የአዲስ አበባ መስተዳድር ትላንት ሳይመሰረት ዋለ

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime.Image

የአዲስ አበባ መስተዳድር ትላንት ሳይመሰረት ዋለ

Postby ENH » Thu Oct 13, 2005 2:54 pm

አስኳል - 11-10-2005

ብሄራዊ ምርጫ እሁድ እለት ፣የአዲስ አበባ አስተዳደርን መስራች ጉባዔ ለማካሄድ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንን በተመለከተ የቅንጅት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትላንት የአዲስ አበባን አስተዳደርን መስራች ጉባኤ ለማካሄድ ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። ይህንን በተመለከተ የቅንጅት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትላንት የአዲስ አበባን ጉዳይ በሚመለከት ሲመክር ውሏል። ይህንን አስመልክተን አስተያየት እንዲሰጡ የጠየቅናቸው የቅንጅቱ ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት ኢንጂነር ግዛቸው ሺፈራው የሚከተለውን ብለውናል «የቅንጅቱ ም/ቤት እሁድ ዕለት ባደረገው ስብሰባ፣ የተወካዮች ም/ቤት ለመግባት እንዲሚሉት ያቀረባቸው ቅድመ ሁኔታዎች አሉ። ይህ ቅድመ ሁኔታ አዲስ አበባን ያካትታል ወይ? በሚል ነበር ስብሰባ የተቀመጥነው። የተወሰኑ አባሎቻችን፣ «አዲስ አበባ ክልል አይደለችም። ቻርተር ሲቲ ናት ለምን አንጠይቅም?» የሚል ጥያቄ አንስተው ነበር። የተወሰኑት ደግሞ፣ «የእሁዱ ውሳኔ አዲስ አበባንም ያካትታል»ና መጠየቅ የለብንም አሉ። ስለሁኔታው ም/ቤቱ ማወቅና መወሰን አለበት በሚል ስብሰባ አደረግን። በስብሰባችንም፣ ውሳኔው፣ አዲስ አበባን ይመለከታል ብለናል።» ሲሉ ኢንጂነር ግዛቸው በተለይ ለአስኳል ጋዜጣ ገልፀዋል።
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest