ኢዴአፓ - መድኅን በቅንጅት የውህደት ሰነድ ላይ ማኅተም አላሳርፍም አለ

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime. Image

ኢዴአፓ - መድኅን በቅንጅት የውህደት ሰነድ ላይ ማኅተም አላሳርፍም አለ

Postby ENH » Mon Oct 24, 2005 2:16 pm

ሪፖርተር - 23-10-2005

የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ውህደት መስራቾች አንዱ የሆነው ኢዴአፓ-መድኅን በውህደቱ ሰነድ ላይ ሰሞኑን ማኅተም እንዲያደርግ ተጠይቆ ፈቃደኛ አለመሆኑን ተጠቆመ። ይህ የፓርቲው አቋም በውህደቱ ፍፃሜ ላይ የራሱን ጥላ ማጥላቱን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

የማየተማመን ባልጀራ በየወንዙ ይማማላል

Postby አቡኑ » Mon Oct 24, 2005 3:36 pm

ታደያ ማን እነሱን አምኖ የከተላቸዋል ለራሳቸዉ ያለሆኑ ተራ ፖለቲከኞች ድሮስ ከስድስት ወር እድመ ካለዉ ፓርቲ ምን የጠበቃል እንደተባለዉ ፓርላማ ብትገቡ ይህቺ ሀገር አብቅቶላት ነበር ማፈሪያ ሁሉ!
ኢህአድግ ለዘላለም ይኑር
አቡኑ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 907
Joined: Tue Oct 11, 2005 7:42 pm
Location: Mars

Postby ጸሀይ » Mon Oct 24, 2005 10:46 pm

ሪፖርተር የሀገር ከሀዲዎች የታሪክ ቆሻሾች ልሳን መሆኑ ግልጽ ነው እናንተ ሆዳሞች ወያኔ ለዘላለም ይኑር እያላቹህ እለሙ ሆኖም በሕዝብ መዐበል ለትስጥሙ የቀራቹህ ጊዜ እሩቅ አይደለም :oops: :oops: :oops:
ጸሀይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Thu Sep 16, 2004 1:05 pm
Location: germany

አይ ጸሀይ.......?

Postby አዳል ሱማሊ » Wed Oct 26, 2005 8:39 pm

ምነው ጃል እንዳመጣላችው መናገር ይህ አባባልሽ ጦማርንና ገናናው ....ወ.ተ እነሱን ነበር ማለት የሚገባሽ ባገር ስላም እንደ አልቃይዳ የሚያሽብሩትን በተቃወምሽ :idea:
አዳል ሱማሊ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 24
Joined: Mon Oct 18, 2004 10:25 pm
Location: united states

የሪፖርተር አቁዋም እነደፖለቲካው የአየር ጸባይ ነው

Postby ዲጎኔ » Thu Oct 27, 2005 6:02 am

ሪፖርተር ገና ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ በአንዳንድ የግል መደብሮች ሳይቀር እነደ አዲስ ዘመን በግዳጅ መልክ ሲቸረቸር የነበረ በወያኔ ትኩስ የውስጥ ዜና ጠቀሜታ በነታምራት ላይ የታቀዱትን የስኩአር ማቃምና ማስቀፍደደ አይነቱን ይዘግብ ነበር

በወያኔና ሻቢያ ፍጥጫ ሰሞንናወያኔ ለሁለት በተሰነጠቀ ወቅት የነተወልደ ቡድን አፈ-ቀላጤ እስከመሆን ደርሶ ብዙ የማናውቀውን ዘከዘከልን

አሁን ደግሞ በቅርቡ ባወጣው ርእሰ አንቀጽ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን በሙሉ እንደአመጽ ቀስቃሽ ለሀገር እንደማይፈይዱ ሲኮንን ባለፉት ሳምንታት ደግሞ ሁለንተናውንና የተነቀፈበትን በተቃዋሚዎችና በብዙሀኑ ህዝብ በወያኔነት በወያኔና መሰሎቹ ደግሞ በተቃዋሚዎች ዘጋቢነት በመፈረጁ ከሁለት ያጣ ሆንኩኝ እያለ የአዞ እንባ ሲያፈስ ነበር:: ዋና አዘጋጁ ጋሼ አማረም በአሜሪካ ድምጽ ቃለ-መጠይቅ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞችን ማህበር አላውቅም እስከማለት የደረሰ ነበር::

ለማንኛውም ነገ ይነጋና ምን እንደሚል ጌታ ያሳየናል!
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Re: የሪፖርተር አቁዋም እነደፖለቲካው የአየር ጸባይ ነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Oct 27, 2005 7:23 am

ሪፖርተር ገና ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባ በአንዳንድ የግል መደብሮች ሳይቀር እነደ አዲስ ዘመን በግዳጅ መልክ ሲቸረቸር የነበረ በወያኔ ትኩስ የውስጥ ዜና ጠቀሜታ በነታምራት ላይ የታቀዱትን የስኩአር ማቃምና ማስቀፍደደ አይነቱን ይዘግብ ነበር


በወያኔና ሻቢያ ፍጥጫ ሰሞንናወያኔ ለሁለት በተሰነጠቀ ወቅት የነተወልደ ቡድን አፈ-ቀላጤ እስከመሆን ደርሶ ብዙ የማናውቀውን ዘከዘከልን

አሁን ደግሞ በቅርቡ ባወጣው ርእሰ አንቀጽ በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያንን በሙሉ እንደአመጽ ቀስቃሽ ለሀገር እንደማይፈይዱ ሲኮንን ባለፉት ሳምንታት ደግሞ ሁለንተናውንና የተነቀፈበትን በተቃዋሚዎችና በብዙሀኑ ህዝብ በወያኔነት በወያኔና መሰሎቹ ደግሞ በተቃዋሚዎች ዘጋቢነት በመፈረጁ ከሁለት ያጣ ሆንኩኝ እያለ የአዞ እንባ ሲያፈስ ነበር:: ዋና አዘጋጁ ጋሼ አማረም በአሜሪካ ድምጽ ቃለ-መጠይቅ የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞችን ማህበር አላውቅም እስከማለት የደረሰ ነበር::

ለማንኛውም ነገ ይነጋና ምን እንደሚል ጌታ ያሳየናል![/quote]

እፎይታን ማለትህ ይሆን?
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1127
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby አቡዬ » Thu Oct 27, 2005 9:26 am

አበው ሲተርቱ< የማን ዘር ነሽና በደንግል ትዳሪ ዘመዶችሽ ሁሉ ድንግል አበዳሪ> እንዲሉ ሪፖርተር ከማን ተወልዶ እዚህ ደረሰና ትክክለኛ ኢንፎርሜሽን ይስጠን ትውልደ ወያኔ እድገተ ወያኔ አንደበተ ወያኔ ድሮም ወያኔ አሁንም ወያኔ
አንድ ሰሞን እኔም ተታልያለሁ የሚሰጠው ኢንፎርሜሽን ህዝባዊነት የተላበሰ ይመስለኝ ነበር እያደር ግን ማንነቱን ቁልጭ አድርጎ በየትኛው ወገን እንደቆመ አሳየን በኔ በኩል ሪፖርተር ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚለየው ነገር ቢኖር በግል ጋዜጣ ስም መቆሙ እንጂ የኢንፎርሜሽን ምንጫቸውና አፈ ቀላቴነታቸው ለአንድ ፓርቲ የቆሙ ናቸው ስለዚህ ሪፖርተር በምንም መልኩ ህዝባዊ ሊሆን ፍጹም አይቻለውም ይህንንም ህዝቡ የሚያውቀው ይመስለኛል
ሪፖርተር ዋልታ ፋናሬዲዮ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወይን ኢፍቲን......ወዘተ የወያኔ አፈ (አንደበት) ናቸው እናም በጣም ተአማኒነት ይጎድላቸዋል
ህዝባዊ ትግል ምንጊዜም አሸናፊ ነው
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ሞት ለፋሽስቱ ወያኔ ኢሀዴግ
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

Postby ልጁነኝ1 » Thu Oct 27, 2005 12:20 pm

አንድ ወገን ከላይ አንስተውታል:: የማንዘር ሆነሽ ድንግል ይኖርሻል ዘሮቺሽ በታሪካቸው ድንግል አበዳሪዎች ናቸው ብለዋል::

እንግዲህ የምናስበው ቢኖር የዛሬዎቹ ገዥዎቻቺንና ታሪካዊ ዘመዶቻቸው በኢትዮጵያ ህልውና ላይ ምን ሰርተው አልፈዋል ነው:: ከኃይለ ሥላሴ ጉግሣ እስከ ደጃዝማች አስረሱ ድረስ ለማለት እንጂ የክፍለ ኃገሯን ሕዝብ ያለመሆኑን ልታውቁልኝ ይገባል::

የዛቺ ክፍለ ሃገር ልጆች እነ ክቡር አቶ: በላይ አባይ:: እነ ክቡር አቶ: አሰፋ ሐብቱ:: ሌሎችም ብዙና እጅግ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች እንዳሉ ይታወቃል:: ከነዚያም ውስጥ አቶ አሰፋ ሃብቱ በሞት ከማህላቺን ተለይተውናል::በህይወት በነበሩበት ጊዜ በብዙ ምክንያቶች አገኛቸው ነበር::ብዙም እንረዳዳ ነበር:: ኃሣባቸእውን ልክ እንደወንድማቸው ያካፍሉኝ ነበር::ነገር ግን ጥሩ ሰው አይበረክትም:: በማህላቺን ስለሌሉ አዝናለሁ::

ወደ መልክቴ ልመለስና በነጻ ፕሬሱ ስም ሪፖርተር የተባለ ጋዜጣ የህወኃት ዜና የፕሮፓጋንዳ ማሺን መሆኑን ከድሮው ከአመሰራረቱ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ በደንብ አድርጎ ያውቀዋል::ይህንንም ጋዜጣ በአድማ ላለማንበብ ማንበርከክ ይኖርባቸዋል::ወይ ከህዝብ ጥያቄና ከህዝቡም ጎን ሊቆም ይገባዋል::

ለናዚው ምንደኛ የህወኃትና ሻቢያ ወያኔ አመራር መቆም የለበትም ሥላለላና የተቃውሞውን ጎራ ለመምታት ለማክሸፍ ከሚጠቀሙበት አንገቱን የቀለሰ እባብ ተመሣሣይ የሚመስለው ሪፖርተር ጋዜጣ እጁን ከሊትዮጵያ ትከሻ ላይ እንዲያነሳ ይጠየቃል::

መለሰና ህወኃድ ከኃዲያን ባንዳዊያኖች በህዝብና በውድና ብርቅ የሆኑት ታጋይ ልጆቿና በእግዚአብሔርም እርዳታ ተጨምሮ ይወገዳሉ ኢትዮጵያም ያለ ልዩነትና ያለገደብ የልጆቿ ሁሉ አገርና መመኪያቸው ትሆናለቺ በዚያን ጊዜ ያሁኑ ሪፖርተርና ከኃዲዎች በታሪክ ይወቀሳሉ ይጠየቃሉም ምክንያት ቢያበዙ ደግሞ ተቀባይነት አያገኙምና መጠንቀቅ ማሰብ ይኖርባቸዋል እላለሁ ሁልጊዜ አሰራራቸውን እከታተላለሁ ጋዜጠኝነት ወገን ያልያዘና ለትክክለኛ ፍርድ ራሱን ያሰለጠነ መሆን ይገባዋል:: ከብዙኃኑም የነጻው ጋዜጠኞች ጎን ይቆማል እንጂ/ ዘር ተልጓም ይስባል የሚለውን ፍልስፍና ይዞ መንጎድ አይኖርበትም በሚል እሰናበታለሁ::

*ቀይ ባህር ዳር ድንበራችን ነው*
ደብረ ቢዘን የኢትዮጵያ አንጡራ ሐብቷ ነው:: በአድዋው የድል ምሽት ውለታ ላይ ያስምምነት አለ ነበረም ያስምምነትን ህወኃትና መሪዎቹ እስካሁን ከሪፖርተራቸው ጭምር ስሙን እንዳይነሳ አድርገዋል:: ያም በሰፊው ህዝብ ተመራጮች ኃይልና በኢትዮጵያ ህዝብም ፍላጎት ተነስቶ ማንኛውም በቁጥጥር ስር የሚሆን ነው::

ካክብሮት ጋር

ልጁነኝ1
ከ(ሰሐሊን)
ልጁነኝ1
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 641
Joined: Tue Dec 30, 2003 2:17 pm
Location: united states


Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests