ሰላም ..ሽበታሞች

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ሰላም ..ሽበታሞች

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Tue Mar 18, 2014 2:46 pm

ሰላም በቅድምያ....
ተጠፋፋን አይደል? ግማሹ..ወደሀገር ቤት ሙቭ አርጎ ወስላ የሆነ ቢዝነስ ኢንቨስትመንት ምናምን ጀምሮዋል....እኔም ለየት ያለ ካውንተር ኢንቨስትመንት ጀምሬ ሳይሳካልኝ እንደማንችስተሩ አሰልጣኝ... ደቪድ ሞዬስ ውሀ ውስጥ የገባ ጥጥ መስዬ ከች አልኩላቹ ..ወዴት? ወደምዬ አሜሪካ ነዋ!!...
እናም እንደተመለስኩስ ሰሞን..በፊት እማዘወትራት ስታርበክስ አድፍጬ ቡና ልላጋ..ቸስ ስል... በስሱ የሚያቀኝ ተራቢ የሆነ አበሻ የፓርኪንግ ጋራጅ ማናጀር.." እንዴ አንተ ነክ!?...እኔ እኮ ቅድም.. እንዲ ጥቁርቁር ያለ አበሻ ሳይ ግዜ አዲስ መጤ ምናምን ነው ብዬ በቆረጣ አይቼ አለፍኩክ..." ሲለኝ ከማማስለው ጥቁር ቡና ... ቀና ብዬ ሀገርቤት ያው ለኢክዌተር ቅርብ ስለሆንን ይሆናላ..እንደወም ቦርጬን ያጠፋልኝ ይሄ ግሎባል ዋርሚንግ የሚሉት ንዳድ ሳይሆን አይቀርም እኔ በጣም ነው ምደግፈው እሱን ነገር ብዬ ፈገገ አሰኘሁትና ለሰላምታ ተቃቀፍን....
ገና ሰላም ሲለኝ ነጭ ዋየርለስ ኢር-ፎን አድርጎ ፓልቶክ ሲቪሊቲ ሩም የአባመላን መሳጭ ፖለቲካ አዘል ጨዋታዎች የሚሰማ የመሰለን ለካስ ተሸውጃለሁ!! አፕል ኢርፎን ነው ብዬ የደመደምኩት ለካንስ...አቶዬ ጆሮዎቹን ሳይፈናፍን ሽበት ጥቅጥቅ ብሎ በቅሎበ ነው...!! ያሳዝናል መላው የአበሻ ህዝብ ጆሮና አፍንጫው ውስጥ ሽበት እስኪበቅልበት ድረስ ምንድነው የሚጠብቀው?

ባይዘዌይ ስለ-አልተሳካው የሀገርቤት ካውንተር-ኢንቨስትመንቴ ከነገወድያ ተመልሼ አጫውታቹሀለሁ...!! አሁን ስቶር ሄጄ ጥቁር የጸጉር ቀለም ልግዛ...ማለቴ ለአፍንጫዬ ሽበት!

... ከመሰናበቴ በፊት ሰላም የሞት ሞታቹን ዋርካን ነፍስ ለመዝራት ውርጭት ውርጭት ለምትሉ ቀደምት ታጋዮች....ሪቾ እና ጌታ...እንዲሁም ሪንካርኔት አርጋቹ የተከሰታቹ እንደ ገልብጤ አይነቱ..እንዲሁም...አግብቶ ደብል መንታ ልጆች አስወልዶዋል ተብሎ የሚታማው ውቃው ( የዮብ ትግስት ይልሀል እንዲ ነው) .... ያ ሼባውስ? ቫያግራ ልቡን አቁማው ይሆን?... ብቻ ስማቹ ያልተጠቀቻቹም.... ከይፈክ ብያለሁ!!
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ጌታ » Tue Mar 18, 2014 3:47 pm

ዘጌ ዘጋምባው ያልሞተ ሰውና ዝንጅብል ነጋዴ ዞሮ ይገናኛል ማለት ይኸው ነው!! ኧረ እንኳን ሰላም ተመለስክ:: አንተ ደህና ሁን እንጂ ብር እንደሆነ ነገ ይመጣል:: እስክትደራጅ ብድር ከፈለክ አሳውቀኝ :lol: :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ገልብጤ » Fri Mar 21, 2014 7:45 pm

ዌልካም ባክ
ዘጌ_ዘጋምባው
ኢኩዌተር ያከሳው

በላ ያፍናጫህን እና የጆሮህን ሽበት ቀባ ቀባ አድርግና ቀደዳውን ቀጽልልን
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ማማዬ » Sun Mar 23, 2014 1:36 pm

ዘጌ-ዘጋምባው በጣም ደስ ይላል መምጣትህ በጣም ነው የምታዝናናኝ ::
"A journey of a thousand miles begins with a single step"
ማማዬ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Wed Apr 03, 2013 12:17 pm
Location: Emamaye gare

Postby ገልብጤ » Sun Mar 23, 2014 2:03 pm

አዳሜ የሰው አገር ቋንቋ እንደ ሰመን ቁምጣ አጥሮሽ ስትላላጭ እያየሁ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: አልኩ

አሁንም የዘጌውን ኒክ ኔም አስተካክለሽ መጣፍ ምነው አቃተሽ

ዘጋንባው .......................እላለሁ ብለሽ
ዘጋምባው......................ብለሽው አረፍሽ

መታሰቢያነቱ እንጉ አጥሯቸው ..ዋት..ዋትን ለሚደጋግሙት ትሁንልኝ

ገልብጤ የ24ቱ ልጅ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ማማዬ » Mon Mar 24, 2014 7:14 am

ገልብጤ የቅናት ነው ያስመሰለብህ !!!
"A journey of a thousand miles begins with a single step"
ማማዬ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Wed Apr 03, 2013 12:17 pm
Location: Emamaye gare

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sun May 04, 2014 6:55 pm

ጌትሽ...ገልቤው...እንዲሁም ማምዬ ማማዬ,.....;ልማታዊ ሰላምታዬን ተቀበሉኝ...

ገልቤውና ማማዬ የዋርካ ጉምቱዎች እንደመሆናቹ መጠን በተገኘው አጋጣሚ ተቃቅፎ ቦምብባርሊ እንዳለው....ፍቅር እንደመስራት ጦርነት ትተዋወጃላቹ? ....

በቀደም የጀመርኩት ታሪክ ባክህ ልጅቷ ማለተም ባለታኳ አንብባው...ሀሪአፕ ብላኝ እጄን ወደላል አስብላኝ እስካሁን እንዳስቦካችኝ ነውና በቃ ለሌላ ታይም ተላልፎዋል....

እስኪ ሌላ ፖስቶች እየሄድኩ የዋርካ ልምዴን በመጠቀም ላማክር/ አስተያየት ልስጥ...
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ጌታ » Mon May 05, 2014 6:23 pm

ገልብጤ wrote:አዳሜ የሰው አገር ቋንቋ እንደ ሰመን ቁምጣ አጥሮሽ ስትላላጭ እያየሁ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: አልኩ

አሁንም የዘጌውን ኒክ ኔም አስተካክለሽ መጣፍ ምነው አቃተሽ

ዘጋንባው .......................እላለሁ ብለሽ
ዘጋምባው......................ብለሽው አረፍሽ

መታሰቢያነቱ እንጉ አጥሯቸው ..ዋት..ዋትን ለሚደጋግሙት ትሁንልኝ

ገልብጤ የ24ቱ ልጅ


ዘጌው እንዲህ ሲመችህ ብቅ ማለት ይልመድብህ::

ገልቡ ደግሞ በዘጌው ስፔሊንግ ወርፈሽናል ለካ? እናርማለን ለወደፊቱ
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests