የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና ፓርቲዎች ውይይት እንዲጀምሩ ጳጳሳት ጠየቁ

The news in Amharic from Ethiopia are stopped as a result of the total repression of the Free Press by the TPLF/EPRDF regime. Image

Postby አቡዬ » Fri Dec 09, 2005 10:38 am

ውድ ዲጎኔ ብዙ ጊዜ የምጸጣቸውን አስተያየቶች አነባለሁ በዕውነት በጌታ ላይ ባለህም እምነትና መመካት አደንቅሀለሁ
ጌታ አሁንም አብዝቶ ይባርክህ አንድ ነገር ግን ልል ዕወዳለሁ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች አንተ የምሰጣቸውን አስተያየቶች ከዕምነት ግሩፕ ጋር እያያያዙ የጠጣመመ ወይም ወደ አንድነት የማያመጣ አስተያየት ሲሰጡ አያለሁ
ይህ መልካም አይደለም አንተን ማለቴ አይደለም ግን አንተን ለማለት የምወደው ነገር ቢኖር እንደዚህ አይነት አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ሲነሱ መልስ ከመስጠት ብትቆጠብ መልካም ነው ሰዎች በዚህ ዘመን የጌታን ቃል እራሳቸው በሚፈልጉትመንገድ እንጂቃሉ እንደሚለው አይወስዱትምና
ዋናም ደግሞ የዕምነት ግንብ ሰርቶ እኔ ኦርቶዶክስ ስለሆንኩ ወይም ካቶሊክ ወይም ደግሞ ፕሮቴስታንት ስለሆንኩ በማለት ሳይሆን መዳን የሚገኘው በአንድ ልጁበክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ ማመኑ ስለሆነ የየትኛው ድርጅት አባል መሆን እንደማያድን በማወቅ በዚህ መልኩ የሚመጡብህን ባታስተናግድ መልካም ነው
አቡነ ተጋዳላይ ጳውሎስንም ማንም ሰው የሚያወግዘው በእምነት አባትነቱ የሚፈለግበትን ባለማድረጉና እንዲያውም ከፋሽስቶች ስለወገነ ይህ ሁሉ ህዝብ ሲጨፈጨፍ በዝምታ በማለፉ እንደ ግለሰብ እንጂ በኦርቶዶክስነቱ አይደለም ስለዚህ የካቶሊኩ ድርጅት በዚህ በድፍረት ወጥተው መናገራቸው ይበሉ የሚያሰኛቸው ነው አሁንም በግልጽ እንዲታወቅ የምፈልገው የምተቸው አባ ተጋዳላይ ጳውሎስንና የርሱን ተከታዮች እንጂ ኦርቶዶክስን አይደለም
ወንድም ዲጎኔ በዕምነት ድርጅቶች መካከል ባለ ልዩነት ክርክር ሊያነሱብህ የሚሹትን ወደ እግዚአብሔር ቃል (መጽሀፍ ቅዱስ) ምራቸው እንጂ መልስ አትስጣቸው
አክባሪህ አቡዬ
በቸር እንሰንብት
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

እሺ አቡዬ ሆድዬ ምክርሽን ተቀብያለሁ

Postby ዲጎኔ » Fri Dec 09, 2005 5:09 pm

እሺ ውዴ አቡዬ ሆድዬ ማለፊያ ምክርሽን ተቀብያለሁ

አሁንም ለዘለአለምም ከወገን ከነገድ የጠራን በክቡር ደሙ የተዋጀን ማዳላት የሌለበት ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው ለሀጢያታችን በመስቀል ተሰቃይቶ የሞተው በሶስተኛው ቀን ከሙታን የተነሳው በክብር በግርማ የሚመለሰው ይክበር!

የትንሳኤ ጌታ በግፈኞች የምትስቃየውን ኢትዮጵያን ያስባት!አሜን አሜን አሜን

ዲጎኔሞረቴው ከአንዲት ቅድስትጥንታዊት ማህበረምእመናና
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby አቡዬ » Fri Dec 09, 2005 10:15 pm

አመሰግናለሁ ወድ ወንድሜ ምክሬን ስለተቀበልከኝ እርስ በራሳችን ተግሳፅ ያስፈልገናልና ለማንኛውም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር ይባርክህ
የጾታ ማረሚያ እንድሰጥ ይፈቀድልኝ ውድ ወንድሜ እኔም እንዳንተ ወንድም ነኝ
በቸር እንሰንብት
አቡዬ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 240
Joined: Tue Jan 06, 2004 6:17 pm
Location: united states

Re: በአዲሱ የማብራሪያ ርእስ እስማማለሁ

Postby Acts 8:26-39 » Sat Dec 10, 2005 2:06 am

ዲጎኔ wrote:እሺ ወዳጀ ልቤ ግብረ ሀዋርያ

"ሌላ ትርጉም እስካልተሰጠው ድረስ "በሚለው የቀደመው አባባል አዲስ ያቀረብከውን የመጽሀፉን አማራጭ ርእስ እየደግፍኩ በእርግጥ ልዩነቶችን ለግንዛቤ የሚያስተምር ይዘትና አላማ ካለው ቅኝትህን አቅርብልን::

በተረፈ ወደወቅታዊ ጉዳዮች እንመለስና ካቶሊኮቹ በይፋ የወያኔን ድርጊት በማውገዝ እርቅና ሰላም የሚወርድበትን ሲጠቁሙ አጣሪ ኮሚሽን ተብዬ የቤተሀይማኖት ተጠሪዎች
ምን ይባላሉ?ተለጣፊ/አደናጋሪ /አዘናጊ ኮሚሽን?

በብዙዎቹ የአለም ሀገሮች የሀይማኖት መሪዎች ከህዝብ ጋር ቆመው አምባገነኖችን ሲያወግዙ የእኛዎቹ ከጥቂቶቹ በቀር "ወያኔን ሺ አመት ያንግስልን' የሚሉት ለምን ይሆን?

እስኪ የእውቁን ደራሲ የዶ/ር አዲስ አለማየሁን "ፍቅር እስከመቃብር" በምናባችን እያሰብን እንደ ጋሼ ጉዱ ካሳ እበላ ባዮቹን የአባ ሞገሴ አይነቶቹን እናጋልጥ:'ጴጥሮስ ያችን ሰአት' ድራማንም እያሰብን ለሀገራችን ሰማእታት የሆኑትን የጀግኖች አባቶቻችንን ፈለግ እንከተል::

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
ዲጎኔሞረቴው የኢትዮጵያ ቅርስ አንድነትና ትውፊት አክባሪ


ዲጎኔ
እኛ እንዲህ ተብሎ ቢጠራስ ያልነው ያንተ ችግር ስያሜው መስሎ ስለታየንና የውይይቱ ትኩረት በመጽሐፉ ይዘት: በውስጡ በሰፈረው ጥልቅና ዝርዝር ክርስትያናዊ ትምህርት ላይ እንዲሆን በነበረን ፍላጎት እንጂ አባታችን አለቃ አያሌው ለድንቅ ሥራቸው የሰጡትን ስያሜ ቢቀየር ከሚል ሐሳብ ከቶ አይደለም::

ለማንኛውም በጉዳዩ ላይ የተስማማን ይመስላልና እዚሁ ላይ እንቋጨው::

መጽሐፉን በሚመለከት "በእርግጥ ልዩነቶችን ለግንዛቤ የሚያስተምር ይዘትና አላማ ካለው ቅኝትህን አቅርብልን" በማለት ያቀረብከውን ሐሳብ ተቀብለነዋል::

ለጊዜው Oct 18, 2005 የጀመርናቸውን
1. የፕሮቴስታንት ሃይማኖት መስራች ማርቲን ሉተር ማን ነው ?
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... hp?t=12710

2. የፕሮቴስታንት ሃይማኖት መስራች ማርቲን ሉተርና ፀረሴማዊነት
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... hp?t=12712

የሚሉ ርእሶች ስላሉን:እነሱን ካጠናቀቅን በኌላ የምናደርገው ይሆናል::
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

የዶክተር ማርቲን ሉተር ያለ ኢትዮጵያዊ አሁን እጅግ ያስፈልገናል

Postby ዲጎኔ » Mon Dec 12, 2005 9:46 am

ወዳጄ ልቤ ግብረ-ሀዋርያ

የመጀመሪያው ምኞቴና ጸሎቴ እንደስያሜህ ግብረሀዋርያዊ መጣጥፎችን እንድታቀረብ እንጂ ባለፈው እንደጠቃቀስኩልህ እነ ኒችን የመሰለ የ19ኛው ክፍለዘመን የክህደት አስተማሪና የ21ኛው ክፍለዘመን ጸረክርስትና ጸሀፊ የነካኒንግሀምን ኑፋቄ እንድትዘግብልኝ አይደለም::
የእነዚህን ከሀዲዎች መጣጥፍ ብፈልግ ከአንተ የውራጅ ዘገባ ይልቅ ቀዳማይ ጽሁፎቻቸውን ካለሁበት አካባቢ በሚገባ ማግኘት እችላለሁ ::
በተረፈ ስለ ዶ/ር ማርቲን ሉተር አንተና መሰሎችህ ከነቃፊዎች እየቃረማችሁ ባቀረባችሁ ቁጥር እኔና መሰሎቼ ለዚህ የሚሊኒየሙ የእምነትና የለውጥ አራማጅ ሰው ያለን አድናቆት ጨምሯል::

እንደአንተ ሳልዘበዝብ በአጭሩ ላስረዳህና ነገሬን ልቁዋጭ:
በመጀመሪያ ደረጃ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ቤተክርስቲያኑ እስከመጨረሻው ድረስ ካቶሊካዊት መሆኗን በጽሁፉ የመሰከረና በዚያችው ቤተክርስቲያኑም የተደረገበት ግዝት ከ500 አመታት በሁዋላ ተነስቶለት እንደትክክለኛ አስተማሪ በመቆጠሩ እርሱን ለቀቅ አድርጋችሁ ስለ እራሳችሁ አንጋፋ ሊቃውንቶች አለቃ ታዬ: አለቃ ተወልደመድህን ገብሩና መሰሎች ግዝት-ምክክር እንዲደረግ ለቤተክህነት ሀሳብ አቅርባችሁ ምህረት ባለማድረግ በረከት ያጣችውን ቤተክርስቲያንና ሀገር ታደጉዋት::

በሚቀጥለው ጊዜ ደግሞ የዳቪንቺ ኮድን ዋቢ አድርገህ ከምታታክተኝ ወደወቅታዊው ጉዳይ አቅንተህ ለእናት ኢትዮጵያ መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ጭቆና እንደ ዶ/ር ማርቲን ሉተር የሚጋደል ጳጳስ: እጨጌ ወይም ቄሰ-ገበዝ መጣጥፍ ብቻ እንድታቀርብ በትህትና እጠይቅሀለሁ::

አክባሪህ ዲጎኔ ሞረቴው ለእናት ኢትዮጵያ መታደስ ዘጋቢ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Acts 8:26-39 » Tue Dec 13, 2005 2:29 am

ዲጎኔ

የአለቃ አያሌውን መጽሐፍ ሳታነብ ተቃወምክ የማርቲን ሉተርን ደግሞ ሳታነብ ትደግፋለህ....
የምትጽፋቸውን ጽሁፎች ሰው የሚመዝን አይመስልህም? ወይስ የዋርካ ታዳሚን intelligence ንቀኸዋል?
ለምሳሌ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት መስራች ማርቲን ሉተርና ፀረሴማዊነት
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... hp?t=12712
በሚል የሚቀርበው መጽሐፍ "on the Jews and their lies" ማን ነው የጻፈው? ራሱ ማርቲን ሉተር አይደለምን?

የፕሮቴስታንት ሃይማኖት መስራች ማርቲን ሉተር ማን ነው ?
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... hp?t=12710በሚለውስ ላይ በመቅረብ ላይ ያለው የሕይወት ታሪክ የማን ነው? የተጠቀሱት ጥቅሶች ከማን የተገኙ ናቸው?

ስለ ማርቲን ሉተር ሕዝባችን እንዳያውቅ የምታከላክሉበት ምክንያት ከማስገረም አልፎ አጠያያቂ ሆኖብናል:: ለማንኛውም ይህንን በሚመለከት ጽሁፎቹን ማውጣት የጀመርን ስሞን ላነሳሃቸው የተለያዩ ተቃውሞዎች በወቅቱ ምላሽ መስጠታችንን ማንም ሊያየው የሚችል ነውና አንመለስበትም:: ይህ አምድ የሃይማኖት አምድ ባለመሆኑም አዲስ የምታቀርበው ጉዳይ ካለ ዋርካ ጄነራል ላይ እንገናኝ::
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

ያመንኩትን አውቃለሁ የማነበውንም

Postby ዲጎኔ » Tue Dec 13, 2005 6:41 am

"ያመንሁትን አውቃለሁና" እንዲሁም የማነበውን(2ጢሞ1:12)

ለትምህርትና ለመታነጽ የሚነበበው ፍቅርን የሚያመላክት በስጋም በነፍስም በረከትን የሚያጎናጽፍ እንጂ የሚገዝትና የሚከስ ጽሁፍ ተቀምሶ መጣሉም ይበዛባታል::

1. የአለቃ አያሌውን "መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና" የመጨረሻ ቃል ልተው አያንጸኝም አላነብም ሌላው ወገኔ እንዲያነብ አልመክርም: ያንጻል ብለህ ሽንጥህን ገትረህ ስለምትከራከርለት ቅኝቱን ጀምረውና በቃሉ ይፈተሻል


2.የኒችና ካኒግሀም የ20ኛውና የ21ኛው ክፍለዘመን የክህደት አስተማሪዎችን የኑፋቄ ጽሁፎች ስለዶ/ር ማርቲን ሉተር ውንጀላ እጅግ በዘረጠጥከው አምድህ ላይ ሴም የተባሉ እንደጠቀሱት እኔም ለ2ና ሶስት ሴሚስተሮች ለንጽጽራዊ ክሪቲሲዝም አንብቤአቸዋለሁ የአንተን ትርጉም ግን ከጨረፍታቅኝት ባሻገር ያለማንበቤ ሊያስወግዘኝ አይችልም

አሁንም ወደዚህ አምድ ርእስ ልመልስህና የጀርመንን የዚያን ዘመን መንፈሳዊና ስጋዊ ባርነት ዶ/ር ማርቲን ሉተር እንደተፋለመ ሁሉ የወቅቱን የኢትዮጵያ ሰቆቃ የሚጋራና የሚያስወግድ ተምሳሌት ብቻ ብናቀርብ ይመረጣል

ዲጎኔሞረቴው ከኢትዮጵያ መንፈሳዊና ስጋዊ ተሀድሶ ግንባር
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Acts 8:26-39 » Tue Dec 13, 2005 7:14 am

ዲጎኔ
"ይህ አምድ የሃይማኖት አምድ ባለመሆኑም አዲስ የምታቀርበው ጉዳይ ካለ ዋርካ ጄነራል ላይ እንገናኝ ::"ብለንህ ነበር:: ሆኖም አንብቦ የመረዳት ችግር ስላለብህ ያንኑ ይዘህ እዚሁ ተመለስክ:: ታድያ ይህ ከቸገረህ ያላነበብከውን መጽሐፍ ብትደግፍና ብትቃወም እንዴት ይፈረድብሃል?

""on the Jews and their lies" ማን ነው የጻፈው? " ብለንም ጠይቀንህ ነበር....ፍየል እዚህ ቅዝምዝም እዝያ እንዲሉ ስለ "የኒችና ካኒግሀም የ 20ኛውና የ 21ኛው ክፍለዘመን የክህደት አስተማሪዎችን የኑፋቄ ጽሁፎች" ታወራለህ:: Schizophrenic የመሆንህ ምልክቶች ናችውና ታሳዝነናለህ...ብዙ በመቀባጠር አዋቂ መምሰል ይቻላል ብለህ አትገምት:: ሳትጠራ ራስህን ሚዛን ላይ ዘልለህ ታስቀምጣለህ:: ቀልለህም ትገኛለህ::የገዛ ጽሁፎችህን መለስ ብለህ አንብብ:: ራስህንም በርጋታ ገምግም::

አሁንም አንብበህ ለመረዳት ሞክር:: በድጋሚ "ይህ አምድ የሃይማኖት አምድ ባለመሆኑ አዲስ የምታቀርበው ጉዳይ ካለ ዋርካ ጄነራል ላይ እንገናኝ ::" ተግባባን??????
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

ግብረ ሀዋርያው ተብዬ የቀለለውን ቃሉና ፍሬው ይለየዋል

Postby ዲጎኔ » Tue Dec 13, 2005 5:17 pm

ለግብረ ሀዋርያ ተብዬው

ሳትሳደቡና ሳትገዝቱ መማማር ማስተማር የማትችሉ መሆናችሁን እያወቅሁ ነበር በትህትናና በአክብሮት የአምዱን ርእስ ጠብቀህ ስለጳጳሳት ሀገራዊ በጎ ስራ አቅርብ ያልኩህ::

አንተ ግን ተመልሰህ በተካንህበት "ቀለልክ"አልከኝ ይሁና ምን ይደረግ ውርስ ትውፊታችሁ ይህ አይደል:የቀለለውን ግን የእግዚአብሄርን ቤት እቃ ለጋለሞታዎች እንዳዋለው የባቢሎን ንጉስ ዛሬም ትናንትም የእግዚአብሄርን መንበር ለአለማዊ ጨቁአኝ መሪዎች የሚያጋሩትን ጳጳሳቶችህን ቅዱስ ቃሉ "መኔ ተቄል ፋሪስ"ይላልና ሚዛኑን ለእውነቱ ጌታ ለክርስቶስ እንተውለት::
አሁን እንደተጠየቅህው የምታደንቀውን 'ተኩላ" ባይ መጽሀፍ ቅኝት ወይም ለእናት ኢትዮጵያ እንደተባረኩት የካቶሊክ ጳጳሶች የሚጋደል ከርእሱ ጋር የሚሄድ አቅርብ::

ዲጎኔ ሞረቴው የእናት ኢትዮጵያ ቀበኛ ሆዳም ጳጳሳት ጸር!
Last edited by ዲጎኔ on Wed Dec 14, 2005 5:17 am, edited 2 times in total.
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ዓልም » Tue Dec 13, 2005 11:40 pm

በዚህ ሰአት በተለይ በአአ በጣም ብርድ ነው ማለት 13ፋራ.... ነበራ እናም እ........ እስረኞቹ እንዴት ነው እባኮዎን.
ዓልም
መንገደኛ
መንገደኛ
 
Posts: 3
Joined: Mon Nov 10, 2003 10:16 pm
Location: götenberg.

Postby Acts 8:26-39 » Wed Dec 14, 2005 12:22 am

ዲጎኔ
እንደተነቃብህ ስታውቅ ክፉኛ ትበሳጫለህ:: ያ ደግሞ የማስመሰያ ጭንብልህን ይገፍፈውና የበለጠ እርቃንህን ትወጣለህ::

ማንም ሊያየው የሚችለው ጉዳይ አንተ ፕሮቴስታንት ሆነህ ለካቶሊክ ቤትክርስትያን ተቆርቋሪ መስለህ መቅረብህ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤትክርስትያንን የሚጎዳ ስለመሰለህ ብቻ ነው::

በዚህ የውይይት ርዕስ ስር "አባ" ጳውሎስና ያዲሳባው ሲኖዶስ ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያናችንን እንደማይወክሉ የገለፅን መሆኑን እያወቅህ
"ዛሬም ትናንትም የእግዚአብሄርን መንበር ለአለማዊ ጨቁአኝ መሪዎች የሚያጋሩትን ጳጳሳቶችህን" ብለህ መቀባጠርህ ቤተክርስትያናችን ላይ ያለህ ስር የሰደደ ጥላቻ መግለጫ ነው:: ማንም የሚያውቀውን በስደት ላይ የሚገኙት እውነተኞቹ አባቶቻችንን ለምሳሌ እነ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ከሕዝባቸው ጋር ሰላማዊ ሰልፍ እስከመውጣት መድረሳቸውን ሐቅ ሽፋፍነህ ልትዘልፋቸው ተነሳህ....የኛ ጳጳሳት እነሱ ናቸውና!
የመለስ ዜናዊን ፋሽሽታዊ አገዛዝ በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ የምንኖር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች አምርረን እንታገላለን:: እንዳንተ ዓይነቱ የተቃዋሚ ካባ ለብሶ ቤትክርስትያናችንን ለመዋጋት የሚሞክር ስናይ ደግሞ ከማጋለጥ ወደኍላ አንልም:: ሸማ በየፈርጁ ይለበሳልና ፀረ-ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮፓጋንዳህን በፀረ-መለስ ፖለቲካ ለመደበቅ አትሞክር::

በድጋሚ "ይህ አምድ የሃይማኖት አምድ ባለመሆኑ አዲስ የምታቀርበው ጉዳይ ካለ ዋርካ ጄነራል ላይ እንገናኝ ::"
አንብበህ መረዳት አትችልምና እዚሁ ላይ መልሰህ ስትንጫጫ ታየኸን ....አለመታደል!
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

ቤተክርስቲያን የጴጥሮስ የጳውሎስ ሳትሆን የክርስቶስ ነች

Postby ዲጎኔ » Wed Dec 14, 2005 4:00 am

መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ ለዚህ ብእረኛ ይመጥናል

ቅድስት ቤተክርስቲያን የጴጥሮስ የጳውሎስ የአጵሎስ ወይም የካቶሊክ የኦርቶዶክስ የፕሮቴስታንት እንዳትባል ቃሉ ስለሚከለክል እስከዛሬ ድረስ በዋርካ ላይ የገልጽኩት አቁዋሜም ሲሆን ድንቁን "ግብረ-ሀዋርያ" ስም ይዘህ ካቶሊክ ፕሮቴስታንት ኦርቶዶክስ ስትል አፈርኩብህ::

እኔ ዲጎኔ የክርስቶሳዊያን አብያተክርስትያናት ሁሉ ወንድም እንጂ አንድ አባት በደብረ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተገኝቼ ቃለ -ምእዳቸውን ሰምቼ የመጣሁበትን አጥቢያ ማህበረ ምእመናን ስገልጽላቸው እንዳሉኝ " የክርስቶስ ማህበረምእመናን እንደቅርጫ ስጋ አይከፋፈልም" እልሀለሁ::

በተረፈ ለኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ያለኝን ፍቅርና አክብሮት አንተና መሰሎችህ ወደመቅደሱ አልገባ ወይም አላስገባ ብላችሁ የተደነቀራችሁ ልትቀንሱብኝ አትችሉም::

በተረፈ አሁንም አባባሌን እያጣመምክ እስከአቀረብክ ድረስ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት እንደማልመለስ አስታውቅሀለሁ::
አሁንም የአምዱን ርእስ ጠብቀህ የወቅቱን የወያኔ አፈና የሚፋለሙ ጳጳሳትና ሀገር ወዳዶች እንቅስቃሴ ላይ ብቻ እንድታተኩርና ካቶሊክ ኦርቶዶክስ ፕሮተስታንት የሚለውን ከፋፋይነትህን እንድታቆም በጥብቅ አሳስብሀለሁ::

ዲጎኔ ሞረቴው የክርስቶሳዊ ማህበረምእመናን ሁሉ ወዳጅ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Acts 8:26-39 » Wed Dec 14, 2005 5:36 am

ዲጎኔ
በድጋሚ "ይህ አምድ የሃይማኖት አምድ ባለመሆኑ አዲስ የምታቀርበው ጉዳይ ካለ ዋርካ ጄነራል ላይ እንገናኝ ::"
አንብበህ መረዳት አትችልምና እዚሁ ላይ መልሰህ ስትንጫጫ ታየኸን ....አለመታደል !
ብለን ነበር ....እንደጠበቅነው እዚሁ ብዙም ሳትቆይ መጣኸው....


በዚህ ስም ዋርካ ላይ ከተመዘገክበት ከ19 Aug 2005 ጀምሮ እስከአሁን ከለቀለካቸው 446 ጽሁፎችህ በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤትክርስትያን ላይ ያነጣጠሩትን ለማወቅ እኮ ቀላል ነው:: profileህ ላይ ሄዶ Find all posts by ዲጎኔ የሚለውን መጫን ብቻ ነው የሚያስፈልገው:: ወይም ደግሞ ይህንን ሊንክ መጫን ነው:
http://www.cyberethiopia.com/warka4/sea ... E%E1%8A%94

ላንተ 'ኮ አልታይ ያለህ የጭንብልህ መውለቅ የአደባባይ ሚስጥር ነው::
የፈለግኸውን እምነት የመከተል ነፃነት አለህ:: ምን አሳፈረህ?? ለምን ያልሆንከውን ለመምሰል ትሞክራለህ?? እኛ የምንልህ ነገር አጭር ቀላልና ግልጽ ነው
ፀረ -ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮፓጋንዳህን በፀረ -መለስ ፖለቲካ ለመደበቅ አትሞክር ::
ነው!!! ተነበበልህ? ገባህ??????

ለመኾኑ ወያኔ በቤትክርስትያናችን ላይ በጫናቸው 'ጳጳሳት' ና "ፓትርያርክ" ተብዬው ምክንያት ቅድስት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤትክርስትያን ላይ ዘመቻ መክፈት ለምን አስፈለገ?
የፖለቲካ ትርፍ ስላለው ነው?? ሕዝባችን በዚህ ግፈኛ አገዛዝ ላይ ያለውን ጥላቻ ተጠቅሞ ቤተክርስትያናችንን ለመጉዳት ነው?? የዋርካ ታዳሚ ይህንን የመገንዘብ ብቃት የለለው መስሎህ ነው?
በስደት ላይ የሚገኙት ሕጋዊው ፓትርያርካችን ብፁዕ ወ ቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እንዲሁም በስደት ላይ የሚገኙት ብፁዓን ሊቃን ጳጳሳት እነ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ፋሽሽታዊውን ስርዓት ለማስወገድ በማካሄድ ላይ ያሉትን ማንም የሚያውቀውን ተጋድሎ አድበቅብቀህ "ጨቁአኝ መሪዎች የሚያጋሩትን ጳጳሳቶችህን " ብለህ መዝለፍህ ምን ይባላል??

አሁንም ቢገባህ በድጋሚ እንነግርሃለን ፀረ -ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮፓጋንዳህን በፀረ -መለስ ፖለቲካ ለመደበቅ አትሞክር ::
ይኼ የተበላ ዕቁብ ነውና ሌላ ካለህ ሞክር!!
በተለይ ግን ለሁሉም የሚታየውን ራስህን ሁን! በእምነትህ አትፈር! እሺ?
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

ከአምዱ ርእስ ጋር ብቻ ለሚሄደው ምላሼ

Postby ዲጎኔ » Wed Dec 14, 2005 6:58 am

የአምዱን ስነምግባር ለመጠበቅ ከርእሱ ጋር ለሚሄደው ብቻ ምላሼን እየሰጠሁ ሌላውን ለዋርካታዳሚ ፍርድ ልተው

አሁንም ደግሜ የማሳስብህ አንተ "ግብረሀዋርያ' የሚለውን ስያሜ መጠቀም የማትችል ገና በብሉይ መንፈስ ያለህና ጌልጌላ ላይ በመሪው ኢያሱ ያለብህ የስም ማጥፋትና የማጣመም ክፉ ሸለፈትህ መገረዝ ያለበት ግለሰብ ነህ::
1. እነዚህ የጠቃቀስካቸው ጳጳሳት በሀገራዊ ጉዳይ በተለይ በጸረ-ወያኔ ተጋድሏቸው ፈለጋቸውን እከተላለሁ ብዬ የጻፍኩትን በዚሁ አምድ ወደሁአላ ሄደህ ተመልከት
2. እኔ በእምነቴ አፍሬ አላውቅም አልጻፍኩምም
3.ፕሮፋይሌን በማሳየትህ እያመሰገንኩህ ስለሁሉም አብያተክርስቲያናት በመጋደል መጻፌን አስታውሰህኛል!
4.ሆዳምና ፈሪሳዊ ጳጳሳት ከመልካም ጳጳሳቱ ይለያሉ
5.በርእሱ መሰረትሌሎች የእምነትሰዎችተቃዋሚዎቹ ከእስር እንዲፈቱና የዜጎች መብት እንዲያስጠብቁ እቀሰቅሳለሁ
6.ለሀገር የሚሰዉ ጳጳሳትን ገድል እዘግባለሁ::
7.የቤተክርስቲያናንና መንግስት መጣመርን እንደቃሉ አወግዛለሁ

ዲጎኔ ሞረቴው
Last edited by ዲጎኔ on Wed Dec 14, 2005 2:56 pm, edited 1 time in total.
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Acts 8:26-39 » Wed Dec 14, 2005 7:35 am

ዲጎኔ
አምዱ የዜና አምድ ነው:: ማንም ግለሰብ የጀመረው አይደለም:: ችግሩ የጀመረው አዲስ አድማስ - 26-11-2005 ያወጣውን ዜና በሚመለከት
አንተ

"እሰየው ነው ይሄ የካቶሊኮች ቅዱስ የእውነት ተሟጋችነት !

እንግዲህ ካቶሊኮችን ለማውገዝ ድሮ የተከተበው የአለቃ አያሌው ታምሩ "መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና " ተሻረ በለኛ !

አሁን እንግዲህ አለቃ አያሌው ወይም ደጋፊዎች የሚጽፉ ከሆነ ርእስ በትህትና ልጠቁም :
" መች ተለመደና ከልጅ ገዳይ ወያኔ ዝምድና ""


በማለት ዜናውን ጠልፈህ አርእስቱን ብቻ በምታውቀው ፈፅሞ ባላነበብከው የአለቃ አያሌው መጽሐፍ ነቀፌታ ስምና የካቶሊክ ቤተክርስትያንን የምታደንቅ መስለህ ያደረግከውን በፀረ -መለስ ፖለቲካ የተደበቀ ፀረ -ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት ነው::

ዝርዝሩን ማንም ወድ ኹዋላ ሄዶ ሊያየው ይችላል::

በእምነትህ የማታፍር ከሆነ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለመምሰል እምታደርገውን ያልተሳካ ሙከራ ትተህ በግልጽ ፕሮቴስታንት ነኝ ብትል ችግር የለውም

የኛ አባቶች ጳጳሳት ንፁሃን ናቸው..."ሆዳምና ፈሪሳዊ" ወያኔ በቤትክርስትያን ላይ የጫናቸው ሲሆኑ እነሱን ተቀበሉ ከሆነ ከፈለግህ አንተ ሰፈር ውሰዳቸው እንጂ እኛ ጋ ቦታ የላቸውም....

አሁንም ቢገባህ በተደጋጋሚ እንነግርሃለን ፀረ -ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፕሮፓጋንዳህን በፀረ -መለስ ፖለቲካ ለመደበቅ አትሞክር :: ፕሮቴስታንት ሆነህ አፍቃሬ ካቶሊክ ለመምሰል አትሞክር:: ይኼ የተበላ ዕቁብ ነውና ሌላ ካለህ ሞክር !!
Acts 8:26-39
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 216
Joined: Tue Apr 26, 2005 8:10 pm

PreviousNext

Return to Warka News - ዋርካ ዜና

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest