ልሳነ ሕዝብ - 28-10-2005
የቅንጅት ተመራጮች በየሚኖሩበት ክፍለ ከተማ፣ ቀበሌና፣ ፓሊስ ጽ/ቤቶች እየተጠሩ ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ ከተሠጣቸው በኋላ ከተመራጭነት ራሣቸውን ካገለሉ 500 ካሬ ሜትር ቦታና 50 ሺህ ብር እንደሚሠጣቸው እየተነገራቸው ሲሆን አዲስ አበባን በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀረበው ሃሳብ መሠረት ቅንጅት ፓርላማ እንዲገባ የአንድ ሳምንት ጊዜ ተሰጥቶት የማይገባ ከሆነ ኢህአዴግ አዲስ አበባን በዘላቂነት ይረከባል።