የቅንጅት መሪዎች ከ15 -20 ዓመት በሚያሳስር አንቀጽ ሊከሰሱ ነው

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime.Image

የቅንጅት መሪዎች ከ15 -20 ዓመት በሚያሳስር አንቀጽ ሊከሰሱ ነው

Postby ENH » Fri Oct 21, 2005 2:36 pm

አዲስ ዜና - 18-10-2005
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

ሰባ ሚሊኦን የኢትዮጲያን ህዝብ ማሰር ማለት እንደሆነ ተረዱት!!

Postby mrmuluwork » Fri Oct 21, 2005 8:42 pm

70 ሚሊዮን ህዝብ የማሰር አቅም ያለው ከሆነ ሞክሮ ማየት ነው::ቅንጅት ማለት ከማንም ኢትዮጵያዊ ጋር የሚሰራ ሕዝባዊ ሰላማዊ ድርጅት ነው::ቅንጅት አገር የሸጠ ባንዲራ የረገጠ እና ያቃጠለ የወንበዴ ክምችት ሳይሆን የውነተኛ የኢትዮጲያ አገርና ሕዝብ ሁሉ ስብስብ ነው::

ባዓለም ላይ አገሩን እና ሕዝቡን የሚሰድብ የሚገድልና የሚያዋርድ ከሃዲ መንግስት ነኝ ባይ ናዚው መለስ ዘናዊ እና ግብረ አበሮቹ ናቸው::
mrmuluwork
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 56
Joined: Fri May 20, 2005 3:09 pm
Location: ethiopia

Postby sewd05 » Fri Oct 21, 2005 9:16 pm

Ethiopian opposition accuses government of killing six members
Oct 21, 2005, 16:38 GMT

Addis Ababa - Ethiopia's leading opposition party, the Coalition for Unity and Democracy (CUD), accused the government Friday of killing 6 of its members and arresting 837 others over the past three weeks.
In a statement, CUD chairman Hailu Shawul accused the government of numerous human rights violations, including the harassment, beating and unlawful arrest of CUD supporters and the forced eviction of opposition leaders from their lands.

More
sewd05
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 79
Joined: Tue May 24, 2005 2:22 am
Location: ethiopia

ለወንበዴ ሕግ የለውም

Postby ሊቃውንት » Sat Oct 22, 2005 12:06 am

ወያኔ ከመሰረቱ የወንበዴ ጥርቅም ነው::እኛ የምናውቀው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ይህም በ1947ዓ.ም. የተፃፈውን ነው::

ወያኔ በሕግ የማይመራ የወንበዴዎች ጥርቅም ሆኖ ሳለ ስለምን ለህዝብ መተዳደሪያ የሚሆን ሕግ ሊያወጣ ይቻለዋል :?:

የመሰናዳት ተግባር ያለማስረጃ ፈጽሞውንብም ሊያስቀጣ አይችልም::ግና ወያኔዎች በጭፍን የሚሄዱ አውሬዎች ስለሆኑ የሚያደርጉትን አያውቁም::

Code: Select all

ወያኔ  አያደርግም  የሚባለው  ምንም  ነገር  የለም :!:
The truth is out there.
ሊቃውንት
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 109
Joined: Sun Oct 10, 2004 9:21 am
Location: Far_east

:-)

Postby ደጉ » Sun Oct 23, 2005 9:10 pm

.... ትናንት በጀርመን አገር ነዋሪ የሆኑ ዶሮዎች ከትናት ጀምሮ በነጻነት ወደ ውጪ እንዳይወጡ አዋጅ ወጥቶባቸዋል ... ከወያኔ አዋጅ ለየት እሚለው ካንድ ዶሮ በላይ ሆነው ሳይወጡ መሰብሰብ መቻላቸው 1 ..... ሌላው ደግሞ ከኤስያ በመጣው የ ዶሮ በሽታ እንዳይጠቁ በማሰብ ነው...ለራሳቸው ደህንነት ሲባል ነው ..እርግጠኛ ነኝ ዶሮዎቹ በዚ ቅር እሚሰኙ አይመስለኝም....:-)
ለወያኔ ግን ለ አንድ አዲስ አዋጅ እሚሆን ህሳብ አለኝ .....ታዲያ ይህ አዋጅ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ቢባል....:-)
.... ይህ አዋጅ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ..የወያኔን መንግስት በሆዱ ያማ ...ሲያማ የሰማ ማንም ቢሆን ለፍርድ ይቀርባል ... የኔ ህሳብ ነው ወያኔዎች እርግጠኛ ነው የናንተም ህሳብ ይህው ነው...;-) :lol:
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4417
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby አቡዬ » Mon Oct 24, 2005 9:43 am

መሪዎችን በማሰር ትግሉን ማፈን አይቻልም እንዲያውም እንደ ሰደድ እሳት እየተስፋፋ እዲሄድ ያደርገዋል እንጂ ፋሽስቱ የወያኔ መንግስት እነኚህን ህዝባዊ ድጋፍ ያላቸውን መሪዎች ካሰረ በእራሱ ላይ የሞት አዋጅ እንዳወጀ ይቁጠረው አሁን ቢሆን ከሞት አያመልጥም ግን የሚወስዳቸው እያንዳንዱ አምባገነናዊ እርምጃዎች ሞቱን ያፋጥንለታል
ህዝባዊ ትግል አሸናፊ ነው
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

ቅንጅትን ማሰር ህዝብን በገሀድ መናቅ ይሆናል

Postby ሳምቻው » Mon Oct 24, 2005 1:19 pm

ጥቂቶቻችን የገመትነው እና ስንጮህለት የነበረው ነገር እየደረሰ ያለ ይመስላል ::

ይሁን'ና ይህን የህዝብ ድጋፍ ያለው የፖለቲካ ቡድን ማሰር ማለት ሞቡቱን በ 7 ወራት ከስልጣን አሽቀንጥሮ እንደጣለው የካቢላ ሪዚስታንስ አርሚ ኢትዮጵያ ውሥጥ ለመፍጠር እንደመዘጋጀት ነው ለኢሀዲግ :: ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ያለው የትጥቅ ትግል ኦልረዲ ከሰለጠኑ ወታደራዊ መኮንኖች ጋር ለማዘጋጀት ሀገሪቱ ምቹ ናት !

የተፈራው ህገ ወጥ ክስ የኢሀዲግን ታሪካዊ ባህሪያት ባለማገናዘብ , ኢሀዲግን በመተባበር ,የተፈጠረ ይመስለኛል :: አሁንም ቅንጅቱ የኢሀዲግን ቅዝምዝም ሊያመልጥ የሚችለው ብሎም ታግሎ ሊያታግል የሚችለው ፓርላማው መሀል ገብቶ ባለው ጠባብ ቀዳዳ እይታገለ እነዚህን በአጉራ-ዘለል የፖለቲካ አስተዳደግ የተወጠሩ ጠባብ ት'እቢተኞችን አላማ በመገንዘብ ነገር የመፈለግ ዘዴዎቻቸውን አስቀድሞ በማጤን ደረጃ በደረጃ እያከሽፈ በመንቀሳቀስ ነው ::አሁንም የረፈደ አይመሥለኝም :.

አቶ መለስ ባለፈው የተጠራውን ኃገር አቀፍ ከቤት ያለመውጣት አድማን በመደራደር ሽፋን በማክሽፍ በተገኘው ፋታ ውስጥ ወደ ፓርላማው የመክፈቻ ቀን ለመጠጋት የቻሉ ሰው ናቸው :: በዚህ ኣጭር ትንፋሽ የማለ እና ያልማለ ፓርላመንታሪ ፓርቲን ለይተው ለመፈረጅ ተጠቅመውበታል ::

ሳም[b]
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

Postby ዞብል2 » Mon Oct 24, 2005 4:55 pm

ሰላም ሳምቻው!! አንድ ጥያቄ እንደዛ ወያኔን እያወገዝህ ስለ ካምፓስ ኑሮ ስትጽፍ የነበርከው ሰው አሁን ግልብጥ ብለህ <ለአምባገነንነት> እውቅና ስጡ እያልክ የምትደሰኩረው....ወያኔዎች በርጫ(ጫት) "በቺኑክ ኮፕተር" ነው ወይስ "በአንቶኖቭ" ያራገፉልህ?? :lol: :lol:

ወንድም ሳምቻው...<ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ተጽኖ ነጻና ቋሚ የሆነ የመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ብሎም መሰረታዊ የፖለቲካ እውቀትና የዲሞክራሲ ጽንሰ ሀሳብ ማስፈጸሚያ ህጋዊ ተቋማት በሌሉበት አገር የሚደረግ ምርጫ የይስሙላና የአምባገነኖችን የሀሰት ህጋዊነትና ተገቢነት ማረጋገጫ ይሆናል>ተግባባን :!: :!:
ሰላም ሁን

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2028
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

አካሔዱን አይቶ ወንበሩን ቀማው

Postby ሳምቻው » Tue Oct 25, 2005 12:15 pm

ዞብል

በጣም የሚገርመኝ ነገር በጭፍን በሚደረግ የፖለቲካ ጉዞ እናሽንፋለን ብሎ ማሰቡ ነው :: ህዝባዊ ትግልን የሰፈር ልጆችን ለሆያ ሆዬ ጭፈራ እንደመጥራት ያህል አቅሎ ማየቱ ጭራሽ ኣይታሰብም ... ::

አንዳንዱ የመነጋገርያው ርእስ ምን እንደሆነ እንኳ በወጉ ሳይገባው "" የፓርላማ ተቃዋሚ ; የኢሀዲግ ተቃውሚ ; የ'ኦነግ ተቃዋሚ ወይ ሲፈልግ የምንም ነገር ተቃዋሚ "" ሆኖ ብዙሀኑን ልምሰል ብሎ ዋርካ ላይ መችክችኩን ብቻ ስራየ ብሎ ይዞታል ::በጽሞና መወያየት ገና አልጀመርንም :: በቡራ ከረዩ ድል አይገኝም :: ተረጋግተህ አስብ :: የጣላትህን አቋቋም ተረጋገትህ ካላጤንክ ስንዘረህ መሳት ያባት አይደል , ተቀድመህ ትመታለህ !! አሁን እየሆነ ያለውም ጉዳይ ይሄ ነው ::

""" አካሄዱን አይቶ የፓርላማ ወንበሩን ቀማው """ የሚል ተረት ሳይጀመር አይቀርም በቅርቡ

እና ብዙ ሰው በቂ ነው ብሎ ያምናል "" በፈጣን ተቃዋሚነቱ "" :: እዚህ ዋርካ ፖለቲክስ ላይ እንደሱ ካላደረገ ብዙ ሰዎች የሚሰድቡት ይመሰለዋል :: ሰዎም በርግጥ ኣይመችም :: አያወያይም :: አብዛኛው 7 ምላስ :: አንድ ጆሮ :: ምንም ጭንቅላት ያለው ነው ::

እኔ የልጆች ጫወታን በመከተል እምነቴን ለማንም ስል አላጥፍም :: ይህንን ትናንት ብዬዋለሁ :: ነገም ከነገ ወዲያም እደግመዋለሁ :: ግልጽ ነው ?

ተቃዋሚ ፕርቲዎቻችን የወያኔን ጭፍን አገዛዝ በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ለማጋለጥ በቂ የሆኑ የፓርላማ ወንበሮቻቸውን በዋዛ የሚያጡበትን አንዳች አጥጋቢ ምክንያት ሳልይዝ በስሜት አፍላ ሆያ-ሆዬ አልነዳም :: አስቸጋሪውን የአፍሪካ የፖለቲካ ባህል ትተህ የኢሀድግን የማርጅናላይዜሽን መርዝነት ብቻ የምታገናዝብ ከሆነ ዲሞክራሲን በአንዲት ጀንበር ከሰማይ በ'ቧንቧ ወደ ኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማታንዥቀዥቅ ትረዳ ነበር ::

ማይኖሪቲ ሳንሆን በግድ ""ማይኖሪቲ ናችሁ "" ተብለን ወደ ፓርላማው መግባታችንን ባ'ላደንቀውም ባ'ልወደውም ከኃገሪቱ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ክራይስ እንጻር : በመሳርያ የተደራጀ ዝግጁ ሀይል ለጊዜው ከማጣት አንጻር ; ከኢሀዲግ ጭፍን ሽፍትነት አንጻር : ትግሉን ሳናቋርጥ ጊዜያዊ ፋታ ለማግኘት ስንል ( በሌሎች ሌሎች ...ምክናቶችም ጭምር )ፓርላማ መግባቱን እቀበላለሁ :: ይሄ መብቴ ብቻ ሳይሆን ግዴታዬም ሆኖ ይሰማኛል !

የጠላሓውን መንግስት እቤትህ ሆነህ ሳይሆን ፊቱ በጽናት ቆመህ ስታማው የህዝብን ስሜት ታሳድጋለህ :: ታጎለብታለህ :: ከምርጫው በፊት የነበረውን "" ፐብሊክ ዲቤት"" አስታውስ ምን አይነት ስነ'ልቦናዊ ውድቀት ለኢሀዲግ እንዳከናነበው :: አሁንም የኢሀዲግ ትልቁ ፍራቻ ወደ አዲሱ ፓርላማ የሚገቡት ማይኖሪቲ ፓርቲስ ሰሚ ያሳጡኛል ብሎ መስጋቱ ሽው ያለብህ አይመስለኝም :: ( ተደጋግሞ ሰለሚሰማው ስለ አጀንዳው አጀንዳው አጀንዳው ........ ጉዳይ አትንገረኝ :: ይህንን በውል የተገነዘበው ቅንጅት ""ፓርላማ አልገባም"" ሳይሆን እያለ ያለው ; መግባት የምችለው አዲስ የወጡት ህጎች ሲታጠፉልኝ ብቻ ነው :: ነው ያለው :: ይሄ ጥሩ ሪያክሽን ነው ለቅንጅት እና ለህዝብ )

የ እኔ አምነት ሁለት ነው :: አንዱ :-

ተቃዋሚው ሀይል ወደ ፓርላማው ገብቶ ግዙፍ የፖለካ ቻሌንጅ ከህዝብ ጋር እንዲፈጥር ማስቻል ነው ( እዚህጋ ማይኖሪቲ ወንበር እንዳላቸው እንደ ብዙዎቹ ልትነገርኝ አትሞክር :: ማይኖሪቲ ፓርቲ ምን ሊሰራ እንደሚችል እኔ'ና አንተ ስለማንግባባ ሳይሆን እንዳይገባህ ትፈልግ ይሆናል ብዮ ስለምሰጋ ብቻ አልፈዋለሁ )

ሁለተኛው እምነቴ :-

በህዝብ አመጽ ኢሀዲግን እናስወግዳለን ብለን የምንስማማ ከሆነ የሚገኘውን ድል በአስተማማኝ ሁኔታ ሊጠብቅ የሚችል የታጠቀ ሀይል በህቡእ ልናደራጅ ያስፈልጋል :: የተገኘውን የህዝብ ድል ልንጠብቅ ካልቻልን ደስታው ከፊታችን ሳይጠፋ የተራቡ ጩሉሌዎች ድሉን ከአይናችን ስር እንደሚጠልፉት ከህልማችን ነቅተን ልናስብበት ይገባል :: ሳትወድ በግድህ የምትጋፈጣው ረጅም ጠምዛዛ ጉዞ ከፊትህ እንዳለ እመን :: ያንን ያለመቀበል መብትህ ሲሆን ""ሳይሄዱ መድረስ "" እንደማይቻል አምኖ መቀበል ደግሞ የምትጠላው ግዴታ ነው :.

ሀገራችንን መውድድ እና በመረጥነው መንግስት መመራት መፈለግ አንድ ነገር ነው :: አካባቢያችንን መቃኘት እና ሊመጣ ከሚችል ያልተፈለገ አደጋ ጋር ዲል ለማድረግ መገድድ ደግሞ ሌላ ነገር ነው :: መዘጋጀት ደግሞ ሌላ ነገር :: ጠላትህ ጡንቻ እንዳለው መካድ አንድ ነገር ነው :: ጡንቻው አንዳለው አምነህ በኣጸፋው መዘጋጀት መቻል ደግሞ ሌላው ገጽታ ነው ::

ወንድሜ የ'ኔ 'ና አንተን የፖለቲካ አድማስ ልዩነቱን ስናጠብ አድረን ብንውል አድሜያችን ዋርካ ላይ የሚያልቅ ይመስለኛል :: ለጊዜው ግን የዎያኔን በአንቶኖቭ ጫት የማራገፉ ጉዳይ ከ እኔ የፖለቲካ አቌም ጋር ሁለቱን ምን እንደሚያዛምዳቸው ለ'ኔ ባይገባኝም በቲ-ሩም ሻይ ወይም በማስተር -ሰን ቤክስ አይተናቃቃህ ጉዳዩን ታጤነው ዘንድ በድጋሜ እጠይቀሀለሁ ::

አክባሪህ

ሳም
Last edited by ሳምቻው on Wed Oct 26, 2005 10:39 am, edited 1 time in total.
ሳምቻው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 197
Joined: Wed Jun 02, 2004 2:03 pm
Location: Germany

ድሮስ ይቀራል እንዴ

Postby አክሱማዊት » Tue Oct 25, 2005 11:39 pm

ወያኔ ሌላው ይቅርና የራሱን ሰው እንኳን አይምርም ሁሉንም ቀኑን ጠብቆ ዋጋውን ይሰጠዋል::እስር ቤት ይጠባል ብላችሁ አታስቡ:ለሰው ነው ቦታ የሚጠበው እንጂ ለ አድጊዎች ሞልቷል::

ወያኔዋ
አክሱማዊት
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Tue Oct 25, 2005 10:27 pm
Location: belgium


Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest