቅቅ

ሓዩ ነን

የደደቦች አኗኗሪ
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ባርናባስ_23 » Fri Dec 07, 2012 6:34 pm

መላ ያለው አይመስለኝም
It always seems impossible until its done
ባርናባስ_23
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 305
Joined: Sun May 31, 2009 2:00 pm

Postby የዳንግላው » Sat Dec 08, 2012 5:05 am

ሀሪከን2 wrote:የዳንግላው
እባካችሁ ይህን ትዳር ለማዳን መላ መፈለጉ ላይ ብናተኩር ምን ይመስላችኋል ??

ወዳጄ አንተም ባልየውም የምትገርሙ ሰወች የድምጽ መቅረጫ ከመግዛት እሱን ኢንስቶል ከማድረግ ከዛም ሚስትየዋን ከመሰለል እንዴት አጭሩ መፍትሄ ተሰወረባችሁ እቤታችን እንድትመጣ አልፈልግም ማለት እንዴት ጔደኛህ ተሳናው አንተስ ይህን ብሎ መምከር እንዴት ተሳነህ ??? :roll:

ሀያትን ተወው እሱ በረሀ እያለ የሰፈረበት የስድብ ሰይጣን ነው እንዲህ በየደረሰበት የሚያሳድበው :roll:

ጌታ ዝትብሀል ሽማግሌ ከሜልሀ ብየሀለው በገዥወቻችን ቌንቌ :lol: :lol:


ሀሪከን በጨዋነትህ አመሰግንሀለሁ:: ይሄውልህ ሰውየውን ብድግ ብሎ አትምጣብኝ ለማለት ልጁ አልተቸገረም:: እኔም አጥቼው አይደለም:: ባልዬው ልጂቱን ነው ብሌም የሚያደርገው አስደፈረችኝ ይላል:: አሁን ግን የብዙዎቻችሁ ሀሳብ እንደዛው ስለሆነ እኔም ደፍሮ እንዲነግረው እመክረዋለሁ:: ጥዋት ጓደኛዬ መኪናውን ከጋራዥ ሲያወጣ አጂሬውም ዎርካውት የሚያደርግ ይመስል ብቅ ይልና ዋሳፕ ይለዋል:: ኮቴውን ተከትሎ ወደ ቤቱ ጥልቅ ይበል እግዜር ይወቀው:: በዛ ላይ ኮ የአሜሪካኖች ፉትቦል ኮች ነው:: ደጉ አልተሳሳተ እረ ዱዱ ሁለት ገበሬዎች ብቻ ሳይሆን የሚያክለው ሁለት ገበሬዎች ከነ ቤተሰቡ ያክላል:: ቁመቱ 6 ፉት ምናምን የእጁ ትልቅነትና የደረቱ ስፋት ከፊቱ ግብዴነት ጋር ቡልዶዘር ይመስላል:: እውነቱን ብነግራችሁ ይህም ራሱ ትልቅ ስጋት ነው:: :(
የዳንግላው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 69
Joined: Sat Dec 18, 2004 9:11 am
Location: Blackburn - Uk

Postby ጩጉዳ » Sat Dec 08, 2012 5:17 am

የዳንግላው wrote:. . . . በዛ ላይ ኮ የአሜሪካኖች ፉትቦል ኮች ነው:: ደጉ አልተሳሳተ እረ ዱዱ ሁለት ገበሬዎች ብቻ ሳይሆን የሚያክለው ሁለት ገበሬዎች ከነ ቤተሰቡ ያክላል:: ቁመቱ 6 ፉት ምናምን የእጁ ትልቅነትና የደረቱ ስፋት ከፊቱ ግብዴነት ጋር ቡልዶዘር ይመስላል:: እውነቱን ብነግራችሁ ይህም ራሱ ትልቅ ስጋት ነው:: :(


በለው :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
ከርቀት ሆናችሁ አለቅን አልተረፍንም ብላችሁ 911 ደውላችሁ ቀውጢ አርጉት:: :lol: :lol: :lol:
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests