ይድረስ እጅጉን ለማከብርህ ለወዳጄ ለባራምባራስ ያየህይራድ ልጅ ለልጅ ቅጣው ያየህይራድ
አባትህ እጅግ በጣም ወዳጄ ነበሩ : ፈሪሀ እግዚአብሄር ያደረባቸው ሰው የሚወዱና ቸር ሰው ነበሩ :: ዘር ከዛፉ አይርቅም እንዲሉ አንተም ይኸው እግዚአብሄር ባርኮህ ለሁላችን መገልገያ ይህንን ገጽ አቅርበህልን የያየህይራድ ዘር ይባረክ እያልን እየተጠቀምንበት ነው ::
አሁን ግን ችግር አለ :: ችግሩ ወዲህ ነው
እርኩስ መንፈስ ዋርካን በምች ከመታው ወዲህ በግል የተጣጣፍነውን ማየት በግል መጣጣፍ አልተቻልም :: በዚህ በለገስከን ገጥ ተዋውቄ የተዋዳጀኋት ፋጤ ጥሩ ጋደኛዬ ሁናለች :: አሁን ግን ከፋጤ ጋር መጣጣፍ ስላልቻልኩ : ሲከፋኝም ፋጤ የጣፈችልኝን እያወጣሁ ማንበብ ስለተቸገርኩ ይህንን እንድታስተካክልልኝ ልጄን እግርህ ላይ ወድቄ እማጠናለሁ
አደራህን ልጄ የፍቅር ነገር ነውና የፋጤን መልክቶች ሁሉንም እንዳሉ አድርገህ ቸል ሳትል ነገ ዛሬ ሳትል : ሳትውል ሳታድር ይቺን ነገር መላ ታበጅላት ዘንድ እለምናለሁ
እግዚአብሄር በቸርነቱ ይባርክህ
ጠጉርክን አለምልሞ ጎፈሬ ያድርግህ
አክባሪህ
ባላምባራስ ቢተው ተካልኝ ከሸንኮራ ሸዋ