አቶ አርከበ 2 ሺህ ቤቶችን ሊያፈርሱ ነው

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime.Image

አቶ አርከበ 2 ሺህ ቤቶችን ሊያፈርሱ ነው

Postby ENH » Tue Oct 25, 2005 8:15 pm

አዲስ ዜና - 25-10-2005

ጥቅምት 1 ቀን አዲሱ ፓርላማ በወሰነው ውሣኔ መሠረት ጥቅምት 3 ቀን ከንቲባው የተበተነውን ካቢኔአቸውን ሰብስበው ስለቀጣዩ የአስተዳደራቸው ሒደቶች ተወያይቷል። ከንቲባው አስተዳደሩ የ2ተኛው ሩብ አመት ዋንኛ እቅዱ ብለው ካቀረቡት ውስጥ ዋነኛው ለሼህ መሐሙዳ አላሙዲን ድጋፍ መስጠትና ክትትል ማድረግ ሲሆን፣ ለሸራተን ማስፋፊያ 40,000 (አርባ ሺህ) ካሬ ሜትር ቦታ ለመስጠት ሲባል በሸራተን አካባቢ የሚገኙ 2000 (ሁለት ሺህ) ቤቶችን ማፍረስ መሆኑን ለተሰብሳቢዎቹ ገልፀዋል።
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

ገና መጀመሪያው ነው

Postby አክሱማዊት » Tue Oct 25, 2005 11:22 pm

ለመጭው አመታት ስንት ጉድ ትሰማላችሁ:የ ቀለበት መንገዱም ቢቻል ተልጦ ወደ ትግራይ ይለጠፋል:ምክንያቱም የ አ.አ ህዝብ ምስጋና አይገባውም.

ወያኒት
አክሱማዊት
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Tue Oct 25, 2005 10:27 pm
Location: belgium

አይ አርከበ !

Postby ኩርኩፋ » Wed Oct 26, 2005 1:25 am

""ወይኔ የድሀ ጎጆዬ አይይ....ዞሮ መግቢያዬ""

እኛ ድሀዎ የሀብታሞች ህይወት ማሟሟቂያ ሆነን ቀረን አባረው አባረው የት ሊከቱን ነው ደግሞ ድሀ አዲስ አበባ አይኑር ያለው ማን ነው?
ኩርኩፋ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 387
Joined: Wed Oct 19, 2005 9:55 pm
Location: united states

Re: አይ አርከበ !

Postby ወርቅሰው1 » Wed Oct 26, 2005 2:20 am

አርከበና አል አሙዲ ናቸዋ! ኩርኩፋዬ!
እነኝህን 2 ት ዘመነኞች ቀለበት መንገዱን አሸክሞ አንድኛውን ወደ ደሴ/ሌላኛውን ወደ አድዋ ማባረ ብቻ ነው::

ደግሞ 25 ፎቅ ያለው ይላል ሌላው ተጨማሪው? ያስገርማል በየጎዳናው ስንት ሕጻና ያለ ሰብሳቢ ባሉበት አገር የሱ እንደዚህ ባቢሎን ለመስራት መሞከር ሰውዬው ያስባል ወይ ያስብለዋል::

ይልቅስ በስሙ ከአስ አበባ እስከ ክፍለ አገሮች አውራጃዎችና ወረዳዎች የሚሰሩ ስንቶች አልሚ እያሉለት እሱ የተለከፈው ቤት በማስፈረስ ላይ ነው::

ታሪክ ይቃረነዋል የሚያደርጋቸውን አማካሪዎቹ ደግሞ ህዝብን የሚንቁ የቀድሞ ፊውዳሎች ናቸው ወይም የነሱ ከሥልጣን መወገድ ያናደዳቸው ስለሆኑ ያም የተሸረበባቸው በዚያቺው አዲስ ስለሆነ ያቁጭት ሁሉ ተዳምሮ ዛሬ የሰው ልጅ ካደገበት ስንት የሶሻል ግንኙነት ካካበተበት በግዚያዊው ዶላር ቀልቡ የማይፈልግበት ተገፍቶ ሲባረር የነገን ጥያቄ ለመመለስ አላሙዲ ተዘጋጅተዋል ወይ?

ከምስጋና ጋር

ወርቅሰው1
ከ(ሰሐሊን)ኩርኩፋ wrote:""ወይኔ የድሀ ጎጆዬ አይይ....ዞሮ መግቢያዬ""

እኛ ድሀዎ የሀብታሞች ህይወት ማሟሟቂያ ሆነን ቀረን አባረው አባረው የት ሊከቱን ነው ደግሞ ድሀ አዲስ አበባ አይኑር ያለው ማን ነው?
ወርቅሰው1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4075
Joined: Wed Nov 05, 2003 9:49 pm
Location: Sehalin

ዱራሰንበት አልሰማም?

Postby ብሔረ አራዳ » Wed Oct 26, 2005 11:21 am

ይኽ ያልተቀደሰ የአር-ካበና የአላሙዲን ሕብረት ያቀደውን ጉዳይ ወንድም ዱራ ሰንበት አልሰማም? ወሬዋ ትንሽ ለብ ለብ ያለች ይመስለኛል:: አንደኛ ዛሬ የተፈጠረውን ውጥረት ተጠቅሞ አርካበ በማያገባውና ባልተመረጠበት ገብቶ ልስጥህ ቢለውም አላሙዲን እሺ የሚል አይመስለኝም;; ሰውየው የነቃና ነገንም የሚያልም ነውና አሁንም ደግሜ ደጋግሜ የምለውና የማምነው ለትንንሽ አንሿካኪዎች እየሸነሸነ ኣር -ካበ የሱ የልሆነውን ያድል ይሆናል ዛሬ የአዲስ አበባ ሕዝብ ስላልመረጠው ሊበቀል መፈለጉና በግላጭ አግኝቶት ሊጎዳውና በዚች ባለቀች ጊዜ ወዳጅ ለመጥቀም መሞካከሩ አይቀሬ ነው:: ነገንም ማሰብ መቻል ግን የሚሳነው አይመስለኝም:: እና ወገኖች መጨረሻቸው የአላሙዲንም ጭምር የሚናፍቅ ጠላታቸው ብቻ ነው:: በዚህ በተባለው መንገድ ከሄዱ ማለቴ ነው::

ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውያን!!
ብሔረ አራዳ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 39
Joined: Wed May 04, 2005 5:43 am
Location: ethiopia

ታድያ አዲስ አበባ እስከመቸ ያይጥ ማርቢያ መሆን አለባት

Postby አቡኑ » Wed Oct 26, 2005 5:26 pm

ይህ የሚደገፍ ሰራ ነዉ በርቱ አቶ አሊሙዲ በርታ አርከበ;
እነዚያ ቅንጀት መናመንት የሚባሉት እንደሆን ወደ ገደሉ አፋፋፍ ደርሰዋል የንሱ አይሰጋም ሽማገሊዉም አላረፍ ካለ ማሰወገደ ነዉ የልቁን ተሰማምቶ ቢእአራ ምከሩት ላባባ ሐይሉ አለበለዚያ እዚያው ሸል ሂዶ አለያም ዝም ብሎ ይኑር የዶክተር ስብሰብ እንድውሆን ላገሪቱ የወደፊት ፖለቲካ ምንም አይፈይደም ይልቁን ፖለቲካዉን ለን ወንዱ መለስ ተዉላቸዉ
አቡኑ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 907
Joined: Tue Oct 11, 2005 7:42 pm
Location: Mars

Postby ዞብል2 » Wed Oct 26, 2005 5:56 pm

አርከበ እቁባይ ከሚባል ነቀርሳ ምን ይጠበቃል ድሮስ? ለነገሩ መሬቱ ተገፍቶ የትም አይሄድ ይሄ ነፍሰ በላ ወያኔ :evil: ሕይወታቸውን ላጡት 42 ንጹሃ ዜጎቻችን አንዱ ተጠያቂ ነው ምክንያቱም 3ሺ ቦዘኔ በአንድ ምሽት አፍሳለሁ እያለ አፈሙዙን ደግኖ ሲያነጣጥር የነበረ አንዱ "ደም መጣጭ ድራኩላ" ነው :evil: :twisted: :evil: :twisted:

ዞብል ከፒያሳ
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2029
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

አዲስ ዜና አለኝ

Postby አክሱማዊት » Thu Oct 27, 2005 2:20 am

ወያኔ ቻይና አገር ውስጥ ፎቅ ይሚነቅል ካምፓኒ ጋር እየተነጋገረ ነው::አላማውም ያው አ.አ ያለውን እየነቀለ ወደ ቲግራይ ለመላክ ነው መቀሌ እንኳን ቦታ የለም ግን ወደ ገረአልታ ይላካል ተብሏል::

የወያኔ ደጋፊ
አክሱማዊት
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 9
Joined: Tue Oct 25, 2005 10:27 pm
Location: belgium

Postby ሰበቡ » Thu Oct 27, 2005 3:24 pm

ተ የደላው መንግስት ተሸንፎም ሊቆጣጠር ያሰኘዋል
ሰበቡ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 127
Joined: Thu Oct 13, 2005 5:01 pm
Location: UK

Postby በማእረጉስ » Sun Oct 30, 2005 12:18 am

አክሱማዊት ምናልባት የምታስቢው በራስሽ ባይሆን ነው እንጂ በጢናሽ ኣይይደለሽም መንገዱ የታቀደው ብድሩም የተገኘውኮ በደርግ ጊዚ ነበር:: ወያኒ የትኛውን መንገድ አይቶ ነው ስለመንገድ እቅድ የሚያቅደው? በዘርና በጎሳ ከመከፋፈልና ሀገርን ድንበር አልባ ከማድረግ በቀር የቀረው ሁሉ ልማት በደርግ ጊዚ የታቀደ መሆኑን ባታውቂ ነው! ለነገሩ ያኒኮ አንቺም የነበርሽበትን ታውቂዋለሽ!
በማእረጉስ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 20
Joined: Sun May 29, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia


Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest