ጥላቻ ሲወፍር

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ጥላቻ ሲወፍር

Postby ሀሁ ለሉ » Sat Feb 03, 2018 9:12 am

ቁምነገርን እንደቀልድ ቀልድን እንደ አሽሙር እውነትን ርክሰት የሳቀን ደስተኛ የለበሰን አዋቂ የነዳን ባለሀብት ያጣን አላዋቂ የሰማሽ ባለጌ የረዳሽ እኩያሽ የመከረሽ ክፉ ሲሆን የኔ ነው የምትይው የሌለሽ ያለሽን ያለየሽ ማወቅ የተሳነሽ ሙሉ ነኝ የማትይ ጉድለትሽ ትምከህትሽ እውቀትሽ እህትሽ እህት እውቀት ሆና በለንደን ከተማ ማህበር እየዘከርሽ ተስካር እያወጣሽ ፅዋ እየጠጣሽ ኑሮሽ ላይ መቆመር እዚ ስትበይ እዛ ለማስመለስ ትርኪምርኪ መፍጠር ውስጥ ልብስ አልብሰሽ እንግዳነው ብለሽ ሶፋ ላይ ማሸለብ ምንድን ነው ትርጉሙ ሰጣቹ ትርጉሙ ይህ ነው እድገታቹ ወግና ባህላቹ ሴት መባላቹ ይህ ነው ክብራቹ እንኳን አገኛቹ የቅርብ ዘመዳቹ...........ዘመድ ስል ትዝ አለኝ ዘመድ ነበራቹ ዘመናይ ሳትሆኑ ሺሻ ሳትጀምሩ ታቱ ሳትባንኑ መድረክ ላይ ሳትወጡ ክለብ ውስጥ ሳትሰምጡ ጭስን ሳትቧክሙ ዘመድ ነበር ያኔ? ሴት የፇታ መገለጯ ብቻ ሳይሆን ሴት ከጥበብ በላይ ረቂቅ የእውቀት ማህደር የብርሃን መነሻ የመፍትሄዋች ሁሉ ክብር ናት ሁሉም ቧታ ግን የፇታ ሴት የሆኑ ይገኛሉ ክብር ሴታዊ ወግ ላላቸው......አዋ ሰለቸኝ የስልጣኔሽ ቲዋሪ የምጥቀትሽ ደረጃ በአፍታ ከጋሪ ወደ ኳንኳርድ ከጥለት ወደጉቺ ከአሩሲ ወደ አርሰናል ሀይበሪ አካባቢ መገኘትሽ ወዳጇችሽ መጤ ጂጄዋች በጩህት ተወልደው በዋይታ ያደጉ ጥበብ የነሳቸው ማወቅ የራቃቸው :: ስልጣኔ ራስን ከመካድ ከራስ ጋር መጣላት ይጀምራል የሚል የጅል ፈሊጥ አይገባኝም ለውጥ የህይወት ሂደት ነው መሰልጠን ወደዋላ መሮጥ ማለት ሳይሆን ወደፊት በማስተዋል መራመድ ነው ባይ ነኝ ሂሳዊ ወይም አሉታዊ አይደለውም ይልቁንም የእናንተ ደቀመዝሙር እንጂ:: ፍፅምና ስላለኝ ይህን ባላልኩ ነበር ስህተትና ብልሹነት እኛም ጋር አለ ስንሳሳት እናፍራለን እንንበረከካለን ግን አንክድም አንተባይም ሀሁ ለሉ እንላለን ........................ ሀሁ ለሉ 08/09/2017
ሀሁ ለሉ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Sat Jan 13, 2007 10:33 am
Location: london

Re: ጥላቻ ሲወፍር

Postby ሾተል » Sun Feb 04, 2018 12:10 am

ሀሁ ለሉ wrote:ቁምነገርን እንደቀልድ ቀልድን እንደ አሽሙር እውነትን ርክሰት የሳቀን ደስተኛ የለበሰን አዋቂ የነዳን ባለሀብት ያጣን አላዋቂ የሰማሽ ባለጌ የረዳሽ እኩያሽ የመከረሽ ክፉ ሲሆን የኔ ነው የምትይው የሌለሽ ያለሽን ያለየሽ ማወቅ የተሳነሽ ሙሉ ነኝ የማትይ ጉድለትሽ ትምከህትሽ እውቀትሽ እህትሽ እህት እውቀት ሆና በለንደን ከተማ ማህበር እየዘከርሽ ተስካር እያወጣሽ ፅዋ እየጠጣሽ ኑሮሽ ላይ መቆመር እዚ ስትበይ እዛ ለማስመለስ ትርኪምርኪ መፍጠር ውስጥ ልብስ አልብሰሽ እንግዳነው ብለሽ ሶፋ ላይ ማሸለብ ምንድን ነው ትርጉሙ ሰጣቹ ትርጉሙ ይህ ነው እድገታቹ ወግና ባህላቹ ሴት መባላቹ ይህ ነው ክብራቹ እንኳን አገኛቹ የቅርብ ዘመዳቹ...........ዘመድ ስል ትዝ አለኝ ዘመድ ነበራቹ ዘመናይ ሳትሆኑ ሺሻ ሳትጀምሩ ታቱ ሳትባንኑ መድረክ ላይ ሳትወጡ ክለብ ውስጥ ሳትሰምጡ ጭስን ሳትቧክሙ ዘመድ ነበር ያኔ? ሴት የፇታ መገለጯ ብቻ ሳይሆን ሴት ከጥበብ በላይ ረቂቅ የእውቀት ማህደር የብርሃን መነሻ የመፍትሄዋች ሁሉ ክብር ናት ሁሉም ቧታ ግን የፇታ ሴት የሆኑ ይገኛሉ ክብር ሴታዊ ወግ ላላቸው......አዋ ሰለቸኝ የስልጣኔሽ ቲዋሪ የምጥቀትሽ ደረጃ በአፍታ ከጋሪ ወደ ኳንኳርድ ከጥለት ወደጉቺ ከአሩሲ ወደ አርሰናል ሀይበሪ አካባቢ መገኘትሽ ወዳጇችሽ መጤ ጂጄዋች በጩህት ተወልደው በዋይታ ያደጉ ጥበብ የነሳቸው ማወቅ የራቃቸው :: ስልጣኔ ራስን ከመካድ ከራስ ጋር መጣላት ይጀምራል የሚል የጅል ፈሊጥ አይገባኝም ለውጥ የህይወት ሂደት ነው መሰልጠን ወደዋላ መሮጥ ማለት ሳይሆን ወደፊት በማስተዋል መራመድ ነው ባይ ነኝ ሂሳዊ ወይም አሉታዊ አይደለውም ይልቁንም የእናንተ ደቀመዝሙር እንጂ:: ፍፅምና ስላለኝ ይህን ባላልኩ ነበር ስህተትና ብልሹነት እኛም ጋር አለ ስንሳሳት እናፍራለን እንንበረከካለን ግን አንክድም አንተባይም ሀሁ ለሉ እንላለን ........................ ሀሁ ለሉ 08/09/2017


አቶ/ወይዘሮ ፊደል ወይም ሀሁ ለሉ..ጥሁፋችሁ ማለፍያ ቢሆንም ግና ግጥምኛ ነው ወይስ ስድ ንባብኛ?እንዴው በክብርነታችን በምናነብበት ሰአት አንዴ እንደግጥም ጭልጥ አድርጎ ጥሁፋችሁ ሊወስደን ይሞክርና እሰይ ግጥም ነው ስንል ወደ ስድ ንባብ ልቀየር ብሎ ትንሽ አጭበረበረንና ነው ወሰኑ ከምኑ እንደሆነ እንድታስረዱን የተማጠንነው እንጂ መልክቱ የቃላት ውልደቶቹ ትንሽ መስተካከል ቢሻቸውም ማለፍያ ሆኖ አግኝተነዋል።

ሾተል ነን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests