እኛም አለን እናንተስ ደህና ናችሁ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

እኛም አለን እናንተስ ደህና ናችሁ

Postby ፋኖፋኖ » Fri Jul 20, 2018 1:33 am

አማን ናችሁ ወይ ብለን ስንጠይቅ በታላቅ ናፍቆትና ፍቅር ነው
እኛ አለን አንድየ ይክበር ይመስገን
እስኪ ፊደል መርገጡን በደንብ ከተያያዝነው በኅውላ ሾተልን ትንሽ ሾጥሾጥ አድርገን ልናስለቅስ አላማ አለን
ሾተል ወያነ መሞቱን ሰምቻለሁ ጥናቱን ይስጥህ
ለማንኛውም አንተም በክብርነታችን ተናፍቀሃል ደስ ይበልህ
ኢትዮጵያውነት በመወለድ በዜግነትና በጸጋ የወረስኩት ህያው ሀብት ንብረት ቅርስ ማንነት ነው : ሰጭም ቀሚም የለብኝ
ፋኖፋኖ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 936
Joined: Wed Nov 08, 2006 10:39 am

Re: እኛም አለን እናንተስ ደህና ናችሁ

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Jul 20, 2018 4:21 am

ፋኖ የጥንት ሰው ሰላምህን ተቀብለናል፡፡ ወያኔ ገና አልሞተም ጣር ላይ ነው፡፡ ምንም እንደማይተርፍ አዋላጁ ሄርማን ኮህን በትዊተር ነግሮናል፡፡ ለማንኛውም አጨብጫቢዎቹና ተለጣፊዎቹ አፈር መስለው በየጥጉ ኦሮሞን ከአማራ ለማባላት አንዴ በዘፈኑ ሌላ ጊዜ ደግሞ በአዲስ ፊንፊኔ ሰበብ የአልሞት ባይ ተጋዳይነት መርዝ ባለቀ ሰእት ይረጫሉና ጠንቀቅ ብለን ጋሼ ደቤ እንዳለው በህዝባዊ በትር እንዝጋቸው!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: እኛም አለን እናንተስ ደህና ናችሁ

Postby ሾተል » Wed Aug 15, 2018 11:40 am

ፋኖፋኖ
አማን ናችሁ ወይ ብለን ስንጠይቅ በታላቅ ናፍቆትና ፍቅር ነው

ውዳችን የጥንቱ የሰገሌ ጊዜው ፈንፋኖ።የሰማይ እርቀቱ…የኩዋክብት ብዛቱ..ጉደኛው አያልቅበት ናሳ ጸሃይ ድረስ መንኮራኩር መላኩ..እግዜር የላከው ዶክተር አብይ እኛን ማስደሰቱ…ምኑ ቅጡ እኝ ደህና ነን ክብሩ ይስፋ።እናንተም ደህና መሆናችሁን ስላወሳችሁን በደህንነታችሁ የደስታ ጮቤ ስንረግጥ የሽማግሌ ወገብ ሆነና ሁለት ግራ እግራችን ቢጠልፈን እንቦጭ..ጧ እርግፍ ብለን ብንዘረርም... ስላየናችሁ ደስ ብሎናል ለማለት ነው።እረ ለመሆኑ አገባችሁ?ወለዳችሁ ወይስ አሁንም አጥር በመዝለል ላይ ናችሁ?አሁንማ እንደናንተ ላለ የአጤ ልብነ ድንግል ጊዜ ውልዶች ሲባል ቫያግራ በተለያየ ከለርና ግራም ቅርጹን እያሳመረ እየመጣላችሁ ነው የሰው ችኮች አለቀላችወ።ያው በቫያግራ ብዛት ልባችሁ እንደ ባግዳድ ቦንብ ፈንድቶ እላዩዋ ላይ ላሽ እስክትሉ ድረስ...ዋጡ...እኛ እዛ ውስጥ የለንበትም።እድሜ ለአበሻ ቅመማ ቅመም።ኮሰረት…ድንብላል…ኮረሪማ…ነጭ በሃር ዛፍ..ቁሩንፉድ…ድኝ..ስናፍጭ…ዳማ ከሴ…በሶቢላ..አሻሮ…ነጭ ሽንኩርት..ወዘተ አለልን።እሱን ቆልተን አምሰን ወቅተንና ፈጭተን ለማኝ አሩን ሳያራ በየቀኑ ምግብ በሆዳችን ሳይገባ ያገር ቤት ጋቢ ተከናንበን እሱን እንታጠናታለን እንጂ ፈረንጃ የሰራውን ኪኒና ለ ባለጌ ነገር አንጠቀማት።ሞኛቸውን ይፈልጉ።እና ካገባችሁም ከወለዳችሁም ንገሩንና እንደሰት።እንኩዋን ደስ አላችሁ እንበል።የምን መንዘላዘል ነው?እኛ ብንዘላዘል ያምርብናል።ገና ዋርካ ስትከፈት ሳንወለድ ልትዘጋ ስትል ጎረመስን…ተዘግታ ስትከፈት ይሄው እንዳለን አለን።
እኛ አለን አንድየ ይክበር ይመስገን

አሜን!
እስኪ ፊደል መርገጡን በደንብ ከተያያዝነው በኅውላ ሾተልን ትንሽ ሾጥሾጥ አድርገን ልናስለቅስ አላማ አለን

ሞክሩና…ቀኑን በሙሉ በክብርነታችን ጽሁፍ ናላችሁ ይዞር ዘንዳ ፈቅዳችሁ ከሆነ ሞክሩና።ቀን ተሌት ታንል ለዛውም ስራ አጥ ዱርዬ ሆነን ስናበቃ ሞክሩንና ያለማቆም ቀኑን ሙሉ የምርቃት መአት ስናወርድባችሁ በመዋል የሳይበር ዋርካን ክብረ ወሰን ካልሰበርን ጭገር ከደረት ጸጉራችን ይነቀል
ሾተል ወያነ መሞቱን ሰምቻለሁ ጥናቱን ይስጥህ

ምርጡ የትግራይ ህዝብ ክፉ አይንካው ዘላለም ይኑር እንጂ ስለወያኔ ድሮም አግብቶን አያውቅም አሁንም ስለማንተዋወቅ አያገባንም።ያንን ስንል ወያኔ የምርጥ ነገር ስም አይደለም ለማለት አይደለም።አንባገነኑን አንድ ትውልድን የጨረሰው በደም ተገንብቶ በደም ተደራጅቶ ደም አፍሦሶ የኢትዮጽያን ህዝብ ደም ያስለቀሰው አረመኔው ደርግን እስከነሰንኮፉ ዳግም ላይፈጠር ድምጥማጡን አላጠፋም ለማለት አይደለም።አሁን ላለንበት እኔና አንተ ደርግ ባይወድቅ ኖሮ ተገደን ብሄራዊ በመሄድ የሆነ ሰሜን ተራራ ላይ በ 15 ቀን የሰልፍ ልምምድ ጦርነት ገብተን ጭንቅላታችንን በጥይት ተበርቅሰን ታሪክ ሆነን እንቀር ነበር ለማለት እንጂ እንደወያኔ ጦረኛ ጀግና የወንዶች ልክ በተግባር አይተን ካረጋገጥነው ውጭ ባለፉት 27 አመት ከመቶ በላይ የመንደር የሰፈር የቀበሌ ተቃዋሚ ፓርቲ ተቁዋቁሞ አንዳችም ጠብ ያለ ነገር ሳያመጡ ይበልጥ ተብሎ ግም ቦቲ ሰባቶች እንዳንተ ያሉ የዋሆቹን ገንዘብ መጥምጦ ሲያበቃ አንዲት 150 ነዋሪዎች የሚኖሩባት ቀበሉሌ እንኩዋን ሳይቆጣጠር ማጠፍያው አጥሮት ሳለ እድሜ የኢሃዴጉ ጀግና ዶክተር አብይ መጥቶ ገላገላቸው እንጂ እስቲ ንገረኝ ከወያኔ የበለጠ ጀግና ካለ?100 ሚልየን ህዝብን እንደፈለገው እንዳሻው አድርጎ ረግጦ የገዛው እኮ እሱን የሚመክት ወንድ ጠፍቶ እኮ ነው።መሃል ላይ ሆኖ ማንንም ሳይወግኑ ለፈረደ እውነቱ ይሄ ነው።የሚገርመው ለ 20 ምናምን አመት የሰው አገርና አስፋልት ሲያደነቁር የነበረ ተቃዋሚ ሁላ ከመጮህ ሳያልፍ ያልታሰበ የቲም ለማ ቡድን ከዛው ከኢሃ ዴግ ጉያ ወጥቶ ለውጥ ማስጀመሩ ድሮም እንለው የነበረው ተቃዋሚ ተብዬ ሁላ ከመጮህ ውጭ ምንም አያመጣ እንዳልነው ሆኖ ነው ያልታሰበ የተቀደሰ ቲም አሁን ለተደሰትንባት ቀን ያደረሰን።እና ተቃዋሚ ተብዬ ሁላ ሊያፍሩ የሚገባው ምንም ለውጥ ላያመጡ የስንቱን ዶላርና ይሮ መጥምጠው ሲያበቁ ኢ ህ አ ዴግ እራሱን ስህተቱን አይቶ ተለውጦ ሲያበቃ ጥሩ ኢሃዴጎችን መልምሎ ከነሱ በመጣ ለውጥ መጣ።አለቀ ደቀቀ።ረጅም እድሜ ለቲም ለማ።በነገራችን ላይ ድሮም እንደምንለው ወያኔን አናውቅም አያውቀንም።ወያኔም ለመሆን የሚያስችለን መስፈርት ኖሮም አያውቅም አልነበረንም።አሁንም ቢሆን አንባገነኑን ደርግ በመጣል የኢትዮጽያ ባለውለታ አይደለም ለማለት የሚደፍር ቢኖር ከህሊናው ጋር የተጣላ አይደለም ለማለት አያስደፍርም።
ለማንኛውም አንተም በክብርነታችን ተናፍቀሃል ደስ ይበልህ

አስታውሳችሁ ስለናፈቃችሁን ደስ ብሎናል።እኛም በክብርነታችን ሆነን ሁላችሁንም ሳትናገሩን የተናገርናችሁ…ልትናገሩን ስታስቡ ያስተሳሰባችሁ ቀለም ደስ አላለንም ብለን የተናገርናችሁ …ገና ለገና ትናገሩን ይሆን ብለን ፈስ ያለው ዝላይ የሚችል መስሎት እንዳዛረጠው በጥርጣሬ ብቻ የጻፍንባችሁ…ልትናገሩን ስትጀምሩ አርባ ክንድ የጽሁፍ ምላሳችንን የጎለጎልንባችሁ ሁላን ናፍቀናል።ዋርካ እንደ አሁኑ የሆኑ ወይ አይጽፉ ወይ አያጽፉ ከየቦታው ቅራቅንቦ እየሰበሰቡ ዋርካን በኮፒ ፔስት ያጣበቡዋት ከብቶች ዋርካን ገደሉዋት እንጂ የድሮዎቻችን ተሰባስበን እንደድሮዋችን ብንፋጭ የምን ፌስ ቡክ ትዊተር ወይም ኢንስታግራም…እንዳለ ያዳምን ዘር ሰብስበን ሸክፈን ስንት ያለንን በየጎራው ባካፈልን ነበር።እርግጠኛ ነኝ ከድሮው ሁላችንም የበሰልን አንብበን ሆነ ተምረን እራሳችንን አስተሳሰባችንን ያዳበርን እይታችንን ያሰፋን ለመጪው ትውልን በጨዋውም አለም ሆነ በብልግናው አለም ሊማሩ የሚችሉትን ከልምድም ሰርስሮ ከማወቅም አንጻር ስንት ነገር ልናካፍል የምንችልበት እምቅ እውቀት ነበር...ግና ምን ያደርጋል 4 የማይሞሉ በሁዋላ የመጣ አይን አወጣዎች ዋርካን መተኛት ሳትፈልግ አስተኙዋት...እንግዲህ ዋርካችን እስክትስተካከል ድረስ የአብይብን ንግግር ደጋግመን በማዳመጥ እየተማርን እየተዝናናን ለሱና ደጋፊዎቹ ረጅም እድሜን እየተመኘን አዲሱ መንግስት ይቅርታ ላይ በማተኮር የሴክዩሪቲውን ነገር ቢያሳሳው በወገኖቻችን ላይ ክፍተቱን መበጠቀም ወገኖቻችንን ዘቅዝቀው በመግደል ሆነ እሳት ውስጥ በመወርወር እንዲሁም በመቀጥቀት ኢሰባዊ ድርጊት ለተፈጸመባቸው እያዘንንና ህመማቸውን በመጋራት በሞታቸው የደም እንባ እያለቀስን መጪውን የሳይበር ዋርካን መጽዳትና የጸሃፊዎች መብዛት ይፈጠር ዘንዳ እየተመኘን እንጠብቃለን።
ፋኖ ፈንፋኖ በድጋሚ ስላየናችሁ ደስ ብሎናል።እስቲ አስገቡልንና ያንን ለመመከት ልክ ልካችሁን ለማለትና ዶቃ ማሰርያችሁ ድረስ እንዳለብላቢት የሰፈር ውሃ ቀጠነ ነገረኛ ከረባታችንን ገርግደን እንደዶፍ ዝናብ ስናወርድባችሁ እንሰንብት።

ክፉ አይንካችሁ።እደጉ…ተመንደጉ...እንቅልፍ የወደዱ እነማን ተባዱ።

ሾተል ነን....በክብርነታችን ሆነን ህዝቤ እየተነፈሰ ባለው የሰላም አየር በደስታዬ ደስታ ነፍሱን ይማረውና እንደ ማይክል ጃክሰን ፈረንጅ ሆኛለሁ።እሱ ብሊች የሚያደርግ መድሃኒት ወስዶ ነው።እኔ ደግሞ ከውሾቼ አሳንቴና ኦባማ ጋር ይሄንን ተራራ የሚያክል የቦቆሎ ገንፎ በመወጠቅ ነው።ሆድ ወደፊት…ቂጥ ወደ ሁዋላ (የኩዋሻኮርና ማራስመስ ማስታወቅያ)
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9658
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: እኛም አለን እናንተስ ደህና ናችሁ

Postby ኮኮቴ » Thu Aug 16, 2018 3:08 pm

እረ ተመስገን ነው ... የጥንቶቹ የጠዋቶቹ ኒኮች .. ዋርካ ላይ ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል! የእነ ሾተል እና ክቡን እንዲሁም የሬቾን ኒኮች በማየታችን ደስ ብሎናል፡፡ ግን ዋርካ ፖለቲካን ምነው ተዋችሁት???

ወንዙ ኮኮቴ

ሾተል wrote:ፋኖፋኖ

o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1291
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests