ሠላም ዋርካውያን
የፈለግነውን እንድንፅፍ ; ሐሳብችንን እንድንገልፅ የፈቀደችልን ዋርካ ምስጋና ይግባትና በሐሳብ መስማማት ; በሐሳብ መለያየት ; በሐሳብ መናቆር ; መፋጨት ወዘተ የተባረኩ እሴቶቻችንን ከዋርካም አልፈን በሀገር ; በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደርጃ እናሸጋግራቸው ::
የትዊተር ዩኒቨርስን ከተቀላቀልኩኝ አጭር ጊዜ ቢሆንም በወቅታዊ ዜናዎች ; በፖለቲካ ; በማህበራዊ ; በሳይንስ ; በጤና ; በቀልድ /ስላቅ ወዘተ ከኢትዮጵያውያኖችም አልፎ በዓለም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ጋር ሀሳብ የምንለዋወጥበትና የምንማማርበትን ጥሩ መድረክ ሆኖ አግኝቼዋለሁ :: ስለሆነም የትዊተር ዓለምን እንድንቀላቀልና የዋርካ ቤተሰብነታችንን ከነልዩነታችንና አብሮነታችን ወደአንድ ደረጃ ከፍ እንድናደርገው በግድ እጠይቃለሁ :lol: :lol:
ይከተሉኝ ...ልከተልዎ ......የትዊተር አድራሻዬ @DagmawiWalelign ነው :!:
ጥብቅ ማሳሰቢያ ......ዋርካ ያስለመደችን አንድ ገፅ ሙሉ ራፖር ፅሁፍና መሰዳደብ በትዊተር አይፈቀድም ......ችግር ነው ጎበዝ :wink: :lol: :lol: :lol: ....ትዊተርን ከመቀላቀልዎ በፊት ሀሳብዎን ቅልብጭ አድርገው መፃፍ ይለማመዱ :lol:
ይመችዎ .....ትዊተር ላይ እንገናኝ :D