"አርቲስት" ሰራዊት እና "ጋዜጠኛ" ሰይፉ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

"አርቲስት" ሰራዊት እና "ጋዜጠኛ" ሰይፉ

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Tue Dec 11, 2012 6:58 pm

እኔ የምለው..ምነው ግን ወረሩን? ይመቻቸው ግን... :D

1. ማስታወቅያ ሰሪ

2. የመድረክ አስተዋዋቂ

3. ፊልም ተዋናይ ( ፊልምከተባለ)

ዳይሬክተር

4. ወጥ ሰሪ ( የሆነ የዱባይ ሆቴል ወጥ እየቀመሱ ሲያስተዋውቁ ስላየሁ ነው ቅቅቅቅቅ)

5. ዲጄ


6. ቶክ ሾው ሆስት

7. ጋዜጠኛ ( ይቺ አነጋራሪ ናት ቅቅቅቅቅ)

እኔ እምለው ሾው ቢዝነስ ውስጥ ዘው ብሎ የገባ ሁሉ ጆርናሊስት ነው እንዴ?

ደሞ "ሰይፉ ሌተርማን" ለምንድነው ሰው ላይ ዝም እያለ የሚያፈጠው? :lol:

http://www.youtube.com/watch?v=eqpbiq2Y2LY

http://www.youtube.com/watch?v=vqXjjDA4c7c

http://www.youtube.com/watch?v=NXNCNcpBdo8
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ዲጎኔ » Wed Dec 12, 2012 5:32 am

ሰላም ለሁላችን
ውድ ዘጌው ስለዚህ የወቅቱ አረሙቻ ቶክ ሾው ሊንክህ አመሰግናለሁ::እንደዛሬ ሳይገባኝ ጊዘዬን ያጠፋሁባቸው ከንቱ ነገሮች 1ዱ ከንቱ ቶክሾውና ረስሊንግ በአጠቃላይ ናቸው::ቶክ ሾው እውነት መስካሪ ለተገፉ ተሟጋች ጥቂት ያሉትን ያህል በርካቶቹ ግን ፋይዳ ቢስ ናቸው::እዚህ ሰይፉ የጠቀሰው ደቪድ ሊተርማን እድሜ ከገፋ ያገባትን ሚስቱን ጥሎ አብራው ቶክ ሾው ከምትሰራ ጋር ዝሙት ፈጽሞ ሳምንት ሳይሞላው የራሱ ቶክ ሾው ላይ የቀረበ እንከፍ ነው::ዴቪድ ሊተርማንን ሰይፉ እነደመልካም ሲጠቅስ እርባና ቢስነቱን ተረዳሁለት:: እጅግ የሚያሳዝን የሰይፉ አባባል ጦቢያዊያን በእንዶድ ልብስ የሚያጥቡ የቤታቸው ጠረን እንዲጠበቅ በወይራ በሉባንጃ ሪፍረሽ የሚያደርጉ አፋቸው ጠረን እንዳይኖረው በሎሚ በፌጦ የሚተጉ እህቶቻችን ግበርውሀ እያሉ የሚጸዱና ሙስሊሞቹ እጅግ በሚያስደስት ሀይማኖታዊ መታጠብ የሚጠቀሙትን ግምት ያላስገባና ሁላችንን ያዋረደ 'ንጽህና ይጎድላቸዋል' ብሎ የሚሰድበን ዘረኛ የሚጠቅስ ራሱን ሰዳቢ ነው::
የነሰራዊት ድሮም ጋሸ ጳውሎስ ኞኞ ባለቤቱን የሰፈር ቡና የከለከለ ብዙ አሉታዊ ነገሮች ጥቂት አዎንታዊ ጉዳዮች ያሉትን አቅርበዋል::እዚህ ቶክሾ ተብየዎች ለህዝቦች ፕሬስ አፈና ምንም ሊተነፍሱ የማይችሉ በገዠው ወያኔ አገዛዝ መልካም ፈቃድ ህዝብ ያሚያጃጅሉ ሀይሌ ገ/ስላሴ ገብጋባ የአርሲ የበቀለባት ምድር ብድራት ግድ የማይለውን ያቀረቡ ናቸው::ድሮ ከያኒና ደራሲ ሀይማኖት አለሙ 'ፊትለፊት' ሲያቀርብ ህዝቡ 'ጎን ለጎን' ያለው ሀይማኖት በፕሮግራሙ ላያ ጫና ያደረገው የተተቸበት የድሮ ቶክ ሾው ይሰትዋል::
ዲጎኔ ሞረቴ የህዝቦች መብት ከሚተነፍሱ ሰፈር በገዥዎች ሳምባ ከሚተነፍሱት ጉዶች ሩቅ ማዶ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Wed Dec 12, 2012 5:49 am

