«ለህልውናችን ስንል ፓርላማ ገብተናል»

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime.Image

«ለህልውናችን ስንል ፓርላማ ገብተናል»

Postby ENH » Thu Oct 13, 2005 2:54 pm

አስኳል - 11-10-2005

ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአስኳል ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ «ህብረቱ ፓርላማ ገብቷል» ሲሉ ገለፁ። ህዝቡ በውሳኔው ከልብ ማዘኑን ለዝግጅት ክፍላችን እየደወለ ሲገልፅ ውሏል።
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

ወይ ጉድ

Postby ማንትሩ » Thu Oct 13, 2005 5:06 pm

ወይ ጊዜ የህዝብ ቃል የሚሰማው የትኛው ፓርቲ ነው? ሁሉ ለሆዱ ያደረ ብቻ ነው ፓሪቲ ሰፖርት ለማድረግ ህዝብ ህዝብ ይባላል ሲደራጁ ደግሞ ያ ህዝብ ይጣላል አንድዮ ይፋረዳችሁ ለሀገሬ ለህዝቤ የሚል መቼ ይመጣ ይሆን? ፓርላማ ገባን አይ ቁም ነገር ተሰራ ማለት ነው?ብቻ ቢወቅጡት የተባለው አይነት ነው ፓርላማ ለመግባት ውሳኔው የናንተ ከሆነ ህዝብ ለናንተ ምንም ነው ማለት ነው?
ለህልውና ስንል ገብተናል አይ እውቀት ትርጉሙን ያገሬ ምስኪኑ ያልተማረው ገበሬ ያስረዳህ ህልውና ይሄ የማይመስል ነው ነገ ሁሉ በግልጽ ማንነታችሁን ያሳየናል ያሳሳሳየየን
ቀን ይፍረደው?????


ቸር ያንጣልን
ማንትሩ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 58
Joined: Mon May 16, 2005 9:45 pm
Location: united states

Re: «ለህልውናችን ስንል ፓርላማ ገብተናል»

Postby ትብብር » Fri Oct 14, 2005 6:10 am

ፖለቲካ ውስት ስትገቡ ምን ገምታችሁ ነበር ዛሬ ህልውና የሚለው ምክንያት ለወሰዳችሁት ውሳኔ ተገቢነት ማረጋገጫ ሆኖ መቅርቡ? አልፎም ከተመራጮችና ከአባላት መካከል መሞታቸውን አቶ መረራ ሲያበስሩ; በከንቱ የፈሰሰውን ደምስ ፍትህ ለማስገኘት የወሰዱትን እርምጃ ባለመስማቴ በጣም ሳዝን; በኔ እስካልመጣ ድርስ ይህንን እርምጃ ወስደናል የሚል መደምደሚያ መውሰዳቸው አሳፋሪ ነው ብየ አምናለሁ;; ከዚያም አልፎ የአንድ አንባገነን መነጽር የጻፈውን ህገመንግስት ለማራመድ የወሰዱት እርምጃ አሳፋሪ ነው;; ግለሰቦች ትልቅ አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም በሀገራችን መንግስት አወቃቀር የህገመንግስትን የበላይነት እንጂ ግለሰቦችን የበላይነት እስካላጠፋን ድረስ; ችግሩ አሁንም በአዲስ ምእራፍ ጉዞቅን የረቀቀ የግለሰብ አንባገነንንት ለማራመድ ትናንት ተቃዋሚ ዛሬ ኮንፓድሬስ ሆነው መገኘታቸው አደገኛ ሚና ተጫውተዋል ብየ አምናለሁ;; ከዚያም አልፎ ህብረትን ከሚዋቅሩት ድርጅቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ከኢሀድግ ጋር መሰረታዊ ቅራኔ ያላቸው ሲሆን የተወሰደውን እርምጃ ሪኮንሲደር ቢያደርጉት ይሻል እላለሁ;;
ትብብር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 119
Joined: Mon Oct 04, 2004 6:34 am
Location: united states

Oct. 14, 1954 Janhoy visited UK, see video

Postby sewd05 » Fri Oct 14, 2005 7:33 pm

መቼ ይሆን ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የነበራትን ክብር መልሳ የምታገኘው

እስኪ ይህን ያንብቡ እንዴት አድርገው በ 1954 ልክ ዛሬ ጃንሆይን እንግሊዞች እንደተቀበሏቸው፡፡
ጃንሆይን የማትወዱ ብዙዎች ብትኖሩም ለኢትዮጵያ የነበራትን ክብር ግን ልትክዱ አትችሉም፡፡ ዛሬ እንኳን የክብር መድፍ ሊተኮስና እና ንግስት ኤልሳቤጥ ልትቀበለን ቀርቶ መኖራችንም ማስታወሷን እጠራጠራለሁ፡፡ ይባስ ብሎ ኢትዮጵያዊያን በለንደን ለማለፍ የትራንዚት ቪዛ ከሚያሰፈልጋቸው ሀገሮች ውስጥ አንዷ ናት::፡፡ ያው የተለመደው እርስ በርሳችንን መነካከሱን እስካልተውን እና እራሳችንን እስካላተከባበርን ድረስ የሚያከብረን የለም፡፡

መቼም አንዳንዶች የምትሉት አታጡም እና ልስማችሁ፡፡

1954: Ethiopian emperor visits UK
Emperor of Ethiopia, Haile Selassie has arrived in Portsmouth on the cruiser the Gambia. His visit is part of a world tour, his first since his triumphant return to Ethiopia in 1941.
Image
sewd05
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 79
Joined: Tue May 24, 2005 2:22 am
Location: ethiopia

Re: Oct. 14, 1954 Janhoy visited UK, see video

Postby ወርቅሰው1 » Fri Oct 14, 2005 8:18 pm

ትክክል ብለኃል ወገኔ!
አዎ "ነብይ በገዛ ኃገሩና ሕዝቡ አይከበርም" የሚለውን እንድታስታውስ እወዳለሁ:: በዚያ የተነሳ ነው::

ኢትዮጵያ አገራቺን ብዙ ያለፉና እንዲሁም ያሏትን ነብያቶች ልንጠቀምባቸው ይገባል::

ምሁራን ነብያት በመጨረሻ ጊዚያት ሰቷታል:: እነሱም ቅንጅት ውስጥ ያሉት ናቸው:: ህዝባቸው ደግሞ ከጎናቸው ተሰልፏል:: ያምንባቸዋል ይሰዋላቸዋልም:: ያንን ያላወቀው ህወኃትና መሪው ተሳስተዋል በሚል እገምታለሁ::

ባድሜ ላዚያች 3 አንግል ለምትባለው ትንሿ ቦታ 70 ሺህ ልጆቹን ሰውቷል:: ለኢትዮጵያ በ20 ሚሊዮን ለመስዋት እንደተዘጋጀ ደንቆሮዎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ያላወቁ ይሆን?

ዛሬ ታላቁን አርቲስ! "አቶ: ደበበ እሸቱን" ከቤቱ ወስደው 3ኛ የሚባለው የምርመራ መዓከል አስገብተውታል አሉን:: የሚያሳዝን:: ይህንና ሌላውን እርምት ማድረግ ይገባል:: በጅማ ባሉት ወጣት ትውልዶችም ላይ ወያኔ ህወኃት እየገደላቸው ሰብስቦም እያሰራቸው ነው::

የሚያስገርመኝ ግን ኤልሳቤጥ አዲስ አበባ የመጣቺ ግዜ በ1967 ልጅ ሳለሁ ከዘመዶቼ እፍቼ አፍሪካ አዳራሽ የነበረው ጋ በአቀበት የተገነባ ያትክልት ቦታ ነበር ከዮቤልዩ ፊት ለፊት እዚያጋ ሆኜ ተቀብያታለሁ::

አዎ ዛሬማ ኢትዮጵያን ንቀዋታል:: የምታስታውሳትም አይመስለኝም:: ያም ሆነ ይህ ስለ አገራቺን ልናስብላት የሚኖርብን እኛው ልጆቿ ነን የርስበርስ ትርምሣቺንን ትተን ለህልውናዋ እንቁም ነው የኔ ጥያቄ ፖለቲካ የሚኖረው አገር ስትኖር ብቻ ነው::

ነታ አገርና ነጻም ህዝብን ለማየት እወዳለሁ የተሻለም ህይወትና የንኑሮ ዕድገት እንድታሳየን ሰርተን እንድንረዳት እመኛለሁ:: ያቺን አገር ማንም ኃላፊነት አለበት:: የኦነግና የሶማሌ/የም ዕራብ ሶማሌ ድርጅት የሚባሉት ካሁኑ ከሠፊው ህዝብ ጋራ እንዲሰለፉ ይገባል:: በኌላ ችግር እንዳይኖ የሚያስፈልገው ያብቻ ነው::

ወያኔ የሞተ ድርጅት ነው:: ግዜው አልፎ ተረት ሆኖ እንደሚቀር አስታውሳለሁ:: ወያኔ የኢትዮጵያ ጠላት ነው:: ወያኔ ወደደም ጠላም ይደመሰሳል:: የኢትዮጵያ ህዝብንም ክንድ ይቀምሳል:: ኢትዮጵያ በሚጨነቁላት ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለቺ::

መንፈስዎን ወደዚህ ያነሳሁት ጥያቄ ውስጥም እንዲያገቡት በሚል ነው ይህን ሁሉ ዝርዝር ያቀረብኩልዎት:: አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንድትቆም በሚረዱት መስመርም ያሳስቡልን::

*ቀይ ባህር ዳር ድንበራቺን ነው*

አክባሪዎ

ወርቅሰው1
ከ(ሰሐሊን)


sewd05 wrote:መቼ ይሆን ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የነበራትን ክብር መልሳ የምታገኘው

እስኪ ይህን ያንብቡ እንዴት አድርገው በ 1954 ልክ ዛሬ ጃንሆይን እንግሊዞች እንደተቀበሏቸው፡፡
ጃንሆይን የማትወዱ ብዙዎች ብትኖሩም ለኢትዮጵያ የነበራትን ክብር ግን ልትክዱ አትችሉም፡፡ ዛሬ እንኳን የክብር መድፍ ሊተኮስና እና ንግስት ኤልሳቤጥ ልትቀበለን ቀርቶ መኖራችንም ማስታወሷን እጠራጠራለሁ፡፡ ይባስ ብሎ ኢትዮጵያዊያን በለንደን ለማለፍ የትራንዚት ቪዛ ከሚያሰፈልጋቸው ሀገሮች ውስጥ አንዷ ናት::፡፡ ያው የተለመደው እርስ በርሳችንን መነካከሱን እስካልተውን እና እራሳችንን እስካላተከባበርን ድረስ የሚያከብረን የለም፡፡

መቼም አንዳንዶች የምትሉት አታጡም እና ልስማችሁ፡፡

1954: Ethiopian emperor visits UK
Emperor of Ethiopia, Haile Selassie has arrived in Portsmouth on the cruiser the Gambia. His visit is part of a world tour, his first since his triumphant return to Ethiopia in 1941.
Image
ወርቅሰው1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4075
Joined: Wed Nov 05, 2003 9:49 pm
Location: Sehalin

Re: Oct. 14, 1954 Janhoy visited UK, see video

Postby ማንትሩ » Fri Oct 14, 2005 9:46 pm

ምን አገናኘው የሀይለስላሴ ይህን ታሪክ ኤልሳቤት ያኔ አከበረች አሁን ናቀች ማማው ሌላ መታወቂያው ሌላ አለ ያገሬ አራዳ እንኩዋን ለዚህ ጊዜ በቃን ይመስላል በሀይለስላሴ ስህተት መስሎኝ ሀገራችን ለዚህ የተዳረገችው ብቻ ሆድ ይፍጀው አለ ጥሌ እኛም ያለውን የቆሸሸውን ታሪክ ባለን አቅም ያረጀን ታሪክ ደካማ ጎን ሳንረሳ ዛሬ አዲስ ህይወት ብንፈጥር አይሻልም?እኛ እንኩዋን ብዙ መቅመስ ጊዜው ባይበቃንም ላልተወለዱት እንደኛ አፍረው ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ኮርተው የሚያወሩበት ታሪካዊ መንግስት ሊያገኙ የሚችሉበት መንገድ በፈጠርን ያ ነበር ታሪክ 19 54 በአውሮፓን ምን አሳሰበን ለምን 1953በኢትዮ አቆጣጠርን ለምን አላሰብንም ያ ቢሳካ የት ነበርን ብናስብ ያ ጅማሬ ለመጨረስ በታገልን ነበር??????


ልቦና ይስጠን
uote="sewd05"]መቼ ይሆን ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ የነበራትን ክብር መልሳ የምታገኘው

እስኪ ይህን ያንብቡ እንዴት አድርገው በ 1954 ልክ ዛሬ ጃንሆይን እንግሊዞች እንደተቀበሏቸው፡፡
ጃንሆይን የማትወዱ ብዙዎች ብትኖሩም ለኢትዮጵያ የነበራትን ክብር ግን ልትክዱ አትችሉም፡፡ ዛሬ እንኳን የክብር መድፍ ሊተኮስና እና ንግስት ኤልሳቤጥ ልትቀበለን ቀርቶ መኖራችንም ማስታወሷን እጠራጠራለሁ፡፡ ይባስ ብሎ ኢትዮጵያዊያን በለንደን ለማለፍ የትራንዚት ቪዛ ከሚያሰፈልጋቸው ሀገሮች ውስጥ አንዷ ናት::፡፡ ያው የተለመደው እርስ በርሳችንን መነካከሱን እስካልተውን እና እራሳችንን እስካላተከባበርን ድረስ የሚያከብረን የለም፡፡

መቼም አንዳንዶች የምትሉት አታጡም እና ልስማችሁ፡፡

1954: Ethiopian emperor visits UK
Emperor of Ethiopia, Haile Selassie has arrived in Portsmouth on the cruiser the Gambia. His visit is part of a world tour, his first since his triumphant return to Ethiopia in 1941.
Image[/quote]
ማንትሩ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 58
Joined: Mon May 16, 2005 9:45 pm
Location: united states

Postby ግልጽ » Fri Oct 14, 2005 10:04 pm

ማሞ ሌላ መታወቅያው ሌላ አሉ:: አሁን እስቲ የዛ የቀጣፊ ጥቁር ላለመባል እንክዋን የሰለሞን ዘር ነኝ እያለ በስንቱ ድሀ ኢትዮጵያዊ ላይ ለዘመናት ያላገጠውን ንጉስ ተብየው እንግሊዝ አገ ሽሽት (አዎ ሽሽት) ከ ህብረት ፓርላማ መግባት ጋር ምን አገናኘው? አየ እናንት ትምክህተኞች ለምን አንዳፉኑ እንደጃማይካመዎቹ እግዚአብሔር ነው ብላችሁ እርፍ አትሉም::
ግልጽ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 38
Joined: Mon Feb 07, 2005 6:14 pm
Location: united states

ግልጽ በግልጽ ብንነጋገር ከአጼው እስከወያኔው ልዩነትም የለው

Postby ዲጎኔ » Fri Oct 14, 2005 10:55 pm

እረ ጎበዝ አብራችሁ አትውቀጡን!

ያልተገራ ፈረስ ጠቅል እያላችሁ
ከማይጨው ደንብሮ ሎንደን ገባላችሁ

ብለን ያኔኮ የፊውዳሉ ቁንጮ ከነግፋቸው እንዲወገዱ ጮህናል ግን የባሱት ጨፍጫፊዎችና ዘረኞች በእግራቸው ገብተው እስከአሁን መከራችን አላባራም

ጃማይካዎች ቢያመልኩዋቸው ወይም አያቴ ለወግ

የሀይለስላሴ ጠላት አይኑን ለጨለማ
ጉልበቱንም ለቄጠማ
ብለው ቢረግሙንም እኛ አይናችንም ሳይታወር ጉልበታችንም ቄጠማ ሳይሆን እስከዛሬ አለን::

ስለዚህ የአጼውን በጎውን አስቀርተን ክፉውን እንደአሉታዊ ታሪካችን መያዝ እንጂ የሞተ ማንሳት በባህላችን ነውር ነውና በግልጽ ስለአሁኑ የህዝባችን ሰቆቃ ሰላማዊ ትግላችንና የዲሞክራቲክ ቅንጅታዊ አታጋዮቻችን ድጋፍ ላይ እንረባረብ!

ዲጎኔ ነኝ ከዸክሀራራ/ሸራተን አዲስ ከታች ግቢ ማዶ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby በማእረጉስ » Sat Oct 15, 2005 12:18 pm

የተከበራችሁ ወገኖቺ እንደተባለው ሁሉ በቀደመው ጊዚ በአለም ደረጃ የነበረን ክብርማ ትዝታው አይረሳኝም ባይኒ ያየሁት ብዙ ነበርና:: ንጉሱም ለኛ በብዙ መልኩ የሚረባ ዘላቂ ነገር ለመስራት ባይታደሉም የሀገራችንን ስምና ክብር በማስጠበቅ ደረጃ ብዙ ሰርተዋል:: ስላለፈ ብቻ ሁሉንም እንደማይረባ ነገር እየጣልንና እየረገምን ልናልፍ ባልተገባን ነበር:: ደርግ እንኩዋን በዚያ ሁሉ ጭካኒው አንዳንድ የሰራቸው በጎ ስራዎች መኖራቸውን መርሳት ከታሪክ ውጭ መሆን ነው:: ወደ ዋናው ጉዳይ ብንመለስ ደግሞ የተቃዋሚዎቹ ፓርላማ መግባት ልክ ነው ወይስ አይደለም? ነው ጥያቂው:: በኒ ግምት መለስ የአምባገነንነቱን ስራ እንዲገፋበት ከማድረግ በስተቀር ገብተው የሚፈጽሙት አጥጋቢ ተግባር አይኖርም:: ስጋቱ ደግሞ ሊያሳስባቸው ባልተገባ ነበረ:: ባለጊዚና ባለ ጠመንጃ ስለሆነ ብቻ ፈርተው ያላቸውን ሁሉ ለመፈጸም ተንጋግተው ከመግባት ቀድመው ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጁ ቢሆኑ ኖሮ መልካም ነበር:: ጋንዲም ሆነ ማንዲላ ለቆሙበትና ላመኑበት ቆመው ፍጻሚያቸው ድል ሆኗል:: ወላዋይ አቅዋም ተይዞ የትም መድረስ አይቻልም:: በነርሱ ልፍረድ ብዪ አይደለም ግን ሕዝብን ለለውጥ መምራት በሕይወት መወራረድም አለበት:: ፈራ ተባ እያሉ በመለስ ጮሊ ምላስና ተንኮል የተባለውን ሁሉ ለማድረግ ግርር ብለው ቢገቡ ምንም ሊሰሩ እንደማይችሉ ይታየኛል:: ለሚያቀርቡት ተቃውሞ ሁሉ በህግና በአንቀጽ ጠፍንጎ ሊያስራቸው እንደሚችል እንደምን ይዘነጋሉ? መለስ እስከመራን ድረስ ደግሞ ወደፊት ታሪክ የሚገልጠው ኢርትራን በሚመለከት የተካሂደና በመካሂድ ላይ ያለ ከፍተኛ ኮንስፓይረሲ እንዳለ በርግጠኝነት አውቃለሁ:: ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ያልቆመ መሪ ነው:: ያው የድሮ ትዝታ እያነሳን ስናወራ እኛም ከታች ያለነው ደግሞ ከከንፈር መጠጣ ያላለፈ ተግባር ላንፈጽምና አብሮ መብላት እንጂ አብሮና ተባብሮ መስራትን ሳናውቅ ዘመኑ ጥሎን እየሂደ ነው:: ምንጊዚም ቢሆን የልብ አንድነትና መደማመጥ እስከሊለን ለወያኒ እድሚ ማርዘማችን ነው:: ለፕሪንስፕል እምቢ የሚል ወኒ እንዲት እናጣለን? ትናንት ማንዲላ ሊታገል ሲነሳ ትናንት ዚምባብዊ ነጮች ሲያሰቃይዋት እንዳልረዳን ለበርካታ አፍሪካውያን ነጻነት ትግል ከፍተኛ ትግል እንዳላደረግን ለራሳችን እንኩዋን የማንበቃ የራሳችንን ተባዮች ማራገፍ የማንችል ሆነን አረፍነው! ተቃዎሚዎች ፓርላማ መግባታችሁ ምንም ፋይዳ የለውም! ምናለ በሉኝ! በነርሱ ሙዚቃ ለመደነስ ካልሆነ በቀር! በደህና ያሰንብተንና እናያለን::
በማእረጉስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun May 29, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ

Postby ስቄ-ልሙት » Sun Oct 16, 2005 12:38 am

ባካቹ እናንተ ናቹ ያልገባቹ !!!

ነገርየው እንዲህ ነበር-----እንዴት በሉ

ወያኔ (መሌ አራዳው,,,,,ራሰ በረሀው) እስኪ ኑ ትንሽ ምርጫ ምርጫ እንጫወት እና ፈረንጆችን ትንሽ ፖኬት መኒ እንጫቸው!!

ብሎ ነበር ምርጫው የተካሄደው,,,,,,አንዳንዱ ያልገባው ወይም የፈረደበት ጮክ ብሎ ሲናገር
የጥይት እራት ሆኖ ቀረ,,,,,,ቢያሳዝንም ነገርየው ፊልም እንጂ እውን መስሎ እስካሁን አይታየኝም ያለው

አንዳንድ አባሎች ተገድለዋል ወደ 30 ሚደርሱ እና ማን ሞኝ አለ ከምገደል
ገብቼ አብሬ ለምን አላጫፍርም እንጂ ነገ ጥዋት አንዱ ወያኔ መጥቶ ግንባሬን ቢደፋኝ ማን ልጄን ሊያስተምርልኝ ነው ?? አታይም ሌሎቹ ሲገደሉ ማንም አልተናገርም ስለዚህ እኔም ብገደል አፉን ሚከፍት ስለሌለ ከምገደል ለህልውናዬ ስል ገብቼ ሲፈቀድልኝ አፌን እከፍታለሁ ዝም በል ከተባልኩ ደግሞ ዝም እላለሁ እንጂ እኔ ሞኝ አደለሁ እንደ ቴዲ ጥይት እስኪያጠጡኝ ምጠብቅ ቴዲ እኮ ቆራጥ ሆኖ ጥይቱን እራሱ ነው የቃማት,,,,,,,በሂወት ቀልድ የለም እንደ ጎማ ነፍቶ ሚመልስህ የለም ይባላል,,,,,አሁንም ቢሆን መሌ አራዳው ያ ራሰ በረሀው ይህ ሁሉ እንዲረሳ ምድረአዳሜን ወደ ጦርነቱ ይልካት እና ዳርድበራችን እየተደፈረ ነው ወገን ሲል ሁሉዋም ጭንቅላት የለሽዋ አገሬን ለሰው እያለች እዛ እሳት ውስጥ ትገባለች,,,,,,,ለማን ለምን እንደሚሞት ሳያቅ ሚሞት ሞልቶዋል ወታደር ሲባል ማሀይም ነው ሚባለው አንዳንዴ እውነት ነው እንጂ የራሴን ሰው ከተማ ውስጥ እያጋደመ እኔን ወደ ጦር ሜዳ ሂድ ብሎ መሳሪያ ሲሰጠኝ እሺ ብዬ አፈሙዙን መጀመሪያ ወደሱ ነበር ማዞረው እንጂ መንጌ እንዳለው ዶሮዋን ሰጥቶ እንቁላልዋን ስጡኝ ማለት ነው የሆነብኝ የኤርትራዋ ጦርነት ልብ ካለው አገሪትዋን ያምጣት እንጂ የደረቀ መሬት ለማምጣት ለምን ትኩስ ደም ይፍሰስ በሉ እሺ ልሳቀው እንጂ በአገራችን ማዘን ከተውኩ ቆይቻለሁ እና እንጸልይ እንጂ ሌላ ምለው የለም

በሰላምምም ዋሉ ዋቆ ነኝ ከጨርቆስ
ስቄ-ልሙት
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 2
Joined: Sun Mar 13, 2005 9:33 am
Location: ethiopia


Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest