የኮሮና ሰሞን ፉገራዎች

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

የኮሮና ሰሞን ፉገራዎች

Postby *Oww Gee » Sat May 02, 2020 12:53 pm

ሰውየው ታክሲ ሾፌር ነበር። ያኔ ነው ታድያ። አሁንማ ዕድሜ ለኡበርና ሊፍት። ታክሲ በቅርቡ
ታሪክ ሆኖ ወደሚዚየም መግባቱ አይቀርም። እኛም ለልጅ ልጆቻችን "ድሮ TAXI የሚል
ፅሑፍ የተለጠፈባቸውና እጅህን አውለብልበህ የምታስቆማቸው ትራንስፖርት ሰጪ
መኪኖች ነበሩ ።" ብለን መተረታችን አይቀርም። ወደተነሳንበት ታሪክ እንመለስ። ሰውየው
የማይደክመው ጠንካራ ሰራተኛ ነበር አሉ። ጠዋት የለ ማታ የለ ... በቃ ዳውንታውንና
ሚድታውን ላይ ሲሽከረከር ነው የሚውለው። አንዴ እንደውም አፏጭተው ያስቆሙትና
"ለመሆኑ አይደክምህም እንዴ?፣" ቢሉት አሉ ... ምን ቢል ጥሩ ነው?! "የሚን መዲካም ኖ
... ሺሪሺር ይዳኪማል ኢንዴ?!" ቅቅቅቅ ።.... ይመቸው አቦ። እናም ይሄው ሰው አንዴ
የመኪና አደጋ ያጋጥመውና መኪናው እስኪሰራ ለ20 ቀናት እቤት ለመዋል ይገደዳል። ይህ
አጋጣሚ ከልጆቹ ጋር እንዲያሳልፍ ይዟቸው ወጣ ብሎ እንዲዝናና ዕድል ይከፍትለታል።
ልጆቹ ለመጀመርያ ጊዜ ከአባታቸው ጋር ፊልም ቤት መናፈሻ ቦታ ሞል ለመሄድ በመቻላቸው
ፍንድቅ ብለዋል። በመጨረሻም ታክሲው ተጠግና ስታልቅ አባት ወደስራው መመለሱ የግድ
ሆነ። ይህን ግዜ ትንሽ ልጁ አባቱን ምን ቢለው ጥሩ ነው?! "አባዬ ... መቼነው በድጋሚ
መኪና የምትጋጨው ?!" መራር ቀልድ ነው አይደል?!
ልክ እንደታክሲ ነጂው የመኪና አደጋ አጋጣሚ ...ኮረናም ብዙ ልጆችና ወላጆችን እንዲሁም
ባልና ሚስትን በጣም አቀራርቧል። "ከየቤታችሁ ነቅነቅ እንዳትሉ!" በተባለ ማግስት ነው
አሉ። አባት በጠዋት ተነስቶና ሪሞቱን ይዞ ቲቪ ላይ ይጣዳል። ወዲያው ከተወለደ ጀምሮ
በአግባቡ አይቶት (ታቅፎት) የማያውቀው ሶስተኛ ልጁ የሕፃን ፊቱን እያሻሸ መጥቶ ፊቱ
ይቆምና ይቁለጨለጫል። አባት ሕፃኑን እያየ ሚስቱን መጣራት ጀመረ አሉ። "ትርንጎዬ ..."
አላት አሉ ጩጬው ላይ አፍጦ " ትርንጎዬ ... ሩሜታችን ወለደች እንዴ?!"
አንዷ ናት አሉ ደሞ። አሷም ባሏም በሁለት ስራ ተወጥረው ማታ ከጨለመ አልጋ ላይ ብቻ
ነበር የሚገናኙት። እናም እድሜ ለኮረና ... ሁለቱም እቤት መዋል በጀመሩ የመጀመርያው
ቀን ማታ ባል መኝታ ቤት ገብቶ ለወንድ ጓደኛው ስልክ ይደውልና
"አንተ ... ሚስቴ ለካ ፍንጭት አላት!" ብሎ ሲያንሾካሹክ ... እሷ ደሞ ሽንት ቤት ውስጥ
ተደብቃ ለሴት ጓደኛዋ " አንቺ ... ሰውየው ለካ ራሰ-በረሐ ነው" ብላ እርፍ።
በእውነት የኮረና ክፋቱ ... ገዳይ መሆኑ ብቻ ነው።
*Oww Gee
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 18
Joined: Sun Oct 29, 2017 2:33 pm

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests