ዲጎኔ wrote:
የተከበሩ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩን የማከብር እንጂ አፌን የማጣብቅባቸው አይደለሁም ስለዚያ መጽሀፍም ሆነ ያኔ ስለተወገዙ ታላላቆቼ የምጮህው
መጽሐፉን በሚመለከት ቀደም ሲል
"የምትለውን የአለቃ አያሌው መጽሐፍ ስሙን ሰምተህ ሳይሆን ገጾቹን አገላብጠህ አንብበህ የምታውቀው ከሆነ በየትኛው ገጽ ላይ ግዝት መፃፉን ጠቅሰህ አሳየንና የምትናገረውን እውነትነት አረጋግጥ :: " ብለን ላቀረብንልህ ጥያቄ መልስ ከሌለህ ስለ መጽሐፉ ለማያውቁና ይህንን ሊያነብቡ ለሚችሉ የዋርካ ታዳሚዎች የሚከተለውን አቅርበናል
የመጽሐፉን ሽፋንና የመጀመርያ ገጽ ያየ ስው እንኳን እንደሚያነበው
1. መጽሐፉ አባ አየለ ተክለ ሃይማኖት የተባለ ካቶሊካዊ የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ስለ ክርስቶስ ባህርያት አካላዊ ተዋህዶ የምታምነው ትምህርት በሚል ስም ሐምሌ 9 ቀን 1951 ላወጣው መጽሐፍ ሙሉ መልስ ሆኖ የተዘጋጀ ነው::
2. አባ አየለ በመጽሐፉ ሽፋን ላይ የኢትዮጵያን ካርታ ሰርቶ አንበሳው (በወቅቱ የኢትዮጵያ አርማ) የቫቲካንን ሰንደቅ ዓላማ እንደያዘ ስላሳየ በወቅቱ ሊቀ ጠበብት አያሌው ታምሩ የመልስ መጽሐፉን "መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና" ብለውታል:: ተኩላ የሮማውያን አርማ እንደነበር ያጤኗል::
3. ከሽፋኑና የመጀመርያው ገጽ አልፎ መጽሐፉን በጥሞና ያነበበ ደግሞ መጽሐፉ አንተ እንደምትለው"የግዘት" መጽሐፍ ሳይሆን በካቶሊክና ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነቶች መሀከል ያለውን ልዩነት አለቃ አያሌው ታምሩ መጽሐፍ ቅዱስን እና ታሪክን ተመርኩዘው በዝርዝርና በጥልቀት ያስተማሩበት ድንቅ ሥራ መሆኑን ሊመሰክር ይችላል!
ዲጎኔ wrote: በአንዲት ቅድስት ጥንታዊት የሀዋርያት ቤተክርስቲያን ትውፊት የማምን በመሆኔ..
እዚህ ላይ ትውፊት ያልከው በእንግሊዝኛው Holy Tradition የሚባለውን ከሆነ ብዙ "Sola Scriptura" ባይ ፕሮቴስታንቶች የሚቃወሙት በመሆኑ ገርሞናል ...ለማንኛውም የተነሳንበት ነጥብ በአባታችን በአለቃ አያሌው መጽሐፍ ላይ የሰነዘርከው አስተያየት ነውና ስለትውፊት ከፈለግህ በዋርካ general ላይ አዲስ ርእስ ክፈትና መወያየት እንችላለን::