የሼህ አል-አሙዲንና የአቶ ስብሀት ነጋ ጉድ ወጣ

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime.Image

የሼህ አል-አሙዲንና የአቶ ስብሀት ነጋ ጉድ ወጣ

Postby ENH » Wed Nov 02, 2005 12:17 pm

አዲስ ዜና - 1-11-2005

በሼህ ሙሀመድ ሁሴን አልአሙዲንና በአቶ ስብሀት ነጋ አቀነባባሪነት 11 ሺህ ታክሲዎችን ወደ አዲስ አበባ በማስገባት አሁን ያሉትን ታክሲዎች ለማስቆም የተዘረጋው ፕሮጀክት ለጊዜው እንቅፋት እንደገጠመው የአዲስ ዜና ምንጮች ገልፀዋል።
ENH
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 198
Joined: Fri Oct 03, 2003 10:37 pm
Location: Addis Abeba, Ethiopia

አይ ነገ

Postby ማንትሩ » Wed Nov 02, 2005 5:30 pm

ይህ ጥጋብ እስከመቼ ይሆን ኢትዮጵያዊው ቢላደን አላሙዲ ይህች ቀን ስታልፍ የት እንደምትገባ ይህ ብር ሽባ ነው የሚያረግህ ከሰራህው ያጠፉህው በኢትዮ ህዝብ ላይ በርክቶዋል መጨረሻህን እናየዋለን ነገ
ቸር ያሳየን
ማንትሩ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 58
Joined: Mon May 16, 2005 9:45 pm
Location: united states

Postby ድራኮላ7 » Mon Nov 07, 2005 8:09 pm

አባባላችሁ ግልጽ አይደለም ጊዜው የነጻ ገበያ ጊዜ ነው ገንዘብ ያለው ይስራ ሌላውም ድሀ እኮ ፈጣሪ አምላክ አለው እንደአሙዲ ብር ባይኖረውም : ንግግራችሁ ግን የቅናት ይመስላል :: ብዙ ለመስራት እንጂ ብዙ ለማግኘት አትመኙ
ድራኮላ7
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 116
Joined: Wed May 25, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

ያገርና የህዝብ ጥቅም ይቅደም?

Postby ቃኘው » Mon Nov 07, 2005 11:26 pm

ስማ ወንድሜ!
አንድ ነገር እንድል ፍቀድልኝ!!! ኢትዮጵያ ሀብታም ሆና ነው እንዴ አል አሙዲ ሁሴን የተባለ ኃብታም:: 7 ዓመት ሙሉ ለሚሰራቸው ሥራዎቹ የአገር ቀረጥ ሳይከፍል የሚሰራው?

በተጨማሪ አገሪቱ በዚህ ከጣሊያን ከወያኔ ከሻቢያ ጦርነቶች ውስጥ ከሶማሌ ወራረ ጋር እየታገለች ያቋቋመቻቸውብ ቀላል ከባድ እንዱስትሪዎች በትንሽ ገንዘብ ገዝቶ ነው እንዴ ሀብታም የሚባልልን:: ኢትዮጵያ ሰጠቺው እንጂ እሱ ቤሣ እንዳልሰጣ እንድታውቅ::

ይህን የማፍያ ቡድን ህወኃት ወያኔና ነጋ መለሰና በረከትን:: በመቃወም ከባልደረባቸው አላሙዲ ሁሴን ጋር በመወቀሳቸው ይሆን እንዴ ስለ ኃብታሞች ህይወት ብቻ ልታወሩልን የፈለጉት?

ወገኔ
እንደሱ አይደለም:: አዲስ አበባ ውስጥ ቀለበት መንገድ ከመሰራቱ በፊት ለደኃው ማረፊያና አቅም ለሌላቸውም የጡረታ ቤትና የህክምና መዓከል በነጻ መሠራት ነበረበት:: እንዲሁም ያየባቢሎናዊያን መሥፈሪያ የሆነው ሸራተን እስከ ዛሬ በደኃው ሕይወት ላይ ምን እያደረሰ እንደሆነ ሊያውቁት ቺለዋል ወይ?

አቶ: ሼሁ መሐመድ አለአሙዲ ሁሴን የሚያስብ ጭንቅላት ቢኖራቸው ኑሮ? ያለትን የቀራትን የወርቅ ማምረቻ ቦታዎቿን በ60 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ከወያኔ ኤፌርት ኮምፓኒ ባልገዙ ነበረ:: ቢያንስ ለመጪው ትውልድ አለኝታውን በመግፈፍ በቶን የሚገመት ወርቆች በማምረት ያገሪቱን ህይወት ባልበዘበዘም ነበር::

ያኔ ወጣት ሣለሁ "ክፉ ውሻ አለ ወደ ግቢው አትቅረብና
ቀጥሎም በሚያሳጥሩት ዙሪያ ግንባቸው ላይ ሽቦና በሲሚንቶውም ላይ የጠርሙስ ስባሪ ይከሰክሱ የነበሩ በወቅቱ ሞጃዎች ይባሉ የነበሩትን አስታወስከኝ::

በሰለጠኑት አገሮች ሃብታሞች እንዲኖሩ ይፈለጋል:: በዚያው ልክ ደግሞ ለአገሪቱ ግንባታና የሶሻል ሕይወቶች ዋናዎቹ ሪሶርሶች ኃብታሞች ናቸው በሚከፍሉት ቀረጥና በሚያሰሯቸው ሠራተኞች ድጋፍ በመስጠታቸው:: በአገራቺን ግን ያይስተዋላል ወይ::

ወያኔውም ልብላ ሃብታሙም ልብላ ደኃውን ማን እንዲያስታውስልዎ ይፈልጋሉ የተመጣጠነ ሁኔታን መፍጠር ይገባል ነው ጥያቄው:: አላሙዲ ስሙ እስልምና ተከታይ ይሁን እንጂ!!! እስላም ማለት ሠላም ማለት ነው:: ይህ ሰው ግን ከእባብ የበለጠ በስውር ሰዎችን የሚነድፍና የሚያስነድፍ ጥቂት አጨብጫቢ ባንዳዎች በዙሪያው ያደረገ ነው::

እኛ ኢትዮጵያዊያን የሁሉም ማህበረሰብ ልጆች ብዙ እናውቃለን ባህል ሆኖ እየሞትንም አለን እንላለን ገዳዮቻቺንን እያወቅናቸው ሳንናገር እናልፋለን ለዚያም ስል ነው ይህን ሰው ያደረጋቸው ነገሮቺን እንድታስብ ይገባኃል:: ከማን ጋር ነው የቆመው:: ንቦ ወይስ ዝንቦ ከሚባለው የማፍያ ቡድን ጋር አይደለም እንዴ የቆመው:: የአርከበ በጆሮው የሚያንሾከሹከው ነጋዴ ግለሰብ ማነው? አርከበ በመሸነፉ ያዲስ አበባ ህዝብና መላዋም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዜጎች ደሆች ስለሆኑ መደብደብ ይኖርባቸዋል::

ፍርዱ ና ቀኑ ይመጣል ሁሉም እንደስራው ያገኛዋል:: የፖለቲካ ፓርቲ አባል አይደለሁም አገሬን የማፈቅር ኢትዮጵያዊነት የሚለውን ስም ብቻ ዤ ነው የጠየቅሁህ እነዚያን ቅንጅቶች እያላቺሁ እንዳትናገሩኝ አስጠነቅቃለሁ ዕለት በዕለትም በአገራቺን ላይ ግፍ የሚፈጽሙባት እነማን እንደሆኑ እረዳለሁ:: በዚያ ምክንያት ብዙ ተናገርኩ መሰለኝ::

አመሰግናለሁ

ቃኘው
ከ(ሰሐሊን)
ድራኮላ7 wrote:አባባላችሁ ግልጽ አይደለም ጊዜው የነጻ ገበያ ጊዜ ነው ገንዘብ ያለው ይስራ ሌላውም ድሀ እኮ ፈጣሪ አምላክ አለው እንደአሙዲ ብር ባይኖረውም : ንግግራችሁ ግን የቅናት ይመስላል :: ብዙ ለመስራት እንጂ ብዙ ለማግኘት አትመኙ
tank you
ቃኘው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Thu Oct 23, 2003 11:35 pm
Location: Man

Postby ድራኮላ7 » Tue Nov 08, 2005 10:52 am

አትበሳጭ ወንድሜ ለኢትዮጵያ ተቆርቁዋሪው በዛ ማለቴ በአፍ ተግባር ላይ ዜሮ አሁን አሁን ምንጭ የሌለው ጽሁፍ እየበዛ ሄዱዋል እንደ ጎዳናው ጋዜጣ : ማንበብ ነው ያንተንም አነበዋለሁ ሠላም ለኢትዮጵያ !!!
ድራኮላ7
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 116
Joined: Wed May 25, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

የማምንበትን ነው የምነግርህ

Postby ቃኘው » Tue Nov 08, 2005 6:59 pm

ግዜው የጉድ ነው:: "ጉድ አንድ ሰሞን ነው" ይባላል:: እኔ ጎዳናው የሚባል ጋዜጣ አላውቅም የምታውቀው አንተ ነህ ነገር ግን የምናገረው መልስም የሰጠሁት የማስበውን ነው::

ከተናገርኩት ውስጥ ደግሞ አንድ ሃብታም እስከዚያ ሄዶ የወርቅ መአድናትን የኒኬልና የንጥረ ነገሮችን ሁሉ በቁጥጥሩ ስር ማድረግ የለበትም::

ወያኔን የም ዕራቡ አገሮች እስካሁን እድል የሰጡት ህዝብን እንደ ሙጃ ሲጨፈጭፍ እስከዚህም ግድ ያልሰጣቸው እንዲሁም የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒቴርም ቁብ ያላደረገው አስደናቂ የሆነበትም:: ወያኔ ፋሺስቱ መለስ የአገሪቷን አንጡራ ኃብት በርካሽ ዋጋ ስለሸጠላቸውና ከዚያም የጥቅሙ ተካፋይ ቀደም ብሎ ስለ አደረጋቸው ነው:: ያም የተፈጸመው ከ 1998-1999 ድረስ በአውሮጳ አቆጣጠር ነው:: በዚያን ወቅት አላሙዲ ሁሤን የኢትዮጵያን ያላትን ቅሪቶቿን እንዳለ ውሰደ:: አዲስ አበባም አያት ቅድሚያቶቻቸው የተቀበሉበትንና ጠዋትም ማታም ሄደው የሚጎበኟቸውን አጽማት ሳይቀር እንዲረሱና እነኛም በሻራተን ስፍራ የነበሩ በራሳቸው ቺግር ተጠምደው ከኌላቸው ያሉትን እንዲረሱ ሆነዋል::

ይህ ሰውን ስለተቃወምኩት ይመስለኛል እንዳተው ሰው ሆኜ ጽፌ ለወገኖቼ የላኩትን መልክቴን እንደ "ጎዳናው ጋዜጣ ትርጉም የሰጠኸው" ይህ አባባልጅህ ግን ጊዚያዊ እንደሆነ ይረዳኛል::

ጂቡቲ የገዛ ወደቧን ለውጪ የአረብ ካምፓኒ እንዲትሸጥ የደለለና በዚያም ጥቅም ውስጥ አላሙዲ 80% የሚያገኝ መሆኑን አትዘንጋው:: አሁን ደግሞ በርበራን ወደብ ጨርሶ ለመግዛት ይፈልጋል:: በኢትዮጵያ ላይ ነገደባት ይህ ሰውን መቃወሜ ያስመሰገነኛል እንጂ ትቺት አያሰነዝርብኝም እላለሁ::

ለማንኛውም ቀረጥ እንኳን በአግባቡ ከውዝፉ ጭምር ሊከፍል ይገባዋል:: የጎዳና ተዳዳሪዎቹ በዚያ ገንዘንዘብ ቤትና ምግብ ልብስና ጤንነታቸው እንዲጠበቅበት::

ካክብሮት ጋር

ቃኘው
ከ(ሰሐሊን)ድራኮላ7 wrote:አትበሳጭ ወንድሜ ለኢትዮጵያ ተቆርቁዋሪው በዛ ማለቴ በአፍ ተግባር ላይ ዜሮ አሁን አሁን ምንጭ የሌለው ጽሁፍ እየበዛ ሄዱዋል እንደ ጎዳናው ጋዜጣ : ማንበብ ነው ያንተንም አነበዋለሁ ሠላም ለኢትዮጵያ !!!
tank you
ቃኘው
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 500
Joined: Thu Oct 23, 2003 11:35 pm
Location: Man

Postby ድራኮላ7 » Fri Nov 11, 2005 6:54 pm

ተወው ወንድም አለም ወሬህ በሙሉ ጫት ቤት የሚተረክ ተረት ተረት ነው ለማንኛውም ጭብጥ እየያዝክ አውራ ሰላም ሁን
ድራኮላ7
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 116
Joined: Wed May 25, 2005 10:19 pm
Location: ethiopia

What an Observation!!!

Postby ሁሉቃ » Fri Nov 11, 2005 8:21 pm

ድራኮላ7 wrote:ተወው ወንድም አለም ወሬህ በሙሉ ጫት ቤት የሚተረክ ተረት ተረት ነው ለማንኛውም ጭብጥ እየያዝክ አውራ ሰላም ሁን


አንድ አንዴ ትርጉም የማይሰጥ ነገር ለመቸክቸክ ምናጠፋውን ጊዜ ምን አለ..ሀገራችን እውን እኛ እንደምናስባት ናት? ለምን በስሜት እንነዳለን የሚለውን ጥያቄ እየጠየቅን ስለ ኢኮኖሚዋ..ሰለፖሊሲያችን ብናነብ ብዙ ከመዘብዘብ እንቆጠብ ነበር.....
ድራኩላ... I really appreciate the way u expressed this NON SENSE WRITER!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ሁሉቃ
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Sun Feb 29, 2004 5:25 pm


Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests