ትክክለኛ መረጃ ከዋናው ምንጭ ሲገኝ በጆርናሊዝም ቌንቌ ""ከፈረሱ አፍ የተገኘ ነው "" ይባላል:: ስለ ሴቶች ከሴቶች በላይ ማን ያውቃል..? እስኪ ሴት የሆናቹ ...ዋርካ ሜዶችን ( Warka mades women ን ) አይመለክትም:: :lol: እውነተኞቹ ሴቶች ሆይ...ከወንዶች የምትፈልጉት ምንድነው..ማለቴ ማፍቀራችሁን ወንድ እንዲያውቅላቹ ለማድረግ የምትሄዱበት መንገድ ምን ይመስላል ..?? እኛ በዚህ ረገድ ሲፈጥረን እንደናተ ስማርት አይደለንም ...በግልጽ ካላወጣጩሁት በስተቀር የምታደርጉት ሙኩራ ሁሉ አይገባንም:: የዛሬ አስር አመት አካባቢ አንዷ የምትወደኝ ልጅ እኔም የምወዳት ባንድ ምሽት በጣም ተቀራረብንና ሰውነቴ እየሞቀ ስለመጣ ልሳምሽ አልኴት:: በርጋታ አንደማትፈልግ ነገረችኝ:: አፍሬ ተውኩት:: ከጊዜ ወደ ጊዜ እይተራራቅን መጣን:: አመታት ካለፉ በኌላ አንድ ቀን ባንድ ፓርቲ ላይ ተገናንኝተን ሞቅ ብሎን የልብ ልባችንን መጫወት ጀመርን::
""ለምንድነው ያኔ ልሳምሽ ስልሽ ግን እምቢ ያአልሺኝ??"" አልኴት...."
"መጀመሪያ እንደምትወደኝ ስላልጠየከኝ ነዋ ...---- !! ""አለችኝ!!
ከኔ ለመለያየት የፈለገችበትና ስሜቷ ያልሆነውን ሰው ለማግባት ምክንያት መሆኔን አዝና ነገረችኝ:: አዘንኩ በራሴም በሷም:: ይሄ የሚያሳየው ቡዙዎቻችን ወንዶች አንዳንድ ቆንጆ ኴሊቲዎች ቢኖሩንም አንዳንድ ቦታ ግን ማቶዎች ነን:: ወይም እኔ ቢያንስ:: :D አትፍሩና ስሜታችሁን ግለጹ....
ሴናሪዮ ልስጥ አንድ ወንድ ትወዳላቹ አይናች ሁን ትጥሉበታላቹ እሱ ግን የናንተን ስሜት አልተረዳም:: በዝምታ ውስጥ ተሸብባቹ መቼም ማፍቀራችሁን ያውቅኛል ብላቹ ካሰባቹ በከባድ እንቅልፍ ላይ ናቹ:: : የናንተ መንገድ እንዴት ነው..ምን ይመስላል በምን ሁኔታ ወይም ታክቲክ ወይም ስትራተጂ ያንን ሰው መውደዳችሁን እንዲያውቅ ልታደርጉት ትችላላቹ ?? ስትራቴጂያቹ ምንድነው..?? :D ሳትፈሩ ፈታ ብላቹ በነጻነት ተወዩዩ:: በነገራችን ላይ ይሄ ቤተ የተከፈተው ክላስ ላላቸው ሴቶች ነው:: በየሰኮንዱ እንደ ዶሮ ""ቁቅ ቁቅ"" እያሉ ለሚያሽካኩት አይደለም:: :lol: እናም ይሄን ፕሮግራም ጸዳ ባለ መልኩ እኔ ክቡራን ሆስት አደርገዋለሁ:: :D መልካም ውይይት::