ሰላም ለሁላችን ይሁን አብደናል ለሚሉትም ጭምር
ዋርካ ላይ ለሁሉ ከመመለስ ተቆጥቤ ያለኝን ሳካፍል ከሌሎችም ከጨዋዎችም ሆነ አብደናል ከሚሉ ለመታነጽ ጎራ እላለሁ::
እብድ ነኛ ባዩ የተሳተፍኩበትን መመልከትህና ማስታወስ ሳደንቅ ማወላገድና ማጣማምህን ግን አልወደድኩትም::ተመከር ያልከኝን ሁሉን በጎ ምክር ከማንም እቀበላለሁ አድናቆቱ ግን ይቅርብኝ::
ስለዘጋቢነትና ጋዜጠኘነት ጥርሴን ሳልነቅል የጀመርኩት የማላፍርበት ሙያ ነው::ዋርካ ላይ ጊዜ ስለሚወስድ አርታኢም ስለማያይልኝ እንዳለ ሀሳቤን አቀርባለሁ በተረፈ በስነቃልና ሚዲያ አንዳች ሳላጋንን ነው የምከትበው::
1.አንድ የትምህርት ቤት ጉዋደኝዬ ኢትዮጲያን የሰርግ ፎክ ዳንስ ጠይቆኝ ያቀረብኩትን እስኪ አንተ አቅርበውና ዋርካዊያን ይገምግሙት:-
ይሄ የማነው ቤት የደራ የኮራ የዚያ እብድ ነው ወይ የዚያ የቀብራራ..
ለባለቤትህ/ካለችህ ባልንጀሬ አይበልሽ ከፋ ሁሉ ያገባል በየወረፋ ባልንጀሬ ስሪ ጉልቻ ከንግዲህ ቀረ የእናት እንጎቻ..እኔ ያልኩትን አውቃለሁ አንተ ይህን ወደእንግሊዝኛ ከመለስክ በሁዋላ አቀርበዋለሁ::መቸስ የእኛ የጥቁሮች ነገር አንድን ጥሩ ጅምር አንሞክርም የሚሞክርን ማበረታታ ሳይሆን ማዋከብ ስራችን መሆኑ ከዚህ ቀደም እንዲህ አባባሎች ትርጉም ላይ የዋርካ ጨዋዎች ተስማተውበታል::ይህን አይነቱን ውርስ ትርጉም በሚገባ የሞከረች የዋርካዋ እቴጌይቱና ዋልጌ ቢሆንም ወያኔው ዳግማዊ ነበሩ::
2. መቸነው ጋዜጠኛ ተመስገንን አስተማርኩ ያልኩት?ያኔ ወያኔ ነጻ ፕሬስ ብሎ ልባችንን ሲያማልል በተከፈቱ ብዙ አምዶች ተሳትፌ ተባባሪ ነበርኩ::ለአማተር ጋዜጠኞች የወያኔን አፈና ሸሽተን በካቴድራል ት/ቤት ያደረግሁ አስተዋጽኦን ከማህበሩ መሪ ጠይቅ::ዲጎኔ በብስራተ ወንጌል ተማሪ ሳለ አዋቂ ጋዜጠኞች ውስጥ በህይወት ያሉ አቶ ሙሉጌታ ሉሌና ድንቅ ጋዜጠኞች ደራሲያን ብርሀኑ ዘሪሁን አማረ ማሞ ሽልማት ሙገሳ እርምት ማግኘቴን ለጉራ ሳይሆን ለሀቅ እጠቅሳለሁ::
ወያኔ ሲገባ አማተር ጋዜጠኛ ማህበር ብለው ያሰለጠናቸው ዛሬ የት ናቸው ተመስገን ወይ ጉዋደኞቹን አጠያይቅ::
ስለእድሜ አክብሮቱ የዋርካ ደናቁርት አይገባቸውም እንጂ እድሜ ጸጋ ነው በሰለጠኑሀገ ሮች ለመሪነት ብስለት ይመረጣል ታዲያ እንደአጼው መጃጀት አይደለም::ዲጎኔ ሽማግሌ አደለም በታደለው ጸጋ ከእድሜው በላይ ታሪኮች የሚከትብ በማንኛውም ታሪክ ኮርስ ባለ ኤ ነውና!
እስኪ የአምዱ ለዛ ይጠበቅ ለአራስ ተብዬ የቀረበን ወደ እንግሊዝኛ መልስና እኔን ለመተቸቱ በርታ ያለበለዚያ እኔ ላይ አፍህን ማጣበቁን አቁም!
ዲጎኔ ሞረቴ የወቅቱ የወያኔ ተለጣፊ ደራሲያን ማህበር መሪ 'ዳግላስ ጴጥሮስ' የጥንት ጉዋደኛ
� wrote:በቅድምያ ለ Recho ማርያም በሽልም ታውጣሽ ካልኩ በሁዋላ...
(አድናቅት.....ይልቅስ ወንድሜ(ምናልባትም አባቴ ወይአያቴ ወይ ቅድማያቴ.... ተመከር... እውን አንተ ተመስገን ደሳለኝን አስተምረሀል?
በ መጨረሻም ምስጋና: ታስታውሳለህ አንዴ ለ ስራ ባልደረቦችህ የ አማርኛ ሰርግ ተረት(አባባል) እንዴት እንደተረጎምክላቸው