«እኔ እስክመጣ ድረስ ውሳኔአችሁ ይዘግይልኝ»

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime.Image

«እኔ እስክመጣ ድረስ ውሳኔአችሁ ይዘግይልኝ»

Postby ENH » Sun Oct 09, 2005 1:45 pm

ኔሽን - 8-10-2005

የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ኃይሉ ሻውል ፓርቲያቸው ወደ ፓርላማ እንግባ ወይም አንግባ በሚለው ላይ የደረሰበትን የ30ለ 27 መከፋፈል እሳቸው ሃገር ውስጥ እስኪገቡ ድረስ ከውሳኔ እንዲያዘገየው በደብዳቤ መጠየቃቸውን «ኢትዮጵያን ሪቪው» ዘገበ።
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

ሀይሉ ሀይላችን የወቅቱ መሪያችን ለኢትዮጵያዊነትድንቅ

Postby ዲጎኔ » Sun Oct 09, 2005 6:23 pm

ሀይሉ ሻውል የወቅቱ መሪያችን
ለኢትዮጵያዊያን መልካም ምሳሌያችን
በሀገራዊ ጉዳይ አስማሚ ሊቃችን
ድሮም አይተንሀል ስትመክት በታኝን
ገና ከጅምሩ አቅርበህ መልስህን
አሳፍረሀታል ወይን ነጻነትን
አፏን አሞጥሙጣ አንተን ስትፈትን
በፕሬስ መግለጫህ ያኔ በሂልተን
እኛም ዘግበናል በሳል ራእይህን

ሀይሉ ሻውል የጎዳናው ቀያሽ
በፖለቲካውም ወያኔን አስለቃሽ
በንግግርህም ታሪክን አስታዋሽ
እናደንቅሀለን አንዲትም ሳትዋሽ
እንደነደደቢት ዘር ከዘር አናካሽ
ድሮ የጸናውን ሀገር መረብ ምላሽ
የሄጉ ፍርድ ቤት ሂደቱ ሲኮላሽ
በአደባባይ ዋሹ ሀገር እንዲበላሽ
መጠምጠም ጀመሩ እንደሴትቹ ሻሽ

ጥለው የናቁትን ሰንደቅ ግባችንን
አረንጉዋዴ ቢጫ ቀዩን አርማችንን
መርዶም ተነፈገ ለመላው ህዝባችን
አፍነን ከረመነው የውስጥ ሀዘናችን
ዛሬ ደግሞ በቃችሁ ቢል ወገናችን
ድፍን ጎጃም ጎንደር መላው ደቡባችን
ወሎ ሸዋ ሀረር ሱማሌ አጋራችን
ወለጋ ከፋ ገሙና ቤንሻጉል ዘራችን
ኢሉአባቦራ ባሌም አርሲያችን
ኤልከሬው አፋሩ የሉሲ ምድራችን
የወያኔ አገዛዝ ከቶ ለምናችን
ብሎ ቢገልጽለት በዚያው በቀያችን
ከማል ሰራረቀው ብዙሀን ድምጻችን
ከጌታሁን ጋር ከዚያ ከጸራችን
ተስፋዬ ከሚሉት ባንዳ ውላጃችን
በለመደው ውሸት ወያኔው ገዣችን

እናም ሀይሉ ሻውል አለብህ አደራ
ለእናት ሀገርህ ለኢትዮጵያ ባንዲራ
አንዳች አይጽጽትህ በሰራህው ስራ
ገና ለትውልድህ እጅግ የሚያኮራ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states


Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest