ገላግሉኝ : ለዳኝነት ተቸገርኩ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby TAዛBI » Wed Dec 12, 2012 2:42 pm

ሰላም ዳግማዊ
እኔ እኮ የፃፍኩት ዳንግላው የሰውየውን "አደገኝነት " ለመግለፅ "ጥቁር አሜሪካዊነቱና ግዙፍነቱን " ስለጠቀሰ ; ይህንን የተሳሳተ አመለካከት ለማሳየት እንጂ 'ነጭ " ሰው ወይም ዴሊቨሪ ቦይ ይግባ አላልኩም

ነገር ግን ጥቁር ስለሆነ ነው የተጠረጠረው ይሔኔ ነጭ ቢሆን አይጠረጠረም ብለሀል ይህንን ነው ተሳስተሀል ያልኩት ሰውየው የተጠረጠረው በቆዳው ቀለም ወይንም በግዝፈቱ አይደለም ያ የተጠቀሰው ለተጨማሪ ገለጻ እንጂ የጠርጣሬው መንስኤ የሰውየው አባወራ በለለበት ጉብኝት ማዘውተሩ ነው
ምንም ሲቲዌሽን በሌለበት ሁኔታ ጎረበታቸውን ቢጠረጥሩ ያንተ አባባል ምናልባት ያስኬድ ነበረ ሰውየው ግን የዛን የዋህ ኮቴ እየጠበቀ እንዴት አደርሽ አብዝትዋል ጓዳ ድረስ እየገባ

ይህ የራስህ አስተሳሰብ ችግር ነው .....አንተ የጓደኛህን /የጎረቤትህን ባለቤት ሞተርሳይክል ብታስተምር ምንድን ነው ችግሩ ባየኸው ; በሰማኸው ነገር ሁሉ click የሚያደርግብህ ከሆነ ሁሉም ሰው እንዳንተ ነው ማለት አይደለም ደግሞ click ለማድረግ የግድ ሞተርሳይክል ላይ መፈናጠጥ የለብህም .....መፅሀፉ እንደሚል "አይቶ የተመኘም ነው " በተጨማሪም ዳንግላው እንዳለው ከሆነ ክሱ "ሞተርሳይክል እንዳለማመዳት አስቀድማ ለምን አላሳወቀችም ነው " በድንገት በር ላይ ተገናኝተው "መንዳት ትፈልጊያለሽ " ቢላት "ቆይ ለባሌ ደውዬ ልንገረው " እንድትል ፈልጎ ነበር በአጋጣሚ ሞተርባይክ የመንዳት አጋጣሚ አገኘች ; መንዳት ፈለገች ; ነዳች ; ለባሏ ዛሬ ሞተር ባይክ ነዳሁኝ " ብላ ነገረች ...ምን አጠፋች

አንዲት ሴት ሞተር ሳይክል ላይ ካፈናጠጠችህ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ንክኪ ከህዋላ ስልምትነካት unless there is something wrong with your libido የሆነ ሀሳብ በጭንቅላትህ ላይ መምጣቱ አይቀሬ ነው ወንድ ደግሞ ስሜቱ ስስ ነው ታጥቦ የተሰጣ ቢኪኒ ካየ እንኳን በኢማጅኔሽን ብቻ ክሊክ ሊያደርግበት ይችላል :) ስለዚህ የወንዱ ምንም ጥያቄ የለውም ሆኖም ከላይ ያወራሁት ስለሴቷ ነው በሞተር ማለማመድ ሰበብ በያጋጣሚው ሆድዋ ከታሸና ከኋላ ከጎረበጣት ሰው ነችና እስዋ ላይም ክሊክ ማድረጉ አይቀርም now she may not act up on that feeling ነገር ግን እንደ introduction ነገር ይሆናል ውሎ አድሮ መሽራተትና መውደቅ አይቀርም

ስለዚህ ነው she should stay away of the mire ብለን የምንመክረው :!:
TAዛBI
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 145
Joined: Mon Dec 22, 2008 8:42 am

Postby የዳንግላው » Thu Dec 13, 2012 8:35 am

ሰላም ላንተ ይሁን ያገር ልጅ ዳግማዊ ዋለለኝ ለጠየከኝ ጥያቄዎች መልስ ልስጥህ:-

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:. . . .....አንተ የጓደኛህን/የጎረቤትህን ባለቤት ሞተርሳይክል ብታስተምር ምንድን ነው ችግሩ :?: ባየኸው; በሰማኸው ነገር ሁሉ click የሚያደርግብህ ከሆነ ሁሉም ሰው እንዳንተ ነው ማለት አይደለም :D [quote/]

አይይ ወንድም ዐለም ማንም ስትሬንጀር ወንድ የማንንም ሚስት ሞተርሳይክል እንዲያስተምር እርግጠኛ ነኝ አንተም አትፈቅድም:: ሰውዬው ወንድምህ ወይም ዘመድ ካሊያም በጣም የምታምነው ጓደኝህ ካልሆነ በቀር ሞተር ሳይክል ማላመድ ፊዚካሊ የሚያነካካ ሴክሿል ስሜት ሊጭር የሚችል ንክኪ ያለው ነገር ነው መተሻሸት መነካካት አይቀርምና::

በተጨማሪም ዳንግላው እንዳለው ከሆነ ክሱ "ሞተርሳይክል እንዳለማመዳት አስቀድማ ለምን አላሳወቀችም ነው" :lol: [quote/]

ወዳጄ ያልኩትን በራስህ ተርጉመህ ፈን ለመፍጠር ከመሞከር አባባሌን በደንብ ተረዳው ፕሊስ :: ሞተር ሳይክል መለማመድ ስፖንታኒየስሊ የመጣ አይመስለኝም አቅደውና ቦታ አመቻችተው ሕእልመት ይዘው ተዘጋጅተውበት በቀጠሮ ነው ሰፈራቸውን ስለማውቅ በቤታቸው በራፍ እንደ ብስክሌት እየተፈናጠጡ የሚለማመዱበት አይደለም:: :idea:

. . . በአጋጣሚ ሞተርባይክ የመንዳት አጋጣሚ አገኘች; መንዳት ፈለገች; ነዳች; ለባሏ ዛሬ ሞተር ባይክ ነዳሁኝ" ብላ ነገረች...ምን አጠፋች :?:

ማን አስተማራት ? እንዴት ? ከማን ጋር ? ስትማር ሌላ አብሯት የቤት ሰው ነበር ወይ የሚሉ ጥያቄዎች መከተል የግድ ይሆናሉ:: ቲ ኤጅ ወጣት ወይም ያላገባች ኮረዳ አይደለች: ያገባች ባለትዳር የልጆች እናት ሆና ሆና ለምን ትንዘላዘላለች ? ?

ሠላም የዳንግላው. . . . ምንም ሳይፈጠር ባል ተብዬው ጓደኛህ በቅናት ጭቅጭቅ መጀመሩን :lol:

1. ምስኪኗ ሚስት ምንም በማታውቀውና ባላሰበችው ጉዳይ የዞረበት ባል ተብዬ ጭቅጭቅ ጀመረ :lol: እስካሁን ከጻፍካቸው ውስጥ የሚስትየዋን አንድም ጥፋት አልቻልኩም......በአንተ ምክር ተደብቃችሁ "ሲያወሩ ቀዳናቸው" ብለኽም እንኳን እሷ ምንም አልተገኘባትም.....የፈረደባት ምስኪን...

ወንድም ዐለም: እኔም እንዳንተው የጎላ ጥፋትዋ ስላልታየኝ ባልዬው ግን በጣም ሲርየስሊ የተቸገረበት ስለሆነ በሁለቱም መሐል ስሆን በጣም ውስብስብ ችግር ስለሆነብኝ ነው ወደ ውይይት ያመጣሁቲ !

2. አይደለም የሚስትየዋ; የጎረቤትዬው ጥፋትም ሊገባኝ አልቻለም

ባይሆን የጎረቤትዬው ጥፋት ግልጽ ነው:: ሰውዬው በጣም ገፋ ገፋ ያደርግዋል:: አስተያየቱ አነጋገሩ ሁሉ ድፍረትና ሌላ ወንድ እንደ መናቅ ያድረገዋል:: ኦ ኦ ! ስላየሁት ነው:: እኔ የቤተሰብ ጓደኛ መሆኔን እያወቀ ከእኔ ፊት አግባብ ያልሆነ ቋንቋ እየተጠቀመ ስነጋገር መስማቴ አብግኖኛል:: ለምሳሌ በጨዋታ መሐል . . . እሷም ስዊት ስለሆነች የምትሰራው ምግብም የሚጣፍጥ መሆን አለበት :: ሲላት ስዊት መሆኗን ለእኔ ለዛውም ከሷ ፊት ሲነገረኝ ወሬ የሚያበዛ ቱልቱላ ጥቁር ብቻ ብዬ አልፌ ነበር አሁን አሁን ግን ዐይኔ ገለጥ ሳደርግ ስለምንድ ነው የሚያወራው የሚል ጥያቄ ክሊክ አርጎብኛል:: እንዲህ ዐይነት ጎረቤት አክሺን ሳይኖር አፍ ብቻ ቢሆንም የሚያጋጭ ለትዳር ጠንቅ እንደሆነ አእረግጬ ልንገርክ::

ሀ. የጓደኞችህና የእሱ ልጆች እንዲጫወቱ እያለ ጎረቤቶቹ ጋር ይሄዳል.....በዛ ላይ እንደነገርከን ከሆነ ጥቁር በብዛት የሌለበት ሰፈር ስለሆነ ጥቁር እንደመሆኑና እነሱም ጥቁር ስለሆኑ ደስ ብሎት ሊሆን ይችላል

ሰውዬው ልጁን ከፊት ከፊት እያስቀደመ ሕጻኑ በራሱ ጓደኞቹን ፈልጎ የመጣ እያስመሰለ መምጣቱ ባለቤት በለለበት መግቢያ ታክቲክ ነው:: እኔም እንድዛው አንተ እንደምታስብ አስብ ነበር ..... ሰውዬው ግን የዐይኑ ቀለም ድፍርስ ነው:: አድፍጦ ባል ቴቤት በለለበት ሹክክ እያለ እየገባ አድቫንቴጅ ለመውሰድ የሚፈልግ ነገር እንደሆነ ግልጽ ነው::

ለ. በምናልባት ደግሞ ሰውየው ሰው ቤት እግር ማብዛትና ማውራት የሚወድም ሊሆን ይችላል......በመኖሪያ ኮምፓውንድ; በስራ ቦታ; መጠጥ ቤት ውስጥ ወዘተ የሚያሰለች ሰው አለ.....ታዲያ መፍትሄው ቀላል ነው.....ጭራሽ በቤትህማ ደጉ እንዳለው ሌላው ቀርቶ "የአይንህ ቀለም አላማረኝምና ሁለተኛ ድርሽ እንዳትል" ማለት መብትህ ነው :lol: ከቻልክ "ያቅሚቲዋን የሐበሻ ወኔ" ለጓደኛህ አካፍለው :wink:

ተንኪዩ አሁን ወደ ብዙሐኑ ሀሳብ መጥተሀል በዚህ እስማማለሁ:: ይህን ለማድረግ አብሱሉትሊ ታጥቄ ተነስቻለሁ::

ሐ. ሞተርሳይክል አለማመዳት.....ከላይ ለታዛቢ ነግሬዋለሁ.....ጓደኛህ ለመሆኑ ከስራ ባልደረቦቹ (ሴቶች) ጋር ሻይ አይጠጣም; አያወራም; መፅሀፍ አይዋዋስም; ልምድ አይለዋወጥም :?: ወይንስ ሀጢያት የሚሆነው ጎረቤት ሞተርባይክ ሲያለማምድህ ነው :?:

ይህ ጉዳይ ግን ከሌላው ለየት ስለሚል መልሱም ከላይ ተቀምጧል::

መ. ቀዳናቸው ባልከው ውስጥ ራሱ ምንም ተጨባጭ ነገር ሳይኖር "መረን የለቀቀ" ብለህ አለፍከው....."መረን የለቀቀ" በጣም ሰብጀክቲቭ ነው :wink: የተቀዳውን እዚህ እንደማትለጥፍልን ቢገባኝም; ምን እንዳለ ንገረን.....በአስተርዮ ማርያም ይዤሀለሁ ሳትጨምር; ሳትቀንስ :lol: ምክንያቱም ይሔ የሐበሻ የጭቅጭቅ መጀመሪያ ነው......"እከሌ በጎሪጥ አየኝ" ይልሀል...ይሔኔ እኮ ሰውየው ጭራሽም አላየው :lol:

ሰውዬው ያለውን ቃል በቃል እንዳልከውም ባልለጥፍም እንግዲያውስ አይዲያውን ልስጥህ:: >> ያችን ጥቁር ስከርት ስትለብሺ ኮ በጣም ያምርብሻል .... ፒንኩን ሱሪ ስትለብሺ ደግሞ ከቤቴ መስኮት እየተንጠራራሁ አንዳንዴ አይሽና እቺ ደግሞ ማናት ብዬ ወጣ ብዬ ሳይ አንቺው ነሽ ይልና ይስቃል በጣም ይስቃል. . . አንዳንዴ ሚስቴ እንዳታየኝ ብዬ ተደብቄ አየት አርግሻለሁ እሷ ለሰውዬው አነጋገር ምንም መልስ ሳትሰጠው ጸጥ ስትል ይሰማል:: ይህን አባባል ቆርጬ ነው ያስቀቀመጥኩቲ::

የሰውዬው አነጋገር አስደስቷት እንደሱ ወሬውን ብትቀጥል ኖሮ ፍጹም ግልቲ ያሰኛት ነበር:ለዚህም ነው እኔ አውዲዮን ከሰማሁ በኋላ የልጅቱ ጥፋተኛ አለመሆን እየነገርኩት ያለሁት ባልዬው ግን ይህ ሰውዬው እንድዛ እስከደፈረ ድረስ ወደ ሚቀጥለው ስቴፕ ላለመሄድ ማቆም የምትችለዋ እሷውነበረች ባይ ነው:: ለምሳሌ እንዲህ ዐይነት ወሬ እንድታወራኝ አልፈልግም አቁም ለምን አላለችም ባይ ነው::

በተረፈ....."ሰውየው ደበረኝ; ቀልቤ አልወደደውምና ቤቴ አይምጣ" ማለት የአባት ነው........

ይህን በድጋሚ ተቀብያለሁኝ አመሰግናለሁ::

. . . ከዚህ ውጪ በቅናትና በራስ ካለመተማመን ምክንያት ምንም ያላደረገችውን ሚስት ከመሬት ተነስቶ መጨቅጨቅና መነትረክ ነውርና ደንቆሮነት ነው :!:

ይህ ገና በሳይንስ አልተረጋገጠም:: :idea:
የዳንግላው
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 69
Joined: Sat Dec 18, 2004 9:11 am
Location: Blackburn - Uk

Postby የቦግዪ » Thu Dec 13, 2012 12:14 pm

አንተንስ ግን አይጠረጥርህም በሌለበት ስትሄድ? :D
Gotta live my life like there's one more move to make.
የቦግዪ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Sun Oct 28, 2012 6:56 pm

Postby ጩጉዳ » Thu Dec 13, 2012 3:39 pm

የዳንግላው wrote: ተንኪዩ አሁን ወደ ብዙሐኑ ሀሳብ መጥተሀል በዚህ እስማማለሁ:: ይህን ለማድረግ አብሱሉትሊ ታጥቄ ተነስቻለሁ::

:lol: :lol: ወገናችን ለመሆኑ እርግጠኛ ነህ ትጥቁ በቂ ነው ?? ለመሆኑ ማነው ያስታጠቀህ ኢራን ወይስ ቻይና ?? :lol: ዋ ሳትዘጋጅ ከቀረብክ ያ ለማዳ አንበሳ ያመረረ እንደሆነ ሶስታችሁንም ቁርስ ያረጋችኋል:: በተረፈ የክርስቲያኑ እግዚአብሄር የእስላሙ አላህ የቬይትናሞቹ ቡዳ ይርዳህ ከማለት ሌላ በወገንነት የምረዳህ የለኝም:: አጠገቤ ብትሆኑ ኖሮ ያለቺኝን የራስ መከላከል ውሹ ካራቴ እውቀት አካልፍላችሁ ነበር::

ከምር ግን ለብዙዎቻችን በጣም ቀላል የሚመስል ይህ ነገር እነኚህን ሁለት ጎጄዎችን እንዴት እንድህ አስጨነቃቸው ? ጎዣሜዎች ለካስ በፋሲል ልጆች በአባ ካሣ ስመ አማራነት ነው ተሸፍነው ያሉት :lol: :lol: [/quote]
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Dec 14, 2012 10:38 pm

ሠላም TAዛBI

እኔ የምለው ሰው እንደመሆናችን መጠን ከእንስሳ የሚለየን በአእምሯችን መጠቀማችን ነው የሚል ነው......አንተ ደግሞ "ወንድ ስሜቱ ስስ ስለሆነ ምንም ሆነ ምን ሞተር ባይክ ላይ አብሮ ከሴት ጋር ከተፈናጠጠ ክሊክ ያደርግበታል" ብለኽ ደምድመሀል.....ክሊክ ያደርግብሀል;አያደርግብህም ዞሮ ዞሮ በግለሰቡ ላይ የሚመሰረት ይመስለኛል.....ስለዚህ ሰውየውን ሁለታችንም ስለማናውቀው በትክክል መናገር ባንችልም...በእኔ አይን ችግር የለውም...በአንተ አይን ችግር አለው......አዝማሪው እንዳለው "አንቺ ጎንደሬ....እንዳገርሽ እንዳገሬ" :D ይመችህ

የዳንግላው wrote:ሰውዬው ያለውን ቃል በቃል እንዳልከውም ባልለጥፍም እንግዲያውስ አይዲያውን ልስጥህ:: >> ያችን ጥቁር ስከርት ስትለብሺ ኮ በጣም ያምርብሻል .... ፒንኩን ሱሪ ስትለብሺ ደግሞ ከቤቴ መስኮት እየተንጠራራሁ አንዳንዴ አይሽና እቺ ደግሞ ማናት ብዬ ወጣ ብዬ ሳይ አንቺው ነሽ ይልና ይስቃል በጣም ይስቃል. . . አንዳንዴ ሚስቴ እንዳታየኝ ብዬ ተደብቄ አየት አርግሻለሁ እሷ ለሰውዬው አነጋገር ምንም መልስ ሳትሰጠው ጸጥ ስትል ይሰማል:: ይህን አባባል ቆርጬ ነው ያስቀቀመጥኩቲ::

ሠላም ወንድማችን የዳንግላው.....እንደምን ሰንብተሀል :?: ችግሩ ተፈታ :?:

ለማንኛውም አሁን በቀጥታ ወደሰውየው ንግግር......ሰውየው የተናገረውን ቃል በቃል ባይሆንም ሀሳቡን ስለነገርከኝ አመሰግናለሁ.....

1. እንደነገርከን ከሆነ ጎረቤትየው የአንድ ትልቅ ዩኒቨርሲቲ የፉትቦል አሰልጣኝ ነው........እናልህ ይህንን ፅሁፍ በስፕሪንግ ብትፅፈው ኖሮ ምናልባት ሰውየው ጊዜ አግኝቶ ሊሆን ይችላል እል ነበር.....ነገር ግን በጦፈው የፉትቦል ሲዝን አሰልጣኝ ሆኖ በየትኛው ጊዜው ነው......ከሰው ቤት አዘውታሪ ሆኖ ቁጭ ብሎ የሚውልው; ጭራሽ ደግሞ በቤቱ መስኮት እየተንጠራራ የሰው ሚስት ወጣች; ገባች እያለ ሲጠብቅ የሚውለው....እንደነገርከን ከሆነ ደግሞ የጓደኛህ ሚስት ደግሞ አብዛኛዋን ጊዜ የምታሳልፈው ቤት ነው.....ስለዚህ ጠንቋይ ቀላቢ ወይንም መስኮት ላይ ተጥዶ የሚውል ሰው ካልሆነ "ጥቁር ቀሚስ' ለብሰሽ; ፒንክ ሱሪ አድርገሽ አየሁሽ የሚልበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም

2. ሀ. አንተና ጓደኛህ ተጠራጥራችሁ ሁለቱ ሲያወሩ ከመቅዳታችሁ በፊት ጊዜ ሁለቱ ብዙ ጊዜ ለብቻቸው ሆነው አውርተዋል...አይደለም :?: ምክንያቱም ጓደኛህም ጥርጣሬ ያደረበት ከቀን በኻላ ነው.....ስለዚህ "ጥቁር ቀሚስ; ፒንክ ሱሪ ለብሰሽ አየሁሽ...ያምርብሻል" የመባባያው ቀን በጣም ያለፈ ይመስለኛል....እኔ እጠብቅ የነበረው "ፒንክ ቶንግሽ" ይመቸኛል አይነት ነገር ነበር :D

ለ. አለ ብለህ የነገርከኝ ነገር እጅግ ብዙ ብር ከሚከፈለው ሀብታም ጥቁር አሜሪካዊ የምጠብቀው ጅንጀና ሳይሆን ደንበኛ የሐበሻ ጅንጀና መሰለኝ :D
ጥቁር አሜሪካዊ እንኳን ሀብታም ሆኖ ነገር ሞልቶለት በባዶ ኪሱ እንኳን ሴት እንዴት ማናገር እንደሚችሉ ያውቃሉ......እንግዲህ አስበው......በመጀመሪያ "ጥቁር ስከርት ስትለብሺ ያምርብሻል" አላት.....አንድ በል....ስለዚህ ከዚህ አባባል የምንረዳው ጥቁር ቀለም ከቆዳዋ ቀለም ጋር እንደሚሄድና ባቷና እግሯ እንደሚያምር ነው.....ከዛ ደግሞ ዘሎ "ፒንክ ሱሪ ስትለብሺ ያንጠራራኛል" አለ :D ትንሽ ግራ ያጋባል....ከቀሚስ ወደ ሱሪ...ከጥቁር ወደ ፒንክ መፈነጣጠር :D .....እኔ አላውቅም.....ግን ከሀብታም ጥቁር አሜሪካዊ በአጭር ንግግር ውስጥ ይህን የመሰለ የስታይል ምርጫ ልዩነት አልጠብቅም

ሐ. የጓደኛህ ሚስት የትርፍ ጊዜ ስራ ዩኒፎርም "ፒንክ ሱሪ" ካልሆነ በስተቀር; ሰውየው በምን አይነት መልኩ "ፒንኩን ሱሪ ስትለብሺ ደግሞ ከቤቴ መስኮት እየተንጠራራሁ አንዳንዴ አይሽና እቺ ደግሞ ማናት ብዬ ወጣ ብዬ ሳይ አንቺው ነሽ" አይልም.....አንዴ ወይም ሁለቴ ቢሆን ኖሮ "ፒንኩን ሱሪ የለበስሽ ቀን" ነበር የሚለው.......ግን እንደእሱ አባባል ሚስትየዋ ፒንክ ሱሪ አዘውትራ ትለብሳለች ማለት ነው.......እንጃ.....ኢትዮጵያ እንኳን ድሮ የቀረ ይመስለኛል "አየለን አታውቀውም እንዴ? ያ ጥቁር ሌዘር የሚለብሰው" :D

3. በመጨረሻም.......አሁንም ሰውየው ላይ ጥፋት አላገኘሁም......."ጥቁር ቀሚስና ፒንክ ሱሪ ያምርብሻል" ማለት ማድነቅ ነው...ኮምፕልመንት ነው......ምን አጠፋ :?: አንተ የሥራ ቦታ ሴት ጓደኛህን ዘንጣ ስታያት; "ዛሬ አምሮብሻል" አትላትምን :?: "አንዳንዴ ሚስቴ እንዳታየኝ ብዬ ተደብቄ አየት አርግሻለሁ" ማለትም እኮ ቀልድ ነው.....ቆንጆ ስለሆንሽ ሚስቴ ሌላ ሴት ለምን ታያለህ ትለኛለች የሚል የአድናቆት አባባል ነው......ጓደኛህ እንደውም ቆንጆ ሚስቱ ውበቷ ሲደነቅ ሊደሰት ይገባው ነበር

ያም ሆነህ ይህ እንደሚሆን አድርጉት.......ከእነሱ ትዳር እኩል የእኔ ጭንቅላትም መበጥበጥ የለበትም :lol:

ሞራል እየሰጠች እንደዚህ የምታስለፈልፈኝ ደግሞ Konjit ናት :D

ሠላም ሁኑ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ሳምራውው33 » Fri Dec 14, 2012 11:14 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:ሠላም TAዛBI

አንተ
ንፍጣም
የመንገድ ላይ ልጅ ቡሽቲው ክቡራን ስለ አቮጋድሮ number አስረዱኝ እያለ የ 9 ክፍል chemistry ግራ አጋብቶት ያለቅሳል እዚ አንተ አንጎልህን የሞላውን
ንፍጥ
ትጎለጉላለህ :lol: :lol: እስቲ እርዳው ከቻልክ በክት ፋይል አመላላሽ :!:በቅቤ የራሰ ዱላም ይዞ እየጠበቀህ ነው እንድትሰድበት :lol: :lol: :lol:
The love of money is the root of all evil.

ሳምራውው 33 የግጥም አርበኛ
ስንኝ ቋጣሪ በውብ አማርኛ ::
_________________
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby HD » Fri Dec 14, 2012 11:17 pm

ቧ, አንተ ማነህ ንምን አባትህ ነው እዚህ መተህ የምታቦጣቡጥ? ለምን ለጎደኛህ ምከረውና ሁላቹም በተሰበሰባቹበት ቦምብ አፈንድቶ አይገላግላቹም? ቧ አሙነአረጋዊ እኛ ጭንቅላታችን በስንቱ ይቦጥቦጥ? እናንተ ሸዋዬዎች ደሞ ኑና እስኪ እዛ ሸገር ቤታችን ሄደን ስለ ቦምብ አሰራር ምናምን አስተምሩን ቧ, አንተ ማነህ ግን ቆይ ጎደኛ ተብዬው ሰውዬው ኪችን እየሰራች ባለችበት መቶ ከሁዋላ እስኪቀረቅርባት ነው የምትጠብቅ? ጅግና ተጋዳላይ አደለህ እንዴ? ቧ, ጠፋኢና, ለምን ወይ መርዝ አጠጥታቹ ሰማታት አታረጉትም ሰውዬውን? አቡነ አራገዊ እኔ ነግርያቹዋለው, ይቺ ልጅ አንዴ ከቀመሰች በሁዋላ መመለሻ አይኖራትም, እኔ ነግሬያለው, የማንም መቀርቀሪያ ሆና ትቀርላቿለች ቧ, እኔ HD ብሆን ገና ድሮ ይሄንን ሰውዬ ለመታገል ጫካ ገብቼ ነበር, አቡናረጋዊ ነው የምላቹ, ቧ ሰሞኑን ደሞ የታንክ መንጃፍቃድ ነው ያወጣሁላቹ, በአቡነ አረጋዊ ስም እንዳልጨርሳቹ
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am

Postby ሀሪከን2 » Fri Dec 14, 2012 11:33 pm

ዳግማታዊ ዋለልኝ
እኔ የምለው ሰው እንደመሆናችን መጠን ከእንስሳ የሚለየን በአእምሯችን መጠቀማችን ነው የሚል ነው ......አንተ ደግሞ "ወንድ ስሜቱ ስስ ስለሆነ ምንም ሆነ ምን ሞተር ባይክ ላይ አብሮ ከሴት ጋር ከተፈናጠጠ ክሊክ ያደርግበታል " ብለኽ ደምድመሀል .....ክሊክ ያደርግብሀል ;አያደርግብህም ዞሮ ዞሮ በግለሰቡ ላይ የሚመሰረት ይመስለኛል .....ስለዚህ ሰውየውን ሁለታችንም ስለማናውቀው በትክክል መናገር ባንችልም ...በእኔ አይን ችግር የለውም .

አጉል መካሪ ቂጥ ያስበዳል ትል ነበር ጎረቤታችን :lol: :lol: ባአቡነ አረጋዊ አሁን ይህ ለወገን የሚሰጥ ምክር ነው?? ዳሩ በዘረኝነት በሽታ ከበሰበሰ ጭንቅላት ምን የተሻለ መፍትሄ ይጠበቃል??? ምንም :roll:

የዳንግላው ሌሎች ሰወች ከላይ እንዳሉህ መፍትሄው አንድ እና አንድ ነው እሱም ደፈረ ብሎ እኔ በሌለሁበት ወደ ቤቴ እንድትሄድ አልፈልግም ማለት
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Dec 14, 2012 11:58 pm

ሀሪከን2 wrote:ዳግማታዊ ዋለልኝ
እኔ የምለው ሰው እንደመሆናችን መጠን ከእንስሳ የሚለየን በአእምሯችን መጠቀማችን ነው የሚል ነው ......አንተ ደግሞ "ወንድ ስሜቱ ስስ ስለሆነ ምንም ሆነ ምን ሞተር ባይክ ላይ አብሮ ከሴት ጋር ከተፈናጠጠ ክሊክ ያደርግበታል " ብለኽ ደምድመሀል .....ክሊክ ያደርግብሀል ;አያደርግብህም ዞሮ ዞሮ በግለሰቡ ላይ የሚመሰረት ይመስለኛል .....ስለዚህ ሰውየውን ሁለታችንም ስለማናውቀው በትክክል መናገር ባንችልም ...በእኔ አይን ችግር የለውም ....በአንተ አይን ችግር አለው ......አዝማሪው እንዳለው "አንቺ ጎንደሬ ....እንዳገርሽ እንዳገሬ " ይመችህ

አጉል መካሪ ቂጥ ያስበዳል ትል ነበር ጎረቤታችን :lol: :lol: ባአቡነ አረጋዊ አሁን ይህ ለወገን የሚሰጥ ምክር ነው?? ዳሩ በዘረኝነት በሽታ ከበሰበሰ ጭንቅላት ምን የተሻለ መፍትሄ ይጠበቃል??? ምንም :roll:

የዳንግላው ሌሎች ሰወች ከላይ እንዳሉህ መፍትሄው አንድ እና አንድ ነው እሱም ደፈረ ብሎ እኔ በሌለሁበት ወደ ቤቴ እንድትሄድ አልፈልግም ማለት

ለመሆኑ የፃፍኩት ምክር ነው እንዴ :?: :wink: :lol: :lol: :lol: ይህን እንኳን የማይለይ ሰው ስለ"ጭንቅላት መበስበስ" ሲያወራ ደግሞ ያዝናናል......ያስቃል.....በርታ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

ቆርጠህ የፃፍከውን.....ምልዑ አድርጌልሀለሁ :wink:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ሀሪከን2 » Sat Dec 15, 2012 7:22 am

ዳግማታዊ
ለመሆኑ የፃፍኩት ምክር ነው እንዴ

አታ ወዲ ሽርሙጣ ምን እያልክ ነው? አቡነ አረጋዊን አንተ ሰውየ ቀውሰሀል የዳንግላው ለጔደኛየ ቸግሮታል ሚስቱን ለአጋንት የመሰለ ጥቁር አጋንት ብድ ሊበዳበት ነው ባሏም ጭንቅላቱ ተቦጥቡጧል እያለ ተጨንቆ ምክር ሲጥይቅ :roll: ለአንተ ደግሞ ጥቁሩ ምንም አያደርጋትም ዝም ብላቹ ነው በከነቱ ጥቁሩን የምትጠረጥሩት እያልክ አይደለ እንዴ የነበረው ???? አቡነ አረጋዊን አንተ ግን ክፉ ነህ እንዲህ አይነት ምክር እየሰጠህ ልጅቷ አጋንት ብድ ተበድታ ትዳሯን ብታፈርስ ምን ትጠቀማለክ?

ደግሞ ምክር አይደለም የጻፍኩት ትላለክ ታዲያ ምን ነበር የጻፍከው???? የዳንግላው የጠየቀው እኮ ምክር ነበር :lol: ቆይ አንተ ግን እንደ መለስ ዜናዊ የክላሽን ጥይት ለጭንቅራትክን ጨርፋለች እንዴ?????
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Dec 15, 2012 7:30 am

ሀሪከን2 wrote:ደግሞ ምክር አይደለም የጻፍኩት ትላለክ ታዲያ ምን ነበር የጻፍከው???? የዳንግላው የጠየቀው እኮ ምክር ነበር :lol: ቆይ አንተ ግን እንደ መለስ ዜናዊ የክላሽን ጥይት ለጭንቅራትክን ጨርፋለች እንዴ?????

ባክህ አታስቀይስ ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

አንተ የጠቀስከው የእኔ ፅሁፍ እኮ ለየዳንግላው የሰጠሁት ምክር ሳይሆን ከTAዛBI ጋር የተነጋገርነው የግል አስተያየት ነው :wink: :lol: :lol: :lol:

ፍሬንድ ተረጋጋ...እንደጆኒ ራጋ....እንዳትሆን እንደሌዲ ጋጋ :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ሚሚ_ካናዳ » Tue Dec 18, 2012 9:42 pm

የዳንግላው:
ዳግማዊ እንዳለው ባለቤትህም ጎረቤትህም ያጠፉት ነገር ምንም አይደለም:: ጓደኛህ በቅናት መንጨርጨርጨሩና አላስፈላጊ የስለላ ቴፕሪኮርደር ከበስተጀርባዋ ከምታጠምዱ መጀመሪያ እምነት በባለቤቱ ላይ ሳይኖረው ይህን ያህል ዘመን መቆየታቸውን ያሳያል:: ሴትን ልጅ እመናት ከዛ እምነት ኤርን ታደርጋለህ :idea: :idea: :idea: የመጨረሻ አድቫይዝ >> ጎረቤታቸው 2ኛ ቤታቸው እንዳይመጣ በቀጥታ ፊት ለፊት ባለቤቴ በለለበት አትምጣ በሉት:: ምንም አትፍሩ ሕግና ሥርዐት ባለበት አገር ነው ያላችሁት::
ሚሚ_ካናዳ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 149
Joined: Wed Dec 15, 2004 7:04 am
Location: canada

Postby ገልብጤ » Tue Dec 18, 2012 10:52 pm

ሴትን ልጅ እመናት ከዛ እምነት ኤርን ታደርጋለህ

:roll: :roll: :roll: :roll:
ሴትም ወንድ ልጅን ማመን አለባት ማለት እኮ ነው...
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

ይህ ነገር እዉን ተከናውኖ ይሆን?

Postby ጫፉ ብቃለ » Thu Dec 27, 2012 6:17 am

ባጠቃላይ ጥሩ ፊክሽን መሰለኝ: :lol:
ጫፉ ብቃለ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 1
Joined: Thu Dec 27, 2012 4:41 am

Re: ይህ ነገር እዉን ተከናውኖ ይሆን?

Postby ገንዳው » Sun Jan 06, 2013 11:29 am

ጫፉ ብቃለ wrote:ባጠቃላይ ጥሩ ፊክሽን መሰለኝ: :lol:

ይህን የመሰለ ፊክሺን ለመጻፍ ይህን ያህል ኢነርጂ የሚከሰክስ ካለ ጊዜ የሚቀልድ ዶማ መሆን አለበት :wink: ግን ከኛ ሕይወት ስታይል ይሁን ባላውቅም በአብዛኛው ዲያስፖራ ሀበሻ አከባቢ እንዲህ ዐይነት አጋጣሚ በጣም ይከሰታል:: እኔ ራሴ የማውቀው የሰማሁት ያየሁት ከዚህ የማይተናነስ ነው:: ለምሳሌ ባንዱ አፓርትመንት ኮምፕሌክስ ውስጥ አራት የሀበሾች ሚስቶች ያስረገዘ ጀግና ታሪክ ..... አያድርስ ነው:: ወንዶቹ በለለቡት ስኒክ እያረገ ካንዱ ወደ አንዱ ቤት እየዘለለ ከሴቶቹ ጋር ሲላፈጥ ያዩት አንዷ አሮጊት ይህ ነገር አላማረኝም በሚል የተነሳ ድ ኤን ኤ ሲመረመር የሁሉም ልጆች የባሎቻቸው ሳይሆን የሆነ አጋጣሚ እንዳለ ይህን ታሪክ ሰምተናል:: :roll: :roll:

ስለዚህ ይህ ታሪክ ፊክሺን ቢሆን እንኳን ሊገጥም ይችላል በሚል ቤነፊት ኦፍ ዳውት ብንሰጥና ብንወያይበት ደግሞ አይከፋም:: መልሶቹንና መካሪዎቹን መከታተል ራሱ ፋሲኔት ያረጋል:: የሰው አዕምሮ ያንዱ ከሌላው እንዴት እነሚራራቅም ማየቱ ራሱ ያስገርማል::
ገንዳው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 334
Joined: Thu Dec 23, 2004 3:46 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest