ሶስቴ?

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ሶስቴ?

Postby Gosa » Thu Jan 03, 2013 8:58 am

ሊንኩን ዛሬ ፌስቡክ ገጼ ላይ አይቼ ሳነበው አሳዘነኝ:: ትንሽ ቆየት ስላለ ምናልባት አይታችሁትም ይሆናል:: እንደ እኔ ያላያችሁት ካላችሁ እስቲ ጊዜ ስታገኙ እዩት
http://www.diretube.com/articles/read-t ... _2179.html
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ስራ ፈት » Thu Jan 03, 2013 9:12 pm

በጣም ያሳዝናል ገና ማየቴ ነው:: ገርጂ አካባቢ በጣም አውቀዋለው ድሮ ድሮ እነ በልጌ, አህመድ. ጦይብ የሚባሉ ከኤርትራ ተፈናቅለው የመጡ ልጆች እሬሳ እየፈነቀሉ የሬሳ ሳጥን ይፖሽሩ ነበር::

ከዛም እሬሳውን እንደነበረ በማስቀመጥ ሳይታወቅ ሳጥኑን ለባለ ተራ ይሸጡታል:: የዚች ልጅ ግን በጣም ያስገርማል:: ከልጅቷ እድሜ ማነስና አንዳንድ ሁኔታዎች ጋር ተደምሮ አንድ የሆነ ነገር ልቤ ክፉኛ ጠርጥሯል ቢሆንም ግን ሳያረጋግጡ ወሬ እንዳይሆንብኝ ግን ፈራው ይቅር ብቻ::

ድምፅ ሰማን የሚሉት ነገር ግን የተለመደና በተለያዩ ቦታዎች የተደጋገመ ነገር ነው:: እንዲያውም በመቃብር አጠገብ የሚኖሩ ሰዎች ይሄ ነገር ለነሱ አዲስ አደለም::

ሁል ግዜ መቃብር አካባቢ ኡ ኡ ታና ዋይታ መስማት የተለመደ ነው:: የትኛው መቃብር እንደሚጮህ ግን ለማወቅ ያስቸግራል:: እኔም ገጥሞኛል::

ገርጂ ብዙ ትዝታ አለኝ:: ቤተክርስትያኗ ያኔ ባረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያጌጠች ትንሽዬ ጎጆ ነበረች:: በኍላ ልወጣ ስል መስራት ጀመሩ መሰለኝ::

ብቻ እንደው ያ አካባቢ እንዴት እንደምወደው አትጠይቁኝ:: ከቤ/ክርስትያኑ ጀርባ ያለው መቃብር ካጠገቡ እልም ያለ ጫካ ነበር:: ፀሀይ ከረር ሲል ያቺ ዛፏ ስር አረፍ ያሉ እንደሆነ ፀጥ ካለው ጫካ ውስጥ የዛፎቹ ሽብሽቦና የወፎቹ ዝማሬ ብቻ ነበር የሚሰማው:: ብዙ ግዜ ታዲያ በጀርባዬ ትንጋልዬ ሰማዩን ስመለከተው አንድም ዳመና የሌለው ፍፁም ሰማያዊ ሆኖ ይታየኝ ነበር:: አይ ጦቢያ አገር እኮ ነው ከልቡ::

እና ይሄውላችሁ ሀይለኛ የሆነ የጠላ ሱስ ነበረብኝ ስንት ኪሎ ሜትር አቋርጠን ከሰፈር ልጆች ጋር, ያቺን ዳገቷን ቁልቁል ተንደርድረን ስናበቃ የኦሮሞዎቹ መንደር የረር ጭልጥ ብለን እንገባለን:: መቼም ዘመዶቼም አይደሉ ብቻ ኦሮምኛ በምናውቃት ስንተባተብ በሳቅ ይሞቱና ለጨዋታ አጠገባችን ይሰበሰባሉ:: ይወዱናል ከተማ የተገናኝን እንደሆነ ያኔ ገርጂ ኮንስትራክሽን ብቻ ስለነበረ ውሏችን እዛ ነውና ይሄንን ብሎኬት ከኛ ጋር እስኪበቃቸው አውርደው ሲጨርሱ ገርጂ ገበያ እህላቸውን ሸጠው እየዘፈኑ ሰፈራቸው ይከትማሉ:: ገርጂና የካ ሚካኤልም ታቦት ሲወጣ በጭፈራ መሬቱን ያንቀጠቅጡት ነበር::

ዘፈን ሲወዱ ለጉድ ነው:: የነሱን እርጎ የመሰለውን ጠላ ታዲያ ገልብጠን ገልብጠን ያን ዳገት እፍ ብለን እንወጣትና ጎርጊስ ጫካ ጋር ስንደርስ ትንፋሻችንን መለስ ለማድረግ ጫካዋ ውስጥ ገብተን አረፍ እንላለን:: ከዚያም ታክሲያችንን ይዘን ወደ ሰፈራችን እንመርሻለን::

ውይ የኔ ነገር የልጅቷን ነገር ትቼ የድሮ ትዝታ መጥቶ ብዙ ቀባጠርኩኝ:: እስቲ እንግዲህ ነብሷን ይማረው ብለን እንለፈዋ እንግዲህ ምን ይደረጋል:: :roll:
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby Gosa » Fri Jan 04, 2013 6:18 am

ስራ ፈት ስለ ገርጂ አካባቢ ብዙ የማውቀው ነገር የለም:: ግን ግልጽነትህን እና አተራረክህን ወድጄልሀለሁ::
የልጅቷ ጉዳይማ በጣም ያሳዝናል:: ይህንን ታሪክ ካነበብኩ ወዲህ አገር ቤት ስላሉት ህክምና መስጫ ተቋማት ብዙ ብዙ አሰብኩኝ:: አሁን ያለሁበት አገር ቢሆን የልጅቷ ሞት እንዲሁ የሚታለፍ ነገር አይሆንም ነበር:: ከማንኛውም ቀዶ ጥገና በኌላ እስከ ሶስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ቀዶ ጥገናው የተደረገለት ሰው ቢሞት ትልቅ ኢሹ ነበር የሚሆነው:: እሬሳውን ፖሊሶች ናቸው የሚወስዱት:: "coroner has to investigate the death of the patient " ባገራችን ደግሞ እንደዚህ አይነት ህግ እምብዛም የሚሰራ አይመስለኝም ከጽሁፉ እንደምናየው:: ወደ ጥልቅ ሜድካል ፕሮሲጀር ፕሮቶኮል ሳንገባ እላይ እላዩን ብቻ ብናይ.
ቀድሞ ነገር ምጥ አርቲፊሻሊ ኢንዲዩስድ ከሆነ የራሱ የሆነ ኮምፕሊኬሽኖች ስላሉት ወደ ቤት ከመመለስ ይልቅ እዚያው አስተኝተዋት የቅርብ ክትትል ማድረግ የሚገባቸው ነው የሚመስለኝ:: ሌላው ሰርጂካል ፕሮሲጀር የፈጸመው ሆስፒታል የተሟላ የአስቸኳይ(Emergency) ጊዜ ዕቃዎች በተለይ ፖርቴብል ኦክሲጂን ሲሊንደርስ የግድ ሊኖረው ይገባው ነበር ኦክሲጅን ያለው አምቡላንስ ከሌለው:: ነብስ ልትወጣ አፋፍ ላይ ቆማ ስለ ኦክስጂን ብዙም ላያውቁ የሚችሉትን ቤተሰቦቿን ገና በየሆስፒታሉ እየዞራችሁ ኦክሲጂን ያለውን መኪና ለምኑ ሊባሉ አይገባም ነበር:: የደም ትራስፊዩዥን ማድረግ የማይቻልበት ሀክም ቤት ውስጥ ቀድሞም ነገር ቀዶ ጥገና እንዴት እንደታሰበ አላውቅም:: ብዙ ጊዜ ለሲዜሪያን የሚሰጠው ማደንዘዣ ሎካል ወይንም ኢፒዱራል መሆን ሲገባው የተሰጣት የጀነራል(የሚያስተኛ) ማደንዘዣ ነገሮች እየተባባሱ መምጣታቸውን በጊዜ እንዳያውቁ ሚና ሳይጫወት አልቀረም ብዬ እገምታለሁ:: ቢሆንም ግን ነርሶቹም ሆኑ ዶክተሩ "ቫይታል ሳይንስ " የሚባሉት እንደ ደም ግፊት የልብ ምት እና በሴሎቻችን ውስጥ ያለው የኦክስጂን መጠን በየጊዜው እየለኩ አስፈላጊውን እርምጃ መወሰድ ነበረባቸው::
ሌላው ግርም ያለኝ ደግሞ የተክለሀይማኖት ሆስፒታል ሀኪም "ብዙ ደም ስለፈሰሳት አንሰራም: ሀላፊነቱን አንወስድም " የሚል መልስ ነው:: ልብ እንኳ መስራት ካቆመ በኌላ ሪሳስቴት ተደርጎ ሰው ወደ ህይወት ይመለሳል:: ህርራሄ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ኤትክሱም ይጎለዋል:: የተቻለህን ጥረህ ብትሞት ምን የሚያስጠይቀው ነገር አለና ነው በዚያ በጭንቅ ሰዐት እንደዚያ አይነት መልስ የሚመልሰው::
እግዜር ነብሷን እንኳ ያሳርፋት በስጋዋ በጣም የተሰቃየችዋን ምስኪን ልጅ::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby ስራ ፈት » Fri Jan 04, 2013 4:56 pm

ሰላም ነው ጎሳ, ከላይ የፃፍከው እውነት ለመናገር ምንም ስህተት የለውም:: ባገራችን አንድ ዶክተር ለስንት በሽተኛ እንደሚደርስ ባላውቀውም እጅግ ብዙ የዶክተር እጥረት እንዳለብን ግልፅ ነው::

አገሪቷ በሌላት ብር የምታስተምራቸው ልጆች ትምህርታቸውን ጨርሰው እነሱም በተራቸው አገር ያገለግላሉ ተብሎ ሲጠበቅ ክንፍ አውጥተው ይበራሉ:: ውጭ አገር ሄደው ታዲያ ታክሲ ይነዳሉ:: :lol: :lol:

ችግራችን ብትወጣው የማያልቅ ተራራ ነው:: እውነት ለመናገር ከኢትዮጵያ ዶክተሮች ይልቅ የባህል ሕክምና አዋቂዎች ለህዝቡ ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጣሉ::

ወረፋው ለጉድ ነው:: የማታየው የበሽታ አይነት የለም በጣም ካልባሰብህ ወይም ወላድ ካልሆነች በስተቀር የሚሄድ የለም:: አንድ ማሞ የሚባል ሰውዬ ነበር ወደ ሳሪስ አካባቢ ነው የሚኖረው የማያውቀው ሰው የለም እሱን መቼም:: እጅግ ውጤታማ የአገር ባህል ሕክምና አዋቂ ነው:: እነሱ እነሱ ትንሽ ህዝቡን ይደግፉታል እንጂ ዶክተሮቹማ ቢቸግር ነገር ናቸው:: እኔ የምለው አንድ ሆስፒታልም እንበለው ክሊኒክ ሲከፈት ማሟላት ያለበትን ነገሮች ካላሟላ እንዴት ይከፈታል :?:

አንዳንድ ግዜ አለ ከማለት የለም ብሎ የተሻለ ፍለጋ መሄድ ይሻላል::
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby Gosa » Sat Jan 05, 2013 2:05 pm

ሰላም ስራ ፈት!
እኔ የምለው አንድ ሆስፒታልም እንበለው ክሊኒክ ሲከፈት ማሟላት ያለበትን ነገሮች ካላሟላ እንዴት ይከፈታል :?:
ወንድሜ ስለ አገር ቤት የሆስፒታል ፈቃድ አሰጣጥ እና ሊሟሉ ስለሚገባቸው ቅድመ ሆኔታዎች የማውቀው ነገር ባይኖርም በበላይነት የሚቆጣጠረው የጤና ጥበቃ ሚ/ር አንድ የጤና አገልግሎት መስጫ ድርጅት ከሚሰጠው አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ መሳሪያ እንዳላቸው ሳይቆጣጠር የሚቀር አይመስለኝም:: ነገር ግን ካለው የአቅም እጥረት አኳያ ጥረታቸውን ብቻ አይቶ የሚያበረታታቸው እንጂ "ይህ ነገር ይጎድላችኌል" እያለ እንደ ሆቴል ቤቶቹ ማሸጉ ላይ የሚቸኩል አይመስለኝም:: እንግዲህ ሳንወድ ድህነታችንን ብሌም ልናደርግ ነው ማለት ነው :) የፌደራሉ ጤና ጥበቃም ብዙ ችግር እንዳለበት ዌብሳይቱ ላይ ያስቀመጠውን ቀንጭቤ አምጥቻለሁ:: http://www.moh.gov.et/English/Resources ... n(HSDP-III)%202005-2010.pdf
The health sector suffers from complex and lengthy procurement procedures resulting in
shortage and irregularity of the necessary drugs, supplies and equipment at the health facilities.
The inefficiency of the procurement system has also resulted in the poor absorption capacity of
funds allocated from HSDP partners. This has the overall effect of poor quality of service at the
grass roots level.
The other major challenges are poor quality control system; substandard storage facilities;
inefficient distribution; inadequate transportation; and poor inventory system. Weakness in
inspection system and poor collaboration with law enforcement bodies has led to wide use of
smuggled, counterfeiting and expired drugs which can have a negative impact on the health of
the population.
Health facilities also suffer from deficient, outdated, poorly maintained medical equipment that
hampers both the preventive (e.g. cold chain, insecticides, spray pumps…) and curative
interventions (e.g. medical equipment for Emergency Obstetric Care services, X-ray machines,
microscopes.). Therefore, the issue of management and supply of drugs, medical equipment and
supplies is among the strategic issues of HSDP-III.

ስለ የጤና ባለሙያዎችም ሆኑ ሌሎች ባለሙያዎች አገራቸውን ትተው መኮብለል የጻፍከው ትክክል ነው:: ብዙዎቻችን አገር ቤት እያለን ስለ ውጪው አለም የነበረን ግንዛቤ ከእውነታው የራቀ ስለሆነ ከዚያ አኳያ የነበራቸውን ስራ ትተው ተሰድደው አማራጭ ሲያጡ በውጪው አለም የማይመጥናቸውን ሲሰሩ ቢታዩ አያስገርመንም:: ማነው ዛሬ አገር ቤት ሄዶ የጉልበት ስራ እየሰራሁ ነው የምኖረው ብሎ ለጓደኞቹ ወይም ለቤተሰቦቹ ያለውን ሀቅ የሚናገረው? እዚህ ላይ ሁሉም ስደተኛ የኢኮኖሚ ነው ማለቴ አይደለም:: በተለያዩ ምክንያቶች የሚሰደዱ ባለሙያዎችም አይጠፉም:: አሁን አሁን እንኳ በመጠኑም ቢሆን የውጪው ሕይወት ጉዳይ እየተባነነበት ይመስለኛል ከድራማዎችም ከፊልሞችም አንደምናየው:: በተሳስሳተ መረጃ አገር ቤት የነበራቸውን ከፍተኛ ቦታ ጥለው በመሰደድ በውጪው አለም እንዳይሰቃዩ እኛም በተቻለን መጠን ሀቁን የመናገር ሀላፊነቱ ያለብን ይመስለኛል::
አንድ ማሞ የሚባል ሰውዬ ነበር ወደ ሳሪስ አካባቢ ነው የሚኖረው የማያውቀው ሰው የለም እሱን መቼም::እጅግ ውጤታማ የአገር ባህል ሕክምና አዋቂ ነው:: እነሱ እነሱ ትንሽ ህዝቡን ይደግፉታል

:D :D ከእንግዲህ ስሄድ አየዋለሁ እስቲ::


ስራ ፈት wrote:


ሰላም ነው ጎሳ, ከላይ የፃፍከው እውነት ለመናገር ምንም ስህተት የለውም:: ባገራችን አንድ ዶክተር ለስንት በሽተኛ እንደሚደርስ ባላውቀውም እጅግ ብዙ የዶክተር እጥረት እንዳለብን ግልፅ ነው::

አገሪቷ በሌላት ብር የምታስተምራቸው ልጆች ትምህርታቸውን ጨርሰው እነሱም በተራቸው አገር ያገለግላሉ ተብሎ ሲጠበቅ ክንፍ አውጥተው ይበራሉ:: ውጭ አገር ሄደው ታዲያ ታክሲ ይነዳሉ:: :lol: :lol:

ችግራችን ብትወጣው የማያልቅ ተራራ ነው:: እውነት ለመናገር ከኢትዮጵያ ዶክተሮች ይልቅ የባህል ሕክምና አዋቂዎች ለህዝቡ ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጣሉ::

ወረፋው ለጉድ ነው:: የማታየው የበሽታ አይነት የለም በጣም ካልባሰብህ ወይም ወላድ ካልሆነች በስተቀር የሚሄድ የለም:: አንድ ማሞ የሚባል ሰውዬ ነበር ወደ ሳሪስ አካባቢ ነው የሚኖረው የማያውቀው ሰው የለም እሱን መቼም:: እጅግ ውጤታማ የአገር ባህል ሕክምና አዋቂ ነው:: እነሱ እነሱ ትንሽ ህዝቡን ይደግፉታል እንጂ ዶክተሮቹማ ቢቸግር ነገር ናቸው:: እኔ የምለው አንድ ሆስፒታልም እንበለው ክሊኒክ ሲከፈት ማሟላት ያለበትን ነገሮች ካላሟላ እንዴት ይከፈታል :?:

አንዳንድ ግዜ አለ ከማለት የለም ብሎ የተሻለ ፍለጋ መሄድ ይሻላል::
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests