ሰላም በቅድምያ....
ተጠፋፋን አይደል? ግማሹ..ወደሀገር ቤት ሙቭ አርጎ ወስላ የሆነ ቢዝነስ ኢንቨስትመንት ምናምን ጀምሮዋል....እኔም ለየት ያለ ካውንተር ኢንቨስትመንት ጀምሬ ሳይሳካልኝ እንደማንችስተሩ አሰልጣኝ... ደቪድ ሞዬስ ውሀ ውስጥ የገባ ጥጥ መስዬ ከች አልኩላቹ ..ወዴት? ወደምዬ አሜሪካ ነዋ!!...
እናም እንደተመለስኩስ ሰሞን..በፊት እማዘወትራት ስታርበክስ አድፍጬ ቡና ልላጋ..ቸስ ስል... በስሱ የሚያቀኝ ተራቢ የሆነ አበሻ የፓርኪንግ ጋራጅ ማናጀር.." እንዴ አንተ ነክ!?...እኔ እኮ ቅድም.. እንዲ ጥቁርቁር ያለ አበሻ ሳይ ግዜ አዲስ መጤ ምናምን ነው ብዬ በቆረጣ አይቼ አለፍኩክ..." ሲለኝ ከማማስለው ጥቁር ቡና ... ቀና ብዬ ሀገርቤት ያው ለኢክዌተር ቅርብ ስለሆንን ይሆናላ..እንደወም ቦርጬን ያጠፋልኝ ይሄ ግሎባል ዋርሚንግ የሚሉት ንዳድ ሳይሆን አይቀርም እኔ በጣም ነው ምደግፈው እሱን ነገር ብዬ ፈገገ አሰኘሁትና ለሰላምታ ተቃቀፍን....
ገና ሰላም ሲለኝ ነጭ ዋየርለስ ኢር-ፎን አድርጎ ፓልቶክ ሲቪሊቲ ሩም የአባመላን መሳጭ ፖለቲካ አዘል ጨዋታዎች የሚሰማ የመሰለን ለካስ ተሸውጃለሁ!! አፕል ኢርፎን ነው ብዬ የደመደምኩት ለካንስ...አቶዬ ጆሮዎቹን ሳይፈናፍን ሽበት ጥቅጥቅ ብሎ በቅሎበ ነው...!! ያሳዝናል መላው የአበሻ ህዝብ ጆሮና አፍንጫው ውስጥ ሽበት እስኪበቅልበት ድረስ ምንድነው የሚጠብቀው?
ባይዘዌይ ስለ-አልተሳካው የሀገርቤት ካውንተር-ኢንቨስትመንቴ ከነገወድያ ተመልሼ አጫውታቹሀለሁ...!! አሁን ስቶር ሄጄ ጥቁር የጸጉር ቀለም ልግዛ...ማለቴ ለአፍንጫዬ ሽበት!
... ከመሰናበቴ በፊት ሰላም የሞት ሞታቹን ዋርካን ነፍስ ለመዝራት ውርጭት ውርጭት ለምትሉ ቀደምት ታጋዮች....ሪቾ እና ጌታ...እንዲሁም ሪንካርኔት አርጋቹ የተከሰታቹ እንደ ገልብጤ አይነቱ..እንዲሁም...አግብቶ ደብል መንታ ልጆች አስወልዶዋል ተብሎ የሚታማው ውቃው ( የዮብ ትግስት ይልሀል እንዲ ነው) .... ያ ሼባውስ? ቫያግራ ልቡን አቁማው ይሆን?... ብቻ ስማቹ ያልተጠቀቻቹም.... ከይፈክ ብያለሁ!!