ዲጎኔ wrote:ቶክ ሾው እውነት መስካሪ ለተገፉ ተሟጋች ጥቂት ያሉትን ያህል በርካቶቹ ግን ፋይዳ ቢስ ናቸው::


ዲጎኔ...እኔ አንተን ስለማከብርህ; በቀባጠርክ ቁጥር ተሸማቅቄ አለቅኩኝ :lol:

በመጀመሪያ ቶክ ሾው ምን ማለት ነው :?: የአንተ እውነት መስካሪና ለተገፉት ተሟጋቾች ደግሞ የትኞቹ ናቸው :?: ያልሆኑትስ :?: ሁሉንም ቶክ ሾው እይ ብሎ ያስገደደህ አለን :?:

ዴቪድ ሌተርማን የሰራው ስራ የራሱ ጉዳይ ነው...እኔን አይመለከተኝም.....የእሱን ሾው የምመለከተው በእርሱ ፅድቅ ሳይሆን ፕሮግራሙ ደስ የሚለኝ ከሆነ ነው......በዚህ አይነትማ ኢየሱስ ራሱ መጥቶ ቶክ ሾው እስኪጀምር ድረስ ማንንም ማየት የለብህም :wink: ክፉ አታናግረኝ...ደንባራ :lol:

ዲጎኔ wrote:እዚህ ቶክሾ ተብየዎች ለህዝቦች ፕሬስ አፈና ምንም ሊተነፍሱ የማይችሉ በገዠው ወያኔ አገዛዝ መልካም ፈቃድ ህዝብ ያሚያጃጅሉ ሀይሌ ገ /ስላሴ ገብጋባ የአርሲ የበቀለባት ምድር ብድራት ግድ የማይለውን ያቀረቡ ናቸው ::


ለፕሬስ መብት ቆሜያለሁ ብሎ በየቀኑ የሚያላዝን ከብት; ሌሎች ለምን ተናገሩ ብሎ ሲራገም በጣም ይገርማል......ደንባራው.....ለፕሬስ ነፃነትና አንተም ደስ እንዲልህ ሲባል ሰይፉና ሠራዊትም መናገር ያቁሙልህ :?: :lol: :lol: :lol: :lol:

የሆነ ጊዜም ብዬሀለሁ......ሌላው ቢቀር እድሜና መፅሀፍ ቅዱስ እንኳን ትንሽ ጭንቅላትህን ከእንቅልፍ አይቀሰቅሱትምን :?: :lol:

አክባሪህ
ዳግማዊ ዋለልኝ
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

(-:

Postby ደጉ » Wed Dec 12, 2012 6:25 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:.....ዲጎኔ...እኔ አንተን ስለማከብርህ; በቀባጠርክ ቁጥር ተሸማቅቄ አለቅኩኝ :lol:

.........የሆነ ጊዜም ብዬሀለሁ......ሌላው ቢቀር እድሜና መፅሀፍ ቅዱስ እንኳን ትንሽ ጭንቅላትህን ከእንቅልፍ አይቀሰቅሱትምን :?: :lol:

....ቶክ ሾውን በሚመለከት እኔ እምለው ነገር የለም ...በብዙዎች ህሳብ እምስማማው ግን 1 ነጥብ አለ...ከ 82ሚሊየን ህዝብ ባላት አገራችን ....በሁሉም የሚዲያ መስክ ተመሳሳይ ፊት ማየት ያሰለቻል....ከልቤ ነው በፕሮግራሙ አይደለም ቅሬታዬ በአዘጋጆቹ...ምናለ ወጣቶችን መድበው እነሱ ከሁዋላ ሆነው ቢረዱዋቸው...? ማስታወቂያውም...ትያትሩም..ፊልሙም....ቶክ ሾውም ሌላ ምን ቀረ... :D
...ዳግማዊ የዲጎኔን ነገር አይደለም እዚህ ዋርካ ነገሩ እግዚአብሄር ጋ ደርሶ ምን እንደሚያደርገው ተቸግሩዋል....ከምሬ ነው እሱን እዚህ ሳውቀው ጀምሮ ለሙከራ የቀቀልኩት ጥቁር ድንጋይ በስሎ ሌላ ጨምሬ እሱም በቅርብ ይበስላል....ዲጎኔ ግን ይህው አለ...አለ :(
..ከአሁን በሁዋላ እድሜውም ሆነ ቅዱስ መጽህፉ በሱ ሂይወት ውስጥ ምንም እሚቀይሩት ነገር የለም....እሚቀርበት እድል ያመለጠው ድሮ የብስራተ ወንጌልን ህንጻ ድንጋይ እያቀበለ ሲገነባ አናቱ ላይ መውደቅ የነበረበት ድንጋይ ቢወድቅበት ነበር...እማዝነው ለ አነት ነው እሱ በቀባጠረ ቁጥር ተሸማቀህ ነጥብ እንዳታክል...? :D
ምንም ጸረ ወያኔ አቁዋም ቢኖረኝ ነጥብ አክለህ በላጲስ ስትጠፋ ማየት አልፈልግም... :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4417
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ዲጎኔ » Wed Dec 12, 2012 7:32 pm

ሰላም ለሁሉ የገባሮቹ መብት አስከባሪ ኒክ ተጠቃሚ ጭምር
እውነትን ለወያኔ ጀሌ መጋት አይሞከርም:: የነሰራዊትአራዊት ቶክሾ ፋይዳቢስ መሆኑ ዘጌው ሲያቀርብ በተገቢ ትንታኔ ሳጠናክር አፍንጫን ሲመቱ አይን ያለቅሳል የወያኔ ፕሬስ አፋኝነት በመጠቀሱ ኡኡታ ከዚያ አክባሪ እያሉ ስድብ::ሊቀ ሊቃውንትህ የቀድሞ የትግል አጋሮቹን የበከተ አንጃ ነጻ ፕሬስን አተላ ከሚል ጀሌ ምን ሊገኝ? ወደነጥቡ ስንመጣ የነሰራዊትሆደአራዊትና መሰሎቹ ቶክ ሾው የሚድያ ውጤት ካልሆነ ከምን ሊመደብ ነው?የታፈኑ ህዝቦች እውነታን በማቅረብ ግፈኞችን እንዴት ይጋለጡ? የአለም ፕሬስ ተሞጋቾች ካወገዟቸው 1ዱ ከፕሬስ አፋኝ የወያኔ አገዛዝ በጎ መጠብቅ ዘበት ነው::እኒህ ሆዳሞች ህዝብ ሲያስቱ በነጻመድረክ ጭምር ሲወሱ ግን ማንነታቸው መግለጽ ግድ ነው::የጦቢያ ህዝቦች ንጽህና የላቸው የሚል ዘረኛን ሰይፉ ሲደግም አይሰማህም ነገር ግን ዲጎኔ ፕሬስ አፋኝ ወያኔን ሲያጋልጥ ተሳደብክ ከንቱ!ሰራዊት አራዊትና አንተ በበላችሁበት ጩሁ እኛም በሀቅ ዘገባቸው የግፈኛ ወያኔ ሰለባዎች የእስክንድርና አንዷለም የተመስገና ሌሎቹ ግፍ ለአለም ማሳወቁን ከዚህ ቀጥሎ ባለው የህዝቦች ልሳን በሆነው ቶክሾው አይነት እንቀጥላለን::
www.ethiofreedom.com

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:

ዲጎኔ...እኔ አንተን ስለማከብርህ :lol:

ደንባራ :lol:

ለፕሬስ ነፃነትና አንተም ደስ እንዲልህ ሲባል ሰይፉና ሠራዊትም መናገር ያቁሙልህ :?: :lol: :lol: :lol: lol:
:lol:
አክባሪህ
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Re: (-:

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Dec 15, 2012 3:51 am

ሠላም ደጉ

ደጉ wrote:....ቶክ ሾውን በሚመለከት እኔ እምለው ነገር የለም ...


እኔም ለዲጎኔ የነገርኩት የአስተሳሰቡን ችግር እንጂ ስለሰይፉ ወይም ስለሠራዊት ቶክ ሾው አይደለም...እሱ ግን አሁን ሌላ ታሪክ ይቀባጥራል :D

በብዙዎች ህሳብ እምስማማው ግን 1 ነጥብ አለ...ከ 82ሚሊየን ህዝብ ባላት አገራችን ....በሁሉም የሚዲያ መስክ ተመሳሳይ ፊት ማየት ያሰለቻል....ከልቤ ነው በፕሮግራሙ አይደለም ቅሬታዬ በአዘጋጆቹ...ምናለ ወጣቶችን መድበው እነሱ ከሁዋላ ሆነው ቢረዱዋቸው...? ማስታወቂያውም...ትያትሩም..ፊልሙም....ቶክ ሾውም ሌላ ምን ቀረ... :D


በጣም እስማማለሁ......በሌላ አቅጣጫም.....እስክስታ ተወዛዋዥነት; መድረክ አስተዋዋቂነት; ጋዜጠኝነት; ፖለቲከኝነት; የሰብዓዊ መብት ተሟጋችነት; የፖለቲካ ድርጅት ቅስቀሳ ክፍል ሀላፊነት; የታሪክ ተንታኝ; ሰላማዊ ሰልፍ መሪነት.....ኧረ ስንቱን....ለብቻቸው ይዘው የሚንገዳገዱ ሳይ ይገርመኛል :D

...ዳግማዊ የዲጎኔን ነገር አይደለም እዚህ ዋርካ ነገሩ እግዚአብሄር ጋ ደርሶ ምን እንደሚያደርገው ተቸግሩዋል

:lol: :lol:

.
...ከምሬ ነው እሱን እዚህ ሳውቀው ጀምሮ ለሙከራ የቀቀልኩት ጥቁር ድንጋይ በስሎ ሌላ ጨምሬ እሱም በቅርብ ይበስላል....ዲጎኔ ግን ይህው አለ...አለ :(
.ከአሁን በሁዋላ እድሜውም ሆነ ቅዱስ መጽህፉ በሱ ሂይወት ውስጥ ምንም እሚቀይሩት ነገር የለም....እሚቀርበት እድል ያመለጠው ድሮ የብስራተ ወንጌልን ህንጻ ድንጋይ እያቀበለ ሲገነባ አናቱ ላይ መውደቅ የነበረበት ድንጋይ ቢወድቅበት ነበር


ሁሉንም ጨርሰህ የምትቀቅለው ጥቁር ድንጋይ ታጣ ይሆናል እንጂ ዲጎኔ...ወይ ፍንክች :D

...እማዝነው ለ አነት ነው እሱ በቀባጠረ ቁጥር ተሸማቀህ ነጥብ እንዳታክል...? :D
ምንም ጸረ ወያኔ አቁዋም ቢኖረኝ ነጥብ አክለህ በላጲስ ስትጠፋ ማየት አልፈልግም... :D

:lol: :lol:

የምማፀነው እኮ ለራሴው አዝኜ ነው......በዚህ አያያዙ ላጲስ አይቀርልኝም :D


ሠላም ዲጎኔ

ዲጎኔ wrote:ወደነጥቡ ስንመጣ የነሰራዊትሆደአራዊትና መሰሎቹ ቶክ ሾው የሚድያ ውጤት ካልሆነ ከምን ሊመደብ ነው ?


ያልተፃፈ ታነባለህ እንዴ :?: ምንድን ነው የምትቀባጥረው :?:

እኔ እኮ ስለሠራዊት ወይንም ሰይፉ ቶክ ሾው አላወራሁም......እኔ ያልኩህ "የፕሬስ መብት ተሟጋች" ነኝ የምትለው አንተ; ጣመህም አልጣመህም የሌላን ሰው የመናገር መብት ለምን ትቃወማለህ ነው :?: ይገባሀል :?: :D

ያልከውን እንየው......ደግመህ አንብበው
ዲጎኔ wrote:እዚህ ቶክሾ ተብየዎች ለህዝቦች ፕሬስ አፈና ምንም ሊተነፍሱ የማይችሉ በገዠው ወያኔ አገዛዝ መልካም ፈቃድ ህዝብ ያሚያጃጅሉ ሀይሌ ገ /ስላሴ ገብጋባ የአርሲ የበቀለባት ምድር ብድራት ግድ የማይለውን ያቀረቡ ናቸው ::....እኒህ ሆዳሞች ህዝብ ሲያስቱ በነጻመድረክ ጭምር ሲወሱ ግን ማንነታቸው መግለጽ ግድ ነው ::


በእውኑ የፕሬስ መብት ተሟጋች እንዲህ ይላል :?: አታፍርም :?:

የፕሬስ መብት ማለት እኮ ማንም ሰው የፈለገውን መናገርና መፃፍ ይችላል እንጂ "ሁሉም ሰው ዲጎኔ የሚጥመውን ብቻ ይናገርና ይፃፍ" ማለት አይመስለኝም :wink:

ከዛሬ ጀምሮ ግን ስለተነቃብህ የ"ፕሬስ መብት ተሟጋች" የሚለውን የፈሪሳዊ ካባህን እዛው ጥለህ ና....ዋርካ ላይ አታጭበርብርበት :D

ሠላም
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ሙዝ1 » Sat Dec 15, 2012 12:35 pm

ሰላም ወንድሞቼ ...
የዲጎኔ ጽሁፎች አንዳንዴ እጅግ በጣም ያሳቅቁኛል ... የሚያሳቅቁኝም አልፌበታለሁ ከሚለዉ የዚያ ትዉልድ ሁለገብ ተሳትፎ አኳያ ሳየዉ ነዉ:: እንጂ ዲጎኔ ሌሎች ኒኮችን ቢሆን ምንም አይሰማኝም .... የሰዎች አለማወቅ ብዙም አያሳቅቅም ... ህይወት በሰጠቻቸዉ እድል አልተጠቀሙም ወይንም እድሉን ከመጀመሪያ አላገኙትም ... ስለዚህ ... አላወቁማ!!!!! ምን ታደርገዋለህ:: የዲጎኔ ችግሩ አለማወቅን መላምድ አይደለም .... አንዳንድ ሰዉ አለማወቁን ያዉቃል ... አለማወቁን አዉቆም ይላመደዋል .... ካለማወቅ ጋር መላመድ ስህተት ቢሆንም አለማወቁን ማወቁ በራሱ በቂ እዉቀት ነዉ --- እንደ እርጎ ዝምብ ንክር ንክር አይልም ... ... ... የሱ ትልቁ ስህተት አላዋቂ መሆኑን አለማወቁ ነዉ ... አለማወቁን ካላወቀ እንዴት ይስተካከል .... በሱ ቤት ያዉቃላ!!! ... እኔ ይህን አስተያየት የሰጠሁ ደጉ አስተያየት ስለሰጠ ነዉ ... ... ደጉ ወያኔን አይደግፍም ወይንም አባል አይደለም ተብሎ በዋርክኛ ይታሰባል ... ... እሱ አስተያየት ባይሰጥና እኔ ብሰጥ ኖሮ .... አላዋቂነቱን .... ወይንም ቢያንስ ሲጽፍ ከርዕስ መንሸራተቱን መንገራችን እንደ ትልቅ የፖለቲካ ድል ያየዉ ነበር --- በሁለት ወያኔዎች ተዘለፍኩ በማለት:: ኤኒዌይ ስለሰዎች ማዉራት ያስጠላኛል .... ይህ ግን ስለሰዎች ሳይሆን ስለ ዲጎኔ ድንፈፍነት ስለሆነ ሰለ ሰዉ እንዳወራሁ አይሰማኝም::

ወደ ቤቱ አርዕስት ስመጣ ... ...
ዘጌዉ ምን ታደርገዋለህ ... ሰዉ ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ ነዉ ሚባለዉ ... ... ... በዘረዘርካቸዉ ዘርፎች መሰማራታቸዉን አምላክ ምስክሬ ነዉ ካንተ ሰማሁ ... ሰራዊት ማስታወቂያ እንደሚሰራ ነዉ ማዉቀዉ ... ... ሰይፉ ደግሞ ቀን ቀን የሙዚቃ ዝግጅት በኤፍ ኤም ሬዲዮ እንደሚያቀርብ አዉቃለሁ ... የሆነ ከ10 -12 ሰዐት መሰለኝ ... እሱም በፊት ነዉ ከ10 አመት በፊት ... ከዛ ባለፈ ሁለቱንም አላዉቃቸዉም ... .... የኛ አገር ሚዲያዎች ምርጫዎቼ አይደሉም ... ... በኔ መስፈርትም አዝናኝም አስተማሪም ሊሆኑ አይችሉም ---- አንዳንዴ ለጤናዬም በማሰብ አልከታተላቸዉም:: ነገር ግን አያቅርቡ አልልም .... ከነሱ የተሻለ አቅርቤ ድክመቶቻቸዉን ካልሞላሁ ቢያንስ ለአድማጮቻቸዉ ክብር ስል አከብራለቸውለሁ --- የአለማየት መብቴን በመጠቀም::
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Re: "አርቲስት" ሰራዊት እና "ጋዜጠኛ" ሰይፉ

Postby ዲጎኔ » Sat Dec 15, 2012 2:44 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን
ወገን ዘጌ ዘጋንባው ተገቢ ወቅታዊ ትችት በተገቢ አምድ አቅርበህ እኔ ሳጠናክር ጸረዲጎኔዎች ከየጉራንጉሩ እየተጠራሩ ቢወርፉኝ አይደንቀኝም:: ትችታቸው ከሎጅክ ተጠየቅ አኩዋያ ሳይሆን ከክፉ መንፈሳቸውና ከእኩይ ፖለቲካቸው የተነሳ ነውና::
ነጥብህ እንዳይረሳ በአግባቡ እዚህ እመልሳለሁ:-
1.ወረሩን ላልከው አዎን በክፉ ፖለቲካና ባህል ወረሩን አስወረሩን
2.ማስታወቂያ ሰሪ -አማራጭ በሌለው የወያኔ ሚድያ ብር ሊመዘብሩ
3.መድረክ አስታዋቂ-ራእይአልባ የ21 አመታትዲክታተር ባለራይ ሊሉ
4.ፊልም-ሂሩትያባቷ ስም በህይወት ዙርያ እንዳላየን የወያኔአርቲ ቡርቲያቸው ፊልም ተባለ ቅቅ
5.ወጥ ሰሪነት-እነርሱ ለወያኔ ለማጎብደድ የማይሰሩት የለም
6.ዲጄ-ቦሌ ጄነራሎቹ በምዝበራ ካሰሩት ህንጻ ስር እምበር ሊጨፍሩ
7.ጋዜጠኛ??CPJአልማቀፍ ጋዜጠኛ ተሞጋች የጦቢያ ፕሬስ ታፍኗል ዘብጥያ ወርዷል ይላል ለነሱ ወያኔ ወዳጄ ሁሉ በጄ ሁሉ በደጄ ፈቃድ ቶክሾው ጋዜጣ በሽ ነው!
ዴቪድ ሊተርማንን አያቁትም በሴሰኝነት አምሳያው ስብሀት ነጋን ለማስደሰት እንጂ ቅቅቅቅ
=============/////////////////=========//////////

[quote ='ዘጌ_ዘጋንባው"]

እኔ የምለው..ምነውግንወረሩን? ይመቻቸው

1. ማስታወቅያ ሰሪ-
2. የመድረክ አስተዋዋቂ-

3. ፊልም ተዋናይ ( ፊልምከተባለ)-
ዳይሬክተር- ጉድ እነዶር ሀይሌ ገሪማ በወያኔ ሹሞች የተገፉት እንዳይሰሙና ክፉኛ እንዳያዝኑ

4. ወጥ ሰሪ ( የሆነ የዱባይ ሆቴል ወጥ እየቀመሱ ሲያስተዋውቁ ስላየሁ ነው ቅቅቅቅቅ)-[b]
5. ዲጄ-

6. ቶክ ሾው ሆስት- ቶክ ሾው ሀገራዊ የብዙሀን ስራ ሲቀርብ ነበር የነሱ ግን ያንድ አናሳ ጎሳ ወርቃማ ብሎ የሚታበይ ነው

7. ጋዜጠኛ ( ይቺአነጋጋሪ ናት)

እኔ እምለው ሾው ቢዝነስ ውስጥ ዘው ብሎ የገባ ሁሉ ጆርናሊስት ነውእንዴ?-

ደሞ "ሰይፉ ሌተርማን" ለምንድነው ሰው ላይ ዝም እያለ የሚያፈጠው?

http://www.youtube.com/watch?v=vqXjjDA4c7c

http://www.youtube.com/watch?v=NXNCNcpBdo8[/quote]
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sun Dec 16, 2012 1:25 am

ውድ ዲጎኔ
ውድ ዳግማዊ
ውድ ደጉ
ውድ ሙዝ

እንደምናቹ? ፕሊስ አትናቆሩ

አምስታችንም ባንድ ነጥብ ስለተስማማን ደስ ብሎኛል:: እኔ እንኳን በትረባ..ነቆራ መልክ ነበር ያሰብኩት ግን ደሞ አንዳንዶቻቹ እንደጠቀሳቹት እነኚህ ግለሰቦች ሁሉንም ነገር በሞኖፖል መያዛቸው ግርም ብሎኛል:: አትሊስት እንግዲ 15 ይርስ መሆኑ ነው ስታይላቸውን ሪሳይክል እንክዋን ሳያረጉ እንዳሉ አሉ:: ታኬታ ብቻ እየቀየሩ ክስቶ ይሉብካል:: ሜይቢ ሜይቢ....ህዝቡም እነሱን ብቻ ማየት እና መስማት ይመቸው ይሆናል...ማን ያውቃል?:: ግንለህዝቡ አማራጮች ተሰጥተውታል ወይ ነው ጥያቄው? በተለይ ኢንተርቴይመንት ቢዝነስ ፍሬሽ ፊቶች ብቅ ብቅ ሲሉ ነው የበለጠ ሙድ ያለው ብዬም አምናለሁ:: እንዲህ ስል የነኝህ ሁለት ሰዎችን ተሰጥኦ በጭራሽ እያንኳሰስኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ:: ሰራዊትን እስካሁን የማደንቅለትን የአብዬ ዘርጋው ካራክተር በኢትዮጵያ ሬድዮ ድራማ ታሪኮች እጅግ የተዋጣለት ነው ብዬ እገምታለሁ:: ሰይፉ ፋንታሁንም ሆሊውድ ጋዜጣን ሲያዘጋጅ ወጣቱን ታርጌት ያረገ አማራጭ ኢንተርተይንመንት ሚንስ ስለጀመረልን አደንቀዋለሁ:: ግን እዚም እዛም በዙ ነው የኔ ትዝብት::

ዳግማዊ..የ አክቲቪስቱ....አርቲስቱ...ተወዛዋጁ...ምናምኑ :lol: :lol: :lol: .... ሎጂካል በሆነ ሁኔታ ዱቅ አርገከዋል!!


Disclaimer: ከላይ ያለው ጽሁፍ በከባድ ምርቃና የተጻፈ ስለሆነ ለሚያስከትለው ውዝግብና መዘዝ ውርድ ከራሴ!!
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Re: "አርቲስት" ሰራዊት እና "ጋዜጠኛ" ሰይፉ

Postby ቁምቢ » Sun Dec 16, 2012 6:31 am

ዘጌ_ዘጋንባው wrote:

ደሞ "ሰይፉ ሌተርማን" ለምንድነው ሰው ላይ ዝም እያለ የሚያፈጠው? :lol:


:lol: :lol: ሰይፉ ሌተርማን..... ጭራሽ ኮፒ ፔስት እኮ ነው ከዚ አገር ቶክ ሾው ጋር..........ለዚ ይመስለኛል ብዙ ግዜ ወዝ የሌለው ነገር የሚሆንብን..... ድሮ ትዝ ካለህ አለቤ ሾው በጣም የምንከታተለውና ህዝብ የሚወደው ቶክ ሾው ነበር..........በዛ ላይ ደግሞ ብዙ የተረሱ ሰዎችን በማፈላለግ እንዲረዱ ያደርግ ነበር አለቤ ነብሱን ይማረውና......ይቺ ሴፉ የምትባል ቅል እራስ ሌተርማን መሆን ፈልጋ መከራዋን ስታይ በሳቅ ገደለኝ.........አንዳንድ ግዜ ኮሜዲያን ስትሆን ሰው በቀልዴ ነው ወይስ በኔ ላይ ነው የሚስቅብኝ ብለህ ማሰብ አለብህ..........ድሮ የማውቃቸው የሰፈር ልጆች ከሴፉ የተሻለ ቀልድ አላቸው.......

ግራና ቀኝ የሚባለውን ግን ወድጄዋለው አሪፍ ፕሮግራም ነው.........ያነጋግራል ያከራክራል አለ አይደል ነቃ ያደርግሀል............

አዲስ ነገር ብትሉ አንድ የሆነ የሀበሻ ሮክ ባንድ አይቼ በጣም ተመችቶኛል ያላየ ይኮምኩም....

http://www.youtube.com/watch?v=hnMCbM2b_Jw

ለትውስታ ደግሞ...
http://www.youtube.com/watch?v=iDGqy88-yTY
የሰው ልጅ
መውደድ ሲችል መጥላቱ
መምከር ሲችል ማማቱ
መስራት ሲችል መቅናቱ
ማስታረቅ ሲችል ማጣላቱ
ያሳዝናል የሰው ፍጥረት በሕይወቱ፥፥
ቁምቢ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Mon Nov 26, 2012 3:55 am

Postby ዉቃው » Sun Dec 30, 2012 2:07 am

ይህ ዕድል ስለተሰጠኝ በጣም አመስግናለሁ ...መንፌው !
እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር በሚባለው መሰረት ....ሁለቱም ሰዎች አይመቹኝም /አራት ነጥብ ::
ጉዟችን ረጅም : ግባችንም ሩቅ ነው !!!!
ዉቃው
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1032
Joined: Sun Jan 07, 2007 2:48 am

Re: (-:

Postby ቱቱያ » Sun Dec 30, 2012 9:27 am

ደጉ wrote:
ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:.....ዲጎኔ...እኔ አንተን ስለማከብርህ; በቀባጠርክ ቁጥር ተሸማቅቄ አለቅኩኝ :lol:

.........የሆነ ጊዜም ብዬሀለሁ......ሌላው ቢቀር እድሜና መፅሀፍ ቅዱስ እንኳን ትንሽ ጭንቅላትህን ከእንቅልፍ አይቀሰቅሱትምን :?: :lol:

....ቶክ ሾውን በሚመለከት እኔ እምለው ነገር የለም ...በብዙዎች ህሳብ እምስማማው ግን 1 ነጥብ አለ...ከ 82ሚሊየን ህዝብ ባላት አገራችን ....በሁሉም የሚዲያ መስክ ተመሳሳይ ፊት ማየት ያሰለቻል....ከልቤ ነው በፕሮግራሙ አይደለም ቅሬታዬ በአዘጋጆቹ...ምናለ ወጣቶችን መድበው እነሱ ከሁዋላ ሆነው ቢረዱዋቸው...? ማስታወቂያውም...ትያትሩም..ፊልሙም....ቶክ ሾውም ሌላ ምን ቀረ... :D
...ዳግማዊ የዲጎኔን ነገር አይደለም እዚህ ዋርካ ነገሩ እግዚአብሄር ጋ ደርሶ ምን እንደሚያደርገው ተቸግሩዋል....ከምሬ ነው እሱን እዚህ ሳውቀው ጀምሮ ለሙከራ የቀቀልኩት ጥቁር ድንጋይ በስሎ ሌላ ጨምሬ እሱም በቅርብ ይበስላል....ዲጎኔ ግን ይህው አለ...አለ :(
..ከአሁን በሁዋላ እድሜውም ሆነ ቅዱስ መጽህፉ በሱ ሂይወት ውስጥ ምንም እሚቀይሩት ነገር የለም....እሚቀርበት እድል ያመለጠው ድሮ የብስራተ ወንጌልን ህንጻ ድንጋይ እያቀበለ ሲገነባ አናቱ ላይ መውደቅ የነበረበት ድንጋይ ቢወድቅበት ነበር...እማዝነው ለ አነት ነው እሱ በቀባጠረ ቁጥር ተሸማቀህ ነጥብ እንዳታክል...? :D
ምንም ጸረ ወያኔ አቁዋም ቢኖረኝ ነጥብ አክለህ በላጲስ ስትጠፋ ማየት አልፈልግም... :D

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በጣም ያስቃል:: የፈለገውን በሉ ሰይፉዪን አትንኩብኝ በጣም ነው የሚያዝናናኝ ቅቅቅቅቅቅ
one love!!!
ቱቱያ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Thu Dec 29, 2005 8:59 am
Location: upthere


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests