ቢሰክርም ለሚስቱ ታማኝ የሆነ ባል...ሎል

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ቢሰክርም ለሚስቱ ታማኝ የሆነ ባል...ሎል

Postby ክቡራን » Wed Jun 28, 2017 1:02 am

አንድ ጊዜ ባል ሚስቱን ሸዉዶ ጭፈራ ቤት ይገባላችኋል…ሲጋት ያመሽና ስክር ጥምብዝብዝ ብሎ ይወጣል..በጣም ስለመሸ እንደምንም እየተንገዳገደ ቤቱ ይደርሳል፡፡ከዛ እሱም እኔም ተራኪዉም አናስታዉስም፡፡
በሚቀጠለዉ ቀን ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነሳ ሃንጎቨር ጭንቅላቱን ሊያፈነዳዉ ደርሷል፡ እራሱን ያገኘዉ ግን አልጋዉ ላይ በትክክል አንሶላዉ ዉስጥ ገብቶ ተኝቶ ነዉ፡፡ገረመዉ…በቃ ሚስቴ ገደለችኝ እንደዛ ሰክሬማ አይታኝ መቼም ቢሆን አታናግረኝም እያለ ከራሱ ጋር ንትርክ ገጥሟል፡፡እንደምንም ተነስቶ ዞር ሲል አልጋዉ ጎን አስፕሪንና ዉሃ በብርጭቆ ተቀድቶ ተቀምጦለታል፡፡ግራ ገባዉ…እንዴ ሚስቴ ናት ይህን ያደረገችዉ ! እንዴት ኣላከበደችም ብሎ ተገረመ፡፡አስፕሪኑን ከዋጠ በኋላ ወደጠረጴዛዉ እየተጎተተ ሄደ በሚስቱ የተፃፈ አጭር መልእክት እንዲህ ይላል ‹የኔ ማር ቁርስ ስለደረሰ የታችኛዉ ክፍል ዉረድና ከልጅህ ጋር ቀማምስ…ዋ ሳትበላ እንዳትሄድ!›
ባል አሁን ተደነጋገረ…እነዴት ያለች ሚስት ነዉ ያገባሁት እያለ ወደታችኛዉ ክፍል ወረደ፡፡ የስምንት አመት ልጁ ቁርስ እየበላ ነበር…ልጁን ግንባሩ ላይ ሳም አድርጎ ‹ትላንት ቤት ሰክሬ ስገባ እናትህ ምን አለች? መቼም ንዴቷን መቆጣጠር እንደማትችል ይገባኛል › አለዉ፡፡
‹ኸረ አባዬ እሷ እንኳን ልትበሳጭ ሳቅ በሳቅ ሆና ነበረ…በሩን ስታንጓጓዉ ከአልጋዋ ብድግ ብላ በሩን ከፍታ አንተን እንደኅፃን ልጅ ተሸክማህ ማለት ይቻላል አልጋ ላይ አስተኛችህ፡፡ከዛ ልብስህን ልታወልቅልህ ስትሞክር ምን አንዳልክ ታዉቃለህ?›
‹ምን አልኩ ? › አለ አባት ተደናግሮ
‹ አንቺ ሴትዮ እንዳትነኪኝ…እኔ ባለትዳር ነኝ በፈጠረሽ አትንኪኝ አልካት!›ሎል
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8932
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests