ሀሁ ለሉ wrote:ቁምነገርን እንደቀልድ ቀልድን እንደ አሽሙር እውነትን ርክሰት የሳቀን ደስተኛ የለበሰን አዋቂ የነዳን ባለሀብት ያጣን አላዋቂ የሰማሽ ባለጌ የረዳሽ እኩያሽ የመከረሽ ክፉ ሲሆን የኔ ነው የምትይው የሌለሽ ያለሽን ያለየሽ ማወቅ የተሳነሽ ሙሉ ነኝ የማትይ ጉድለትሽ ትምከህትሽ እውቀትሽ እህትሽ እህት እውቀት ሆና በለንደን ከተማ ማህበር እየዘከርሽ ተስካር እያወጣሽ ፅዋ እየጠጣሽ ኑሮሽ ላይ መቆመር እዚ ስትበይ እዛ ለማስመለስ ትርኪምርኪ መፍጠር ውስጥ ልብስ አልብሰሽ እንግዳነው ብለሽ ሶፋ ላይ ማሸለብ ምንድን ነው ትርጉሙ ሰጣቹ ትርጉሙ ይህ ነው እድገታቹ ወግና ባህላቹ ሴት መባላቹ ይህ ነው ክብራቹ እንኳን አገኛቹ የቅርብ ዘመዳቹ...........ዘመድ ስል ትዝ አለኝ ዘመድ ነበራቹ ዘመናይ ሳትሆኑ ሺሻ ሳትጀምሩ ታቱ ሳትባንኑ መድረክ ላይ ሳትወጡ ክለብ ውስጥ ሳትሰምጡ ጭስን ሳትቧክሙ ዘመድ ነበር ያኔ? ሴት የፇታ መገለጯ ብቻ ሳይሆን ሴት ከጥበብ በላይ ረቂቅ የእውቀት ማህደር የብርሃን መነሻ የመፍትሄዋች ሁሉ ክብር ናት ሁሉም ቧታ ግን የፇታ ሴት የሆኑ ይገኛሉ ክብር ሴታዊ ወግ ላላቸው......አዋ ሰለቸኝ የስልጣኔሽ ቲዋሪ የምጥቀትሽ ደረጃ በአፍታ ከጋሪ ወደ ኳንኳርድ ከጥለት ወደጉቺ ከአሩሲ ወደ አርሰናል ሀይበሪ አካባቢ መገኘትሽ ወዳጇችሽ መጤ ጂጄዋች በጩህት ተወልደው በዋይታ ያደጉ ጥበብ የነሳቸው ማወቅ የራቃቸው :: ስልጣኔ ራስን ከመካድ ከራስ ጋር መጣላት ይጀምራል የሚል የጅል ፈሊጥ አይገባኝም ለውጥ የህይወት ሂደት ነው መሰልጠን ወደዋላ መሮጥ ማለት ሳይሆን ወደፊት በማስተዋል መራመድ ነው ባይ ነኝ ሂሳዊ ወይም አሉታዊ አይደለውም ይልቁንም የእናንተ ደቀመዝሙር እንጂ:: ፍፅምና ስላለኝ ይህን ባላልኩ ነበር ስህተትና ብልሹነት እኛም ጋር አለ ስንሳሳት እናፍራለን እንንበረከካለን ግን አንክድም አንተባይም ሀሁ ለሉ እንላለን ........................ ሀሁ ለሉ 08/09/2017
Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር
Users browsing this forum: Google [Bot] and 7 guests