ኤርትራ የተመድን የሄሊኮፕተር በረራ አገደች

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime.Image

ኤርትራ የተመድን የሄሊኮፕተር በረራ አገደች

Postby ENH » Fri Oct 07, 2005 11:36 pm

ጦቢያ - 6-10-2005

ኤርትራ የተመድ በድምበር አካባቢ በሄሊኮፕተር የሚደረገው የበረራ ቅኝት እንዳይካሄድ ያሳለፈችውን ውሳኔ በመቃወም የፀጥታው ምክር ቤት ለሁለቱም ሀገሮች ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ሬውተርስ የዜና ምንጭ በትናንትናው ዕለት አስታወቀ። ከትናንት ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ምግብና መድኃኒት እንዲሁም የታመሙ የፀጥታ አስከባሪ አባላትን እንዲሁም የጥበቃ ስለላ ሥራ ለመሥራት የሚመላለሱትን ሄሊኮፕተሮች በድምበሯ ላይ እንዳይበሩ አግዳለች ሲል ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጿል። የፀጥታው ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ባስተላለፈው ኦፊሴላዊ ውሳኔ ኢትዮጵያና ኤርትራ እንደገና ወደ ሌላ ዙር ጦርነት እንዳይገቡ አስጠንቅቋል። ከዚሁ ጋር በማያያዝ 15 አባል ሀገሮች ያሉበት ምክር ቤት ለተመድ የሰላም አስከባሪዎች ደህንነት ሲባል የኤርትራ መንግሥት ሄሊኮፕተሮች እንዳይበሩ ያሳለፈችውን አደገኛ ውሳኔ ባስቸኳይ ማንሳት እንዳለባት አስጠንቅቁዋታል።
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest